በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ...

29
ነጻ ፍቃድ 2015 0 www.tlcfan.org በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Transcript of በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ...

Page 1: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

0 www.tlcfan.org

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

1 www.tlcfan.org

ነጻ ፍቃድ የመጀመሪያ እትም

Copyright ©2001 የሁለተኛ እትም REVISED 2015

መብቱ የተጠበቀ ነው፦

All rights Reserved to: Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

FOUNDER OF THE LION S CALL FOR ALL NATION INTERNATIONAL MINISTRY

Permission is granted to copy and quote freely

from this publication for non-commercial purposes.

Page 3: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

2 www.tlcfan.org

ማውጫ

ርዕስ ገጽ

1. ነጻ ፍቃድ ጥያቄ ................................................................................. 3

2. የሁሉ የበላይ ማነው? ........................................................................ 11

3. ሃጢያት እንደ እዳ ............................................................................. 13

4. ኢዮቤልዮ የዕዳ ፍጻሜ ....................................................................... 14

5. የምድር ሕግ .................................................................................... 15

6. ባለቤትነትና ነጻ ፈቃድ ...................................................................... 17

7. በባለቤትነት የሚመጣ ተጠያቂነት ....................................................... 18

8. ማጠቃለያ ......................................................................................... 28

Copyright © 2001

All rights Reserved to Leon

Page 4: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

3 www.tlcfan.org

የነጻ ፍቃድ ጥያቄ

ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን ጥያቄ መልስና የእግዚአብሔርን

ሁሉን ተቆጣጣሪነት፣ እርሱ ብቻውን ገዢ መሆኑንና ገደብ የሌለው ስልጣኑን እንድንመለከት

ይረዳናል ብዮ አምናለሁ። ሁሉ ክርስቲያን እግዚአብሔር የሁሉ ተቆጣጣሪና ገዥ እንደ ሆነ

አምናለሁ ይላል። በሌ በኩል ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪዎች ወይም አዋቂዎች

የእግዚአብሔርን የሁሉ የበላይነትና ገዥነትን በተመከተ በዝርዝር ሲጠየቁ ገዢነቱን በስውር

ይክዳሉ።

እንዲህ የሚሉ ሃሳቦችንም ያመነጫሉ፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለመልአክት ደግሞም

በመቀጠል ለሰው ልጆች ነጻ ፍቃድ ሰጠ ይህ በማድረጉም ደግሞ እርሱ ሁሉን መግዛቱን አቆመ።

ሰው በራሱ ፍቃድ እንዲመላሰ ነጻ ፍቃድን ስለሰጠው ደግሞ ሰው በሚያደርገው ማንኛው ነገር

ሁሉ ተጠያቂ ይሆን ዘንድ ነው ያላሉ።

ይህ ሃሳባቸው በዚህ ቢያበቃ ጥሩ ነበር ነገር ግን በመቀጠል እግዚአብሔር የፈጠረው

የመላዕክት አለቃ አንድ ቀን ነጻ ፍቃዱን በመጠቀም የእግዚአብሔርን ዙፋን ሊገለብጥ መፈንቅለ

መንግስት እንዳስነሳ በሙሉ አፋቸው ሳያፍሩ አፋቸው ከፍተው ይናገራሉ። አንዳንድ ጥቅሶችንም

ያለ ቦታቸው በማስገባት ይህን ሃሳባቸን ሊያሳምኑ ይጥራሉ ሰዎችንም ያስታሉ።

ይህ መፈንቅለ መንግስት ያስነሳው የመላእክት አለቃ በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያንኖች

በብዛኛው ሉሲፈር የሚባለው የመላዕክቶች አለቃ ነው ብለው ያምናሉ። መልአኩ ከእርሱ ሃሳብ

ጋር የተስማሙ ሌሎች መላእክቶችን አቀናጅቶ በእግዚአብሔር መንግስት ላይ ግልበጣ ያከናወነው

ይህ የመላእክቶች አለቃ አሁን ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው ነው ይላሉ። ይህን መፈንቅለ መንግስት

በእግዚአብሔር ላይ ሲያደርግ እርሱን አግዘው እግዚአብሔርን የተዋጉት መላእክቶች እግዚአብሔር

ከፈጠራቸው መላእክቶች መካከል 1/3 እንደ ሆኑ በቤተክርሲያን ሳይቀር ይህ ታስተምራለች።

እነርሱ ይህን መፈንቅለ መንግስት ያከናወኑበት ምክንያት እነርሱ እንደ ሚናገሩት ብዙ

ግልጽ አይደለም። ቃሉም ይህን ሃሳብ ጠለቅ ብለን ስንመረምር ፈጽሞ አይደግፈውም። ሉሲፈር

በቅናትና በምቀኝነት ተነስቶ እግዚአብሔርንም ለመምሰልና ራሱን እንደ አምላክ ለማድረግ ፈልጎ

ነው ሲሉ አንዳዶች ደግሞ የሰው ልጆችን ክብር ስለፈለገ ነው ብለው ያምናሉ። ይህን ሁሉ

የሚሉበት ምክንያት ዋናው ለማስረገጥ የፈለጉት የሰው ልጆችና መላእክት ነጻ ፍቃድ አላቸው

የሚለውን ቃል ለማሳመንም ጭምር ነው። አለበለዚያ ሰውንም ሆነ አመጹ የተባሉትን መልእክት

እንዴት መኮነን ይቻላል? የግድ የሚከሰስ መገኘት አለበት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰው

መልካምና ክፉውን እንዲመርጥ ምርጫ ሲሰጠው በዘፍጥረት ላይ እናያለን። ታዲያ ሰው ፍቃድ

የለውምን? በእርግጥ እላለሁ ሰው ፍቃድ አለው። ነገር ግን ምንም እንኳ ሰው ፍቃድ ቢኖረውም

ይህ ፍቃዱ ነጻ ፍቃድ አይደለም። በዮሐንስ 6፥44 ላይ ኢየሱስ እንዲህ ይለናል፦

Page 5: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

4 www.tlcfan.org

“አብ ካልሳበው በቀር ወደ ወልድ ሊመጣ የሚችል ማንም ሰው የለም።” ብሎ እርግጡን

ይነግረናል። “ካልሳበው” የሚለው ቃል ትክክለኛ ቃል ነው። ታዲያ የቱ ላይ ነው ነጻ ፍቃዱ? መሳብ

በግሪኩ helkuo means It is translated in the King James as John 6:44

draw him: and I will

“44 የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም።”

NT: #1670, helkuo (hel-koo'-o); or helko (hel'-ko); akin to

NT:138; to drag (literally or figuratively). John 21:6,

draw

“6 እርሱም። መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው፥ ስለዚህ ጣሉት፤

በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው።”

ይህ መሳብ የሚለው ቃል አንድ አሳ አጥማጅ በመረቡ አሳዎች አጥምዶ እንደ ሚስብ

ነው። በመረብ ውስጥ ያለው አሳ አንድ ጊዜ ወደ መረቡ ከገባ በኃላ የቱ ጋር ነው ነጻ ፍቃዱ?

አንዴ ከተያዘ ለማምለጥ ምንም የራሱ የሆነ ነጻ ፍቃድ የለውም። አሳው ግን በተያዘበት መረብ

ውስጥ ሆኖ ቦታን በዚያው በመረቡ ውስጥ መቀያየር መንፈራገጥ ወይም ጸጥ ብሎ መተኛት

እጁን የመስጠት ፍቃድ ወይም ምርጫ አለው። እኛ ሰው ሰለ ሆንን ከአሳ የተሻለ ሰለ ምናስብ

አሳው ነጻ ፍቃድ እንደ ሌለው እናውቃለን። ነገር ግን አሳው ነጻ ፍቃድ እንደ ሌለው ላያውቅ

ይችላል። ይህ መሳብ ወይም መጎተት የሚለውን ቃል በያቆብ መልዕክት ላይ ደግመን

እናገኘዋለን። ያቆ.2፥6

“6 እናንተ ግን ድሆችን አዋረዳችሁ፥ ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን?

ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን?”

ባለጠጋው ከቤት እየጎተተ ሊያወጣን ሲመጣ አልወጣም ልንል በራሳችን ነጻ ፍቃድ

አለን? ልንከስህ እንፈልጋለንና ወደ ፍርድ ቤት ትመጣልናለህን ብለውስ ድሃውን ይለምኑታል?

አይደለም። ነገር ግን እነዚህ ባለጠጎች ለማንም ነጻ ፍቃድን ሳይሰጡ ዘው ብለው ቤት ውስጥ

ገብተው እየጎትቱ በፍርድ ፊት ደሃውን ያቆማሉ። ይህ ደግሞ ተጎታቹ ምንም ነጻ ፍቃድ እንደ

ሌለው ያሳያል።

Page 6: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

5 www.tlcfan.org

ደሃውን ሰው ብንሆን ልንጮህ ልንፈራገጥ ሌላም ሌላም ልናደርግ እንችላለን። ነገር

ግን በራሳችን ነጻ ፍቃድ የለንም። ምክንያቱም ከእርሱ ከፍ ያለ ስልጣን ያለው በእነርሱ ላይ

ወስኗልና ነው። ሰለዚህ ወደዱም ጠሉም ይህን ሊፈጽሙት ግድ ነው። ተጎትቶ ሊፈረድበትና

ሞትም ከሆነ ሊሞት ግድ ነው።

“ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።” ዮሐ. 12፥32

will draw all men unto me

እዚህ ጥቅስ ላይ ኢየሱስ ይህንኑ መሳብ የሚለውን ቃል ሲጠቀመው እንመለከታለን

ደግሞም ኢየሱስ ሰዎች ምንም የሚያመካኙበት ሌላም የሚሉት ነገር አልተወም። እርሱ ጌታችን

የበላይ ባለስልጣን ነው። ሁሉ እስባለሁ ካለ የቱ ጋር ነው ነጻ ፍቃድ? ሰው ፍቃድ አለው። ነገር

ግን ነጻ ፍቃድ የለውም። እነዚያ ሃብታም ሰዎች ደሃዎችን ወደ ፍርድ ይስቡ እንደ ነበር ኢየሱስም

ሁሉን ወደ እርሱ እንደ ሚስብ ተናገረ።

የእነርሱ ፍቃድ ከእነርሱ በላይ በሆነ ፈቃድ እንደ ተወሰደው ደሃ ሰው ኢየሱስም

በሰው ልጆች ላይ ይህን እንደ ሚያደርግ ተናገረ። ይህ መሳብ የሚለው ጥልቅና ጠንካራ የሆነ ነጻ

ፍቃድ አለ ብለን ለምናምን ሰዎች ምንም አይነት መፈናፈኛ የማይሰጠን፣ የማይወድቅና የማይሻር

ፍጥጥ ያለ የሕያው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው።

“37 አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ

ወደ ውጭ አላወጣውም፤ 38 ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን

ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።39 ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ

እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው”

ዮሐ 6፥37-39

እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠው ሁሉ ወደ ኢየሱስ ይመጣል። በፍቃዳቸው እንኳን

መጣን የሚሉ ሰዎች ቢኖሩ የመጡት መጀመሪያውኑ እግዚአብሔር በራሱ ነጻ ፈቃድ ወደ ኢየሱስ

እንዲ መጡ ስለላካቸው ደግሞም ለኢየሱስ ስለሰጣቸው ወይም ስለጠራቸው ነው።

የሰው ምርጫ ወደ ኢየሱስ እመጣለሁ ማለት ብቻ ነው። እነርሱ በራሳቸው ፈቃድ

የመጡ ቢመስላቸው እንኳ እግዚአብሔር እነርሱ በማይረዱበት ሁኔታ ወደ ልጁ ያመጣቸውና

በሰውር ስለእነርሱ ደህንነትን የሰራው እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው። ኢሳ.45

እግዚአብሔር ስለ መረጣቸው እነርሱ ደግሞ እግዚአብሔርን ይመርጣሉ ማለት ነው።

የእኛን መንገድና ጉዞ የሚመራም ሆነ የሚወስን እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ማን እንደ

ሆነና የሁሉ ገዢነቱና ተቆጣጣሪነቱ የስልጣኑን የሃይል መጠን ስንረዳ የእኛ ፍቃድ ከእርሱ ነጻ

ፈቃድ የመነጨ እንደ ሆነ መሻትንም ሆነ ማድረግንም በእኛ የሚያደርግ እርሱ እንደ ሆነ

እንገነዘባለን።

Page 7: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

6 www.tlcfan.org

ወደ እርሱ በጣም በቀረብን ቁጥር የእርሱ ገዢነት እየጨመረ ምርጫችንን እንኳን

ሳይቀር እየቀነሰ መሄድ ይጀምራ። ከዚያ እንደ ኢየሱስን የአንተ ፍቃድ ይሁን ማለት

እንጀምራለን። ስለዚህ የእኔ ጥያቄዎች እነዚህ ናቸው፦ ሰዎች ለምን የእግዚአብሔርን ሁሉ

ገዥነትና ተቆጣጣሪነት ይጠራጠራሉ? ለምንስ ለራሳቸው ነጻ ፍቃድ እንዳላቸው ራሳቸውን

ለማሳመን ይጥራሉ? ከዚህ ከነጻ ፍቃድ ከማግኘት ጀርባ ያለው ፍላጎትስ ምንድ ነው?

ሰው ነጻ ፍቃድን ለመጠበቅ የሚፈልግበት ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉት።

እነርሱም፦ የመጀመሪያው የሰው ትዕቢትና ኩራት ነው። ይህም ሰው ለመዳን አንድ ነገር መስራት

ስለ ሚፈልግ ወይም በደህንነቱ ላይ ተሳትፎ ማሳየት ስለሚፈልግ ነው።

ይህንን የተሳትፎ ሥራ ደግሞ ሰው እራሱን በነጻ ፍቃድ ውስጥ ካላስቀመጠ ሊሰራው

ሰለ ማይችል ነው። አንዳንዴ ሰዎች ራሳቸው ወደ ጌታ እንደ መጡ አድርገው ሲናገሩ እንሰማለን።

ይህ ከንቱ ኩራትና ትምክህት ነው። ይህም በሰውየው ውሳኔ እግዚአብሔር እንደተደሰተበት

ለማሳየት የሚሄዱበት መንገድና አብ ሳይጠራኝ መጣሁ ወድጄና ፈቅጄ መጣሁ ለማለት

በሥራቸውም ለመመካት ነው። ኤፌ.2፥8-10

ይህም እግዚአብሔር ካለ እኔ ፍላጎት ምንም ሊያደርግ አይችልም፡ የሚልን አደገኛ

የሆነ የተሳሳተ መረዳትና ሰውየውንም ሆነ የሚሰሙትን ሰዎች የሚያበላሽ ሃሳብ ውስጥ ይጥላል።

ይህም እግዚአብሔርና እኔ አብረን አደረግን የኔ ድርሻ አደረኩ የእርሱ ድርሻ ደግሞ ያደርጋል

የሚል ድምዳሜ ላይ ይመጣሉ።

ሰው የሚናገረውን ሳያስተውልም ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካክላል።

ከእግዚአብሔር ጋር እንኳን በሥራ እንድንተባበር ብንደረግ በመጀመሪያ ደረጃ ሃሳቡን

የሚያፈልቀው ወደዚያ ሃሳብ የሚያስገባን ሥራውን በልባችን የሚያኖር የምንሰራበትንም ሃይል

የሚሰጠን እግዚአብሔር እራሱ ብቻ ነው። ሰለዚህ የመጀመሪያው የነጻ ፍቃድ የማግኘት ፍላጎት

ምክንያት የሰው እኔነት ነው። እኔ አደረኩ፣ እኔ መጣሁ፣ እኔ ይህን ስላደረኩ፣ እኔ… እኔ… እኔ…

እኔ…….

ሁለተኛው ደግሞ የአዳም በግል ወይም በነጻ ፍቃድ የመኖር ምኞት በስው ውስጥ

ስላለ ነው። (Adamic self-life) ይህ የእኔነት ሕይወት ከድሮ አባታችን ከአዳም ጀምሮ በደም

ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በእኛም የሚኖር ስፍራውን ለእግዚአብሔር መልቀቅ እንቢ አልፈልግም

የሚል ያለመታዘዝ ማንነት ነው። ከዚህም የተነሳ ለእግዚአብሔር ነጻ ፍቃድና ፍላጎት ወይም

ትዕዛዛት መገዛዝ ወይም መታዘዝ አንፈልግሞ። ይህም ሥጋዊ አዕምሮ ‘ego’ ነው።

ሰው ሁሉን ለመግዛት ፍላጎት ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። ይህን ፈላስፋዎች የሰው ልጅ

የምድር እይታ ይሉታል። ይህም እይታ በሰው አዕምሮና ውሳኔ ላይ ያተኮረ ነው። ስለዚህ ሁለተኛ

ምክንያት የሰው ልጆች አሰተሳሰብ በምድር እንዲገን ከፍ ከፍ የማድረግ ፍላጎት ነው።

Page 8: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

7 www.tlcfan.org

ሦስተኛውና የመጨረሻው ሰዎች ነጻ ፍቃድን የሚያምኑበት ምክንያት ወደፊት

በዝርዝር ልንመለከተው የምፈልገው ሲሆን ይህም ክፉ በዓለም እንዳለና ለዚህ በዓለም ላለው ክፋት

እግዚአብሔርን ተጠያቂ ላለማድረግ የሚደረግ የሰውና የሃይማኖተኞች ርብርቦሽ ነው።

ሃይማኖተኛ ሰዎች ለክፉው ለሰይጣን ነጻ ፍቃድ ካልሰጡት በቀር እግዚአብሔርን

ዓለም ስላለው ክፋት በተጠያቂነት ሰፍራ ላይ ስለሚያስቀምጠው የዚህ ስካት ነጻ ፍቃድን የሙጥኝ

እንዲሉ አድርጓቸዋልና ነው። ስለ ሰራውም ሥራ ሆነ ስለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን

ከሃላፊነት ነጻ ስለማያወጣው ነው። ይህንንም ለማጽናት እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ ከሆነ ይህ

በዓለም የሚሆነው ሁሉ ለምን ይሆናል? ለምን የሰዎች መከራ እንዲኖር ይፈቅዳል? ለምን ሕጻናት

ሲሰቃዮ ዝም ይላል? የሚሉና ይህን የመሳሰሉ ጥያቄቆችንና ስተቶችን በግድ አስተምራሉ።

ክርስቲያን ቲዮዎሎጂያንና ፈላስፋዎች ስለ ሦስተኛው ሃሳብ የሚቃረን ሃሳብን

ይሰነዝራሉ። አንደኞቹ እግዚአብሔር ሰለ ክፋት ያለውን ሃሳብ ምን እንደ ሆነ ባናውቅም

እግዚአብሔር ሁሉን ለበጎ ይለውጠዋል፣ ይቀይረዋል የሚሉ ናቸው። መሰረታቸውም ይህ ጥቅስ

ነው። (ሮሜ.8፥28) ሌሎቹ ደግሞ ሁሉ ክፋት የሆነው እየሆነም ያለው ከሰው እውቀት ማነስና

ይህን እንዲያደርጉ ከሚያደርጋቸው ከሚገፋፋቸው ዲያቢሎስ የተነሳ ነው ብለው ያምናሉ።

ስለዚህም በዓለም ስላለው ክፋት ተጠያቂው ሰውና ዲያቢሎስ ነው ይላሉ።

ኤርሚያስ ስለ መመለስ የሚለው ነገር አለው፦

“18 ኤፍሬም። ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና

መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ። 19 ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤

የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም ብሎ ሲያለቅስ ሰማሁ።” ኤር.31፥18-19

was chastised, as a bullock unaccustomed to the yoke: turn thou me, and I shall be turned;

for thou art the LORD my God. 19 Surely after that I was turned, I repented; and after that I

was instructed, I smote upon my thigh: I was ashamed, yea, even confounded, because I

Jeremiah 31:18-19

በመንፈስ ኤፍሬም ራሱን እንደ ወይፈን መስሎ ሲጸልይ ኤርሚያስ ሰማ። ይህም

በእርሻ ላይ ሳለ ጌታ ሲመልሰው እንደሚመለስ ተናገረ። መመለስ ማለት ንስሃ መግባት ማለት

ነው። ኤርሚያስ እንደ ሚያሳየው ወይፈኑ ተመልሶ ትክክል መስመሩን እንዲይዝ ማድረግ

የገበሬው ድርሻ እንደ ሆነ ያሳያል። ወይፈን የኤፍሬም ነገድ አርማና ሰንደቃላማ ነው። ዘሁ.2

ኤፍሬም ወደ እግዚአብሔር መመለስና ለጌታ መገዛትን አላወቀም ነበር። ኤፍሬም ግን ወደ ጌታ

እግዚአብሔር ጸሎቱን አላቆመም። እግዚአብሔርን መልስኝ እመለሳለሁ ይለዋል።

Page 9: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

8 www.tlcfan.org

ይህም እግዚአብሔር ሊመልሰው የሚችል እርሱ ብቻ እንደ ሆነ ያለ እርሱ መመለስ

እንደማይችል ስላወቀና ስለተረዳ ነው። አባታችን ገበሬው ያለተገራን ወይፈንን ሁሉ የሚገራ

ብቸኛ አምላክ ነው። ኤርሚያስ በመንፈስ ካየው ነገር ሊያሳይና ሊያስተምረን የፈለገው የሁሉ

ጀማሪ እግዚአብሔር መሆኑን ያለ እርሱም አንዳች ነገር ሊሆን እንደማይችል ነው። እግዚአብሔር

የመጀመሪያውን የማዳን መንገድ እራሱ ጌታችን ካልጀመረልን በቀር እርሱ ራሱ ካልመለስን በቀር

አንዳችንም በራሳችን ፈጽመን ለመዳን ወደ እርሱ መመለስ ፈጽሞ እንደማንችል አሳየን።

እግዚአብሔር ራሱ ካልሳበው በቀር ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ ከቶ ማንም የለም።

እግዚአብሔር ሁሉ ከመጀመሪያ ካቀደው ሁሉን ወስኖታል ማለት ነው። ኤፌ.1፥4-11

“predestination” ቀድሞ መወሰን የእግዚአብሔር ሥራና የእግዚአብሔር ብቸኛ ብቃቱን የሚያሳይ

መርህ ነው። ይህን ለምን ታደርጋለህ ብሎ እርሱን የሚያዘው ወይም በሥራው እርሱን

የሚያርመው ማንም የለም። ሁሉን ለብቻው ያለ አጋዠ ማድረግ የሚችል በራሱ ብቁ የሆነ

አምላክ ነው። ሮሜ.9፥14-33,11፥29-36

“አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና።” ኤር.17፥14

ኤርሚያስ እንደምንመለከተው ማን ጀማሪ እንደ ሆነ ማን ተጠቃሚ እንደ ሆነ በግልጽ ያሳያል።

ሰው በራሱ አንዳች ማድረግ አይችልም። በሰው ሃሳብ ውስጥ ምንም መልካም ነገር የለም። ሁሉ መልካም

የሆነ ነገር ሁሉ ከላይ ከብርሃናት አባት የሚወጣ ከእርሱም የተቀበነው ብቻ ነው።

” 16 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። 17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ

ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት

አባት ይወርዳሉ። 18 ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን”

ትልቁ እግዚአብሔር የሚሰጠን ከሰማይ የሚወርድ መልካም ስጦታ ደግሞ ወደ እርሱ መመለስ

ወይም ንስሃ ነው። ሮሜ.2፥4

the goodness of God leadeth thee to repentance

እግዚአብሔር ወደ ንስሃ የሚመራን እርሱ ከሆነ ለራሳችን ቀብድ መስጠት አቁመን

ክብሩን ሁሉ ለእርሱ ልንሰጠው የሚገባን አይመስላችሁም? እግዚአብሔር ስለ ሰጠን ንስሃና

ምሕረት ልናመሰግነው ልናከብረውና ልናመከው ይገባል። እግዚአብሔር ለእርሱ ጥሪ

እንድንመልስ ባያደርገን ኖሮ መጀመሪያውኑ እርሱን ልንሰማና ልንታዘዘው አንችልም።

እግዚአብሔር ሁሉ የሚያደርግ ሁሉን የሚስብ ከሆነ ታዲያ ነጻ ፍቃድ የቱ ላይ ነው? ሰው ሁሉ

ወደ ኢየሱስ በራሱ ፍቃድ እንደ መጣ በሚያስበው ለራሱ መልካም ስምን ሊወስድ ስለሚፈልግ

ነው።

Page 10: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

9 www.tlcfan.org

ሕይወቴን ለጌታ ሰጠሁ፣ ሙሉ ጊዜዮን ለጌታ ሰጠሁ….ወዘተ በማለት ሰው የራሱን

ክብር በኩራት ሊያቆም ይፈልጋል። እግዚአብሔር ሰው ወደ ደህንነት የሚያመጣና የሚስብ ከሆነ

ከእርሱ ባህሪ ጋር የሚጋጭ ነው ብለው ያስባሉ። ምክንያቱ ለእነርሱ እግዚአብሔር ጨካኝ ለሰው

ነጻ ፍቃድ ሰለ ሰጠ ብዙ ይጠብቅበታል ብለው ስለሚያምኑ ነው።

“11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥

በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ 13

እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም

ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።”

ይህ የእግዚአብሔር ቃል ሰው ነጻ ፍቃድ አለው ከሚል ሃሳብ በጣም የራቀ ሃሳብን

የሚያሳይ ነው።

Which were born, not of blood, nor of the will of the flesh, nor of

the will of man, but of God 1 John 1:13

የሥጋ ፍቃድ ሰውን ዳግም ሊወለድ ፈጽሞ አይችልም። የሰውም ፍቃድ በሰው ፍቃድ

ላይ በመጫን ሰው ዳግም እንዲ ወልድ ማድረግ አይችልም። ሁሉ ሊሆን የሚችለው

በእግዚአብሔር ፍቃድ ብቻ ነው። ዮሐንስ ይህን ሃሳብ የእግዚአብሔርን ሁሉን ገዢነትና ጀማሪነት

ደግሞም የሁሉን ተቆጣጣሪነት በግልጽ እየደጋገመ በወንጌሉ ያስቀምጠዋል። ዮሐንስ ስለ ነጻ

ፍቃድ ክርክር ሳያውቅ ይህን ጻፈውን? አይደለም። በእኛ ዘመን ስለዚህ ጉዳይ ጥያቄና ክርክር

እንዳለ ሁሉ በዚያን እርሱ በነበረበት ዘመን ክርክር እንደሚኖር ግልጽ ነው።

ዮሐንስ ወንጌሉን በጻፈበት ዘመን በይሁዳ ሦስት ታላላቅ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች

ነበሩ። የሰዱቃውያን፣ የጻፎችና የፈሪሳዊያን ትምህርት ቤት ናቸው። ሰዱቃዊያን በእግዚአብሔር

ሁሉ ገዥነትና ተቆጣጣሪነት ያምናሉ። ጻፎች ደግሞ ሰው ነጻ ፍቃድ አለው ብለው ያምኑ ነበር።

ፈሪሳዊያን ደግሞ እግዚአብሔር የሚረዳቸውን ይረዳል ብለው ያምኑ ነበር። ይህ አንድ በልጅነቴ

የምስማውን አባባል ያስታውሰኛል “እርዱኝ እረዳችኃለሁ” የሚለው ቃል ነው። ይህን አባባል

የሚያምኑ አሁንም አሉ። ይህ ሁሉ የእነዚህ በይሁዳ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ቲዮሎጂያን እውቀት

አሁን እስካለንበት ቀን ድረስ ሲወርድ ሲዋረድ መጥቷል። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገር

ሁሉን ነገር በፍቃዱ እንደ ሚያደርግ ያሳየናል። ኤፌ.1፥11

“እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን

በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።”

Page 11: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

10 www.tlcfan.org

ብዙ ክርስቲያኖች ሆኑ ተመራማሪዎች አውቀውት ሆነ ሳያውቁት የእግዚአብሔር ሁሉ

ገዢነትና አድራጊነት (sovereignty) ሲያስወግዱ ሲክዱ መመልከት የተለመደ ነው። ይህን ክብሩን

ከእርሱ ወስደው ለዲያቢሎስና ለሰው ይሰጡታል። እግዚአብሔር ምንም ሊያደርግ ባልመቻሉ

ከእርሱ ጋር የማይተባበሩትን ሁሉ ሲሞቱ ጠብቆ ለመቅጥት ቁጣን እንደሚያጠራቅም አሁን ግን

ምንም ሊያደርግ እንደማይችል አድርገው ይገምታሉ። ይህም እግዚአብሔር ያልተቀበሉት

ለዘላለም ስቃይ አንድ ቀን ከፍርድ በኃላ እንደ ሚጥላቸው በመደምደም የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ

በዚህ ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን ያደርጉታል።

እግዚአብሔር አንድ ሰው በእርሱ እስኪያምንለት ድረስ በትግስትና በተስፋ ስውን

የሚጠብቅ፣ ጠብቆ ጠብቆ ያ ሰው በእርሱ ካላመነ ስላላመነ እግዚአብሔርን ብዙ በማስጠበቅ

ስላሳዘነ ወደ ሲዖል ይወርዳል ይቃጠላል ይላሉ። በእውነት እግዚአብሔር ምንም ነገር ማድረግ

አይችልምን? ታዲያ አማኞች እግዚአብሔርን ከማመን ይልቅ ዲያቢሎስን ቢፈሩ ምን የሚስደንቅ

ነው? በከንፈራቸው እግዚአብሔርን እናምናለን ሲሉ ቆይተው ወደ ቤታቸው ሲገቡ በልባቸው

እግዚአብሔር በምድር ላይ ግቡን ለመፈጸም የግድ የሰዎች እርዳታ እንደ ሚያስፈልገው የሚያምኑ

በመካከላችን አሁን ያሉ ብዙዎች ናቸው።

እግዚአብሔር ሰው ወደ እርሱ እንዲመለስ ሲጠብቅ ዲያቢሎስ ግን የወደደውን

በፈለገው ሰዓት ሰውን ሁሉ ወደ ሲዖል ያግዛል። ብዙ ጊዜ ሰዎች ዲያቢሎስ ይህን እንዳደርግ

አደረገኝ ይላሉ። ነገር ግን አንድ ጊዜ እንኳን እግዚአብሔር እንዲ አስደረገኝ ሲሉ መስማት

በቅዱሳኑ ዘንድ እንኳ እስካሁን ብርቅ ነው። ምክንያቱም ዲያቢሎስ ክፉና የሰው መብት

የማይጠብቅ ነገር ግን በሰው ፍቃድ ላይ የሚጫን ሲሆን እግዚአብሔር ግን መልካምና ጥሩ ስለ

ሆነ የሰውን ፍቃድ እንደማይጫን ስለ ሚያስቡ ነው። እግዚአብሔር በእኛ ውሳኔ ላይገባ ራሱን

ወስኗል ብለው ስለ ሚያምኑም ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር እኛ የምንወስነውን ውሳኔ ፈጽሞ

ሊያፈርስ ወይም ክፉ ከሆነ ለመልካም ሊገለብጥ አይችልም ይላሉ። ምክንያቱም እኛ በነጻ

ፍቃዳችን መርጠነዋልና ነው። እንግዲህ ይህ ከሆነ የሁሉ ስልጣን ባለቤት ሰው፣ ዲያቢሎስ ወይስ

እግዚአብሔር?

እግዚአብሔር በእኛ አካል ውስጥ ሲኖር ሳለ እኛ ነጻ ፍቃድ ስላለን ሃጢያትን እንሰራለን

አይደል? ነገር ግን ዲያቢሎስ በሥጋችን ሲያድር ደግሞ ሃጢያት እንሰራለን። ይህ ሲሆን እኛ

ሰራነው ወይስ ዲያቢሎስ አስቶን ስራነው? ምን አይነት ዕብደት ነው ወገኔ? ዲያቢሎስ ፍቃዳችን

ይጫናል እግዚአብሔር ግን ፍቃድን አይጫንም ምን? አፋችሁ ላይ እጃችሁን ጫኑ። ይህ ከሆነ

በመጨረሻ 99% የሰው ልጆችን የሚወስደው ዲያቢሎስ መሆኑ ነዋ? መልሱን ለአንባቢው

ተዋለሁ።

Page 12: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

11 www.tlcfan.org

የሁሉ የበላይ ማነው?

ሰይጣን ሁሉን ገዥነት ከእግዚአብሔር ነጠቀውን? እንዲህ አይነቱን ደካማ ጥንቃቄ

የጎደለውና አቅመቢስ እግዚአብሔር ነው የምናመልከውን? እዚህ ጋር ስለ ነጻ ፍቃድ ቆም ብለን

በማሰብ በእግዚአብሔር ቃል ነገሩን መንጥረን የምንመረምርበት ዘመን ይህ ያለንበት ነው።

እግዚአብሔር ከላይ እንዳየነው አይነት አምላክ ከሆነ እንዴት ብሎ ነው ትንቢትን የሚናገረው?

እንዴትስ ትንቢቱ እንደ ሚፈጸም ዕርግጠኞች ልንሆን እንችላለን? ያኔ ዲያቢሎስ እንዳመጸበት

አሁን ደግሞ ማን ያምጽበት ይሆን? ያኔ ሁሉን ሊቆጣጠር ካልቻለ አሁና ወደ ፊትስ እንዴት

አድርጎ ሁሉ ሊቆጣጠር ይችላል? እግዚአብሔር በቸኛና የሁሉ የበላይ ነው።

አንዳዶች ሰው ገና ምርጫውን በነጻ ፍቃዱ ስላልገለጸ እግዚአብሔር ይጠብቃል፦

የሚሉም አሁን አልታጡም። ሰዎች ይህን አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ እግዚአብሔር በነገሮች

ሁሉ ላይ መቆጣጠር አይችልም ማለታቸው ነው። አላዋቂዎችን ዝም እናሰኝ ዘንድ ይህ

የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው። እስቲ ራሳችንን እንጠይቅ ጳውሎስ ወደ ጌታ በተቀየረበት ጊዜ ምን

ያህል ነጻ ፍቃድ ነበረው? ብርሃን ከሰማይ መጥቶ ጣለው፣ አይኑን አሳወረው፣ ከሰማይ የወጣ

ድምጽ ተናገረው፣ አንተ ወይም አንቺ በእርሱ ቦታ ብትሆኑ ለጌታ እንቢ ለማለት ትችሉ ነበርን?

ጳውሎስ ራሱን የሃጢያተኞች ሁሉ ቁንጮ እንደ ሆነ ራሱ ይናገራል።1.ጢሞ.1፥15

ይህን የሚያህል ሃጢያተኛ ጌታ በመሬት ላይ ጥሎ ከዚህ ጀምሮ የእኔ እቃ ነው ብሎ ካለ ይህ

የጳውሎስን ነጻ ፍቃድ የጣሰ ነው ወይስ ያልጣሰ? ይህ እንግዲህ አንዳዶች ከሚሉት ነጻ ፍቃድ

ሊቃረን ነው ወይም እግዚአብሔር ያዳላልን? ይህ ከእኛ ይራቅ። ይህን ለጳውሎስ እንዳደረገ ለሰው

ልጆች ሁሉ ቢያደርገው ምን ይሆን ነበር? ወደ ፊት ይህ ያደገዋልን? ጉልበትን ሁሉ ሊያንበረክክ

ምላስን ሁሉ ጌትነቱን ሊያሳውጅ ይችላልን? ኢሳ.45፥23-25

እንግዲህ ሰዎች እንደ ሚሉት እግዚአብሔር የነጻ ፍቃድን መብት ስጥቶን ከሆነ

እንግዲህ ጳውሎስን ሲያድን እግዚአብሔር ይህን የነጻ ፍቃድ መብት ጳውሎስን ገፎታል ማለት

ነው። ይህ ደግሞ እግዚአብሔርን ፍጹም አያደርገውም። የሰው ልጆች እግዚአብሔር ሁሉን

አያድንም ብለው ያምናሉ። እንዴትስ እግዚአብሔር ሰው ለይቶ ለጥቂቶች ብቻ ይገለጣል?

እግዚአብሔር የሰው ልጆን ሁሉ የሚወድድ ከሆነ ለሰው ልጆች ሁሉ እንደ ጳውሎስ ለምን

አያደርግላቸውምን? የሚሉም አይታጡም። እግዚአብሔር የሰው ልጆች ሁሉ አሁን በአንድ ጊዜ

ማዳን ከፈለገ ሊያድን ይችላል። ማድረግ ያለበት አንድ ነገር ቢኖር ለጳውሎስ እንዳደረገ ለሰው

ልጆች ሁሉ ማድረግ ነው። ሁሉንም በመሬት ላይ እየጣለ እኔ ኢየሱስ ነኝ ካለ ሁሉ ያምናል።

ያኔ ማን ይቃወመዋል ማንስ አልክተልህም ይለዋል?

Page 13: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

12 www.tlcfan.org

ለጳውሎስ እንዳደረገ ለሰው ልጆች ሁሉ በየተራ እንዲህ ቢያደርግ ለምን እንዲህ

ታደርጋለህስ የሚለው ይኖር ይሆንን? ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ማድረግ ግን አልፈለገም።

እግዚአብሔር ሁሉ እርሱ በፈቀደበትና ባቀደበት ቀን ያደርገዋል። ነገር ግን ይህ ሁሉ ሚስጥር

ቤተክርሲያንን የሚያስደስታትት አይመስለኝም። 1.ቆሮ.15፥22 እግዚአብሔር እርዳታ

የሚያስፈልገው እርዳታ ያጣ አምላክ አይደለም። እውነቱ ግን እግዚአብሔርን ሁሉን የሚቆጣጠር

እርሱ ነው። ክፋትንም እርሱ በፈለገው ሰዓት ያቆመዋል። ዋናው ቁም ነገሩ ከእግዚአብሔር ሁሉን

ገዢነትና ሁሉን ተቆጣጣሪነቱን “sovereignty” መውሰድ ሳይሆን ነገሮች ሁሉ አሁን ባሉበት

ሁኔታ ያሉት ለምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ በእግዚአብሔር ቃል መመለስ ነው። ይህን ለማወቅ

ደግሞ እግዚአብሔር ማን እንደ ሆነ በማንነቱ ማወቅን ይጠይቃል። እስቲ በትግስት ቃሉ ቀስ

በቀስ አብረን በልበ ሰፊነት እንመርምር፦

Page 14: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

13 www.tlcfan.org

ሃጢያት እንደ እዳ

ሃጢያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ዕዳ የሚቆጠር ነው። ሃጢያትን በምንሰራበት

ወቅት ለሕጉ ባለ እዳዎች እንሆናለን። ሕጉ አንድ ሰው ጎረቤቱን ቢበድል ሕጉ እንደሚበይንበት

ለጎረቤቱ እዳውን ይመልሳል። ይህም የሚመልሰው ለበዳዮ እንደ እዳ ሰለሚቆጠርበት ነው።

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በጠየቁት መሰረት ጸሎትን ሲያስተምራቸው እንዲህ አለ፦

Forgive us our debts, as we forgive our debtors (Matthew 6:12).

ሉቃስ ይህንኑ ጸሎት ደግሞ ሲጽፈው እዳ ብሎ ማቴዎስ ያስቀመጠውን እርሱ ደግሞ

ሃጢያት ብሎ አስቀመጠው። ከዚህ ተነስተን እዳ ማለት ሃጢያት ማለት እንደ ሆነ በቀላሉ መረዳት

እንችላለን። Forgive us our SINS

በሰዋዊ አስተሳሰብ እዳ ለሁል ጊዜ የሚቀጥል ሊከፈል የማይችል ነገር ነው። ለዕዳም

ሰው የሚሰጠው ዘላለማዊ ቅጣትን ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕግ ለእዳ እንደ ሰው ዘላለማዊ

ቅጣትን አይሰጥም። ሰዎች የእግዚአብሔርን ሕግና ባሕሪውን ካለማወቃቸው የተነሳ የብሉይ ኪዳን

እግዚአብሔር በጣም ጨካን እንደ ሆነ የሚያስቡ በጣም እጅግ ብዙ ሰዎች ናቸው።

አንዳንድ ሰዎች ልክ ማቴዎስ 18 ላይ እንዳለው ሊከፍለው የማይችለው እዳ እንደ

ነበረበት ሰው ነን። ሌሎችን ማስጨነቅ እንወዳለን። ከዕዳው ብዛት የተነሳ ይህ ሰው ሚስቱ፣

ልጆቹና ያለው ሁሉ እዳውን እስከሚከፍል ድረስ ተሸጡ ያም ሆኖ እዳውን መክፈል አይችልም

ነበር። ምክንያቱም እዳው ከአቅሙ በላይ ነበር። ያለው ሁሉ በዕዳ ቢያዝም የጠፋውን ንብረት

ፈጽሞ ሊተካ አልቻለም።

“23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች። 24 መቈጣጠርም

በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። 25 የሚከፍለውም

ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ፣”

ይህን አስቡ አዳም በእግዚአብሔር ሚስት ተሰጥቶት ነበር። ልጆችም ነበሩት። ደግሞም

በምድር ላይ ይገዛ ዘንድ ግዛትም ተሰጥቶት ነበር። አዳም ያለው ሁሉ ሚስት፣ ልጅና በምድር

ያለው ሁሉ ነው። አዳም ሃጢያትን ሲሰራ ይህ ያለው ሁሉ ለሃጢያት ተሸጠ። ሰው ሁሉ የሃጢያት

ባሪያ ሆነ። ኢየሱስም የሃጢያትን እዳ እስከ ሚከፍልበት ቀን ድረስ ምድር የአዳምን ሃጢያት እዳ

መዝገብ ይዛው ነበር። ኢየሱስ የእዳ መዝገባችንን ከፈለና ከሃጢያት ነጻ አወጣን። ኢየሱስ የሰሙ

ትርጉም ራሱ አለሙን ከያጢያት የሚያድን ማለት ነው። ስሙን ስንጠራ ምን እያልን እንደሆነ

መገንዘብ ይገባናል። ከሃጢያት ባርነት ደግሞ ነፃ ስንወጣ የኢየሱስ ባሪያዎች የጽድቅ ባሪያዎች

እንሆናለን። ይህም ጳውሎስ በሮሜ.1፥1, ላይ ራሱን እንደገለጸ ማለት ነው። ሮሜ. 6፥15-19

ያንብቡ።

Page 15: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

14 www.tlcfan.org

ኢዮቤልዮ የእዳ ፍጻሜ

በማቴዎስ 18 ላይ ያለው ሰው እዳ (ሃጢያት) እስከ መቼ ድረስ በግዞት የሚያቆየው

ነበር? በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ ለማንኛውም አይነት እዳ ነጻ የሚወጣበት ኢዮቤልዮ የሚባል

የቀን ገደብ እንዳለው ቃሉ ይናገራል። ይህ ታላቁ የእግዚአብሔር የምሕረት ሕግ ነው። ማቴ.18፥

22

ሰው ራሱን የፈለገ ቢሆን በእዳ ለዘላለም የመሸጥ ምንም አይነት ነጻ ፍቃድ የለውም።

ምክንያቱ ራሱን ለሁል ጊዜ መሸጥ እንዳይችል እግዚአብሔር በኢዮቤልዮ ሕግ ገደብ

አድርጎበታልና ነው። ይህ ሕግ ለመጣስም ሆን ማሻሻያ ለማድረግ ምንም ስልጣን ለሰው የለውም።

እዚህ ጋር ነጻ ፍቃድ የሚባል ሃሳብ ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያከትማል። ምክንያቱም እኛ

የእኛ የራሳችን ባለቤት አይደለንም። በራሳችን ላይ ያለን ስልጣን ውስን ነው። ሰናገባ በትዳር

ውስጥ ስንገባ ደግሞ በራሳችን ያለችንን ትንሿ ስልጣናችንን እንኳን ካገባነው ሰው ጋር

እንካፈለዋለን።

ባለቤትነት“Ownership” የእግዚአብሔር ነው። የሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር ስለሆነ እኛ

ያለን በተሰጠን ነገር ላይ ሁሉ ሕይወታችንንም ጨምሮ ከእርሱ ፍቃድና ስልጣን በታች የሆነ

ስልጣን ነው። ይህ ባለቤትነት ስንል ልክ አንድ ሰው የመሬት ወይም የቤት ባለቤት እንደሚሆን

ባለቤትነት ማለት ይህ ነው። በእግዚአብሔር አይን ሲታይ እኛ በምንም አይነት ነገር ላይ ባለቤት

የሆንበት ነገር የለንም። የምድር ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር እራሱ ነው። ዘሌ.25፥23 በዚህ ምድር

ላይ ግን ከእግዚአብሔር ሕግና የበላይነት ከጌታችን በታች የሆነን ስልጣን ከእርሱ ከራሱ

ተቀበለናል።

ለእኔ ይህ እውነት ከበራልኝ በኃላ በዓለም ያለው ክፋት ሆነ ምን ያህል እዳ ሰው

ይኑርበት ምንም ያህል ይህ ዓለም ወደ ከፋ መንፈስ ዝቅጠት ይውደቅ ኢዮቤልዮን ስለማያልፍ

እግዚአብሔር እጅግ አድርጌ ስለ ከበረው ሕጉ አከብረዋለሁ። በእውነትም ዳዊት እንዳለው

የእግዚአብሔር ሕግ ነፍስን ይመልሳል። ኢዮቤልዮ የማይችለው፣ የማይገድበውና የማይከፍለው

ምንም አይነት እዳ የለም። ኢዮቤልዮ የማይሰርዘው ማንኛውም አይነት እዳ የለም። የእግዚአብሔር

ሕግ ምሕረትን የተሞላ ነው። ማቴ.23፥23, ያቆብ.2፥13

ታዲያ እግዚአብሔር ጳውሎስን እንዳዳነ የሰው ልጆችን ሁሉ ለምን አያድንም?

ጳውሎስ ነጻ ፍቃዱን ተጭኖለት ስላዳነው ከእግዚአብሔር ለየት ያለ እንክብክቤ ተደርጎለታልን?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ የሃጢያተኞች ቁንጮ እንደ ሆን በእራሱ ላይ የሚመሰክረውን ይህን ሰው

ይህን አይነት ማዳን ካደረገለት ታዲያ ለምን ለሌላው ሰው ይህንን አያደርገውም? ለሚጠፉት

ሰዎች ተጠያቂው ማነው?

Page 16: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

15 www.tlcfan.org

የምድር ሕግ

ፈጣሪያችን እግዚአብሔር የምድር ሕግ አለው። ይህን የነጻ ፈቃድ ሃሳብ በጥቂቱ

ከተረዳን ከዚህ ያለፈ በጣም ልንረዳው የምንፈልገውን ነገር አለ። ይህም ስለ ነጻ ፍቃድ ሳይሆን

ሰለ ባለቤትነት “ownership” ነው። ይህን በደንብ ለመመልከት የእግዚአብሔር ሕግና ቃል ውስጥ

የተለያዮ ጥቅሶችን እንመልከታለን። ይህም ከምድር ሕግ ጋር የተያያዘ ነው።

“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” ዘፍ.1፥1

መቼም ቢሆን አንድ ነገር ለመጀመር ከዘፍጥረት መነሳት መልካም ነገር ነው። ሁላችን

እግዚአብሔር ፈጣሪ እንደ ሆነ እናምናለን? አንዳንድ የሃይማኖት ድርጅቶች ምድርን ዲያቢሎስ

እንደ ፈጠረው ያምናሉ። የጥንት ግሪኮች የሚታየውና የሚጨበጠው ግዑዙ ዓለምና በውስጡ

ያለው ክፋት በዲያቢሎስ የተፈጠረ ለሰው ልጆች የተዋወቀ ርኩስ ነገር ነው ብለው ያምናሉ።

ይህ በእግዚአብሔር ቃል ሰናየው መሰረት የሌለው ውሸት ነው።

የሚታየው ነገር በእግዚአብሔር የተፈጠረና በራሱ በእግዚአብሔር “መልካም” መሆኑ

የተመሰከረለት እንጂ የሚታየው ጉዑዙ ዓለም በዲያቢሎስ የተፈጠረ ወይም የክፉ ውጤትና ክፉም

አይደለም። ዘፍ.1፥10,12,18,21,25,31

ክርስቲያን እንደ መሆናችን መጠን ሁሉን እግዚአብሔር እንደ ፈጠረ እናምናለን።

እግዚአብሔር ደግሞ መልካም አምላክ እንጂ ክፉ አምላክ አይደለም። የብሉይ ኪዳኑ አምላክ

የአዲስ ኪዳኑም አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነው።

አንዳንድ ሰዎች የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔር በጣም የሚቆጣ ጨካኝ ነገር ግን የአዲስ

ኪዳኑ ደግሞ መልካም የሚወደድ አምላክ ነው ብለው ያምናሉ። እንግዲህ እነዚህ ሰዎች እርስ

በእርሱ የሚቃረን ባሕሪ ያለው አምላክ ያመልካሉ ማለት ነው። ለእኔ ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው።

እግዚአብሔር ሰውን ጨምሮ ሁሉን ፈጥሯል። ዘፍ.2፥7

“7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው። በአፍንጫውም

የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።”

እዚህ ላይ ተመልከቱ እግዚአብሔር ሰውን ያበጀው ከምድር አፈር ነው። ይህ አካል

የተበጀለት በዘፍ.1፥1 ላይ ከተፈጠረው ምድር ነው። ዲያቢሎስ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ

ከፈጠረው ከምድር ለዚህ በእግዚአብሔር ለተፈጠረው ሰው አስቀድምሞ ከፈጠረው ከምድር አፈር

አካልን አበጀለት። ለዚህ ነው እግዚአብሔር ሰውን እንኳን ሃጢያት ከሰራ በኃላ አፈር ነህና ወደ

አፈር ትመለሳለህ የሚለው። የሥጋ ሞት በምንሞትበት ወቅት ሥጋችን ወደ አፈርነት ይለወጣል።

ይህም አፈር አካላችን አስቀድሞ የተበጀበት የአካላችን መሰረት ነው። ዘሌ.25፥23-24

Page 17: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

16 www.tlcfan.org

“23. ምድርም ለእኔ ናትና። እናንተም ከእኔ ጋር እንግዶችና

መጻተኞች ናችሁና ምድርን ለዘላለም አትሽጡ።24.

በርስታችሁም ምድር ሁሉ መቤዠትን ለምድሪቱ አድርጉ።”

ይህ የእግዚአብሔር የምድር ሕግ ነው። ምድር ሁሉ ጊዜ የግድ መቤዠት ይገባታል።

እግዚአብሔር የምድር ሕግ ስላለው ሕዝበ እስራኤል ከነዓን ሲገቡ ኢያሱ መጀመሪያ በነገድ

ከዚያም በየግለስብ ምድርን አከፋፈላቸው። እያንዳዱ ስው የራሱ የሆነ ምድር ተሰጠው የራሱ

የሆነ ምድር በእግዚአብሔር ወረሰ። ይሁንና ምድር ብትሰጣቸው ምድሪቱ ግን የእነርሱ

አልነበረችም ምድር የእግዚአብሔር ነበረች። እነርሱም በምድር ላይ የበላይነት ስልጣን

ከእግዚአብሔር ከእርሱ በታች በመሆን እንዲያስተዳድሩ ስልጣን ተሰጣቸው።

በዚህ ባለንበት ዘመን መንግስታት “eminent domain” የሚሉት ነገር አላቸው።

የአንድ መንግስት በምድር ላይ ይህ የታወቀ ስውር አገዛዛቸው ወይም ሕጋቸው ነው። ምንም

እንኳን ቤት የሰራንበት መሬት ለእኛ እንደ ሆነ በወረቀት የተረጋገጠ መረጃ ብንይዝም እንኳን

መንግስት በቤቱ ላይ የሚያልፍ መንገድ መስራት ቢፈልግ ይህን “eminent domain” ስልጣኑን

በመጠቀም ቤታችንን እራሱ የቤቱን ዋጋ በመተመን ያፈርሰዋል መንገዱንም ይሰራል።

በቀላሉ ይመጣሉ መሬቱን ይገዙታል። እዚህ ጋር እንቢ ማለት ፈጽሞ አይቻልም።

እንግዲህ መንግስት በእጃችን ላይ ምንም እንኳን በወረቀት የተረጋገጠ መረጃ ባይሰጡንም ቤታችን

በቆመበት ምድር ሁሉ ላይ “eminent domain” አላቸው።

ልክ እንደዚሁ ደግሞ እግዚአብሔር ደግሞ ከምድር አፈር በተበጀው አካላችንና ምድር

ላይ “eminent domain” አለው። ይህም እግዚአብሔር ሁሉ ስለ ፈጠረ ነው። የተፈጠሩት ነገሮች

ምንም ቢሆኑ ፈጣሪው ባለቤት ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ስለ ፈጠረ የሁሉ ባለቤትነት

“ownership” እርሱ ነው። እስራኤል ሁሉ ምድርን ሲወርስ በምድር ላይ የተሰጠው የተወሰነ

ስልጣን ነው። በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጣሪነትን ባለቤትነትን ለማንም ሰጥቶ አያውቅም።

የምድር ባለቤት እርሱ ነው። ስልጣን ደግሞ በባለቤቱ ፍቃድ ላይ የተወሰነ እንጂ ምድሩን

ሊያስተዳድር በተሰጠው ሰው ፍቃድ ላይ አይደለም።

Page 18: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

17 www.tlcfan.org

ባለቤትነትና ነጻ ፍቃድ

እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው። እግዚአብሔር ምድንን በመፍጠር

ባለቤትዋ ከሆነ እኛም ከምድር አፈር ተበጅተናል። በእርሱም ተፈጥረናልና የእኛ ባለቤት እርሱ

እግዚአብሔር ነው። እንግዲህ እዚህ ላይ ልብ ብለን እናስብ አንተ ነጻ ፍቃድ አለህ ወይም የለህም

አይደለም ጥያቄው። ዋናው ቁምነገሩ የአንተ ባለቤት ማነው ነው። who owns you? በባለቤትነት

እግዚአብሔር የምድር ባለቤት መሆኑን የሚክድ አለን? እግዚአብሔር ሰውን ከዚህ ከምድር አፈር

ሰርቶታልን? እግዚአብሔር ሁሉ ከፈጠረ እንግዲህ የሁሉ ባለቤት እርሱ ነው። የሚታየው ቢሆን

የማይታየው በእርሱ ተፈጥሯልና የሁሉ ባለቤት እርሱ ነው። ቆላ.1፥15-17

ቀኑን ሙሉ ሰው ነጻ ፍቃድ አለው ወይም የለውም እያልን ጥቅስ እያነሳን ልንከራከር

እንችላለን። ነገር ግን ወደ ባለቤትነት እውቀት ከመጣን ግን ሁሉ ቀላል ከክርክር የሚያርቅ

መልካም መልስ ይሆናል። ዋናው የሁሉ ባለቤት ማነው ነው? ምክንያቱም ይህንን ልናውቅ

ይገባናል።

በዘጸ.21 ላይ ያሉት የእግዚአብሔር ሕጎች ስናጠና ባለቤትነትን ማወቅ በጣም

እግዚአብሔርን ለመረዳት ወሳኝ ቁልፍ እንደ ሆነ እንገነዘባለን። እንግዲህ ይህን እኛን አሁን ጥያቄ

ሊመልስልን የተገባው በምድር ላይ ላለው ለዚህ ለክፉ ነገር ተጠያቂው ማን ነው? የሚለው ጥያቄ

መልስ ነው። ቤተክርሲያን የእግዚአብሔርን ከተጠያቂነት ዞር ለማድረግ ስትል በትምህርቷ

ለሰውም ሆነ ለመላእክት ነጻ ፍቃድ የሚሰጥ ትምህርት አውቃ ይሁን ሳታውቅ በቤቷ ተክላለች።

በምድር ላይ ስለ ሚሆነው ማንኛውም ክፉ ነገር እግዚአብሔር ተጣያቂ ለማድረግ

ማንም አይደፍርም። ስለዚህም ይህን ሃላፊነት በሰውና በዲያቢሎስ ላይ ሰዎች ይጭናሉ።

ከእግዚአብሔር ተጠያቂነትን ለማውረድ ካልሆነ ታዲያ የነጻ ፍቃድ ትምህርት መኖሩ ዓላማ የቱን

ችግር ለመፍታት ነው? ነጻ ፍቃድ የሚል አንድ ጥቅስ እንኳን በቃሉ ውስጥ የለም። ታዲያ ለምን

እናሰተምረዋለን?

ዲያቢሎስን የፈጠረው ማነው? ሰውንስ የፈጠረው ማነው? እግዚአብሔር ደግሞ ሁሉ

ከፈጠረ በመፍጠር ሕግ የባለቤትነትንና የተጠያቂነትን ስፍራ ይይዛል። ክፋትን ሰውም ይሁን

ዲያቢሎስ ቢፈጥረው የሁለቱም ፈጣሪ እግዚአብሔር እስከ ሆነ ድረስ እርሱን ከተጠያቂነት ፈጽሞ

ነጻ አያወጣውም። ምንም እንኳን ፍጡሩ የተፈጠረው እንበልና ነጻ ፍቃድ ቢኖረውም በተፈጠረው

ነገር ላይ የሚመጣው ማንኛውም ችግር ተጠያቂው እንደ ሕጉ ፈጣሪው እራሱ ነው። በዚህም ሆነ

በዚያ እርሱን ከተጠያቂነት በሰዋዊ ጥብና እውቀት ነጻ ማውጣት ማንም አይችልም። ምክንያቱም

እግዚአብሔር በሕጉ ራሱን ተጠያቂ አድርጓልና።

Page 19: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

18 www.tlcfan.org

በባለቤትነት የሚመጣ ተጠያቂነት

ይህንን ሃሳብ በይበልጥ ለመረዳት የባለቤትነትን ሕግ ከእግዚአብሔር ቃል እንመልከት።

“33.ሰውም ጕድጓድ ቢከፍት፥ ወይም ጕድጓድ ቢቈፍር ባይከድነውም፥

በሬም ወይም አህያ ቢወድቅበት፥ 34. የጕድጓዱ ባለቤት ዋጋቸውን

ለባለቤታቸው ይክፈል። የሞተውም ለእርሱ ይሁን።” ዘጸ.21፥33-34

ass fall therein; 34 the owner of the pit shall make it good, and give money unto the owner of

Exodus 21:33-34

እዚህ ላይ ተጠያቂነትን እንደ ምንመለከተው ከባለቤትነት ጋር የተያያዘ መሆኑን ነው።

ሰው ጉድጓድ ቆፈረ ነገር ግን ማንም ወደዚያ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እንዳይሰናከል የሚያደርግ

ቅደም ተከተል ያለው መከለያ ወይም መከላከያ አላደረገበትም። ስለዚህ በሬው እንበልና በራሱ

ነጻ ፍቃድ ወደ እዚህ ጉድጓድ እራሱን ጣለ። ምናልባት ይህ በሬ ይህን በማድረጉ መሃይም፣

የማይገባው፣ እየተነገረው የማይሰማና የማይታዘዝ ሆኖ ሊሆን ይችላል። እንደ እግዚአብሔር ሕግ

መሰረት ተጠያቂው ማነው? ጉድጓዱን የቆፈረው ሰው ነው።

እንግዲህ ይህ ነው የተጠያቂውን ማንነት ምክንያትና ገደብ የሚያበጅ ሕግ ይህ ነው።

በሕጉ መሰረት ምንም እንኳን በሬው ራሱን በጉድጓድ ውስጥ ቢጥልም ተጠያቂው ግን የጉድጓዱ

ባለቤት ነው። ስለዚህም ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የሞተውን በሬ ለራሱ ይገዛዋል። ልክ በሬውን

እንደ ሕያው በሬ ቆጥሮ ለበሬው ባለቤት የበሬውን ዋጋ ይመልሳል። የሞተው በሬ ደግሞ ለእርሱ

ይሆናል።

በዔደን ገነት ውስጥ እግዚአብሔር ጉድጓድን ቆፈረ ጉድጓዱን እግዚአብሔር

አልሸፈነውም። ስለዚህም ሰው ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ወደቀ ሞተ። ሰው ለምን ወደቀ? ለምንስ

ሞተ? እግዚአብሔር በዔደን ዛፍን ስለ ተከለ ለሰውም ከእርሱ በራሱ ፍቃድ እንዲ በላ ነጻ ፍቃድ

ስለ ሰጠ ነው እንበል። እግዚአብሔር ሰው ይህን ነገር እንደሚያደርግ አስቀድሞ በቀደመ እውቀቱ

ያውቅ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ሰው እንዳይወድቅ ጉድጓዱን አልሸፈነውም። እንግዲህ

እግዚአብሔር እዚህ ላይ ጉድጓዱን እንደ ቆፈረው ሰው ቅድሚያ ዝግጅት ወይም ማንም ገብቶ

እንዳይወድቅ ከለላ አላደረገም ማለት ነው። በመልካምና ክፉ በምታስታውቀው ዛፍ ከተበላች በኃላ

ከለላት። በፊት አሰቀድሞ ግን ማንም ወደ እርሷ እንዳይቀርብ አልከለላትም ነበር። ሰው ከዚህ

የተነሳ ወደቀ እግዚአብሔር ሰው እንዳይወድቅ ማድረግ ሲችል ከለላ ባለማድረጉ ሰው ወደቀ።

Page 20: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

19 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር ሰው ሃጢያት ከመስራት መከልከል ይችል ነበር? አዎ ይችል ነበር።

ዛፉን ለመትከል ወይም ከተከለው በኃላ ሰው ገብቶ ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከለላ ሊያበጅለት

ይገባ ነበር። ይህ ብቻ አይደለም ሰው ወደዚህ ጉድጓድ እንዲወድቅ ወይም ይህን የዛፍ ፍሬ

እንዲበላ የሚያደርግ የሚፈታተን ዲያቢሎስ በዔደን ገነት አስቀድሞ ባልፈጠረም ነበር። ፈታኙ

ሰይጣን ከእግዚአብሔር እውቀት ውጪ ወደ ሰው መጣን? እግዚአብሔር የገነት አላርሙን

ማብራቱን ረስቶስ ዲያቢሎስ ይህ እድል ተጠቅሞ እግዚአብሔር ሳያውቅ በዔድን ሰውን ሊፈትን

ገባን? እግዚአብሔር ወየው ረስቼው አይ እኔ አለን? በእውኑ እግዚአብሔር ይህን ያህል መሃይም

የሆነ አምላክ ነውን? ይህ ከእኛ ይራቅ። እግዚአብሔር በሥራው ፍጹምና ጻድቅ ነው።

እውነቱና እኔ የማምነውና የማመልከው አምላክ የመጨረሻውን ከመጀመሪያው

የሚያውቅ አምላክ ነው። እግዚአብሔር ምንም ነገር በአጋጣሚ “surprise” አላደረገውም።

እግዚአብሔር ጉድጓድ ቆፍሮ ሰው እደሚወድቅ እያወቀ ክፍት ተወው ይህም የራሱ የሆነ

መለኮታዊ ዓላማ ስላለው ነው። ደግሞ እንደ ሕጉ ራሱን እግዚአብሔር ተጠያቂ ለማድረግ ነው።

ከዚህም የተነሳ ውድቀት ከእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ አንዱ ሆነ። ይህ የእግዚአብሔር እቅድ

ሰውን እንዲወድቅ አደረገው። እግዚአብሔር እንዳቀደውም ሰው ወደቀ። በእግዚአብሔር

የባለቤትነት ተጠያቂ ሕግ መሰረት እግዚአብሔር አሁን ሰለ ሰው ልጅ ውድቀት ራሱን ተጠያቂ

አደረገ። ስለዚህ እንደ ሕጉ መሰረት ታዲያ እግዚአብሔር ምን አደረገ?

እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ላከ ይህም የሰውን ልጆች ሁሉ ከወደቁበት ጉድጓድ ወደ

ራሱ እንዲስባቸው እንዲያወጣና እንዲወስዳቸው የእርሱ እንዲሆኑ ነው። በዚህም ሆነ በዛ ሁሉ

የእግዚአብሔር ነው።

የዓለም ሁሉ ሃጢያት እዳ በመስቀል ላይ ከፈለ። ምክንያቱም ሁሉ ፍጥረት በአዳም

ውድቀት ውስጥ ሆኖ ሰው ሁሉ ለሞት ተገዝቶ “subject to death” ነበርና ነው። ሮሜ.8፥20-21,

11፥32 የሞተውን በሬ በልጁ በኩል በደሙ ገዛው አሁን የሞተው በሬ በአዳም ውስጥ የሞተው

ሰው ሁሉ ነው። በኢየሱስ ደግሞ በሕያው በሬ ተቀይሮ የእርሱ ሆነ። የሞተው ለእርሱ ይሁን

ሕያውን ይክፈል የሚለው ሕግ በኢየሱስ በእግዚአብሔር ፍቃድ በመስቀል ታልፎ በመሰጠት

ተፈጸመ። ሐዋ.2፥23 ሃሌ ሉያ

“ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም።”

ሮሜ.8፥20

“14 ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ

ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።

Page 21: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

20 www.tlcfan.org

15 ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ

ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ

ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ። 16 አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን

እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ

በደል ለማጽደቅ መጣ። 17 በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና

የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ። 18

እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ

ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ። 19 በአንዱ ሰው

አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን

ይሆናሉ።” ሮሜ.5

ይህ ምን ማለት እንደ ሆነ በእውነት ትረዳላችሁን? እግዚአብሔር የወደቁና የሞቱትን

ሁሉ ገዛ አሁን ሁሉ የእርሱ ናቸው። መውደቅን ያመለጠ ሰው ነበርን? እውነት ነው አሁን

በእምነት ማየት ካልሆነልን በቀር ሁሉ የእርሱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ሁሉን እንደሚገዛ ማየት

ከባድ ነው።

እግዚአብሔር በራሱ ሕግ መሰረት ተጠያቂነትን በራሱ ላይ አድርጓል እግዚአብሔር

ደግሞ እጁን አጣምሮ ስለ ሆነው ነገር ዝም ብሎ አልተቀመጠም። ነገር ግን ስለ ሞተው በሬ

የሚገባውን ዋጋ በመክፈል የሞተውን በሬ ለራሱ በመግዛት ሕጉን በሚገርም ሁኔታ ፈጸመው።

ይህ ነው የአዲስ ኪዳን መልካም ዜና “ወንጌል” የኢየሱስ ደም የዓለምን ሰው ሁሉ ለመግዛትና እዳ

ለመክፈል በቂ መለኮታዊ የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው። የመስቀሉ ስራ ሌላ ተጨማሪ የሰው

ጥረትና ማንኛውም አይነት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የማያስፈልገው በውድ ልጁ ብቻ የተሰራ

ታላቅ መለኮታዊ እቅድን የያዘ ድንቅ ሥራ ነው።

2 እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ

ኃጢአት እንጂ።3 ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።4 አውቄዋለሁ የሚል

ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።”1ዮሐ.2፥2

and not for ours only, but also for

the sins of the whole world 1 John 2:2

በጉድጓድ ስለ ወደቀው በሬ በቅርበት እስቲ እንመልከት። በሬው አውቆም ሆነ ሳያውቅ

ሳያየው ወደ ጉድጓዱ ቀረበ፣ በሬው በነጻ ፍቃዱ፣ በእውርነቱ ወይም በአላዋቂነቱ ጉድጓድ ውስጥ

ወደቀ። ሕጉ በትክክል እንደሚናገረው የፈለገ ይሁን ጥያቄው ያለው በሬው ያውቃል ወይም

አያውቅም? ዕውር ነው ወይስ ያያል? ራሱ ፈልጎ ነው ፈልጎ አይደለም?

Page 22: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

21 www.tlcfan.org

በነጻ ፍቃዱ ተጠቅሞ ነው አይደለም? የሚል ጥያቄ ላይ ጊዜ አያባክንም። ነገር ግን

ሁሉ የበሬውንም ጥፋት ጨምሮ የጉድጓዱ ባለቤትን በጠያቂነት ያቆማል። የጉድጓዱ ባለቤት ስለ

ሞተው እንዲከፍል የሞተውንም እንዲወስድ ይደረጋል። በሌላ መልኩ ደግሞ በሬ እንዲጠፋ

ቢያደርግ በሌባው በሬውን ቢያሰርቀው አሁንም አደራ ተቀባዮን ባለቤት ከተጠያቂነት

አያድነውም።

“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በበሬው ፋንታ አምስት

በሬዎች፥ በበጉም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።” ዘጸ.22፥1

ምንም እንኳን በአጋጣሚ ቢወድቅ ወይም ቢሰረቅ ባለቤቱን ጠባቂውን ተጠያቂ

ያደርገዋል። ሰው በራሱ ፍቃድ ወደቀ ወይም ሌባው ዲያቢሎስ ሃሳቡን ሰርቆት ወደቀ እዚህ ላይ

ምንም እንኳን እውነታ ያለው ቢመስል ይህ አስፈላጊ አይደለም። ዋናው የዛፉ ባለቤት ማነው?

ሌባውን ዲያቢሎስ የፈጠረው ማነው? ነው። የባለቤትነት ሃላፊነት ጥያቄ ከሁሉ በላይ የሆነ ሁሉን

የሚጠቀልል ነው። ሌላ የእግዚአብሔር ሕግ ደግሞ እንመልከት።

“አዲስ ቤት በሠራህ ጊዜ ማንም ከእርሱ ወድቆ ደሙን በቤትህ ላይ እንዳታመጣ

በጣራው ዙሪያ መከታ አድርግለት።” ዘዳ.22፥8

house, then thou shalt make a battlement for thy roof, that

Deuteronomy 22:8

በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ሰው ጣሪያን ቢሰራ በጣሪያው ዙሪያ መከታ (አጥር)

ማድረግ በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት የግድ ይገባዋል። ይህም ማንም ሰው ከጣሪያው ላይ ወድቆ

እንዳይሞት ነው። ነገር ግን የቤቱ ባለቤት በጣሪያው ዙሪያ አጥር ሳያደርግ ሰው ከጣሪያው

ከከፍታው ላይ ወድቆ ቢሞት ተጠያቂው በጣሪያው ዙሪያ አጥር ያላደረገው የቤቱ ባለቤት ነው።

እግዚአብሔር የዚህ የሟችን ሰው ደም ከባለቤቱ እጅ ይጠይቃል።

አንድ የጎረቤት ሰው አንድን ሰው ከጣሪያው ላይ ገፍቶ ቢጥለው ሰለ ነፍስ ማጥፋት

በሚጠየቀው የእግዚአብሔር የነፍሰ ገዳይ ሕግ መሰረት ጣዮ ሰው ነው። ነገር ግን ይህ አሁንም

ባለቤቱን ነጻ አያወጣውም መከታ (አጥር) ማድረግ ሲገባው ስላላደረገበት አሁንም የቤቱ ባለቤትም

ከገፍታሪው ጋር በፍርድ ተጠያቂ ነው። ነገር ግን ሁለቱ የተለያየ ቅጣት ይቀበላሉ።

በመጀመሪያ ሕጉ የሚጠይቀው የቤት ባለቤት ማን ነው? የሚል ጥያቄ ነው። እርግጥ

ቤቱ ያንተ ወይም ያንቺ ከሆነ ተጠያቂ አንተ ወይን አንቺ ነሽ። በድንገት እንኳን የሆነ ነው ብንል

ከተጠያቂነት አናመልጥም።

Page 23: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

22 www.tlcfan.org

የእግዚአብሔር ቤት ሰማይና ምድር መላው የሚታየውም ሆነ የማይታየው ዓለም

ነው። አሁን ማደሪያው በሰማይ ነው ወደ ምድር ደግም የሚመጣው ማደሪያውን ከሰው ልጆች

ጋር በአዲስ ሰማይና በአዲስ ምድር ለማድረግ ነው። በምድር ላይ ቤቱን መስራት ሲጀምር ሰው

ወደቀ ተጠያቂው ማነው? ሁላችንም እንደምንስማማው እግዚአብሔር ሰውን ከጣሪያ ላይ

አልገፋውም ወይም ገፍትሮ አልጣለውም። ስለዚህ ማንም እግዚአብሔር ስለ ነፍሰ ገዳይነት

ሊጠይቀው አይችልም። ደግሞም ተጠያቂነትን ከእግዚአብሔር ለማንሳት ብለን ደግሞ በዲያቢሎስ

ላይ ብቻ አናመካኝም ወይም ሰው ግድ የለሽ ስለ ሆነ ራሱን ከጣሪያ ከከፍታ ላይ ጣለም ልንል

በሰው ላይ ብቻም ልናሳብብ አንችልም። ስለዚህ በሙሉ የሰው ጥፋት ነው ብለን በሰው ላይ

ልንደመድምም አንችልም። የምንችልበትም ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃም የለንም። የቤቱ

ባለቤትነት ሕግ የሆነው የራሱ የእግዚአብሔር ሕግ እግዚአብሔርን ተጠያቂ እንደሚያደርገው

ያረጋግጣል። ገፍታሪውና አጥር ያላበጀው ባለቤት ሁለቱም ተጠያቂዎች ናቸው። ለሁለቱም

የሚፈርደው የተለያየ ሕግ ነው።

ይህን ሃሳባችንን በይበልጥ ደግሞ እንድንረዳ የሚያደርገን ሦስተኛ ምስክራችን የሆንው

ቃል ደግሞ እግዚአብሔር ቃል እንመልከት።

“ማንም ሰው ወደ እርሻ ወይም ወደ ወይን ስፍራ ከብቱን ቢነዳው፥የሌላውንም እርሻ ቢያስበላ፥

ከተመረጠ እርሻው ከማለፊያውም/ በኩሩን/ ወይኑ ይካስ።” ዘጸ.22፥5

shall feed in another man's field; of the best of his own field, and of the best of

Exodus 22:5

አንድ በሬ በራሱ ፍቃድ የታጠረውን አጥር ጥሶ ሄዶ የሌላውን እርሻ ቢያጠፋ ምን

ይሆናል? በሬውም ቅጥሩን ጥሶ ስለ በላው ወይም ሰለሚሆነው ነገር ሁሉ ተጠያቂው ማነው?

ከፋይስ ሊሆን የሚገባው ማነው? ሕጉ ግልጽ ነው ከፋይ የበሬው ባለቤት ነው። ለምሳሌ የበሬው

ባለቤት አጥሩን ከፍቶ በሬውን ወደ ሌላ ሰው እርሻ አሰገብቶ ብላ ካልበላህ እገድልሃለሁ ብሎ

በሬውን አፉን ወደሚበላው ቢያስጎነብሰው በሬውም በርሻው ላይ የተዘራውን ለመብላት ቢገደድ

ተጠያቂው ማነው?

የበሬው ባለቤት ነው። የአስገዳጁ ባለቤት ደግሞም አስገዳጁ ነው። እዚህ ላይ ባለቤቱ

አውቆ አጥሩን አስጥሶታልና ሕጉ እጥፍ ቅጣትን ይጠይቃል። የበሬው ባለቤት ለእሻው ባለቤት

ዋጋውን ለባለ እርሻው ይመልሳል። በሬው ግን ማንም ሳይገፋው በራሱ ፍቃድ ቢኔድና ቢበላ

አሁንም ተጠያቂው የበሬው ባለቤት ነው። ነገር ግን አንድ ጊዜ ይከፍላል እንጅ እጥፍ

አይጠየቅም።

Page 24: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

23 www.tlcfan.org

ችግሩን ሁሉ በበሬው ላይ መጣል ባለቤቱን ነጻ አያወጣውም። በሬው በራሱ ፍቃድ ገብቶ

በላ ሌላ ሰው ገፍቶት ወይም ዲያቢሎስ ገፍቶት በላ ባለቤቱን ከተጠያቂነት ፈጽሞ አያድነውም።

የእግዚአብሔር ፍጹም ዘላለማዊ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ከሕጉ ውጪ አይሰራም። ሕጉ ለእኛም

ሆነ ለእግዚአብሔር የሚሰራ መለኮታዊ መንፈሳዊ በመንፈሳዊው ዓለም የሚሰራ መንፈሳዊውን

ዓለም ሕልውና የሰጠ ከራሱ ማንነት የወጣ ሕግ ነው።

የቲዮሎጂያን የነጻ ፍቃድ ለሰው ሆነ ለመላእክትና ለዲያቢሎስ መስጠት እግዚአብሔርን

ከተጠያቂነት ለማራቅ ነው። እግዚአብሔር ግን በቃሉና በሕጉ ራሱን ተጠያቂ እንዳደረገ

ያሳየነናል። ሰው እንጂ እግዚአብሔር ጠበቃ አያስፈልገውም። የነጻ ፍቃድ ትምህርት ያመጡት

“evolutionists” ናቸው።

የሚታየውና የማይታየው ዓለም ባለቤት እግዚአብሔር እንደ ሆነ መናገርን አይደፍሩም።

አንዳዶች ደግሞ ይህ የሚታየው ዓለም የዲያቢሎስ ነው ብለው ያምናሉ። እግዚአብሔር ግን

ሰማይም ሆነ ምድር የእርሱ እንደ ሆኑ እርሱ ራሱ እንደ ፈጠራቸው በቃሉ ይናገራል። በእነርሱ

ላይ ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ራሱን ተጠያቂ ያደርጋል። በጥቅሉ ራሱ እግዚአብሔር ሃላፊነትን

ይወስዳል። ሰው እንደ ሰውነቱ በሕጉ የሚገባውን ይቀበላል። ይሁንና ሰው ነጻ ፍቃድ የለውም።

ልክ እንደዚሁ ደግሞ የግሪክ ፈላስፎች ከእግዚአብሔር ላይ ተጠያቂነትን ለማንሳት

ሲሉ ሌላ ከእግዚአብሔር የሚያንስ ትንሽ አምላክ ክፋት ፈጠረ አለ ብለው ያምናሉ። ይህን

“Demiurge” ብለው ይጠሩታል። የዲያቢሎስ ምሳሌ ማለት ነው። ነገር ግን መልካም የሆነ

እግዚአብሔር እንዴት ክፉ የሆነውን ግዑዙን ዓለም እንዲፈጥር ለ“Demiurge” ለዲያቢሎስ እንደ

ተወለት ምንም መረጃ የሚሰጡት የላቸውም። እግዚአብሔርን ምንም ያህል ከተጠያቂነት

ብናርቀው እግዚአብሔር ራሱ ደግሞ ደጋግሞ በሕጉና በተለያያ ጊዜ ነብያትን በማስነሳት ራሱ

እግዚአብሔር ተጠያቂነቱን ይናገራል። እግዚአብሔርን ወይስ ሰውን እንስማ? የሰውን ወይስ

የእግዚአብሔርን ሃሳብ እናገልግል?

ስለዚህ ባለቤትነት ከነጻ ፍቃድ ለሚባለውና ከሁሉ ነገር የበለጠ ሁሉን ጠቅልሎ የያዘ

ታልቅ ሚስጥርን የያዘ የእውነት ቃል ነው። ባለቤትነትና የባለቤትነትን ተጠያቂነት መመልከት

እንችላለን። ከዚህ እውነት በመነሳት ነው እኔ የነጻ ፍቃድ ክርክር ምንም ጥቅም እንደ ሌለው

የማምነው። ነጻ ፍቃድን እግዚአብሔር ያልሰጠውን ለሰውም ሆነ ለዲያቢሎስ ብንስጥ ለነገሩ ምንም

አይነት መፍትሄ አናመጣም። እግዚአብሔር ምን ጊዜም ቢሆን ራሱ ካስቀመጠው ከማይሻረው

ሕጉ የተነሳ ተጠያቂ ነው። ከተጠያቂው ከእግዚአብሔር ወገን ሆነን ከእርሱ እይታ ኃላ ሆነን

ብንመለከት ነጻ ፍቃድ ሰጠን አልሰጠን ምንም ለውጥ አያመጣም።

Page 25: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

24 www.tlcfan.org

“ እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል

ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ።”ዘጸ.22፥6

የሌላውን ሰው እርሻ ለማቃጠል ብዮ አውቄ እርሻውን በእሳት ብለኩሰው ተጠያቂው

እኔው እሳቱ በመጀመሪያ ደረጃ ያነደድኩት እኔው ነኝ። እዚህ ጋር በአጋጣሚ ነው ሳላውቅ ነው

የሚል ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይንት የለውም። ይህም የባለቤትነት ተጠያቂነት ሕግ

ነው። በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ነጻ ፍቃድ የሚባለው ነገር በእግዚአብሔር ፍርድ ቤት ውስጥ

ከቶ ስፍራ የለውም። ነጻ ፍቃድ የሚለውን ትምህርት ቤተክርሲያን እስከ አሁን እያስተናገደች

ያለችው እግዚአብሔርኝ ከተጠያቂነትን ለማንሳትና በምድር ላይ ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ሰውን

ተጠያቂ ለማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር ዕቅድ ዓላማውና ከሃሳቡ የራቀ ነው።

እግዚአብሔር ሰውን ፈጥሮታልን? አዎ እግዚአብሔር ሰው እዳይወድቅ ማድረግ

ይችል ነበርን? አዎ ! እግዚአብሔር ሰውን ያሳተውን ዲያቢሎስ ፈጥሯልን? አዎ! ኢዮ.12፥16,

ኢሳ.45፥5-7, ቆላ.1፥15-16, ሮሜ.11፥36 እንግዲህ በዚህ በሦስቱ ሕግ የምናምን ከሆን

እግዚአብሔር በሦስቱም ሕግ መሰረት እግዚአብሔር ሰለ ሆነው ነገር ሁሉ ተጠያቂ ያደረገው

ራሱን ነው።

ስለዚህ አባቢዬ ሰማ!!! ነጻ ፍቃድ የእግዚአብሔር አላማና እቅድ ውስጥ የለም። ይህ

ለቅዱሳን “central issue” ሊሆን አይገባውም። መካከለኛ መርሃችን ሊሆን የሚገባው “ownership”

ባለቤትነት ነው።

በአዲስ ኪዳንም ሆነ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሚታየውም ሆነ በማይታየው ዓለም

ሰለ ተፈጠሩት ነገር በሙሉ ባለቤት እንደ ሆነ ደጋግሞ ይናገራል። ይህ ደግሞ በመለኮታዊው

በከበረው በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት እግዚአብሔር ስለ ፈጠረው ነገር ሁሉ ተጠያቂ ያደርገዋል።

ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ሕጉን በሚገባ በመፈጸም ሁላችንን በመስቀሉ ሞት በአንድ ልጁ

በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ገዛን። ሕጉ የሚጠይቀውን እግዚአብሔር አሟላ። አሁን እኛ የራሳችን

አይደለንም። በዋጋ ተገዝተናልና ነጻ ፍቃድ የሚባል የለንም። ነጻ ፍቃድ ያለው እግዚአብሔር

ብቻ ነው። ነጻ ፍቃድ አለኝ የሚል ሰው እኔ እግዚአብሔር ነኝ የሚል እርሱ ነው። ነጻ ፍቃድ

ያለው ራሱን ገድሎ ማስነሳት የሚችል ጌታ ብቻ ነው። ሰው ራሱን ሊገድል ይችላል። ነገር ግን

ራሱን በሕይወት ሊያኖር አይችልም። ስለዚህ ስውም ሆነ ማንኛውም እግዚአብሔር የፈጠረው

ፍጥረት ነጻ ፍቃድ የሚባል የለውም። ነገር ግን የሰው ልጆች ፍቃድ እና ምርጫ አላቸው።

የሌላቸው ነጻ ፍቃድ ነው።

Page 26: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

25 www.tlcfan.org

እኛ የእግዚአብሔር እግዚአብሔርም የእኛ ነው። ለዚህም ነው እግዚአብሔር ለሰው

ልጆች ሁሉ የሞተው። እግዚአብሔር ለ2% ሃጢያተኛ ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ ሞቷል።

ቤተክርሲያን ልትሰብከው የሚገባ የምስራች ወንጌል ይህ ነው። እግዚአብሔር 100 በግ እንጂ 99

አያረካውም። ይህን የምስራች የመንግስት ወንጌል በእውነት ተረድቶ መናገር እጅግ የሚያኮራ

ነው። ኢየሱስ በወንጌል እመኑ ያለን ይህን አይነቱን ወንጌል ነው።

እንደ ባለቤትነቱ እግዚአብሔር የሚጠየቅበትን ሁሉ ፈጽሟል። ነገር ግን አሁን ገና ይህ

ሚስጥር ለብዙዎች አልተገለጠም ሲገለጥ ግን ሁሉን በግልጽ መመልከት እንችላለን። ይህ እውነት

ግን ዘላለማዊና የአሮጊቶችን ተረት ሁሉ በቅርብ ከቤቱ የሚጠርግና እየጎላ የሚሄድ እውነት ነው።

እውነት ቢቀበርም ተቀብሮ አይቀርም።

Page 27: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

26 www.tlcfan.org

ማጠቃለያ

እግዚአብሔር ሁሉ በሚታየውና በማይታየው ዓለም ያለውን ነገር ሁሉ ፈጥሯል።

እግዚአብሔር ግማሹን ለክብር ግማሹን ለውርደት የሆኑ እቃዎች አድርጎ ፈጥሯል። 2.ጢሞ.2፥

20-26 እግዚአብሔርን ይህን ለምን አደረክ ሊለው የሚችል ማንም የለም? ሮሜ.9፥14-25 ይህን

ሁሉ ሚስጥር በዚች ጠባብ አዕምሮ ልንረዳ ከቶ አንችልም።

እግዚአብሔርን ለመጠየቅ እኛ ማነን? ሽክላው ሽክላ ሰሪውን እንዲ አድርገህ ለምን

ስራኸኝ ሊለው ይችላልን? እንግዲህ ይህን ሁሉ ትተን ነጻ ፍቃድ እንደ ሌለን ተረድተን

እግዚአብሔርን የሁሉ ባለቤት መሆኑ በማወቅ የሚገባውን ክብር ልንስጠው ይገባል።

ሰው ለምን እንዲወድቅ እንደ ተደረገ ክፋትም ምድር ለምን እንደ ወረረ በቀላሉ

መመልከት የምንጀምረው የአምላካችንን ማንነትና ሕጉን በደንብ ጠንቅቀን ስንማር ነው።

እግዚአብሔር ሳያወቁ ምንም ዓይነት የእውነት እውቀት ማወቅ ከቶ አይቻልም። የእግዚአብሔር

ሚስጥር ጥልቅ ነው። ይህም እግዚአብሔር ራሱን በማወቅ ውስጥ ጥቂት በቂት እርሱ በመንፈሱ

በረዳን መጠንና፣ እይታችንን እንደከፈተልንና አይበታችን የሆነውን ልባችንን የሞላልን መጠን

ያህል ከእርሱ የምንቀበለው ነው።

“30 እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን ከአለመታዘዛቸው የተነሣ

ምሕረት እንዳገኛችሁ፥ 31 እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ

ዘንድ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። 32 እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን

በአለመታዘዝ ዘግቶታልና። 33 የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ

ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። 34 የጌታን ልብ

ያወቀው ማን ነው? 35 ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ

አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው? 36 ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም

ክብር ይሁን፤ አሜን።” ሮሜ.11

ምንም እንኳን ሁሉን ባናውቅ እኛ የምናምን አሁን በምድር ያለው ክፋትና መከራ

ልንቀበለው ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን ምንም እንዳል ሆነ እንቆጥራለን። ይህም በእግዚአብሔር

ላይ ባለን እምነት ነው። ሮሜ.8፥18 በምድር ላይ ስላለው ስለ እያንዳንዱ ክፋት ማብራሪያ የለኝም

በምድር ላይ ስላለው ክፋት እርሱ የገለጠልኝን ያህል አውቃለሁ። አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት

አውቃለሁ እምነቴ በእርሱና በቃሉ በሕጉ ላይ ነው።

Page 28: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

27 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪና የሁሉ የበላይ እንደ ሆነ አውቃለሁ። ሁሉም አሁን

መልካም መስሎ የማይታየውን ነገር ሁሉ ለመልካም ሰርቶት እንደማይ በእግዚአብሔር ትልቅ

እምነት አለኝ። ምንም እንኳን በዓለም ላይ በየስፍራው እየሆነ ያለው ነገር አሁን የሚያሳዝን

ቢሆንም አንድ ቀን ግን ሁላችን ወደ ኃላ ዞር ብለን ተመልክተን እግዚአብሔር ሁሉ

እንዳስተካከለውና እንዳደሰው ስንመለከት በሥራው ከበፊት የበለጠ እንረካለን ደግሞም ለዘላለምም

እንገዛለታለን። የፍቅሩንም ጥልቀትና ምሕረቱን እንመልከታለን።

ይህ የእያንዳዳችን የእምነት ጉዳይ ነው። እኔ የእግዚአብሔር ቃል ከሚናገረው ውጪ

ማንኛውንም የሰው ልጆች የራሳቸውን ስዕል የሰጡትን እግዚአብሔር ማምለክና መከተል ካቆምኩ

ሰነባብቻለሁ። ለቅዱሳን ሁሉ ጥማቴና ናፍቆቴም በቃሉ እንዲኖሩ ካሮጊቶች ተረትና ከሰዎች

ፍልስፍና እንዲርቁ ነው። ለእኔ በቃሉ የተገለጠ እግዚአብሔር ለእናንተም የማይገለጥበት ምንም

ምክንያት የለውም። ለሚፈልጉኝ እገኛለሁ ያለ እግዚአብሔር እርሱ ብቻ ነው። እግዚአብሔርን

ፈልጉ በሁሉ ነገር ትጸናላችሁ። እርሱ ለሚለምኑት ድንጋይ፣ ጊንጥ ወይም እባብ አሰጥም ይልቁኑ

መንፈሱን በልግስና ይሰጣል። ቃሉ እንደሚል የእውነት እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው።

ትክክለኛ የእውነት እውቀት ማግኘት የክርስቶስን ሕይወት በእኛ ላይ ያመጣል።

እግዚአብሔር የሚሰራውን ሁሉ እርሱ ያውቃል። እግዚአብሔር ለሰው ከእርሱ በታች

ምድርን እንዲያስተዳድር ስልጣን ቢሰጠውም መቼም ቢሆን ሰው የምድር ባለቤት ሊሆን

አይችልም። ሰው ሰውን ሊፈጥር ፈጽሞ አይችልምና ነው። ያልፈጠርከው ነገር ደግሞ ባለቤት

ነኝ ልትል አትችልም። ይህ ዕብደት ወይም ዕውርነት ነው። ካበድንስ በእግዚአብሔር እውነት

እንደ ሐዋርያት ዕብዶች እንባል እንጂ የራሳችን ከንቱ የሆነ ሃሳንና ተረት ተረት ነገር የሙጥኝ

ብለን አይሁን።

ለእውነት እንጂ ለዲያቢሎስ ውሸትና ለጌታ ጠበቃ አንቁም። ጌታ ራሱ ጠብቃ ነው

ጠበቃ አያስፈልገውም። ጠበቃ የሚያስፈልገው ሰው እንጂ ስይጣንና እግዚአብሔር አይደለም።

በምድራችን ላይ ስልጣን አለን። ነገር ግን የበላይ ገዥነት “sovereignty” ወይም የባለቤትነት

መብት ፈጽሞ የለንም። ስልጣናችን ፈጽሞ ውስን ነው።

ለምድር የመቤዠት ሕግ እንዳለው አይተናል ነገር ግን ምድር በመቤዠት ሕግ እንኳን

ሳትቤዠ ብትቀር ታላቁን የምሕረት ሕግ ኢዮቤልዮን ባለችበት ሁኔታ ሆና ልታልፍ ለዘላለምም

እንደዛ እንድትኖር ጌታ አይፈቅድም። ከላይ እንዳመለከትኩ ይህ የእግዚአብሔር ታላቁ የምሕረት

ፍርድ ነው። ይህ ምሕረት ያቆብ እንዳለው በፍርድ ላይ የሚመካው ምሕረት ነው። ዘሌ.25፥54

Page 29: በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል feqaade.pdfነጻ ፍቃድ 2015 3 የነጻ ፍቃድ ጥያቄ ይህ መጽሐፍ ስለ ነጻ ፍቃድ ሰዎች የሚኖራቸውን

ነጻ ፍቃድ 2015

28 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር በሕጉ ያጸናውን ማንም ሰው ፈጽሞ ሊሽረው አይችልም። ነጻ ፍቃድን

ደህና ስንብት ብላችሁ በጊዜው አሰናብቱልኝ። እግዚአብሔርን ታውቁ ዘንድ ትጉ። መቤዠትን

ሳያገኙ ለተሰናበቱ የሰው ልጆች ሁሉ የምስራቹን ኢዮቤልዮን ሕግ አስቡና እግዚአብሔር ስለ

ሚስጣቸው ምሕረት በማሰብ እግዚአብሔር አመስግኑ። እንደ ማርያም ምሕረት እንደበዛላችሁ

መጠን በይቅርታ ማድረግና አምሕረት በመልካም ሥራችሁና አኗኗሯችሁ በሰው ሁሉ ፊት

የተገለጠ ኑሮን ኑሩ። ሌሎችን የሚምር የምሕረት አዕምሮ እንደ ኢየሱስ ይሁንላችሁ።

ማራናታ…ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በቶሎ ና!!!

ሰው፣ መልእክትና ሴጣን ነጻ ፍቃድ የላቸውም!!!! ነገር ግን ፍቃድ አላቸው።

ነጻ ፍቃድ ያለው አምላካችን እግዚአብሔር ብቻ ነው።

……………………………………ተፈጸመ……………………………………….