2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል።...

24
የሞጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MONTGOMERY COUNTY PUBLIC SCHOOLS) ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org የፌዴራል እና የስቴት ሕጎች፣ የሞጎሞሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች፣ እና የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) አስተዳደር ደንቦች፣ እና ሌሎች መመሪያዎች፣ ሊለወጡና በዚህ ሕትመት ላይ የተገለጹትን ለመተካት ይችላሉ። የተማሪ ስም፡ __________________________________ አድራሻ፡ _____________________________________ ስልክ፦ ______________________________________ መብቶችና ግዴታዎች Rockville, Maryland 2017–2018 የተማሪ መመርያ ስለ SR&R እንግሊዝኛ

Transcript of 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል።...

Page 1: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

የሞጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች(MONTGOMERY COUNTY PUBLIC SCHOOLS)

ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org

የፌዴራል እና የስቴት ሕጎች፣ የሞጎሞሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች፣

እና የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) አስተዳደር ደንቦች፣ እና ሌሎች

መመሪያዎች፣ ሊለወጡና በዚህ ሕትመት ላይ የተገለጹትን ለመተካት ይችላሉ።

የተማሪ ስም፡ __________________________________

አድራሻ፡ _____________________________________

ስልክ፦ ______________________________________

መብቶችና ግዴታዎች

Rockville, Maryland

2017–2018የተማሪ መመርያ ስለ

SR&R እንግሊዝኛ

Page 2: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

የትምህርት ቦርድ 850 Hungerford Drive, Rockville, Maryland 20850 ስልክ፦ 301-279-3617ኢ-ሜይል:- [email protected]ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org/boe

ወ/ሮ. ሼብራ ኤል. ኢቫንስ(Mrs. Shebra L. Evans)ዲስትሪክት 4

Mr. Michael A. Dursoሚ/ር ማይክል ኤ. ዱርሶፕሬዚ ደንትዲስትሪክት 5

ወ/ሮ ፓትሪሻ ቢ ኦኔይል(Mrs. Patricia B. O’Neill) ዲስትሪክት 3

ዶ/ር ጃክ አር. ስሚዝ(Jack R. Smith, Ph.D).የት/ቤቶች የበላይ ኃላፊ

ዶ/ር አንድሩ ኤም. ዙከርማን(Andrew M. Zuckerman, Ed.D).ዋና የሥራ ሀላፊ

ዶ/ር ኪምበርሊ ኤ. ስታታም (Kimberly A. Statham, Ph.D).የት/ቤት ድጋፍና መሻሻል ም/የበላይ ኃላፊ

ዶ/ር.ማሪያ ቪ. ናቫሮ(Maria V. Navarro Ed.D.),የኣካዴሚ ዋና ኃላፊ

ወ/ሮ ረቤካ ስሞንድሮውስኪ(Mrs. Rebecca Smondrowski)ዲስትሪክት 2

Dr. Judith R. Docca ዶር. ጁዲት ኣር. ዶካም/ፕረዚደንትዲስትሪክት 1

ሚስ ጃኔት ኢ. ዲክሰን Ms. Jeanette E. DixonAt Large

ሚ/ር ማቲው ፖስት(Mr. Matthew Post)የተማሪ ኣባል

የት/ቤት አስተዳደርድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org

ራእይ

ለእያንዳንዱና ለማንኛውም ተማሪ እጅግ የላቀውን የህዝብ ትምህርት በማቅረብ ትምህርት እንዲሰርፅ እናደርጋለን።

ተልእኮ

እያንዳንዱ/ዷ ተማሪ በኮሌጅም ሆነ በስራ ስኬታማ እንዲ(ድት)ሆን ኣካዴሚያዊ፣ ፈጠራዊ የችግር አፈታት፣ እና የማህበራዊ ስሜታዊ ክህሎቶች ይኖሩ(ሯ)ታል።

ዋነኛ ኣላማ

ሁሉም ተማሪዎች በወደፊት ኑሮኣቸው የዳበረ ህይወት እንዲኖራቸው ማዘጋጀት።

ዋነኛ እሴቶች

ትምህርትግንኙነቶችአክብሮትልቀትፍትህ/ሚዛናዊነት

ሚስ. ጂል ኦርትማን-ፉዎስ(Ms. Jill Ortman-Fouse)At Large

Page 3: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

© ጁላይ 2017

ሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (Montgomery County Public Schools)

Rockville, Maryland

በሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (Montgomery County Public Schools)

ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org

መብቶች እና ግዴታዎች

2017–2018የተማሪ መመርያ ስለ

Page 4: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

የ2017–2018 የት/ቤት ቀን መቁጠርያ Montgomery County Public Schools2017

ጁላይ 4 የነፃነት ቀን—ፅ/ቤቶች እና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ኦገስት 23፣ 24፣ 25፣ 28፣ 29፣ 30፣ 31 እና ሴፕት. 1

የመምህራን የባለሙያ ቀን

ሴፕተምበር 4 የሰራተኛ ቀን—ፅ/ቤቶች እና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ሰፕተምበር 5 ለተማሪዎች የመጀመርያ የትምህርት ቀን

ሴፕተምበር 21 ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት የለም

ኦክቶበር 6 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን

ኖቬምበር 9 ሁሉም ተማሪዎች ኣስቀድመው የሚለቀቁበት ቀን፤ የሩብ ኣመት ፕላን መጨረሻ

ኖቨምበር 10 K–8 ኣስቀድመው የሚለቀቁበት ቀን

ኖቨምበር 17 K–8 ኣስቀድመው የሚለቀቁበት ቀን

ኖቬምበር 22 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን

ኖቨምበር 23 እና 24 ታንክስጊቪንግ—ፅ/ቤቶች እና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ዲሰምበር 25፣ 26፣ 27፣ 28፣ 29የዊንተር እረፍት—ለተማሪዎችና ለመምህራን ት/ቤት የለም፤ ፅ/ቤቶች ዲሰምበር 25 ይዘጋሉ

2018

ጃንዩወሪ 1 ኣዲስ ኣመት ቀን—ፅ/ቤቶች እና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ጃንዋሪ 15 የዶር. ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ጁር. ቀን—ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ናችው

ጃንዩወሪ 25 ኣስቀድሞ መለቀቂያ ቀን ለሁሉም ተማሪዎች፤ የሩብ ኣመት ፕላን መጨረሻ

ጃንዩወሪ 26 የመምህራን የባለሙያ ቀን

ፌብርዋሪ 19 የፕሬዚደንት ቀን—ፅ/ቤቶች እና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ማርች 2 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን

ማርች 26፣ 27፣ 28፣ 29፣ 30፣ እና ኤፕረል 2

የስፕሪንግ እረፍት—ለተማሪዎችና ለመምህራን ት/ቤት የለም፤ ፅ/ቤቶች ማርች 30 እና ኤፕረል 2 ይዘጋሉ

ኤፕሪል 9 ኣስቀድሞ መለቀቂያ ቀን ለሁሉም ተማሪዎች፤ የሩብ ኣመት ፕላን መጨረሻ

ሜይ 28 የሜሞርያል ቀን—ፅ/ቤቶችና ት/ቤቶች ዝግ ናቸው

ጁን 12ለተማሪዎች የት/ቤት የመጨረሻ ቀን፤ ኣስቀድሞ መለቀቂያ ቀን ለሁሉም ተማሪዎች

ጁን 13 ለመምህራን የባለሙያ ቀን

የትምህርት ኣመቱ በኣስቸኳይ ሁኔታዎች ቢደናቀፍና ት/ቤቶች ለሶስት ወይም ከዚያ በላይ ቀኖች ቢዘጉ፣ የመጀመርያ ማስተካከያ ቀን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን ያካትታል፤- ጃንዩወሪ 26፣ ማርች 26፣ ማርች 27፣ ጁን 14፣ እና ጁን 15።

ተቀባይነት ያገኘበት፡- 2/27/17

Page 5: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

የተማሪዎች መገልገያዎች

ከሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ጋር ምንጊዜም መገናኘት ይችላሉ። ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.orgአጠቃላይ ሥርአቱን የሚመለከት መረጃና የአስቸኳይ ሁኔታ ማስታወቂያዎች ለማግኘት፡-

• MCPS በትዊተር፡- www.twitter.com/mcps• MCPS በስፓኒሽኛ፡- www.twitter.com/mcpsespanol• የMCPS ማስጠንቀቂያ፡- www.montgomeryschoolsmd.org/alertMCPS• የMCPS QuickNotes ኢ-ሜይል መልእክቶች እና ዜና መጽሔት፡- www.mcpsQuickNotes.org• የMCPSን የመረጃ አገልግሎት ይጠይቁ

−ስልክ፡- 301-309-MCPS (6277) − የስፓንሽኛ ነፃ የቀጥታ መስመር 301-230-3073 −ኢ-ሜይል፡- [email protected]

• MCPS ቴሌቪዥን (www.mcpsTV.org{21}፤ Comcast 34፣ RCN 89፣ Verizon 36)}• የተቀረፀ የአስቸኳይ ጊዜና የአየር ሁኔታ መረጃ፡- ስልክ፡ 301-279-3673

የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) የወጣት የችግር/የአደጋ ጊዜ /አስቸኳይ የቴሌፎን መስመር . . . . . . . . .301-738-9697

የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) የአስቸኳይ ሁኔታ ማእከል ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .240-777-4000ነፃ የቀጥታ ስልክ ቁጥር፦ 301-738-2255

የደህንነትና የፀጥታ አስጊ ሁኔታዎችን ለማስታወቅ፡- የMCPS Safe Schools (ሠላም/ደህንነታቸው የተጠበቀ ት/ቤቶች) ለ24 ሰአት ክፍት የሆነ ነጻ የቀጥታ መስመር፦ . . . .301-517-5995የMCPS የደህንነትና የፀጥታ መምርያ ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-279-3066የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) የልጆች ደህንነት-ጥበቃ(መከላከያ) አገልግሎቶች፣

የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (24 ሰዓት) 240-777-4417፣ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .240-777-4815 TTYየሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) የጎልማሳ/የአዋቂ ደህንነት ጥበቃ-መከላከያ አገልግሎቶች ለድኩማን ጎልማሶች/አዋቂዎች ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .240-777-3000የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) የፖሊስ መምርያ፣ የልዩ ተጠቂዎች ምርመራ ክፍል (24 ሰዓት) ስልክ፦ . .240-773-5400የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery Count) ፖሊስ አጣዳፊ ላልሆነ ጥሪ የስልክ ቁጥር፦ . . . . . . . . . . . . . . . . .301-279-8000

የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) ፖሊስ:- የአደንዛዥ እፅ እና ውንብድና/ወሮበሎች/Gang መጠቆሚያ አስቸኳይ መስመር 240-773-GANG (4264) ወይም . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 240-773-DRUG (3784)የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች የመረጃ መስመር

የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች አጠቃላይ መረጃን . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .በ311፣ 301-251-4850 TTY ያግኙ/ያናግሩ ከሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) ውጭ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .240-777-0311

ከኮምፒተርና ኮምፒተር ኔተዎርኮች ጋር ለተገናኙ ጉዳዮች የጥቆማ መስመር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1-800-843-5678 በት/ቤቱ መዋቅር ውስጥ ያልተገባ የኦንላይን (የኢንተርኔት ላይ) እንቅስቃሴ/ተግባር ሲፈጸም ለመጠቆም/ሪፖርት ለማድረግ [email protected]

ጠቃሚ መገናኛዎችካውንቲ-አቀፍ የተማሪ አስተዳደር (ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/student-leadership)

• የተማሪ አመራር አስተባባሪ፣ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት፣ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልክ፦ . . . . . .240-314-1039ተማሪ የቦርድ አባል (www.montgomeryschoolsmd.org/boe/members/student.aspx)

• የትምህርት ቦርድ ጽ/ቤት ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-279-3617የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተባባሪ የበላይ ኃላፊ ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-315-7362የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተባባሪ የበላይ ኃላፊ ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-315-7370የትምህርት ቤት አስተዳደርና አፈጻጸም መምሪያ ተባባሪ የበላይ ኃላፊ ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-279-3444የተማሪ እና ቤተሰብ ድጋፍ እና ተሳትፎ ጽ/ቤት ተባባሪ የበላይ ሀላፊ ስልክ፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .240-314-4824የቤት ሥራን (እገዛ) የተመለከተ ነፃ የቀጥታ ጥሪ መቀቢያ መስመር (HHL)—www.montgomeryschoolsmd.org/departments/itv/hhl/301-279-3234 ወይም ቴክስት . . . . . . . . .724-427-5445

የሰክሽን (Section) 504 አፈፃጸም ተቆጣጣሪ ሹም፦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .301-517-5864

የ(MCPS) ድረ-ገጽ መገልገያዎችየድረ-ገጽ አድራሻዎች{45}፡- www.montgomeryschoolsmd.org• ይፈልጉ:-

• የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የት/ቤት ማውጫ• የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የሰራተኞች

ማውጫ• የኮሌጅና የስራ ማእከል• ጉልበት ማሳዬት፣ ጥቃት/ትንኮሳ፣ ዛቻ/ማስፈራራት• የማህበራዊ ሚዲያዎችንና ሌሎች የዲጅታል መሳሪያዎችን

ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ መጠቀም (Cybercivility)ና የኢንተርኔት ደህንነት (CyberSafety)

• የኮርስ መግለጫ/ጥንቅር (Course Bulletin) • የዲፕሎማ መስፈርቶች• የሜሪላንድ (Maryland) 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ግምገማዎች

• HHL• ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አደራረግ• መመርያዎች እና ደንቦች• ልዩ ፕሮግራሞች• ስልታዊ የፕላን ዝግጅት• የተማሪ ገመና የመሸፈን/ግላዊነት (Privacy) መብት• የተማሪ መብቶች እና ግዴታዎች መመሪያ እና የተማሪ

የስነ-ምግባር ደንብ• የተማሪ አገልግሎት ትምህርት• ሃይማኖታዊ ብዝሃነት ማስከበሪያ መመርያዎች• የልጅን በደልና ቸል የማለት ክሶችን ሪፖርት ስለማደረግ

Page 6: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን
Page 7: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

ሀ ስለ መብቶችና ሃላፊነቶች የተማሪ መመርያ¡ 2017–2018 ¡ i

ማውጫመግቢያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1ነፃ የህዝብ ትምህርት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1የተማሪ ተሳትፎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1ገመና የመሸፈን/ግላዊነት የመጠበቅ መብቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1(በክፍል) የተገኙበት ጊዜ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1 ምክንያታዊ/የተፈቀዱ ቀሪዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 ያልተፈቀዱ ቀሪዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 በቀሪነት ጊዜ ያመለጠ ስራ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2የክፍል ስራ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አደራረግ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2 የላቀ ችሎታ/Honors/፣ ከፍተኛ-ደረጃ፣ እና የላቀ ደረጃ አመዳደብ/ Advanced Placement/ (AP) ኮርሶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3የተማሪ አገልግሎት ትምህርት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3የተማሪ አስተዳደር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3 ተሳትፎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3 የፋካልቲ/Faculty/ ድጋፍ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3 የተማሪ አስተዳደር ስልጣኖች. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3የመጠየቅና ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4 ንግግር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4 ስብሰባ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4 ማመልከቻዎች/አቤቱታዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4 ሕትመቶች፣ አፈጻጸሞች፣ እና መረጃዊ ቁስ/ማተሪያል . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4 የፖለቲካ ቁሳቁስ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4 የፖሊቲካዊ ዘመቻዎች ተሳትፎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5የአርበኝነት/የአገር ወዳድነት ልምምዶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5የሀይማኖት ነፃነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5ክበቦች፣ ቡድኖች፣ እና የተማሪ ድርጅቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5 ት/ቤት-የሚደግፋቸው ድርጅቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5 ያለት/ቤት ድጋፍ የሚካሄዱ የተማሪ ድርጅቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5አለባበስና፣ ንፅህና/የፀጉር አያያዝ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6ቴክኖሎጂ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6 ሃላፊነት የተሞላበት አጠቃቀም የተማሪ መመርያዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6 የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6ፀረ-መድልዎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6ጉልበተኝነት ማሳዬት፣ ትንኮሳ፣ ወይም ማስፈራራት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7 ወሲባዊ ትንኮሳ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7የተማሪ መዝገቦች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8ፍተሻ እና መያዝ/መውረስ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8የት/ቤት ጥበቃና ደህንነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 8 በስቴት አስፈላጊ የሆኑ/መሟላት የሚገባቸው ጣልቃ-ገብ የጤና ስራዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9 አለርጂ ለሚቀሰቅሱ ነገሮች/ከባድ የአለርጂ ምላሽ ግንዛቤ (Anaphylaxis Awareness) . . . . . . . . . 9 ስለ ስኳር በሽታ/Diabetes/ግንዛቤ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9 ስለ ናሎክሶን እና ኦፒኦይድ (Naloxone and Opiod) መዳኒቶች ግንዛቤ . . . . . . . . . . . . . . . . 9ደህንነት/ጤናማነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9ሥነሥርዓት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9 ይግባኝ፣ ቅሬታ አቀራረብ፣ ፍትህ የማግኘት አካሄድ (Due Process) . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9 የት/ቤት ደረጃ ውሳኔ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9 በርእሰመምህር ውሳኔ ላይ ይግባኝ ስለመጠየቅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .10 በኦፔሬሽን ዋና ኃላፊ ውሳኔ ላይ ይግባኝ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .10ተቀጥያ—የMCPS ደንቦች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 11-13አጭር የቃላት ዝርዝርና ማስታወሻዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .14የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ፀረ-መድሎ መግለጫ . . . . . . . . የጀርባ ሽፋን ውስጠኛው ገጽ

Page 8: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን
Page 9: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ¡ 2017–2018 ¡ 1

መግቢያይህ መፅሔት ተማሪዎች በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ስለሚኖራቸው መብቶችና ሃላፊነቶች መመርያ ነው። ይህ መጽሔት እዚህ ላይ የMCPS ደንቦች ተብለው የተጠቀሱት እና ተማሪዎችን የሚመለከቱ የስቴት እና የፌደራል ሕጎች፣ የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች፣ እና የMCPS ደንቦች፣ እና ሌሎች መመሪያዎች አጭር መግለጫ ነው። በማንኛውም የተለዬ ሁኔታ ይህ የተማሪ መብቶች ፍጹም መግለጫ/ትንታኔ አይደለም። ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ በየክፍሉ መጨረሻ ላይ ተለይተው የተጣቀሱትን ህጎች፣ ፖሊሲዎች፣ እና ደንቦች ያንብቡ። የቦርድ መመርያዎችና የMCPS ደንቦች በwww.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy ይገኛሉ።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ሕጎች የሚለወጡና በዚህ ሕትመት ውስጥ በተካተቱት መግለጫዎችና ማጣቀሻዎች ላይ የበላይነት አላቸው።

ዋና ዋና ተፈጻሚ የMCPS ደንቦች ዝርዝር በዚህ መመሪያ ገጽ 11 ላይ ይጀምራል። MCPS Regulation JFA-RA፣ የተማሪ መብቶች እና ግዴታዎች/ሃላፊነቶች{60}፣ በሁሉም (ክፍሎች) ላይ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል። ሌሎች ተጨማሪ ማጣቀሻዎች ከእያንዳንዱ ክፍል ግርጌ ላይ ተጠቅሰዋል።

¡ ነፃ የህዝብ ትምህርትእድሜአቸው ሴፕቴምበር 1 ላይ 5 ዓመት የሞላቸው፣ እናም በት/ቤት መጀመርያ ቀን ላይ 21 አመት እድሜ ያልደረሱ፣ የሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) ነዋሪዎች በሕዝብ ት/ቤቶች ያለክፍያ በነፃ መከታተል ይችላሉ። ይህ መብት እስከ ከከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ምረቃ ድረስ፣ ወይም ተማሪው/ዋ 21 አመት በሚሆንበት/በምትሆንበት የትምህርት አመት መጨረሻ፣ የትኛውም ቀድሞ እሰከሚከሰተው ሁኔታ ድረስ የሚቆይ/የሚሰጥ ነው።

የአካል ጉድለት ያለባቸው የሞንጎሞሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ እድሚያቸው 21 እስከሚሆንበት የትምህርት አመት ድረስ ነጻ ተስማሚ/ተገቢ የሕዝብ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው።

¡ የተማሪ ተሳትፎስለያንዳንዱ ኮርስ አጠቃላይ አላማዎችና አፈፃጸማቸውም ስለሚገመገምበት መስፈርት ተማሪዎች መረጃ ይሰጣቸዋል። ተማሪዎች በትምህርት ክፍል እንቅስቃሴዎች የመሳተፍና በትም/ክፍል ደንቦች፣ ግዴታዎች፣ እና ያፈፃጸም ሂደቶች የመገዛት ሃላፊነት አለባቸው።

ከፋኩሊቲ ጋር በመመካከር፣ በትምህርት ቀን ከመደበኛ ፕሮግራም በተጨማሪነት እና/ወይም ከት/ቤት ቀን ውጭ ተማሪዎችን በሚስቡ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች ሊሰጡ በሚችሉ በተመረጡ ርእሶች ላይ ሴሚናሮች፣ ስብሰባዎች፣ ወይም አጭር የትምህርት ኮርሶች እንዲዘጋጁ/እንዲሰጡ ሀሳብ ሊያቀርቡ ይችላሉ።

ተማሪዎች ፕሮግራሞችን ለመንደፍ/ለመቅረጽ ከርእሰ መምህራን እና ከአስተዳደር አባላት ጋር ተባብረው ይሰራሉ። ፕሮግራሞቹ ከዲስትሪክቱ ስልታዊ ቅድሚያ ትኩረቶች እና ከ MCPS’ መሠረታዊ የትምህርት ተልእኮ ጋር የተገናዘበ እና ከተሳታፊዎቹ እድሜና ብስለት ጋር የሚጣጣም እንዲሁም በአወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ ሚዛናዊነትን የጠበቀ አቀራረብ መሆን አለባቸው።

ተማሪዎችን የሚመለከት ዋና ዋና የቦርድ ፖሊሲ ክለሳ ወይም ቀረጻ በሚደረግ ጊዜ የተማሪ ተወካዮች እንዲሳተፉ ይደረጋል። እንደዚህ ዓይነቱ ተሳትፎ ሊከናወን የሚችለው በስብሰባዎች ላይ የተማሪ ተወካዮችን በማሳተፍ፣ ወይም ክለሳው በማናቸውም ደረጃ ላይ እያለ ተማሪ አስተያየት እንዲሰጥበት በመጠየቅ ይሆናል፡ ተማሪዎች በአካባቢ ትልቅ ት/ቤት ተማሪዎችን የሚመለከት መመሪያ/ደንብ ክለሳ በሚደረግበት ጊዜ እንዲሳተፉ ተመሣሣይ መብት አላቸው። ተማሪዎችን የሚመለከቱ አበይት የአካባቢ ት/ቤት መመርያዎች ወይም ደንቦች ከመዳበር ወይም ከመከለሳቸው በፊት የተማሪ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ቅጅዎች፣ ከበቂ (አስተያየት መስጫ) ጊዜ ጋር፣ ለተማሪዎች አመች በሆኑ ቦታዎች ይቀመጣሉ።

በስቴት እንዲሟሉ ከሚጠየቁት በቤተሰብ ህይወት እና የሰው ልጅ የጾታዊ (ወሲባዊ) ግኑኝነት ባህሪ እና በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር አጠቃላይ የጤና ትምህርት ስርአተ ትምህርት (Comprehensive Health Education Curriculum) ክፍሎች አካል በሆኑ የክፍል እንቅስቃሴዎች ተማሪው/ዋ እንዳ(ይ)ትሳተፍ ወላጆች/አሳዳጊዎች ከጠየቁ፣ ለተማሪው/ዋ ተለዋጭ እንቅስቃሴዎች ይቀርቡለታል። የMCPS Regulation IGP-RA፣ አጠቃላይ የጤና ትምህርት ማስተማሪያ ፕሮግራምን ይመልከቱ{62}።

¡ የግል ህይዎት/ግላዊነት መብትየተማሪ የግል ህይዎት/ግላዊነት ጉዳይ በት/ቤት አስተዳደር አባላት ይከበራል።

እንቅስቃሴው የተማሪው/ዋን ውጤት፣ ሃይማኖት፣ መርሆዎች፣ ወይም አካላዊ ሁኔታው/ዋን በማጋለጥ የተማሪው/ዋን የግል ህይዎት/ግላዊነት መብት ይጥሳል ብለው ወላጅ/አሳዳጊ ወይም ተማሪው/ዋ ካመነ/ች ተማሪዎች ወይም ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው ለእንቅስቃሴው ተለዋጭ እንዲቀርብ የመጠየቅ መብት አላቸው። ተማሪዎች የቤተሰብ የግል መረጃ የሆኑ ክስተቶች ወይም የግል ልማዶች/አመሎች፣ ግንኙነቶች፣ ምርጫዎች፣ ባሕሪያት፣ ውሳኔዎች፣ ወይም ችግሮች ሳይገልጡ፣ ወይም ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን ከሌሎች ጋር ሳያወዳድሩ ትምህርታዊ ዓላማዎችን በክፍል ውስጥ ውይይት፣ የተሰጡ ሥራዎች /ተግባራትን በመስራት፣ ወይም በሌላ መንገድ የማከናወን መብት አላቸው።

ተማሪዎች የMCPS አውቶቡሶችን ጨምሮ በMCPS ንብረት፣ ወይም በትምህርት ሰዓቶች በሕዝብ ማዘውተርያ አካባቢዎች ለሚገኙ ለድምጽና ቪዲዮ ካሜራ ክትትል/ቁጥጥር ሊዳረጉ እንደሚችሉ እና፣ ማንኛውም ተማሪ አነዚህን በመሳሰሉ የድምጽና ቪዲዮ የክትትል ካሜራዎች በሚገኝ መረጃ መሠረት የስነ-ስርዓት ርምጃ ሊወሰድበት/ባት ይችላል። በነዚህ ሁኔታዎች ተማሪዎች ገበናችን/ምስጢራችን ይከበራል ብለው መጠበቅ የለባቸውም።

ማጣቀሻዎች:- የMCPS ደንብ JOA-RA፣ የተማሪ መዝገቦች

¡ ክትትል (በክፍል ውስጥ ተማሪው/ዋ መገኘቱ/ትዋን መቆጣጠሪያ)

ለተማሪ ስኬት በትምህርት ገበታ ላይ በየእለቱ መገኘት አስፈላጊ ሲሆን እንዲሁም አንድን የትምህርት ማቴሪያል በደንብ ማወቅን ለማሳየትና የኮርሶች ክሬዲትም ለማግኘት ይጠቅማል/ያስፈልጋል። ተማሪዎች ት/ቤት እንዲከታተሉ እና ወደ ት/ቤትና የመማርያ ክፍሎች በወቅቱ እንዲደርሱ ይጠበቅባቸዋል።

ተፈቅዶላቸው ካልሆነ በስተቀር፣ ተማሪዎች በትምህርት ቀን ወደ መማርያ ክፍሎችና ወደ ሌሎች ተፈላጊ እንቅስቃሴዎች መሄድ አለባቸው። የትምህርት ክትትል ሁኔታ በተማሪው/ዋ ሪፖርት ካርድ አማካኝነት ለወላጆች/ሞግዚቶች ይገለፃል። ተማሪው/ዋ ሙሉ ቀን በትምህርት ገበታ ላይ ተገኝቷል/ታለች ተብሎ የሚታሰበው በትምህርት ቀን ውስጥ አራት ሰአቶች ወይም ከዚያ በላይ ከተገኘ/ች ብቻ ነው። ተማሪው/ዋ ግማሽ ቀን በትምህርት ገበታ ተገኝቷል/ታለች ተብሎ የሚታሰበው በትምህርት ቀን ውስጥ ቢያንስ ሁለት ሰአቶች፣ ነገር ግን ከአራት ሰአቶች በታች፣ ከተከታተለ/ች ነው።

በአካባቢ ት/ቤት አሰራር መሰረት፣ አንድ/ዲት ተማሪ ከት/ቤት ከቀረ/ች፣ ት/ቤቱ የመቅረቱን/ቷን ምክንያት ይከታተላል።

Page 10: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

2 ¡ 2017–2018 ¡ A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES

ምክንያት/ፈቃድ ያላቸው መቅረቶችበሚከተሉት ምክንያቶች ብቻ ተማሪዎች ከት/ቤት መቅረት ይችላሉ፡-

• የቅርብ ዘመድ ከሞተ• ህመም (በህመም ምክንያት ለረዥም ጊዜ መቅረት የሚያስከትል ከሆነ ርእሰ

መምህሩ/ሯ ከወላጅ/ሞግዚት የሃኪም ማስረጃ ሊጠይቅ/ልትጠይቅ ይችላል/ትችላለች።)

• የፍርድ ቤት መጥሪያ• እርግዝና እና ወላጅ አስፈላጊ የሆነበት ጉዳይ• ኃይማኖታዊ በዓል ለማክበር• የስቴት አስቸኳይ ሁኔታ• መታገድ• አደገኛ የአየር ሁኔታ (ተማሪው/ዋ ከቤት ወደ ት/ቤት ለመመላለስ የአየር

ሁኔታ የሚያሰጋ ከሆነ)• መደበኛ ትራንስፖርት መጥፋት (ለምሳሌ፣ አውቶቡሱ ካልመጣ)• የርእሰ መምህር ፈቃድ

በተዘረዘሩት ምክንያቶች ተማሪዎች ከት/ቤት ከቀሩ፣ ወደ ት/ቤት ከተመለሱ በሶስት ቀናት ውስጥ ከወላጅ/አሳዳጊ ማስታወሻ ማምጣት አለባቸው። ለምሳሌ፣ አንድ ተማሪ ረቡዕና ሃሙስ ከት/ቤት ቢቀር/ብትቀር እና ዓርብ ቢመለስ/ብትመለስ፣ ስለመቅረቱ/ቷ ምክንያት የሚያብራራ ማስታወሻ በሚቀጥለው ማክሰኞ ማቅረብ አለበ(ባ)ት። አለዝያ መቅረቱ ያልተፈቀደ ተብሎ ይታሰባል። ተማሪዎች 18 ዓመት እድሜ ወይም ከዚያ በላይ ወይም ያገቡ ከሆኑ፣ የMCPS ቅጽ 281-12Eligible Student Declaration Form (ብቃት ማረጋገጫ ፎርም) ከሞሉ በኋላ የራሳቸውን ማስታወሻ መፃፍ ይችላሉ። እድሜ የሚያሟላ ያለ ምክንያት/ያለፈቃድ የሚቀር/የምትቀር ተማሪ ከወላጅ/አሳዳጊ ጋር በጥገኝነት የሚኖር ከሆነ ለተማሪው አስቀድሞ ሳይገለጽ ያለፈቃድ ከት/ቤት ስለመቅረቱ/ቷ ተጨማሪ ማሳወቂያ ሊላክ ይችላል።

ርእሰ መምህሩ/ሯ ተማሪዎችን የተማሪው/ዋ ወላጅ (ወይም እድሜ የሚያሟላ/የምታሟላ ተማሪ) ቢያንስ ከአምስት ቀናት በፊት ፈቃድ እስከአገኙ ድረስ ለሥራ ወይም ለሌላ ተግባር የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዲያመልጣቸው ሊፈቅድላቸው ይችላል/ልትፈቅድላቸው ትችላለች ተማሪዎች ከሚከተሉት አንዳቸውን ለማድረግ ከት/ቤት ቢቀሩ ርእሰ መምህሩ/ሯ ይቅርታ ያደርግላቸዋል/ታደርግላቸዋለች፡-

• የኮሌጅ ግቢ ለመጎብኘት• በኮሌጅ የመተዋወቅያ ፕሮግራም ለመሳተፍ• ስራ ለመቀጠር ቃለ መጠይቅ ለማድረግ• የጋራ ትምህርት ፕሮግራም አካል የሆነ ስራ ለመስራት• የአጭር ጊዜ ወይም የሙሉ ጊዜ ስራ ለመሳተፍ

የቤተሰብ እረፍቶች በአብዛኛው አይፈቀዱም። ከተለመደው ውጭ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ግን፣ ርእሰ መምህሩ/ሯ መቅረቱን ይቅርታ ማድረግ ይችላል/ትችላለች። አንድ ት/ቤት እንከን ለሌለበት "በት/ቤት መገኘት" ሽልማት ማዘጋጀት ቢፈልግ፣ ያለባቸው ብቸኛ ቀሪ ቀናት በሀይማኖት ምክንያት የተፈቀዱ ቀናት ለሆኑ ተማሪዎች ሽልማቱን መከልከል/ማስቀረት አይችልም።

ፈቃድ የሌላቸው ቀሪዎችእላይ በተገለጹት ሁኔታዎች መሰረት ያልተፈቀደ ቀሪ "ያልተፈቀደ ቀሪ" ነው። አንድ/ዲት ተማሪ አንድ የትምህርት ቀን ከቀረ/ከቀረች እና ፈቃድ/ይቅርታ ከሌለው/ከሌላት፣ ተማሪው/ዋ ባመለጠው/ባመለጣት በያንዳንዱ የትምህርት ክፍል ያለፈቃድ መቅረት ይመዘገብበታል/ይመዘገብባታል።

ያለፈቃድ በተቀረበት ቀን ርእሰመምህሩ/ሯ ተማሪው/ዋ ከትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዳይሳተፍ/እንዳትሳተፍ መከልከል ይችላል/ትችላለች። እያንዳንዱ ት/ቤት በየቀኑ በት/ቤት መገኘትን፣ በት/ቤት የተገኙበትን ቀናቶች ለመቆጣጠር፣ እና (ጣልቃ-ገብ) ርምጃዎችን ለማቅረብ/ለመውሰድ አካሄድ/አሠራር ይዘረጋል።

ህጋዊም ይሁን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከመጠን ያለፈ ቀሪ እና/ወይም አርፍዶ የተመጣባቸው ቀናትን ያስመዘገቡ የአንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች አግባብ ወደሆነ የጣልቃ-ገብ አገልግሎት ርምጃ ሊላኩ ይችላሉ በርእሰመምህሩ/ሯ ወይም በእርሱ/ሷ ተወካይ ፈቃድ፣ ደጋግሞ የመቅረት አዝማሚያ ያሳዩ ተማሪዎች በት/ቤት በመደበኛነት መገኘትን ለመጨመር የተቀረጹ ከበድ ያለ የጣልቃ-ገብነት አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ ወደ ተገቢው ሠራተኛ ወይም ከት/ቤት ውጭ ወደ ሚገኙ ሌላ ኤጀንሲዎች ሊላኩ ይችላሉ። አምስት ቀኖች ወይም ከዚያ በላይ ከት/ቤት ያለፈቃድ የቀሩ ተማሪዎች ት/ቤት ቀሪ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ይሰጣቸዋል።

በክፍል ውስጥ ሦስት ቀናቶችን ከፈቃድ ውጭ ቀሪ ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች (በክፍል) ሊወድቁ/ሊደግሙ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው ሲሆን ወደ አማካሪዎቻቸውና አስተዳደራቸውም ይላካሉ/ይመራሉ። ሦስት ቀኖችን ካረፈዱ/ይቅርታ ያልተደረገላቸው አርፋጆች እንደ አንድ ቀን ያለፈቃድ ሕገ-ወጥ መቅረት ተደርጎ ይቆጠራል። ካውንስለሩ/ሯ/አማካሪው/ዋ ከተማሪው/ዋ እና ከወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር ይመካከራል/ትመካከራለች፣ ለቀሪዎቹ የቀረቡትን ምክንያቶች ያረጋግጣል/ታረጋግጣለች፣ እንዲሁም አግባብ የሆኑ እርምጃዎችን ይወስናል/ትወስናለች።

ከክፍል ያለፈቃድ ለአምስት ቀናት ቀሪ የሆኑ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ማናቸውም ቀሪ በስህተት እንደተመዘገበ ራሳቸው ወይም ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው ከአመኑ፣ የMCPS ቅጽ 560-26A፣ Appeal of Attendance Recordingን፣ እንዲያቀርቡ፣ ወይም ከአማካሪዎቻቸው/አስተዳዳሪዎቻቸው ጋር በመሆን በትምህርት ገበታ ላይ የመገኘት ማሻሻያ ርምጃዎች እቅድ እንዲያወጡ ወዲያውኑ ይነገራቸዋል/እንዲያውቁት ይደረጋሉ። አንድ ይግባኝ ወይም መቅረትን ለማስወገድ የሚወሰድ የጣልቃ-ገብ/ርምጃ እቅድ በተማሪው፣ በወላጅ/አሳዳጊ፣ ወይም በአማካሪ/አስተዳዳሪ ሊጀመር/ሊጠነሰስ ይችላል። የአማካሪው/አስተዳዳሪው ቡድን ተማሪው/ዋ ሳይከታተል/ሳትከታተል ለቀሩበት ክፍለ ጊዜ ስለ ማካካስ ከመምህሩ/ሯ ጋር ይመካከራል እንዲሁም መረጃውን ለተማሪው/ዋና ለተማሪው/ዋ ወላጅ/አሳዳጊ ያሳውቃል። ትምህርት ላይ መገኘት/መቅረት የተመለከተ የይግባኝና የጣልቃ-ገብነት/ርምጃዎች እቅድ ቅጾች በምክር አገልግሎትና በአስተዳደር ጽ/ቤቶች እንዲሁም በት/ቤቱ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል። አስተዳዳሪው/ዋ የጣልቃ-ገብ እቅዱን ከመረመሩ በኋላ (በፊርማቸው) ያጸድቁታል። ተማሪው/ዋ ወይም በትምህርት ገበታ ላይ መገኘትንና አለመገኘትን በተመዘገበበት ሁኔታ ላይ ይግባኝ መጠየቂያ ቅጽ ወይም በትምህርት ገበታ ላይ መገኘትን ማሻሻያ የጣልቃ-ገብ/ርምጃ ሳያሟላ/ሳታሟላ እና/ወይም ከህግ ውጭ በመቅረቱ የበለጠ ከቀጠለ/ች፣ ተማሪው/ዋ በዛ ኮርስ/ትምሀርት የመውደቅ አደጋ ላይ እንደሆነ/ች ተደርጎ ይወሰዳል።

በቀሪነት ወቅት ያመለጡ ስራዎችየቀሩበት ህጋዊ ይዘት የፈለገውን ይሁን ያመለጣቸውን ስራ ለማስተካከል መጣር ለተማሪዎች እጅጉን አስፈላጊ ነው። ተማሪዎች ከማናቸውም ክፍል ከቀሩ በኋላ ሲመለሱ መምህራን ተመጣጣኝ ነገር ግን የተለየ ስራ ወይም ግምገማ መሰጠት ይችላሉ። ላልተፈቀዱ ቀሪዎች፣ በርእሰ መምህርሩ/ሯ እና በአመራር ቡድኑ በፀደቀው አካሄድ/አሠራር መሰረት፣ መምህራን ላመለጡ/ላልተሰሩ ስራዎች ወይም ግምገማዎች ክሬዲት መንሳት ይችላሉ።

ማጣቀሻዎች፡- ውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አደራረግ/አቀራረብ (Grading and Reporting)የMCPS ደንብ IOA-RA፣ የባለተሰጥኦና የላቀ ችሎታ ትምህርት (Gifted and

Talented Education)የMCPS ደንብ IQB-RA፣ ከስርአተ-ትምህርት ውጭ የሆኑ እንቅስቃሴዎች

(Extracurricular Activities)የMCPS ደንብ JEA-RA፣ የተማሪ በክፍል/በትምህርት ገበታ መገኘት ሁኔታ

መዝገብ (Student Attendance)የMCPS ደንብ JGA-RB፣ እገዳና ስንብት (Suspension and Expulsion)የMCPS ደንብ JGA-RC፣ የአካል ጉዳተኝነት ያለባቸው ተማሪዎች እገዳና

ስንብት (Suspension and Expulsion of Students with Disabilities)ሜሪላንድ የተማሪ የመዝገብ ስርአት መመርያ (Maryland Student Records

System Manual)የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት የኮርስ መፅሄት(MCPS

High School Course Bulletin)

¡ የክፍል ሥራውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብየውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ ልምምዶች ፍትሃዊ፣ ትርጉም ያላቸው፣ እና ለሁሉም ተማሪዎች ጥብቅ የአፈፃፀም መመዘኛ ደረጃዎችን የሚያሟሉ ይሆናሉ። ውጤቶች/ማርኮች/ በት/ቤት ስርአት ውስጥ በአጠቃላይ የፀና ትርጉም ይኖራቸዋል እናም የሚመሰረቱት፣ በስርአተ ትምህርት እንደተጠቀሰው፣ በክፍል ደረጃና ከኮርስ በሚጠበቁት ላይ ነው። የቦርድን መመርያ IKA፣ የውጤት አሰጣጥና ሪፖርት አደራረግን፣ በwww.montgomeryschoolsmd.org/departments/policyይመልከቱ።

ከ1ኛ-5ኛ ክፍሎች፣ ውጤቶች በክፍል ደረጃ የትምህርት (አካደሚያዊ) ስኬትን ያንፀባርቃሉ/ያሳያሉ። መምህራን ተማሪዎች እውቀታቸውን፣ ምክንያታዊ አስተሳሰባቸውንና የፈጠራ ችሎታዎቻቸውን፣ እንዲሁም በቃል፣

Page 11: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ¡ 2017–2018 ¡ 3

በጽሁፍ፣ እና በአፈጻጸምና በውጤቶች የአካዴሚያዊ ስኬት ክህሎቶቻቸውን ማሳየት የሚችሉባቸውን በርካታና የተለያዩ እድሎች ለተማሪዎች በማቅረብ ግንዛቤአቸውን ይፈትሻሉ።

ከ6ኛ-12ኛ ክፍሎች፣ ውጤቶች የሚያንፀባርቁት ኮርሶቹን ለማጠናቀቅ የሚጠበቀውን የትምህርት (አካደሚ) ስኬትን ነው። በመካከለኛ ት/ቤቶችና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ውጤት ለመስጠት፣ እንደገና ለማስተማር/እንደገና ለመገምገም፣ እና ለቤት ሥራ መምህራን የMCPSን ከ6ኛ-12ኛ ክፍሎች አካሄዶች/አሰራሮችን (MCPS Procedures in Grades 6–12) ተግባራዊ ያደርጋሉ።

አስተማሪዎች ለአንድ ተግባር ወይም ለግምገማ የሚሰጡት ውጤት/ነጥብ ከ50 በመቶ ያላነሰ መሆን አለበት። ተማሪው/ዋ የተሰጠው/ጣትንን ተግባር ለመፈፀም መሰረታዊ መስፈርቶች እንኳ ለማሟላት ጥረት አላደረገም/ችም ወይም ተማሪውው/ዋ በአካዴሚያዊ ማጭበርበር ተሳትፏል/ፋለች ብሎ/ላ ካመነ/ች አስተማሪው/ዋ ዜሮ መስጠት ይችላል/ትችላለች። በትምህርት ማጭበርበር ምሳሌ የሚከተሉትን ያካትታል። በነዚህ ባይወሰንም፤ ያልተፈቀደውን፣ ሚዛናዊ ያልሆነ፣ የተጭበረበረ፣ መቀበል/መውሰድ/መስጠት፣ በሌሎች ተማሪዎች ላይ ይሉኝታቢስ/መቅኖ ያጣ ጥቅም ለመውሰድ ማጭበርበር፣ በተፅእኖ፣ ክህደት፣ ሌብነት/ስርቆት፣ ማታለል፣ ንግግር፣ ምልክት፣ በሰውነት እንቅስቃሴ ማዘናጋት፣ መገልበጥ፣ ወይም ማናቸውም ሌላ ዘዴ ተማሪዎችና ወላጆች/አሳዳጊዎች በግምገማዎች ወይም በሌላ ውጤት/ማርክ የተሰጠበት ስራ ውስጥ የሚገኝ መረጃ እንዳያጋሩ ወይም እንዳያሳራጩ ይጠበቅባቸዋል።

መምህራን የማስረከቢያ ቀኖችና የጊዜ ገደብ ይወስናሉ። መምህራን ማስረከቢያ ቀንና የጊዜ ገደብንየማስረከቢያ የመጨረሻ ሰአት/ እንዲለዩ/እንዲነጥሉ ይጠበቅባቸዋል፤ ቢሆንም፣ ማስረከቢያ ቀንና የጊዜ ገደብ አንድ ላይ የሚወድቁበት/የሚሆኑበት ወቅት ሊኖር ይችላል። ከማስረከብያ ቀን በኋላና በጊዜ ገደብ (deadline) የቀረበ ስራ ከውጤቱ/ከማርኩ ከአንድ የፊደል ደረጃ ወይም ከ10 በመቶ ባልበለጠ ዝቅ ሊደረግ ይችላል። ከጊዜ ገደብ በኋላ ገቢ የተደረገ ስራ ዜሮ ተብሎ ይመዘገባል።

መምህራን ተጨማሪ ክሬዲት አይሸልሙም።

እነዚህ አካሄዶች ለወላጆች/አሳዳጊዎች እና ተማሪዎች በMCPS ድረ-ገፅ www.montgomeryschoolsmd.org/info/grading{72}፣ እና በት/ቤቶች ዋና ፅ/ቤቶች ይገኛሉ።

የላቀ ደረጃ (Honors)፣ ከፍተኛ ደረጃ(Advanced-level)፣ እና ለከፍተኛ ደረጃ ምደባ Advanced Placement(AP) ኮርሶች

ርዕሰ መምህራኑ የላቀ ትምህርቶች/ኮርሶችን (Honors፣ advanced-level፣ and/or AP courses) ፈተናዎች/ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ/ለመቀበል ብቃት፣ ተነሣሽነት፣ ወይም ችሎታ ያላቸው ሁሉም ተማሪዎች የመሳተፍ እድል ማግኘታቸውን ያረጋግጣሉ። እያንዳንዱ ት/ቤት የላቀ ማዕረግ፣ ከፍተኛ-ደረጃ፣ እና ወይም ለAP ኮርሶች ምደባ (Honors, advanced-level, and/or AP courses ) ፀንተው ፕሮግራሙን እና ከፍተኛ-ደረጃ የኮርስ ስራዎችን ለመከታተል ብቃት እና ትጋት ላላቸው ተማሪዎች በሙሉ እንዲገቡ ክፍት ማድረግ አለበት። የተማሪ ጥንካሪዎች መግለጫን (profile) በሚከተሉት በርካታ መመዘኛዎች ላይ ጠንካራ ግምገማ በማድረግ ማወቅ/መወሰን ይቻላል

• ኮርሱን ለመውሰድ የቅድሚያ መስፈርቶች የዕውቀት ደረጃ (A፣ B፣ ወይም C ውጤቶች/ማርኮች)

• የወላጅ/ሞግዚት "የብቃት/ችሎታ/" የድጋፍ ሀሳቦች/ምስክርነት• መደበኛ የፈተና ውጤቶች፣ እንደአግባቡ• ከበድ ያሉ/ተፈታታኝ ስራዎችን ተቋቁሞ ለመፈፀም ፈቃደኛነት• የተማሪ ፍላጎት ወይም ተነሳሽነት• የመምህር/አማካሪ (የችሎታ/ብቃት) የድጋፍ ሀሳቦች/ምስክርነት• የስራ ናሙናዎችና የመረጃ ሰነዶች

¡ የተማሪ አገልግሎት ትምህርትየሜሪላንድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማን ለማግኘት የሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ ከምዝገባ፣ ክሬድት፣ ኮርሶች፣ እና የብቃቶች የምረቃ መስፈርቶች በተጨማሪ የአገልግሎት ትምህርት ሠዓቶችን ማጠናቀቅ አለባቸው። የአገልግሎት ትምህርት ሰአቶች የ5ኛ ክፍልን ከጨረሱ በኋላ ከሚመጣው ሰመር /summer/ ጀምሮ ለማጠራቀም ይችላሉ። ከአንድ (ት/ቤት) ወደ ሌላ ለተዘዋወሩ ተማሪዎች ከሚደረግ የተወሰነ አስተያየት በስተቀር ተማሪዎች ከምረቃ በፊት 75-የአገልግሎት ትምህርት ሰአት ማጠናቀቅ አለባቸው።

የMCPS ተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት ዝርዝር ፕሮግራም በwww.montgomeryschoolsmd.org/departments/ssl/ ወይም በማናቸውም መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት አስተባባሪን በማነጋገር ሊገኝ ይችላል።

ማጣቀሻዎች፡- COMAR 13A.03.02.05 የተማሪ አገልግሎትየተማሪ አመራር አስተባባሪ፣የተማሪ አገልግሎት ትምህርት፣ እና በጎፈቃድ

አገልጋዮች፦ 301-279-3454 or [email protected]

¡ የተማሪዎች አስተዳደርተሳትፎተማሪዎች የተማሪዎች አስተዳደር የማቋቋምና የመሳተፍ መብት አላቸው። ተማሪዎች በተማሪ አስተዳደር ድርጅት አማካኝነት በት/ቤት ጉዳዮች ድምፃቸውን የማሰማት መብት አላቸው። ተማሪዎች ተጠያቂነቱ ለተማሪዎች የሆነ ውጤታማ የተማሪ አስተዳደር ድርጅት ለመፍጠር የመስራት ሃላፊነት አለባቸው። በህጋዊ መንገድ ት/ቤት የገባ/ች፣ አካዳሚያዊ ብቃት ያለው/ላት፣ እና በት/ቤቱ መተዳደርያ ደንብ (ህግ-መንግስት) የተቀመጡትን ማናቸውንም መስፈርቶች የሚያ(ምታ)ሟላ ማንኛው(ዋ)ም ተማሪ የተማሪዎች አስተዳደርን ለመምራት ለመወዳደርና ቦታውንም ለመያዝ ይችላል/ትችላለች። ተማሪዎች የተመራጭነቱን ቦታ ይዘው ለመቀጠል በትምህርት ችሎታቸው ብቁ ሆነው መቀጠል አለባቸው። ይህም ማለት የተመራጭ ቦታ ለመያዝ አንድ/ዲት ተማሪ ቢያንስ 2.0 አማካይ ነጥብ ውጤት እንዳለው/እንዳላት ማረጋገጥና የተማሪ ውጤት መግለጫ ወረቀት ላይ ከአንድ ባላይ የመውደቂያ ነጥብ እንዳይኖረው/ራት ያስፈልጋል። በተማሪዎች አስተዳደር መሳተፍ የአገልግሎት ትምህርት ሰአቶችን ማግኘት ያስችላል።

የመምህራን/የፋኩሊቲ ድጋፍየት/ቤት ሠራተኞች አባላት የተማሪን በተማሪ አስተዳደር የመሳተፍ መብት ይደግፋሉ። የተማሪዎች አስተዳደር ተማሪዎች በት/ቤቱ ስራ/እንቅስቃሴ ላይ ሀሳባቸውን ማቅረብ እንዲችሉ ማስቻሉን ርእሰ መምህሩ/ሯ ያረጋግጣል/ታረጋግጣለች።

በፀደይ/ስፕሪንግ ወራት፣ የተማሪ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለሚመጣው አመት የአማካሪ መሾምን በሚመለከት ከርእሰ መምህሩ/ሯ ጋር ይመክራል፣ እናም አማካሪው/ዋ ከመሾሙ/ሟ በፊት የተማሪዎቹ አስተያየት በጥንቃቄ ይታያል።

የት/ቤት አስተዳደር አባላት የተማሪ አስተዳደር አስፈላጊ አቅርቦቶችና የክፍል አገልግሎት እንዲያገኝ ያግዛሉ።

አስተዳደሩ ባፀደቀው የተማሪ አስተዳደር እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ ከትምህርት ክፍል የቀሩ ተማሪዎች በፈቃድ ስለመቅረታቸው ማስረጃ ይያዝላቸዋል ነገር ግን ያመለጧቸውን ስራዎች የማካካስ ሃላፊነትም ይኖራቸዋል።

የተማሪዎች አስተዳደር ስልጣኖችእንደአስፈላጊነቱ ከት/ቤት ሰራተኞች/አማካሪ ጋር በመማከር ተማሪዎች ለተማሪ አስተዳደሩ መተዳደርያ ደንብ ወይም በስራ ላይ ላለው መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያዎች በፅሁፍ የማዘጋጀት ሃላፊነት አለባቸው። ሁሉም የመተዳደርያ ደንቦች የርእሰ መምህሩ(ሯ)ን ውሳኔ የመስጠት ስልጣን እውቅና የሚሰጥ አንቀፅ ማካተት አለባቸው። የMCPSን ደንቦች እስካልጣሰ ወይም በርእሰ መምህሩ/ሯ ምዘና በት/ቤቱ ውጤታማ የስራ ሂደት ላይ በጉልህ ጣልቃ ይገባል ተብሎ እስካልተገመተ ድረስ ተማሪዎች ርእሰ መምህሩ/ሯ የተማሪ አስተዳደር መተዳደሪያ ደንቡን ወይም በሱ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ያጸድቀዋል/ታጸድቀዋለች ብለው የመጠበቅ መብት አላቸው። ያልፀደቀበት ምክንያቶች ለተማሪዎች በፅሁፍ ይገለፅላቸዋል የአስተዳደሩን ቅሬታዎች አስመልክተው የመተዳደርያ ደንቡን ለመከለስ እድል መሰጠትም አለባቸው።

ተማሪዎች፣ በተማሪዎች አስተዳደር አማካይነት፣ በተማሪ አስተዳደር ለሚቀርቡ ማሳሳቢያዎች በአምስት የትምህርት ቀኖች ውስጥ ከት/ቤቱ አስተዳደር መልስ የማግኘት መብት አላቸው። ማሳሰብያዎች ተቀባይነት ካላገኙ ወይም ካልተስተካከሉ አስተዳደሩ፣ በጽሁፍም ሆነ በቃል፣ ምክንያቶችን ያቀርባል/ይሰጣል። ማሳሰቢያዎቹ ሰፊ ወይም ውስብስብ ከሆኑ፣ የት/ቤቱ አስተዳደር፣ ከተማሪዎች አስተዳደር ተወካዮች ጋር በመመካከር፣ የቃል ወይም የፅሁፍ መልስ የሚሰጥበትን ተቀባይነት ያለው የጊዜ ገደብ ይወስናል።

Page 12: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

4 ¡ 2017–2018 ¡ A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES

እስከያዙ/እስካሳዩ ድረስ ወይም የሚሸጡ ወይም በሌላ ሁኔታ የሚሰራጩ ህትመቶቸ ከሆኑ ደግሞ በMCPS ውስጥ በሚ(ምት)ማር ተማሪ እስከሆኑ ድረስ።

• ተማሪዎች በት/ቤት ድጋፍ የማይዘጋጁ ሕትመቶችና ማስታወቂያዎችን ለመለጠፍ/ለማስቀመጥ በተፈቀዱ ሰሌዳዎች ላይ፣ ግርግዳዎች ላይ ወይም ሌሎች ለተመሳሳይ አገልግሎት መጠቀምያ ቦታዎች ላይ በግልጽ እንዲታይ ለማድረግ እና በት/ቤት ላልተዘጋጁ ተመሣሣይ ጽሑፎችና ማስታወቂያዎችን የመገደብ ስርዓትን በመከተል/በማክበር ለማሰራጨት፣ ለመለጠፍ/ለማስቀመጥ መብት አላቸው።

• ተማሪዎች በአካባቢ ት/ቤት በተዘረጋው አካሄድ ወይም "MCPS ደንብ JFA-RA" ስለ ተማሪ መብት እና ግዴታዎች/ሃላፊነቶች በተገለጸው መሠረት የት/ቤትን ድጋፍ ሰጭ አካል/ስፖንሰርስ ውሳኔ ይግባኝ የመጠየቅ መብት አላቸው።

ርዕሰ መምህሩ/ሯ በተማሪ የተዘጋጀውን የሕትመት ሥራ ወይም ሌሎች የማስታወቂያ፣ ወይም የማስታወቂያ ማቴሪያል ስርጭት እንዳይደረግ ለማገድ፣ ለማስቆም፣ ወይም ለመከልከል የሚችለው/የምትችለው፤ በሚከተሉት መመዘኛዎች ተሞርኩዞ ብቻ ነው።

ጸያፍ,የሚያጥላላ, የብልግና, የሚያነሳሳ, ስም የሚያጠፋ, አስነዋሪ, ወይም የትንኮሳ፣ የማስፈራራት፣ የማሸማቀቅ ቋንቋዎችን ያዘለ ከሆነ፤

• መተማመኛ/ማረጋገጫ የሌለው ግላዊነትን የሚዳፈር ከሆነ• ተማሪዎችን ግልጽና ሊፈጸም የሚችል አደጋ እንዲጠነስሱ የሚያነሳሳ ከሆነ፣

(ሀ) የሕገወጥ ድርጊት ኮሚሽን፣ የካውንቲውን የቦርድ መርኆች መጣስ፣ እና ወይም የ MCPS ደንቦችና ሕጎች፣ ወይም (ለ) በሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ያለውን የሕዝብ ት/ቤት የቁሳቁስና/ንብረት ሥራ በከባድ ሁኔታ ማደናቀፍ፣ "ከባድ ማስተጓጎል" ማለት፣ በት/ቤት ስራ ጣልቃ መግባት, ወይም በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሥርዓት በሌለው ሁኔታ ለአመፅ መነሳሳት፣ አድሞ ከት/ቤት መቅረት፣ አድሞ መቀመጥ፣ ንብረት ማውደም፣ እና ረግጦ መውጣት

• የስቴት ወይም የፌደራል ሕግን የሚፃረር ከሆነ ለምሳሌ፦ ይህ የሚያካትተው አደገኛ የሆኑ በተማሪዎች ላይ የጤና ጠንቅ ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም ለደህንነታቸው የሚያሰጉ ቁሳዊ ነገሮችን፣ ወይም ተማሪዎችን ለጎጂ መዳኒቶች፣ ለአልኮል፣ ትምባሆ ለመጠቀም ወይም ለማጬስ፣ ወይም ማናቸውም ለአመፅ መንስኤ/ሁከት፣ የሚያነሳሱ፣ ጾታ፣ ሕገ-ወጥ መድሎ፣ ወይም ሌላ ሕገ-ወጥ ድርጊቶች

ቢሆንም ስለእንደነዚህ ያሉ ድርጊቶች ኃላፊነት የተሞላበት ውይይት እንዳይካሄድ ለመከልከል ይህን መመሪያ መጠቀም አይገባም። የአንድ ተማሪን ዝግጅት/መሰናዶ፣ የተማሪን ህትመት፣ ወይም በተማሪዎች የጽሁፍ/ማቴሪያል ስርጭት በተመለከተ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ርእሰ መምህራን መከተል የሚገባቸውን አካሄድ የMCPS ደንብ JFA-RA ዘርግቷል።

የፖለቲካ መገልገያ/ቁስማንም ሰው፣ ህገ መንግስታዊ ያልሆነ፣ ህገ ወጥ፣ የስቴት የምርጫ ህጎችን የሚፃረር፣ ወይም፣ በርእሰ መምህሩ/ሯ አስተያየት/አስተሳሰብ፣ ለትምህርት አካባቢ የረብሻ አደጋ ያመጣል ተብሎ የተገመተ የምርጫ ዘመቻ ፅሁፍ/ህትመት ማሰራጨት አይችልም። ይህ ውሳኔ ይግባኝ ሊባልበት ይቻላል። የይግባኙ ቅደም ተከተል በዚህ መፅሔት (ገፅ 9) የይግባኝ-አቤቱታ አቀራረብ ሂደት (Appeals-Complaint Procedure—Due Process) ተገልጿል።

እነዚህን ደንቦች መከተል ከተቻለ ሌላ ፓለቲካዊ ጽሑፎች/ማቴሪያሎች ሊሰራጩ ይችላሉ።ጽሑፎች/ማቴሪያሎችን ለሰው ሁሉ ከማደል ይልቅ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ብቻ ማቅርብ። ይህን ህግ ሳይጥሱ ስርጭት ማድረግ የሚያስችሉ ጥቂት መንገዶች እነዚህ ናቸው፡- ፍላጎት ላላቸው ብቻ ማሰራጨት፣ መግለጫ ቦታ ማዘጋጀት፣ ወይም ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ መለጠፍ።• አንድ ተማሪ የፖለቲካ ቁሶችን በእግረኛ መንገዶች፣ በካፊቴሪያ፣ በሕንፃ

ውስጥ መተላለፊያዎች፣ ወይም የተማሪ አስተዳደር ክፍሎችና ስፍራዎች ላይ ሆኖ ማሰራጨት ይችላል። ተማሪዎች በመማርያ ክፍሎች፣ በሚድያ ማእከል፣ ወይም በሌሎች የት/ቤት ክፍሎች በትምህርት ቀን የፖለቲካ ቁሶችን ማሰራጨት አይችሉም፣ ከነዚህ በስተቀር-• ክፍሉ ለፈቃደኛ መሰብሰብያ ጥቅም የሚውል ከሆነ፣ ወይም• ማቴሪያሉን በክፍል ውስጥ የመደበኛ ማስተማሪያ ፕሮግራም አካል፣

ወይም የበጎ ፈቃድ መድረክ፣ ወይም በተማሪዎች የሚካሄድ ሴሚናር ላይ መጠቀሚያ ሲደረግ፣

• የፖለቲካ ቁስ ሁልጊዜ ከትምህርት ክፍለጊዜ ውጭ ብቻ መሠራጨት አለበት።• የምርጫ ዘመቻ ቁሳቁሶች የፈቃድ መስመር እንዲኖራቸው ያስፈልጋል (የMCPS

ደንብ KEA-RA፣ በፖሊቲካ ምርጫ ውድድር ተሳትፎና የምርጫ ውድድር ቁሳቁሶች ስርጭትን) ይመልከቱ።

የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ፣ የተማሪዎች አስተዳደር አማካሪ፣ እና ርእሰ መምህሩ/ሯ በየወቅቱ እየተገናኙ ስለ ተማሪዎች አስተዳደር ድርጅት ግስጋሴና ቅሬታዎች ይመካከራሉ።

መጣቀሻዎች፡-የMCPS ደንብ IQD-RA፣ ከስርአተ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉ

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት የMCPS ደንብ IQD-RB፣ በተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ለሚሳተፉ

የመካከለኛ ት/ቤት ተማሪዎች አካዳሚካዊ ብቃት MCPS Regulation IQD-RB, Academic Eligibility for Middle School Students Who Participate in Extracurricular Activities

የMCPS የተማሪ አመራር፡- 301-444-8620 (http://www.montgomeryschoolsmd.org/departments/student-leadership/ )

¡ የመጠየቅና ሀሳብን የመግለጽ ነፃነትንግግርበስቴት ወይም ካውንቲ የስርአተ-ትምህርት ሰነዶች የተቀመጡትን ገደቦች ባልጣሰ ሁኔታ ተማሪዎች አማራጭ ሀሳቦችን እንዲገመግሙ እና የራሳቸውን አስተያየት መያዝ እንዲችሉ ግላዊ አስተያየታቸውን መግለጽ፤ እና የመደምደሚያ ሀሳብ ላይ ከመድረሳቸው በፊት መረጃ መተንተን እና መገምገም እንዲችሉ፤ በአከራካሪ/አነጋጋሪ ርእሶች ላይ የተለያዩ ሀሳቦች የማግኘት መብት አላቸው፤። ተማሪዎች በሚማሩባቸው ኮርሶች ላይ የሚቀርቡትን የተለያዩ አመለካከቶችን እና አስተሳሰቦችን በአፅንኦት የመከታተል እና በሚካሄዱት ውይይቶች የራሳቸውንም ሃሳብ/ተሳትፎ እየተካለበት፣ የሌሎችን የተላያየ አመለካከት/ሃሳብ ማክበርና መረን/ብልግና/ስድነት እንዳይሰፍን እና በሌሎች ሃሳብ ላይ አዎንታዊ የትምህርት እና የሥራ አካባቢን የሚበክሉ እንዲሁም ሁሉም ዘንድ የመከባበር ሁኔታን የሚያበላሹ አዋራጅ/የዘለፋ/የስድብ ቃሎችን ከመጠቀም/ከመናገር የመቆጠብ ሃላፊነት አለባቸው።

ስብሰባተማሪዎች ለነሱ አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ለማካሄድና በሰላማዊ መንገድ ለመሰለፍ የመሰብሰብ መብት አላቸው። ተማሪዎች ያቀዱት ተግባር/እንቅስቃሴ በት/ቤት ቀን ይፈቀድ እንደሆነ እና እንዳልሆነ፣ የሚካሄድበትን ሰአት እና ቦታ፣ እንዲሁም የሚያስፈልገውን የቁጥጥር አይነት በተመለከተ ከት/ቤት አስተደደር ጋር የመማከር ኃላፊነት አለባቸው። ተማሪዎች በተጨማሪ ከት/ቤት ሰራተኞች ጋር ተባብሮ የመስራት፣ እንቅስቃሴው ስርአት የያዘ መሆኑን ለማረጋገጥ እርምጃዎች የመውሰድ፣ አና የተሳተ ስራን የማካካስ ሀላፊነት አለባቸው።

አቤቱታዎችተማሪዎች ከት/ቤት አስተዳዳሪዎች የመገናኘትና አለመግባባቶችን ማጣራትና ለአቤቱታ መነሻ በሆኑ ርእሶች የመረጃ መለዋወጫ መድረክ የማዘጋጀት ሃላፊነት አለባቸው። የት/ቤት ሥራዎችን እስካላደናቀፉ ድረስ፣ ተማሪዎች አቤቱታዎችን ከትምህርት ክፍለጊዜ ውጭ የማሰራጨት መብት አላቸው። ተማሪዎች የሚያቀርቧቸው አቤቱታዎች የተማሪዎችን እና ሌሎች በት/ቤት ማህረሰብ የሚገኙ ሰዎችን ጤና ወይም ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን የማያበረታቱ መሆናቸውን እንዲሁም ስም የሚያጠፋ/የሚያጎድፍ ወይም ባለጌ/ጸያፍ አለመሆናቸውን ወይም በሌላ ሁኔታ በት/ቤቱ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ ማስተጓጎል የማያስከተሉ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ይህን ሃላፊነት ለማሟላት ካልቻሉ የት/ቤቱ አስተዳደር የአቤቱታዎችን መሰራጨት ለማቆም/ማስቆም ይችላል። በት/ቤት ደረጃ፣ ተማሪዎች በአምስት የትምህርት ቀኖች ውስጥ መልስ የማግኘት መብት አላቸው።

ሕትመቶች፣ (የመድረክ) ዝግጅቶች፣ እና መረጃዊ መገልገያዎችሕትመቶች፣ የመድረክ ዝግጅቶችን፣ እና መረጃዊ መገልገያዎችን በተመለከተ ተማሪዎች የሚከተሉት መብቶች አሏቸው።

• ተማሪዎች በት/ቤት የተደገፉ ሕትመቶችን (ለምሳሌ፦ ጋዜጣዎች፣ ዓመታዊ መጽሀፍት፣ የሥነጽሑፍ መጽሔቶች) እና በት/ቤት የተደገፉ እንቅስቃሴዎችን (ለምሳሌ፦ የት/ቤት ጭውውቶች (plays)፣ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች) ለማዘጋጀት መብት አላቸው።

• ተማሪዎች እታች የሚገኙትን መመሪያዎችና የት/ቤት ድጋፍ/ስፖንሰር አቅጣጫና ምሪት እስከተከተሉ ድረስ በት/ቤት የተደገፉ ህትመቶችንና ዝግጅቶችን ይዘት የመወሰን መብት አላቸው።

• ተማሪዎች ት/ቤት ስፖንሰር ያላደረጋቸውን ህትመቶች የማሰራጨት መብት አላቸው፣ ህትመቶቹ የስፖንሰር አድራጊውን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም

Page 13: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ¡ 2017–2018 ¡ 5

ተሳትፎ በፖሊቲካ ምርጫ ውድድሮችከ9–12 ክፍሎች የሚገኙ ተማሪዎች በወላጅ/አሳዳጊ ስምምነት፣ በርእሰ መምህሩ/ሯ ወይም የርሰ መምህር ተወካይ ፈቃድ፣ እና የፖለቲካ ተወዳዳሪው ወይም ድርጅቱ በተሳትፎው ተስማምቶ ከሆነ በትምህርት ሰዓቶች በፖለቲካ የምርጫ ዘመቻ ሊሳተፉ ይችላሉ። ተቀዳሚ (primary) ወይም አጠቃላይ ምርጫ ልክ ከመካሄዱ በፊት ባለው የሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለእንደዚህ አይነቱ ተሳትፎ በአንድ የትምህርት አመት በድምሩ ሶስት የትምህርት ቀኖች ፈቃድ ለተማሪዎች ሊሰጥ ይችላል። የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሠዓቶችን በፖለቲካ ዘመቻ በመሳተፍ ለማግኘት ተማሪዎች MCPS Form 560-50, Individual Student Service Learning (SSL) Requestበመሙላት ለማንኛውም የፖለቲካ አገልግሎት ቢሮ ለሚወዳደር ሰው አገልግሎት ከመሰጠቱ በፊት ፈቃድ ጠይቆ ማግኘት ያስፈልጋል።

ማጣቀሻዎች፡-የMCPS ደንብ KBA-RB፣ የMCPS ድረ-ገጽ የትምህርት አለማዎችና አስተዳደርየMCPS ደንብ KEA-RA፣ በፖለቲካ የምርጫ ውድድር ተሳትፎ እና የምርጫ

ውድድር ቁሳቁሶች ስርጭትየMCPS Regulation IGT-RA፣ ስለ ኮምፒውተር አጠቃቀም ስርአቶች፣ ስለ

ኤሌክትሮኒክ መረጃዎች፣ እና ስለ ኮምፒዩተር አውታር ደህንነት/ጥበቃ የተጠቃሚ ሀላፊነቶች

የMCPS ደንብ IID-RA፣ በMCPS የትምህርት መስመሮች/Cablecast የሚሰራጩ ፕሮግራሞች

¡ የአገር ወዳድነት እንቅስቃሴዎችተማሪዎች በት/ቤት በሃገር ወዳድ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ እና/ወይም ለማየት እድል ይኖራቸዋል።

ተማሪዎች በአገርወዳድነት እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ ፈቃደኛ ካልሆኑ እንዳይገደዱ፣ ወይም ቅጣት እንዳይደርስባቸው፣ ወይም ሃፍረት እንዳይደርስባቸው መብታቸው የተጠበቀ ነው።

አንድ ተማሪ ሌሎች የአገር ወዳድ እንቅስቃሴዎች በሚሳተፉት ላይ ጣልቃ በመግባት ማስተጓጎል/ማቃወስ አይ(ት)ችልም።

ማጣቀሻዎች- የሜሪላንድ ማብራርያ ኮድ፣ የትምህርት አንቀፅ ክፍል 7-105 (Annotated

Code of Maryland, Education Article, Section 7-105)

¡ የሃይማኖት ነፃነትተማሪዎች የሚከተሉት መብቶች አሏቸው—

• ከኃይማኖት ጋር ያልተያያዙ ከሆኑና የኃይማኖት ነክ ድርጊቶችን የማያካትቱ በት/ቤት አማካይነት የሚካሄዱ የሆኑ እንቅስቃሴዎች፤ እና

• በኮርሶች ወይም ት/ቤት በሚያካሄዳቸው የምረቃ ፕሮግራሞች ወይም ስብሰባዎችን በመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ኃይማኖት ነክ እምነቶች በማይሰበክባቸው አካባቢ፤ እና

• ት/ቤት የማያካሂደው የተማሪዎች የፀሎት ቡድንን ጨምሮ፣ የሌሎችን መብት የማይጋፋ/የማይፃረር ወይም የት/ቤትን ሥራ የማያደናቅፍ እስከሆነ ድረስ ተማሪዎች በት/ቤት ውስጥ እንደ እምነታቸው ለማምለክ ይችላሉ።

ቦርዱ የMCPS ተማሪ ሕብረተሰብን ልዩ ልዩ ኃይማኖቶችን፣ እምነቶችን፣ እና ባህሎችን ለማክበርና እውቅና ለመስጠት ቁርጠኛ ነው/ቁርጠኝነቱን ገልጧል። MCPS የኃይማኖት ልዩነቶችን ስለማክበር መመሪያየ MCPS ህጎችን በሚመለከት ዲስትሪክቱ እንደ ማመሳከሪያ የሚመራበትን መግለጫ ይፋ ያደርጋል።

ማጣቀሻዎች:-የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS)ኃማኖታዊ ብዙህነትን ስለማክበር

መመርያዎችየMCPS ደንብ IKB-RA፣ የቤት ስራ ሂደቶች

¡ ክበቦች፣ ቡድኖች፣ እና የተማሪ ድርጅቶች

ተማሪዎች የMCPS ሕጎችን በማበክበርና በመጠበቅ በሚመለከታቸውና ለመሳተፍ በሚያስችሏቸው ክለቦች፣ ቡድኖች፣ እና በተማሪ ድርጅቶች የመሳተፍ መብት አላቸው።

MCPS ሁሉን አቀፍ የሆነና በት/ቤቶች መካከል የሚካሄድ የአትሊቲክስ ፕሮግራም የMCPSና የMaryland Public Secondary School Athletic Association (የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች አትሌቲክስ ማህበር) መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ሁሉም ተማሪዎች ያቀርባል። በት/ቤቶች መካከል የሚካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ስለ ጤንነት እና ደህንነት ጋር የተዛመደ ሁነታዎችን በሚመከት ከሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ድረ-ገጽ www.montgomery schoolsmd.org/departments/athletics/ማንበብ ይጠበቅባቸዋል።

ማጣቀሻዎች፡- የስርአት-አቀፍ አቲሌቲክ/Systemwide Athletics/ ዳይሬክተር: 240-453-

2594

በት/ቤት የተደገፋ/ስፖንሰር የተደረጉ ድርጅቶችበተወሰኑ ት/ቤት በሚደግፋቸው ድርጅቶች ለመሳተፍ፣ ተማሪዎች በአካዴሚ ብቁ ሆነው መገኘት አለባቸው። ተማሪዎች በክለቦች፣ በቡድኖች፣ ወይም የተማሪ ድርጅቶች ላይ በመሪነት ደረጃ ለመስራት ለመመረጥ ወይም ምደባ የሚፈልጉ ተማሪዎች ጥሩ ስነ-ምግባር፣ ሕግ አክባሪነትን፣ የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶችን ህጎች መታዘዝ ጨምሮ መልካም ጠባይ፣ በMCPS ቅጥር ግቢም ይሁን ከውጭ ምሳሌ መሆን ይጠበቅባቸዋል። የዲሲፕሊን ህጎችና ደንቦችን ለማስጠበቅ ርእሰ መምህራን ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ላይ ቁጥጥር/ገደብ የማድረግ ስልጣን ይኖራቸዋል። የተፈቀደላችው የተማሪ ድርጅቶች በት/ቤት መገልገያዎች የመጠቀም መብት አላቸው። ይህም የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ የድምፅ ማስተላለፍያ/ማጉያ መገልገያዎች፣ እና የፎቶኮፒ መሳርያዎች አግባብነት ያለው አጠቃቀምን ያካትታል።

ት/ቤት ስፖንሰር የማያደርጋቸው የተማሪ ድርጅቶችከዚህ የሚከተሉትን ሃላፊነቶች እስካሟሉ ድረስ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ክፍለጊዜ ውጭ ስብሰባ የማካሄድ መብት አላቸው።

• ስብሰባው የደህንነት ወይም የፀጥታ አደጋ ስጋት አያስከትልም። • ስብሰባዎቹ በፈቃደኝነትና በተማሪዎች ተነሳሽነት የተዘጋጁና በት/ቤት

ያልተወከሉ ወይም በት/ቤት የተደገፉ ተደርገው የማይወሰዱ ናቸው።• የት/ቤት ሰራተኞች ስብሰባዎችን ስፖንሰር አያደርጉም ወይም አያስተዋዉቁም፤

ሆኖም ግን የት/ቤት ሠራተኛ አባል ስለደህንነት ጥንቃቄ ሊቆጣጠር ይችላል።• የት/ቤት ተቀጣሪዎች ስብሰባዎቹን አይመሩም ወይም አይሳተፉም፣ የሃይማኖት

ስብሰባዎችም ቢሆኑ።• ስብሰባው በት/ቤቱ ውስጥ ከትምህርት እንቅስቃሴዎች አፈፃጸም ጋር በማንኛውም

ሁኔታና ጣልቃ የመግባት/የማደናቀፍ ሁኔታ ይኖረዋል ተብሎ አይታሰብም።• የት/ቤት አባል ያልሆኑ ሰዎች ስብሰባዎቹን ለመምራት ወይም በስብሳበዎቹ

በተከታታይ ለመሳተፍ አይችሉም።• የህዝብ ገንዘብ ለስብሰባዎቹ ወጪ አይደረግም (ለመሰብሰቢያ ቦታ አቅርቦት

ወጪ አይጨምርም)።

ማጣቀሻዎች፡- የቦርድ ፖሊሲ IOB፣ የአካል ጉዳተኝነት ያለባቸው ተማሪዎች ትምህርትየMCPS ደንብ IGO-RA፣ የአልኮል፣ የትምባሆ፣ እና ተማሪዎችን የሚያካትቱ

ሌሎች አደንዛዥ ዕፅ የመሳሰሉ ክስተቶች መምርያዎች የMCPS ደንብ IQD-RA፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጪ እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉ

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃትየMCPS ደንብ IQD-RB፣ የመካከመደበኛ ትምህርት ውጪ በሆኑ እንቅስቃሴዎች

የሚሳተፉ ከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት

Page 14: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

6 ¡ 2017–2018 ¡ A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES

¡ አለባበስ እና አጋጌጥበማህበረሰቡ የአለባበስ መመዘኛዎችና በአካባቢ ት/ቤት የዲሲፕሊን መመርያ በሚፈቅደው መሠረት፣ ተማሪዎች ለት/ቤት በአግባቡ የመልበስና መጋጌጥ ራሳቸውን የመንከባከብ ሃላፊነት አለባቸው። በሚከተሉት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር ተማሪዎች በአለባበስና ራስን በመንከባከብ ፈሊጥ ላይቀጡ ይችላሉ፡-

• በት/ቤት እንቅስቃሴዎች ስራ የማደናቀፍ አዝማምያ ካለው፤• በትምህርት አካባቢ ውካታ/የሚያቃውስ ሁኔታ የሚቀሰቅስ ከሆነ፤• ጤና ወይም ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ፤• ያንድ ኮርስ ወይም እንቅስቃሴ ተቀባይነት ያለው መስፈርት የማያሟላ ከሆነ፤• ከውንብድና ጋር ግንኙነት ካለው፤• ብልግና/አስነዋሪ፣ ፀያፍ፣ ያልታረመ፣ ስድ፣ ራቁት፣ ወይም ፆታዊ የግብረ

ስጋ ባህርይን የሚያጋልጥ፤ ወይም• ትምባሆ፣ አልኮል፣ ወይም አደንዛዥ እፆች መጠቀምን የሚያራምድ ከሆነ።ማጣቀሻዎች፡- የMCPSየተማሪ ስነምግባር መመሪያ-Student Code of Conduct

¡ ቴክኖሎጂየተማሪ ኃላፊነት የተሞላበት የመመርያዎች አጠቃቀም Student Responsible Use GuidelinesMCPS ከተልእኮው ጋር የሚሄዱ የኮምፒውተር መሣርያዎችን፣ የኮምፒውተር አገልግሎቶችን፣ ከት/ቤቶች እና ከተማሪዎች ጋር መገናኛ የውሂብ/የኔትዎርክ አገልግሎት ያቀርባል። ለMCPS ተማሪዎች ክፍት የሆነው ስፋት ያለው በርካታ የመረጃ ቴክኖሎጂ አዳዲስ መልካም እድሎችን እና ስጋቶችን ያስተዋውቃል። የት/ቤት ሠራተኞች እና የእያንዳንዱ ተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ ተማሪዎችን ቴክኖሎጂን በሚገለገሉበት ጊዜ ተገቢ/መልካም የአጠቃቀም ስነ-ምግባር እንዲኖራቸው ማሳወቅ እና መሠረት ማስያዝ የጋራ ኃላፊነት ነው። በት/ቤቶች፣ የተማሪዎች የድረ-ገጽ/ኦን ላይን መገናኛ መስመር አጠቃቀም እንቅስቃሴዎች በስርአት-አቀፍ ቴክኖሎጂ የመከላከል ጥበቃ እርምጃዎች በት/ቤት ሰራተኞች አማካይነት ቁጥጥር ይደረግባቸዋል። ተማሪዎች መረጃዎችንና መገልገያዎችን ከስርቆሽ፣ በተንኮል ከሚደረስ ጉዳት፣ ከአልተፈቀደ አጠቃቀም፣ ከሚያስተጓጉልና ከኪሳራ መጠበቅ/መከላከል እንዲሁም የአካባቢ፣ የስቴትና፣ የፌዴራል ህጎችን ማክበር አለባቸው።

የ MCPS ተማሪዎች በጠቅላላ በ MCPS የሚወጡትን ህጎች MCPS Regulation IGT-RA, የኮምፒውተ ስርዓቶች፣ ኤሌክትሮኒክ መረጃዎች፣ የውሂብ መገናኛ ደህንነት፣ MCPS Regulation COG-RA, እንዲሁም የግል ሞባይል መገልገያዎች፣ የሚከተሉትን ጨምሮ መከተል የሚጠበቅባቸውን የአጠቃቀም ስርአት ለመከተል መስማማት አለባቸው፡

• ተማሪዎች የMCPSን አውታረ መረብ በውጤታማነት፣ በአግባቡ፣ እና ከት/ቤት ጋር ለተያያዙ አላማዎች ይጠቀሙባቸዋል እናም በዲስትሪክቱ፣ በተማሪው፣ ወይም በተማሪው ቤተሰብ የቀረቡ ማናቸውንም የቴክኖሎጂ መገልገያ፣ የሌሎች ተማሪዎችንና የት/ቤት ሰራተኛ እንቅስቃሴን ከማቃወስ ይቆጠባሉ።

• ተማሪዎች በኢ-ሜይልና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች (ለምሳሌ፣ ትዊተር፣ ብሎግስ፣ ዊኪስ፣ ፖድካስቲንግ፣ ቻት፣ ፈጣን መልእክት፣ የውይይት ሰሌዳዎች፣ ምናባዊ የመማርያ አካባቢዎች) (e.g., Twitter, blogs, wikis, podcasting, chat, instant-messaging, discussion boards, virtual learning environments) ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ይጠቀማሉ።

• ተማሪዎች ለሌሎች ስለ ሀሳባቸውና ስራቸው እውቅና ይሰጣሉ።• ተማሪዎች የግል መረጃዎችን (የቤት/ሞባይል ስልክ ቁጥሮችን፣ የፖስታ አድራሻ፣

እና የተጠቃሚ ሚስጥር ቃል) እንዲሁም የሌሎችን በሚስጢር ይይዛሉ።• ተማሪዎች ከአግባብ ውጭ የሆነ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ወድያውኑ

ያስታውቃሉ።• አግባብነት የሌለው አጠቃቀም ተለይቶ ካልታወቀ የ MCPS ኃላፊዎች የትኛው

አይነት አጠቃቀም ከአግባብ ውጭ መሆኑን ለማወቅ/ለማረጋገጥ ደንብ እና መመሪያዎችን ለመጠቀም እንደሚችሉ ተማሪዎች ይረዳሉ።

• ሁሉም የMCPS መሳርያዎች የMCPS አውታረ መረብ፣ እና ተማሪዎች የሚጠቀሙባቸው የMCPS አውታረ መረብ አካውንት የMCPS ንብረት መሆናቸውን እና ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው፣ እንደሚከፈቱ፣ እና በአውታተረ መረብ ፋይል እንደሚያዙ ተማሪዎች ይገነዘባሉ።

• ተማሪዎች (ህግን/መመሪያን) የሚተላለፍ/የማያከብር ድርጊት ቢፈጽሙ፣ ድርጊታቸው ኮምፒዩተር ከማግኘት መብት/ጥቅም መታገድን፣ የስነስርአት ርምጃ፣ እና/ወይም ወደ ህግ አስፈጻሚዎች መመራት የሚያጠቃልሉ እርምጃዎችን ሊያስክትል እንደሚችል ይረዳሉ።

የግል ሞባይል መገልገያዎች ስልክ፣ ኢ-ሪደርስ፣ ታብሌት፣ ኮምፒውተሮች፣ ወይም ሌሎች የድምፅ መቅጃ ወይም ካሜራ ያላቸው፣ (Mobile phones, e-readers, tablets, personal computers, or other devices equipped with microphones, speakers, and/or camera) ሌሎችም ተመሣሣይነት ያላቸው ከMCPS ያልቀረቡ መሣሪያዎች በሙሉ የግል ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎች (PMDs) ተብለው ስለሚፈረጁ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች ደንብ "MCPS Regulation COG-RA"የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎች/መሣሪያዎች እና MCPS Regulation IGT-RAስለ ኮምፒውተር ሲስተሞች፣ ኤሌክትሮኒክ መረጃዎች፣ እና የመረጃ-መረብ ደህንነት

በMCPS ንብርት ላይ እስከተገኙ ድረስ ተማሪዎች ኢንተርኔት ለማግኘት ጎጂ የሆኑ የኢንተርኔት አውታሮችን(ሳይቶች) አቅም ለመቀነስ ማጣራት (filtering) እና ሌሎች ቴክኖሎጂያዊ እርምጃዎች በሚካሄድበት የMCPS ኔትዎርክ (የግል ተንቀሳቃሽ/የእጅ ስልክ ኔትዎርክ ሳይሆን) መጠቀም አለባቸው።

ሁሉም ተማሪዎች የሚከተሉትን በጥብቅ ይከተላሉ።

• ተማሪዎች የግል PMDs በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች MCPS ንብረት ውስጥ ይዘው ሊገኙ ይችላሉ ነገር ግን በግል ለመጠቀም የተማሪዎቹ እለት እሰከሚጠናቀቅ ለመክፈት/ለመጠቀም አይችሉም።

• ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲመጡ ወይም ከት/ቤት ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ወይም ት/ቤት ለሚያካሄደው እንቅስቃሴ ት/ቤት በተኮናተረ አውቶቡስ ሲጓዙ አውቶቡሱን በሰላም የማሽከርከር ስራ ካላደናቀፈ የMCPS ሕጎችን በማክበር የግል የእጅ ስልኮቻቸውን ለመጠቀም ይችላሉ።

• ተማሪዎች የግል መገልገያዎቻቸውን ለመጠቀም ባልተፈቀደላቸው ጊዜ ዝግ መደረጉን እና ከእይታ ውጭ ማስቀመጣቸውን ሁልጊዜ የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባቸው።

የተለየ ሁኔታ፡-

የአንደኛ ደረጃ (ኤሌሜንታሪ) ት/ቤቶች• ከ3-5 ክፍል መምህራን የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎችን (PMDs) ለማስተማር

ዓላማ መፍቀድ ይችላሉ።

የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች • የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎችን

ለማስተማር ዓላማ መፍቀድ ይችላሉ።• በእያንዳንዱ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ርእሰ መምህር ፈቃድ/ውሳኔ ተማሪዎች

የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎችን በምሳ እረፍት ጊዜአቸው ሊጠቀሙ ይችላልሉ።

• ርእሰ መምህራን የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎች ለመጠቀም የተከለከሉ ቦታዎችን ለይተው ለመወሰን ይችላሉ።

ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች• የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎችን ለትምህርት

ዓላማ ለመጠቀም መፍቀድ ይችላሉ።• የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በምሣ ዕረፍት ጊዜ የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎቻቸውን

ለመጠቀም ይችላሉ። • ርእሰ መምህራን የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎች ለመጠቀም የተከለከሉ ቦታዎችን

ለይተው መመደብ ይችላሉ።

የሌሎችን ግል ህይወት/privacy/ የሚነካ፣ የተማሪዎችን ደህንነት እና ጤንነታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል፣ ስድ/ፀያፍ፣ ወይም በሀሰት ስም የሚያጎድፍ፣ የት/ቤትን ሥራ የሚያውክ፣ የሌሎችን የፈጠራ ስራ የሚያጭበረብር/የሚሰርቅ፣ ወይም ንግድ የሚያስተዋውቅ መረጃ ከሆነ፣ የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎችን (PMD) በመጠቀም ማስተላለፍ አይፈቀድም።

የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎቹ (PMDs) የMCPS ደንቦችን ባልተከተለ መንገድ ጥቅም ላይ ከዋለ በት/ቤት ባላሥልጣናት ሊነጠቁ/ሊወረሱ ይችላል። በግል ተንቀሳቃሽ የመገልገያ እቃዎች መጥፋት፣ በእቃዎቹ ላይ የስርቆት ወንጀል መፈጸም፣ ወይም ብልሽት መድረስ ወይም እነዚህን የመሰሉ ማናቸውም መሣሪያዎች ባልተፈቀደ ሁኔታ ለመጠቀም MCPS ኃላፊነት ወይም ተጠያቂነት አይወስድም።

ማጣቀሻዎች፡-የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ደንብ "MCPS Regulation COG-RA"፣

የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎችየMCPS Regulation IGT-RA፣ የኮምፒውተር ስርአቶች፣ የኤሌክትሮኒክ

መረጃዎች፣ እና የአውታረ መረብ ጥበቃ ተጠቃሚ ሀላፊነቶችMCPS የተማሪ ስነምግባር ደንብ Student Code of Conduct)(

Page 15: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ¡ 2017–2018 ¡ 7

¡ አድሎዎን (አድሎአዊ አሠራርን) ስለማስቀረት

ጠቅላላ ተማሪዎች እና ሠራተኞች፤ በግለሰብ ባህርይ ወይም በሚታይበት/ባት ሁኔታ ሊሆን ይችላል/ትችላለች በማለት ትንበያ ተሞርኩዘው ሳይሆን ዘር፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ የዘር ሃረግ፣ ብሔራዊ መነሻ፣ ሃይማኖት፣ ስደተኝነት፣ የስደተኝነት አቋም፣ ጾታ፣ የጾታ ልዩነት፣ የጾታ መገለጫ፣ የጾታ ምንነት፣ የቤተሰብ/የወላጆች አቋም፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ዕድሜ፣ የሰውነት ወይም የአዕምሮ እክል፣ ድህነት እና የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ አቋም፣ ወይም ቋንቋ፣ ወይም ሌሎች ሁኔታዎች ሳይገድቧቸው በሕግ ወይም በሕገመንግሥት የተጠበቁ መብቶች እና ግንኙነቶችን በመጠበቅ የጋራ መደጋገፍና መከባበርን ለማስፈን ጥረት እንዲያደርጉ ቦርዱ ይጠብቃል።

ማናቸውም የጥላቻ/ሁከት ወይም ለዓመፅ መንስኤ የሚሆኑ ነገሮች እና ሕገ-ወጥ መድሎአዊነት የማይታለፉ/ይቅር የማይበሉ ናቸው። የቦርዱ መርህ/ፖሊሲ "Board Policy ACA"መድሎ የሌለበት የእኩልነት/ፍትሃዊና፣ የዳበረ ባህልን በማስፈን ሁሉንም የግል ልዩነቶችን በመቻቻል አወንታዊነት እንዲሰፍን ተማሪዎችን ሁላቀፍ/ዓለም አቀፍ ማህበረሰብነትን አስተሳሰብ ይዘው እንዲያድጉ ለማዘጋጀት መመዘኛዎች ነው።

መድሎአዊነት የሚያካትተው በቅንዓት ተገፋፍቶ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ምንም እርግጠኝነት በሌለው ነገር በይሆናል የግል ባህርይ የጥላቻ ድርጊቶች፣ የሃይል/የአመጽ ድርጊቶች፣ ደንታቢስነት፣ የንቀት ተግባር፣ የበቀል እርምጃ፣ ማንቋሸሽ፣ ማዋከብ፣ ጥቃት/ትንኮሳ፣ መሳደብ፣ ማስፈራራት፣ ዝርፊያ፣ ወይም ንብረት ማውደም/ማፈራረስ፣ የትምህርት ወይም የሥራ አካባቢ ላይ እንቅፋት/የሚያስተጓጉሉ እንቅስቃሴዎችን መፈጸም ናቸው። ኣድልዎ ላይላዩን ግልጽ ያልሆነ ነገር ግን ግለሰብ ባለበት ሁኔታ ወይም ግምታዊ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ተገቢ ያልሆነ ተፅእኖ ያላቸው ልዩነቶችን የማድረግ ስነምግባሮችን ወይም ልምዶችን በተጨማሪ ያካትታል። ኣድልዎ ዘረኝነትን፣ በጾታ የበላይነት ማመንን/sexism፣ እና በድርጅታዊ መዋቅሮች ስር የሰደዱ ጥላቻዎችን ከሞላ መገለጫዎቻቸው ጋር ያካትታል።

የትምህርት ቤት አስተዳደር የአድልዎ ቅሬታ ሰሚ ክፍል (The Office of School Administration Compliance Unit) በተማሪዎች ላይ በግል ሁኔታቸው ምክንያት ለሚደርሱባቸው በትምህርት ቤት ደረጃ ለመፍታት የማይቻሉ ጉዳዮች ከዚህ በታች የተመለከቱ ቅሬታዎች፣ ስጋቶች፣ ጥያቄዎች፣ የሚቀርቡበት ክፍል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት በዚህ መመሪያ የጀርባ ሽፋን ውስጠኛ ገጽ ላይ የሚገኘውን የፀረ-አድሎአዊነት መግለጫ ይመልከቱ። በግላዊ ሁኔታቸው ምክንያት ማዋከብ፣ መደንፋት፣ ማስጨነቅ፣ ጭቅጨቃ፣ ዛቻና ማስፈራራት ቢደርስባቸው ተማሪዎች ለMCPS Form 230-35, ወከባ፣ መጨቅጨቅ፣ ወይም ማስፈራራትበ MCPS ደንብ JHF-RA ላይ እንደተገለጸው ወከባ፣ መጨቅጨቅ፣ ወይም ማስፈራራት

ማጣቀሻዎች፡-የቦርድ ፖሊሲ "Board Policy ACA" ፀረ-መድሎ፣ ሚዛናዊነት፣ እና ባህላዊ

ብቃት/አቻነት የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች የተማሪ ስነ-ምግባር መርኆ "MCPS

Student Code of Conduct" የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች የሠራተኛ ስነ-ምግባር መርኆ "MCPS

Employee Code of Conduct" የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ኃይማኖታዊ ልዩነቶችን ስለማክበር መመሪያ

"MCPS Guidelines for Respecting Religious Diversity"

¡ አመፅ፣ ወከባ፡ ወይም ማስፈራራትማሸማቀቅ/ዛቻ፣ ትንኮሳ፣ ወይም ማስፈራራት ከባድ እና በቀላሉ የሚታለፉ አይደሉም። MCPS Form 230-35ማሸማቀቅ/ዛቻ፣ ትንኮሳ፣ ወይም ማስፈራራት ሪፖርት ማድረግያ ቅጽ ስለ ማሸማቀቅ/ዛቻ፣ ትንኮሳ፣ ወይም ማስፈራራት ውንጀላ ቅጹ መሞላት ያለበት በተማሪ/ዋ፣ በወላጅ፣ በአሳዳጊ፣ ወይም በተማሪው/ዋ የቅርብ ዘመድ፣ ወይም በት/ቤት ሥራ ባልደረባ ነው። የተሞላው ቅጽ ጥቃት የደረሰበት/የደረሰባት ተማሪ ለሚማርበት/ለምትማርበት ት/ቤት ለርእሰ መምህሩ መቅረብ አለበት። ለተጨማሪ መረጃ ወይም ዕርዳታ በማንኛውም ጊዜ ትምህርት ቤቱን ያነጋግሩ።

ማሸማቀቅ፣ ዛቻ፣ ትንኮሳ፣ ወይም ማስፈራራት ሆንብሎ በቃላት፣ በአካል፣ ወይም በጽሑፍ የሚደረግ ወይም ታስቦበት በኤሌክትሮኒክስ ግንኙነት በትምህርት አካባቢ ላይ ጥላቻ ለማሳደር በከባድ ሁኔታ በተማሪው/በተማሪዋ የመማር ጥቅማጥቅሞች ላይ፣ የተለያዩ እድሎች፣ ወይም በአሰራር ወይም በተማሪው/ዋ አካል ወይም ሥነ-ልቡና ደህንነት ላይ ጣልቃ ገብነት እናስ፡-

(1) ወይም (ሀ) (a) ትክክለኛ በሆነ ወይም በይሆናል የታሰበ የግል ሁኔታዎች ተገፋፍቶ ዘር፣ ጎሣ፣ ቀለም፣ የትውልድ ሃረግ፣ ብሔራዊ ማንነት፣ ኃይማኖት፣ የስደተኝነት አቋም፣ ፆታ፣ የጾታ ማንነት፣ የጾታ መገለጫ፣ ጾታዊ ባህርይ፣ የቤተሰብ/የወላጆች አቋም፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ እድሜ፣ የአካል ወይም የአእምሮ ስንኩልነት፣ ድህነት ወይም የማርበራዊ ኤኮኖሚያዊ አቋም፣ ቋንቋ ወይም ሌሎች በሕገ መንግስት ወይም ህጋዊ ከለላ የተደረገላቸው ተዛማጅነት ያላቸው ሁኔታዎች፣ ወይም (ለ) (b) ማስፈራራት ወይም ከባድ ዛቻ፣ እና

(2) ወይም (a) የተፈጸመው በት/ቤት ንብረት ውስጥ፣ ት/ቤት በሚያካሄደው/በፈቀደው እንቅስቃሴ ክንውን ወቅት ወይም በት/ቤት አውቶቡስ ላይ፣ ወይም (b) በከባድ ሁኔታ የት/ቤትን የሥራ ሂደት የሚያደናቅፍ

የኤሌክትሮኒክስ መገናኛዎችን በመጠቀም ማስፈራራት፣ ማስጨነቅ፣ ዛቻ እና የሌላ ግለሰብ ስነልቡናን የሚነኩ መልክቶችን ማሰራጨት (Cyberbullying ) ። በኤሌክትሮኒክስ ማስፈራራት “Cyberbullying” ማለት በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች፣ ማለትም እንደ ስልክ፣ የእጅ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ወይም ታብሌት የመሳሰሉ በመጠቀም የተላለፉ፣ እና የማህበራዊ ድረ ገጽ አጠቃቀምንም ያጠቃልላል።

ፆታዊ ወከባፆተዊ ወከባ በቦርድ ፖሊሲ ACF መሰረት የሚገለፀው፣ ፆታዊ ወከባ፣በሚከተሉት ሁኔታዎች ስር የሚከናወን እንድ ያልተፈለገ ፆታዊ አቀራረብ፣ የፆታ ግነኙነት ጥያቄዎች፣ እና/ወይም ሌላ ተገቢ ያልሆነ የቃል፣ የፅሁፍ፣ ወይም ፆታ ነክ አካላዊ ስነምግባር፡-

• በግልፅ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ፣ በስራ ሁኔታ፣ በማስተማር፣ ወይም በሌሎች የት/ቤት እንቅስቃሴዎች በዚህ አይነቱ ተግባር መሳተፍ፡

• የጾታ ግንኙነት ለማድረግ ወይም ለዚህ አይነቱ ተግባር ተጠይቆ ባሳየው እምቢታ ምክንያት ጥያቄ የቀረበለት ግለሰብን የሚነካ/የሚጎዳ እርምጃ ሠራተኛነት ላይ ወይም የአካዴሚ እርምጃ ጉዳት የማድረስ ርምጃ ሲወሰድ።

• እንደዚህ አይነቱ ድርጊት በግለሰቡ ስራ እና ወይም አካዴሚያዊ ክንውን ምክንያታዊ ያለሆነ ጣልቃ ሲገባ ወይም የሚያስፈራ፣ አሉታዊ፣ ወይም ጎጂ ስራ ወይም የትምህርት አካባቢ ሲፈጥር።

በተማሪዎች ወይም በሠራተኞች የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት ተገቢ ያልሆነ እና የMCPS ደንቦችን የሚጻረር ነው። ጾታዊ የማስገደድና/የማስፈራራት ሁኔታ ሪፖርት መደረግ ያለበት ለት/ቤት ሠራተኛ ወይም ለርእሰ መምህር በ "MCPS ደንብ ACF-RA" መሠረት ጾታዊ ማስገደድና/ማስፈራራት የMCPS ቅጽ 230-35 ጥቃት/መፈታተን፣ ትንኮሳ፣ ወይም ዛቻና ማስፈራራትን ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ፆታዊ ወከባ የልጅ ማጎሳቆል ወይም ቸልተኝነት ስነምግባርንም ሊያካትት ይችላል። የተጠረጠረ ማጎሳቆል ወይም ቸልተኝነት ወድያውኑ ለChild Welfare Services/የልጅ ደህንነት አገልግሎቶች (በተጨማሪ Child Protective Services/የልጅ ከለላ አገልግሎቶች ተብሎ በዘልማድ ለሚጠራው) በMCPS ደንብ JHC-RA፣ የልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነት ሪፖርት ምርመራ የተቀመጡትን ቅደም ተከተሎች በመከተል መቅረብ አለባቸው። በደል/እንግልት/ማጎሳቆልን ወይም ቸልተኝነትን እያዩ ሪፖርት ለማድረግ ማመንታት የተሳሳተ አቅጣጫ ነው። የጾታዊ ማስፈራራት ጥቃት ጥቆማው በርእሰመምህሩ/ሯ ላይ ከሆነ ጥቆማው መቅረብ ያለበት በተባባሪ ዋና የትምህርት ተቆጣጣሪ ጽ/ቤት አማካኝነት ለሠራተኛ ትግበራ እና ግንኙነት ጽ/ቤት መሆን አለበት።

በፆታዊ ወከባ ቅሬታ ምርመራ ወቅት፣ አመልካቿ/ቹ ከተከሳሹ/ሿ ጋር ፊት ለፊት መገናኘት ወይም በምንም ሁኔት መጋጠም አይኖርባትም/አይኖርበትም።

ማጣቀሻዎች-የMCPS የACF-RA ደንብ፣ ፆታዊ ወከባ/መፈታተን (Sexual Harassment)የMCPS ደንብ JHC-RA፣ ስለ ልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነት ሪፖርት

እና ምርመራ (MCPS Regulation JHC-RA, Reporting and Investigating Child Abuse and Neglect)

የMCPS የJHF-RA ደንብ፣ መበደል፣ ማዋከብ፣ ወይም ማስፈራራት (Bullying, Harassment, or Intimidation)

የMCPSየተማሪ ስነምግባር ደንብ - Student Code of Conduct

Page 16: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

8 ¡ 2017–2018 ¡ A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES

¡ የተማሪ መዝገቦችርእሰ መምህራን ለሁሉም ተማሪዎች መዛግብት መያዝ አለባቸው። የተማሪ መዝገብ በMCPS ቅጾች የተመዘገቡ መሰረታዊ መረጃዎችን የያዘ ክምችት ማህደር አለው። ባንዳንድ ሁኔታዎች፣ ሚስጢራዊ ማህደር ሊፈጠር ይችላል። የት/ቤት ሰራተኞች ሚስጢራዊ ማህደር ሲፈጥሩ ወላጆችን/ሞግዚቶችን ማሳወቅ አለባቸው።

ከት/ቤት ሰራተኞች ጋር በሚካሄድ ስብሰባ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው የተከማቸ የተማሪ ሬኮርድ የማየት መብት አላቸው። ሲጠየቅ፣ የት/ቤት ሰራተኛ የተከማቸ የተማሪ ሬኮርድ ለተማሪዎችና ለወላጆች/አሳዳጊዎች ማብራራት ወይ መተርጎም ይችላል።

የትምህርት ዓመት በተጀመረ በ30 ቀኖች ውስጥ ቅጽ MCPS Form 281-13 ስለ ተማሪ የግል ህይወት ጉዳይ/ግላዊነት/ገመና በየፈርጁ ዝርዝር ያካተተ ዓመታዊ መመሪያና መግለጫለሁሉም የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች MCPS ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ይሰጣል። ይኼውም ዝርዝር የያዘ ማውጫ/መመሪያ ተብሎ ይቆጠራል። እነዚህ ፈርጆች የሚያካትቱት፣ ከሌሎች መረጃዎች መካከል፣ የተማሪው(ዋ)ን እና የወላጆችን/አሳዳጊዎችን ስም፣ የኢ-ሜይል አድራሻ፣ እና ስልክ ቁጥር፤ የተማሪ የልደት ቀንና ቦታ፤ የሚሳተፍበት/የምትሳተፋቸው በወግ የታወቁ እንቅስቃሴዎችና ስፖርቶች፤ ከሁሉም በቅርብ ጊዜ የተከታተለ(ች)ው ት/ቤት። የቤት አድራሻዎችና የስልክ ቁጥሮች ሊገለፁ የሚችሉት ለወላጆች/አሳዳጊዎች ድርጅቶች፣ ለመምህራን፣ እና ለት/ቤት ተማሪዎች፤ ለሚሊታሪ ቅርንጫፍ፤ በት/ቤቱ ወይም በትምህርት ቦርድ ለተቀጠረ ሰው፤ ወይም ለሜሪላንድ የማህበረሰብ/community ኮሌጅ ብቻ ነው። ወላጆች/አሳዳጊዎች የተወሰነ ወይም ጭራሹንም የግል መረጃዎችን ለተወሰነ ጊዜ በይፋ እንዳይገለፅ መከልከል ይችላሉ፣ እናም፣ እንደማኛውም ሌላ የተማሪ ሬኮርድ፣ መረጃው በሚስጢር ይያዛል።

ተማሪዎች ሲጎለምሱ፣ ተማሪዎችና ወላጆች/አሳዳጊዎች የተማሪን መረጃ በሚመለከት ተመሳሳይ መብት አላቸው። ቢሆንም፣ የእድሜ ብቃት ያላቸው በወላጆቻቸው ጥገኝነት የሚኖሩ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች ያለ ተማሪው/ዋ ፈቃድ የልጃቸውን መረጃ ለማግኘት ይችላሉ።

ማጣቀሻዎች- የMCPS መመሪያ JOA-RA፣ የተማሪ የተመዘገበ ፋይል

¡ መፈተሽ/መፈለግና መያዝየMCPS ሠራተኞች በተማሪው ላይ ወይም እቃውን ፍተሻ የሚያካሄዱበት እና በፍተሻ የተደረገበትን ነገር ለመያዝ የሚያስችላቸው ሁኔታዎች በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ደንብ "MCPS Regulation JGB-RA" ፍተሻ ማካሄድ እና መያዝ/መንጠቅ Search and Seizure ከተማሪዎች እጅ ያልተፈቀደ ነገርን ለመንጠቅ/ለመያዝ ፍተሻ ሲካሄድ በተቻለ መጠን በት/ቤት የሚካሄድን የተረጋጋ የሥራ ሁኔታ በማያደናቅፍ መልኩ እና ፍተሻ የተደረገባቸውንም ተማሪዎች ለሃፍረትና ለመሸማቀቅ እንደማይዳርግ/ለመቀነስ በተቻለ መጠን ጥንቃቄ ይደረጋል።

ፍተሻ ለማድረግና ያልተፈቀደ ነገር ለመንጠቅ/ለመያዝ ኃላፊነት ያላቸው፤ ርእሰ መምህሩ/ሯ፣ ወይም ምክትል ርእሰ መምህሩ/ሯ፣ ወይም የ MCPS የት/ቤት ደህንነት ጥበቃ (DSSS) ሥራ ባልደረባ እና/ወይም በ MCPS ተቀጣሪ የሆነ የት/ቤት የጥበቃ ሥራ ባልደረባ እና ት/ቤት ባሰማራው ጉዞ ላይ ያለ/ያለች ከርእሰ መምህሩ/ሯ ወይም ከተወካይ በጽሁፍ ኃላፊነት የተሰጠው/የተሰጣት ፍተሻ ስለማድረግ ጭምር ስልጠና ያገኘ/ች መምህር

መቆለፊያ ሣጥን፣ ወይም እቃ ማስቀመጫ ክፍል፣ ወይም ሌሎች ከት/ቤት የተሰጡ ቁሳቁሶች የተማሪ የግል ንብረት ተደርጎ ስለማይቆጠር እንዲህ ዓይነቶቹን ቁሳቁሶች ላይ ፍተሻ ለማካሄድ ተማሪው/ዋ ያልተፈቀደ ነገር መያዙን/መያዟን እርግጠኛ መሆን አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። ቢሆንም፤ የተማሪውን በመቆለፊያ ሳጥን ውስጥ ወይም በእቃ ማከማቻ ቦታ ላይ ያለ የተማሪ በጀርባ እቃ መያዣ ቦርሳ ወይም የሴት ተማሪ ቦርሳ (e.g., backpacks or purses) ፍተሻ የሚደረገው ያልተፈቀደ ነገር መያዙን ሲታመንበት እና በማናቸውም እንዲህ ዓይነት ፍተሻ በተማሪው/ዋ ላይ ወይም እቃቸው ላይ ፍተሻ በሚካሄድበት ወቅት ተጨማሪ የት/ቤት ሠራተኛ አብሮ መኖር አለበት።

ማጣቀሻዎች፡- የMCPS ደንብ JGB-RA፣ መፈተሽ/መፈለግና መያዝ (Search and Seizure) በሜሪላንድ የትምህርት ኮድ (Annotated Code of Maryland)፣ የትምህርት

አንቀፅ፣ §7-308ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/security/

¡ የት/ቤት ደህንነትና ፀጥታአወንታዊ የመማርያ አካባቢ እንዲሰፍን/እንዲኖር ለማድረግ የተማሪዎችና የሰራተኞች ደህንነት ወሳኝ ነው። የት/ቤቶቻችን ደህንነትና ፀጥታ ሁሉንም ሰው የሚመለከት ጉዳይ ነው። ለአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ዝግጁ ለመሆንና ለት/ቤት ደህንነት ቅድመ ዝግጁነት፣ ሁሉም ት/ቤቶች የት/ቤት አስቸኳይ ሁኔታ ዕቅድ አዳብረዋል። አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ የሚጠይቅ መተንበይ የማይቻል፣ ዕቅድ ያልተደረገ ሁኔታ ነው። አስቸኳይ ሁኔታዎች የቦምብ ማስፈራራት፣ የወንጀል ተግባር፣ አደጋዎች፣ እሳት፣ የአደገኛ ቁሱች ኣድራጎቶች፣ ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን የሚያካትቱ በእነዚህ ግን ያልተወሰኑ ናቸው። Lockdown/መዝጋት፣ Evacuate/ለቆ መውጣት፣ እና Shelter/መጠለያ የተባሉ ቅደም ተከተሎች የተዘጋጁት ለት/ቤት አስቸኳይ ሁኔታ ምላሽ ርምጃ እንዲሆኑ ሲሆን የት/ቤት አስችኳይ ሁኔታ ዝግጁነት ዕቅድ አካልም ናቸው። ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ኣባላት፣ እና ወላጆች/ሞግዚቶች የእነዚህ ቅደም ተከተሎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ወሳኝ ነው።

ሎክዳወን/"Lockdown" በMCPS መገልገያ የሚደርስ አስቸኳይ ሁኔታን ለመግለፅ የሚውል ቃል ነው። ሎክዳወን/"Lockdown" በህንፃ ውስጥ ወይም ውጭ አደጋ በማንዣበብ ላይ እንዳለና ወደ አስቸኳይ ሎክዳወን/"Lockdown" ሁኔታ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ የአስተዳደር አባላትን የሚያስጠነቅቅ ነው። ሁሉም ተማሪዎች የጎልማሳ/አዋቂ ሰው ክትትል እንዲደረግላቸው ይጠይቃል። ተማሪዎችና የሰራተኛ አባሎች በፍጥነት ወደ አንድ ሊጠበቅ የሚችል ቦታ እንዲሄዱ፣ ፀጥ እንዲሉ፣ እና የአስተዳደር አባል ትእዛዝ እንዲከትሉ ያስፈልጋል። ከስፍራው ማስለቀቅ/ማስወጣት (Evacuate) በት/ቤት ውስጥ የሚደርስን አስቸኳይ ሁኔታ ለመግለፅ ስራ ላይ የሚውል ቃል ነው። ስለ እሳት አደጋ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ወይም በአስተዳደር አማካይነት የሚነገር የድምፅ ማጉያ ማስታወቂያ እንደተሰማ ሁሉም ተማሪዎችና የሰራተኛ አባሎች ህንፃውን በፍጥነት ለቀው መውጣት አለባቸው። መጠለያ አግኝ (Shelter) በMCPS መገልገያ ወይም ባቅራቢያው ለሚደርስ አስቸኳይ ሁኔታ መኖሩን አስተዳደር አባላትን ለማስጠንቀቅ ስራ የሚውል ቃል ነው። ሁሉም ተማሪዎች መኖራቸው እንዲረጋገጥና በአዋቂ ቁጥጥር ስር ህንፃ ውስጥ እንዲሆኑ ይጠይቃል። ሶስት ዓይነት የመጠለያ ማስጠንቀቂያዎች አሉ፡- የህዝብ ደህንነት፣ መጥፎ የአየር ሁኔታ፣ እና ከመጠን በላይ የሆነ የአደገኛ ቁሳቁሶች መለቀቅ። ተማሪዎችን፣ የት/ቤት ስራ አባላት፣ እና ወላጆች/አሳዳጊዎች ማንነታቸውን ሳይገልጹ/ሳያሳውቁ የደህንነትና የፀጥታ ስጋት/ቅሬታዎችን ሪፖርት እንዲያቀርቡ ለማስቻል፣ የትም/ቤት ደህንነት የአስችኳይ ጥሪ መስመር (Safe Schools Hotline) በቀን ለ24 ሰአት/ በሳምንት 7 ቀናት ሰዎች ተመድበውበታል። የሚደውለውን ሰው መታወቂያ/መለያ አይጠይቅም። ያስታውሱ፣ በት/ቤቶች ደህንነትና ፀጥታ ሁሉም ሰው ደንታ አለው፣ እነዚህም ስጋቶች ሃላፊነት ላለው አዋቂ ወይም ለSafe Schools Hotline በወቅቱ ሪፖርት መደረግ አለባቸው።

MCPS Safe Schools 24-Hour Hotline:- 301-517-5995

በቀን 24 ሰአት በሳምንት ለ7 ቀኖች ሰራተኛ የተመደበባቸው ተጨማሪ አስቸኳይ መስመሮች፡-

የሞንጎሞሪ ካውንቲ ፖሊስ (Montgomery County Police) —አስቸኳይ ሁኔታ ያልሆነ፡- 301-279-8000የእፅ መጠቆሚያ የአስቸኳይ ጥሪ መስመር፡- 240-773-DRUG (3784)የወንበዴ/ወሮበላ መጠቆሚያ የአስቸኳይ ጥሪ መስመር፡- 240-773-GANG (4264)የአደንዛዥ እፆችና የወንበዴ ጥቆማዎች፡- 240-773-TIPS (8477)

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የጤና እና የህዝብ አገልግሎት መረጃ መስመር (Montgomery County Health and Human Services Information Line) (ከሰኞ እስከ ዓርብ 8:30 a.m.–5:00 p.m.) 240-777-0311, TTY 240-251-4850

የMCPS የት/ቤት ደህንነት ጥበቃና ፀጥታ መምርያ (MCPS Department of School Safety and Security):- 301-279-3066

ድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/security/

ማጣቀሻዎች፡-የMCPS ደንብ EKA-RA፣ ለአስችኳይ ሁኔታና ለአሰቃቂ አደጋ ዝግጁነት

(Emergency and Disaster Preparedness)

Page 17: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ¡ 2017–2018 ¡ 9

¡ ስቴት ጣልቃ የሚገባባቸው የጤንነት ሁኔታዎች (State Required Medical Interventions)

ለMCPS የድንገተኛ/አስቸኳይ ሁኔታ ተጠሪን እና የጤና መረጃ ለማቅረብ/ለመስጠት ወላጆች/አሳዳጊዎች በmyMCPS Parent Portal ላይ የተማሪ የድንገተኛ/አስቸኳይ ሁኔታ መረጃ /Student Emergency Information/ ክፍልን ወይም የ MCPS ቅጽ 565-1፣ የተማሪ የድንገተኛ/አስቸኳይ ሁኔታ መረጃን መሙላት አለባቸው። ተለይተው የሚታወቁ የጤንነት ሁኔታዎችን እንደሚከተልው ተገልጸዋል፡-

ስለ ከባድ አለርጂክ ግንዛቤ (Anaphylaxis Awareness)ወላጆች/አሳዳጊዎች የተማሪን ልዩ የጤንነት ሁኔታ ወይም በኃኪም ምርመራ አለርጂክ እንዳለበት/እንዳለባት ተለይቶ የሚታወቅ እና ስለሚወስደው/ስለምትወስደው ተገቢ ህክምና/መድኃኒት ለት/ቤት ማሳወቅና እንዲሁም ፈቃድ መስጠታቸውን ማረጋገጫ ቅጽ ሞልተው የመስጠት/የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው። Parents/guardians are responsible for notifying schools of a student’s special health care needs or diagnosis of anaphylaxis, providing appropriate medications, and completing appropriate authorization form(s). እነኚህ የህክምና መድሃኒቶች ለልጅዎ/ተማሪዎ አስቸኳይ/አጣዳፊ ወቅት እንዲጠቀምበት/እንድትጠቀምበት በት/ቤቱ የጤና ክፍል ይቀመጣል። These medications will be kept in the school’s health room for your student’s use in case of an emergency. ሁሉም ት/ቤቶች ሠራተኞቻቸውን የአለርጂ ምልክቶችን ለይተው ማወቅ እንዲችሉ እና በአስቸኳይ/አጣዳፊ ወቅት ለመጠቀም እንዲቻል መጠባበቂያ መድኃኒት እንዲኖርና አጠቃቀሙን ጭምር epinephrine auto-injectors (e.g. EpiPens) ለመስጠት እንዲችሉ ማሰልጠን አለባቸው። በየት/ቤቱ የተመደቡ ሠራተኞች epinephrine auto-injectors መስጠት እንዲችሉ የሠለጠኑ ናቸው። የወላጅ/አሳዳጊ ፈቃድ ከተሰጣቸው እና "MCPS Form 525-14" ቅጽ ላይ ተሞልቶ ከሆነ ተማሪዎችም epinephrine auto-injectors ለመያዝ ይችላሉ፣የአለርጂ በሽታ ላለበት/ባት ተማሪ የአስቸኳይ ሁኔታ እንክብካቤ Epinephrine Auto Injector የጉዳት ካሳ ስላለመፈለግ/ስላለመጠየቅ የተደረገ ስምምነት መግለጽ "Release and Indemnification Agreement for Epinephrine Auto Injector" ጫ

ስለ ስኳር በሽታ ግንዛቤ "Diabetes Awareness" ተማሪው/ዋ የስኳር በሽታ/diabetes ካለበት/ካለባት ወላጆች ለት/ቤት የማሳወቅ ኃላፊነት አለባቸው። ስለተማሪው/ዋ የስኳር በሽታ/ diabetes እንክብካቤ፣ አደራረጉን ጭምር የሚገልጽ (DMMP) ወይም ከሃኪም የተጻፈ የህክምና ጥንቃቄ የተሟላ፣ ትክክለኛ፣ እና ወቅታዊ የጤና መረጃ በየጊዜው መወሰድ ያለበት እና በአስቸኳይ/ድንገተኛ ጊዜ መደረግ ያለበት የህክምና ርዳታ ከህክምና መገልገያዎች ጋር እናም ተገቢው ፈቃድ የመስጠት ቅጽ/ቅጾች ተሞልቶተው ተማሪው/ዋ የሚያስፈልገው/የሚያስፈልጋት የህክምና ሁኔታ ላይ ለውጥ የተደረገ ነገር ካለ ወላጆች/አሳዳጊዎች ለት/ቤት በትክክል የማሳወቅ ኃላፊነት አለባቸው።

የስኳር በሽታ/diabetes ያላቸውን ተማሪዎች በየቀኑ የመከታተልና የመርዳት ኃላፊነት ያለባቸው ሠራተኞች የተማሪውን DMMP ወይም ከጤና ባለሙያ የሚታዘዘውን ህክምና በመስጠት ለመርዳት እንዲችሉ ተጨማሪ ስልጠና ያገኛሉ። የት/ቤት ማህበረሰብ የጤና ነርስ ተማሪው/ዋ ት/ቤት በሚፈቅድላቸው ትምህርታዊ የመስክ ጉዞዎች ላይ በትክክል ለመሳተፍ እንዲችል/እንድትችል፣ በአግባቡ የስኳር በሽታ ክወናን/ቁጥጥር እውቀት ያለው "diabetes management activities" ተገቢውን የት/ቤት ሥራ ባልደረባ ለመወከል ከት/ቤቱና ከወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር በመተባበር ትሠራለች/ይሠራል።

ስለ Naloxone and Opioid ግንዛቤ/Awarenessበሜሪላንድ "Start Talking Maryland Act of 2017" እንደተገጸው የሜሪላንድ ት/ቤቶች ዲስትሪክቶች ስለ ሄሮይን እና አፒዮይድ ሱሰኝነት/ጉዳት እና የመከላከል ርምጃ በስፋት ማስተማር እንዳለባቸው ይገልጻል። የት/ቤት ነርስ፣ የት/ቤት የጤና አገልግሎት ባለሞያዎች፣ እና ሌሎችም በ MCPS የሚታወቁ ሠራተኞች ከመጠን በላይ የተወሰዱ መድኃኒቶችን ማርከሻ ለመስጠትና ጉዳቱን ለመቆጣጠር ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። Naloxone, or other overdose-reversing medication, ለተማሪዎች በድንገተኛ ሁኔታ ጊዜ የሚያገለግሉ መድሃኒቶች በት/ቤት ይቀመጣሉ።

ማጣቀሻዎች፡- በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች አልኮሆል፣ ትምባሆም እና ሌሎች ሕገ-ወጥ

መድሃኒቶች አጠቃቀምን ስለመከላከል የቦርድ ፖሊሲ /Board Policy IGN, Preventing Alcohol, Tobacco, and Other Drug Abuse in Montgomery County Public Schools/

የMCPS ደንብ JPC-RA፣ ለተማሪዎች የህክምና አሰጣጥ መመሪያ /MCPS Regulation JPC-RA, Administration of Medication to Students/

MCPS ደንብ JPD-RB፣ ተማሪዎች ስለሚያጋጥሟቸው ድንገተኛ/አስቸኳይ የአለርጂ ጥንቃቄ አወሳሰድ መመሪያ JPD-RB "MCPS Regulation JPD-RB, Emergency Care for Students Experiencing Anaphylaxis"

MCPS ቅጽ 525-12፣ በጤና ባለሞያ የታዘዙ መድሃኒቶችን በመጠቀም ሕክምና እንዲደርግ የተሰጠ ኃላፊነት /MCPS Form 525-12, Authorization to Provide Medically Prescribed Treatment/፡- የፈቃድ እና ከተጠያቂነት ነፃ ማድረጊያ ስምምነት Release and Indemnification Agreement

MCPS ቅጽ 525-13 በጤና ባለሞያ የታዘዙ መድሃኒቶችን በመጠቀም ሕክምና እንዲደርግ የተሰጠ ኃላፊነት፡- የፈቃድ እና ከተጠያቂነት ነፃ ማድረጊያ ስምምነት

MCPS ቅጽ 525-14 የአለርጂ ችግር ያለበ(ባ)ት ተማሪ የህክምና እርዳታ አሰጣጥ/እንክብካቤ የኤፕነፍሪን ኦቶማቲክ መርፌ ፈቃድ እና ከተጠያቂነት ነፃ ዋስትና መስጫ ስምምነት /Release and Indemnification Agreement for Epinephrine Auto Injector/

¡ መልካም ጤንነትተማሪዎች ስለ ግል ጤንነታቸው ሃላፊነት እንዲወስዱ፣ እና ጤናማ የአመጋገብ ልምድ፣ በየቀኑ የአካል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይበረታታሉ። የቦርድ ፖሊሲ JPG /Board Policy JPG/, ደህና መሆን/ጤንነት የአካል እና የአመጋገብ ጤንነትበት/ቤት የልጆች ጤነኛ አመጋገብ እና የአካል እንቅስቃሴዎችን የማዘውተር ባህል እንዲዳብር እና ጤንነታቸው እየተጠበቀ ለመማር እንዲችሉ ለመደገፍ የቦርዱን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው።

የMCPS ስለመልካም ጤንነት መመሪያ JPG-RA /MCPS Regulation JPG-RA, Wellness/:- የአካል እና የአመጋገብ ጤንነትበ/ት ቤቶች አካባቢ የአካል ብቃት እና የአመጋገብ ጤንነትን፣ ማህበራዊ እና ስሜታዊ ደህንነት እና ባህርይን እና እንቅስቃሴዎችን ለጤናማ የአኗኗር ዘይቤ የሚጠቅሙ መልካም ተምሳሌቶችን ለማስተማር ቅደም ተከተልን ለማስፈን ይረዳል። በትምህርት ቀናት መጀመሪያ፣ በመካከል እና ከትምህርት በኋላም የአካል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ በጣም ይበረታታል።

¡ ዲሲፕሊንተማሪዎች ደህንነት፣ አወንታዊ/ቅንነት እና መከባበር የሰፈነበት የት/ቤት አካባቢ በመጎናጸፍ የተማሪን ትምህርት የመቅሰም ተሳትፎ የማሳደግ መብት አላቸው። ት/ቤት ተገቢ ስነምግባር መማር የሚቻልበት ቦታ ስለሆነ፣ ዲሲፕሊን የተማሪዎችን ስነምግባራዊና የእድገት ፍላጎቶች ማሟላት እና በርትአዊነት የሚተግበሩ እና የመልሶ ማቋቋም ዲስፕሊን ፍልስፍና የሚያንፀባርቁ ቀጣይ ስልቶችና አፀፋዊ መልሶች ማካተት አለበት።

ማጣቀሻዎች- የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች የተማሪ ስነምግባር መመሪያ "MCPS

Student Code of Conduct"የMCPS ደንብ JGA-RA፣ የመማርያ ክፍል አስተዳደርና የተማሪ ስነምግባር

ጣልቃገብነቶችየMCPS ደንብ JGA-RB፣ እገዳና ስንብትየMCPS ደንብ JGA-RC፣ ስንክልና ያላቸው ተማሪዎች እገዳና ስንብት

¡ ይግባኞች-የቅሬታ ቅደም ተከተል—ተገቢው ሂደት

ይህ ክፍል የተተለመው ቅሬታ፣ የአድልዎ አቤቱታ፣ መታገድ ወይም ስንብት የማያጠቃልል የዲሲፕሊን እርምጃ፣ ወይም የስክልና ትምህርት ያላቸው ግለሰቦች አዋጅን የመሳሰለ በሌላ ህግ ወይም ደንብ ተለዋጭ የአለመግባባት እርቅ በተለይ የቀረበባቸው ሌሎች ጉዳዮች ውስጥ ለሚገኝ ለያንዳንዱ ተማሪ ስለ ርትአዊ አስተዳደር መረጃ ለማቅረብ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ህክምና ለመስጠት የት/ቤት ሕግ ከፌደራል እና ከስቴት ሕጎች ጋር፣ እንዲሁም ከቦርድ መርኆ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት።

Page 18: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

10 ¡ 2017–2018 ¡ A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES

በት/ቤት ደረጃ ውሳኔA. ተማሪው/ዋ ለ --- መብት አለው/አላት

1. በመግባባት ደረጃ መፍትሄ ለማግኘት1 ከርእሰ መምህሩ/ሯ ወይም ተውካዩ/ይዋ ጋር መገናኘት፣ ወይም

2. ርእሰ መምህሩ/ሯ ወይም ተወካዩ/ይዋ በአግባቡ አቤቱታውን እንዲመለከት/እንድትመለከት በፅሁፍ መጠየቅ። (የMCPS ቅጽ 270-8፣ ከህዝብ የመነጨ ቅሬታ)

ተማሪው/ዋ A.1 ከመርጠ/ች፣ ነገር ግን በመግባባት ሂደት ወይም

በቀረበው መፍትሄ ካልተደሰተ/ች፣ ወይም ኣቤቱታ ከቀረበበት

እለት ጀምሮ 15 የትምህርት ቀናት ምንም ውሳኔ ሳይሰጥ ከታለፈ፣

ርእሰ መምህሩ/ሯ አቤቱታውን በአግባቡ እንዲመለከተው/

እንድትመለከተው ተማሪው/ዋ በፅሁፍ ለማስመዝገብ ይችላል/

ትችላለች።B. ርእሰ መምህሩ/ሯ የተማሪው(ዋ)ን አቤቱታ በይፋ በሚመለከት/

በምትመለከት ወቅት፣ ተማሪው/ዋ አቤቱታውን የሚደግፉ ምስክሮችና ማስረጃዎችን የማቅረብ መብት አለው/አላት። ቅሬታ በጽሑፍ በቀረበ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ርእሰ መምህሩ/ሯ በቀረበው ጉዳይ ላይ ቅሬታ አቅራቢው/ዋ ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ (ቀን እና ሰዓት) ለመያዝ ያነጋግራል። ከፅሁፍ አቤቱታ ከተቀበለ(ች)በት፣ ወይም ከተቀጠረው የስብሰባ ቀን፣ በ10 ቀኖች ውስጥ፣ ርእሰ መምህሩ/ሯ የጽሁፍ ውሳኔ በመስጠት ቅጂውን ለባለጉዳዩ /ለባለጉዳይዋ ያስተላልፋል/ታሰላልፋለች። አቤቱታው ውስብስብ ከሆነ ወይም በ10 ቀናት ውስጥ በአግባቡ ሊፈታ ካልተቻለ ርእሰ መምህሩ/ሯ የጊዜ ገደቡን በተጨማሪ 10 ቀናት ለማራዘም ይችላል/ትችላለች።

የርእሰ መምህሩ/ሯ ውሳኔ ይግባኝA. የይግባኝ አቀራረብ ተማሪው/ዋ በተሰጠው ውሳኔ የማይ(ት)ስማማ ከሆነ/ች፣ ተማሪው/ዋ

ከርእሰ መምህሩ/ሯ የፅሁፍ ውሳኔ ወይም ውሳኔ መሰጠት ከነበረበት ቀን፣ ከሁለቱ በሚቀድመው ቀን፣ በ15 የትምህርት ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ወደ ዋና የሥራ ሃላፊ ወይም ወደ ተወካዩ ይግባኝ ለማለት ይችላል/ትችላለች ይግባኙ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፡-1. የአቤቱታውና የርእሰ መምህሩ/ሯ ውሳኔ ድህረ እይታ እንዲደረግባቸው

ጥያቄ2. ሁሉም ተፈላጊ ሃቀኛ መረጃዎች3. የሚጠየቀው መፍትሔ/ፍትሕ

B. የይግባኝ ድህረ እይታ1. ዋና የሥራ ኃላፊ በት/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ የተሰየመ/ውክልና

ያለው ነው/ያላት ናት እናም ጉዳዩን እና የተያያዙ መረጃዎችን ምርመራ ያደርግባቸዋል/ታደርግባቸዋለች።

2. ተጨማሪ ምርመራ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ይግባኙን ከተቀበለ/ች በ15 የትምህርት ቀናት ውስጥ ዋናው የስራ ኃላፊ ወይም ተወካይ፣ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ በመስጠት ለተማሪው(ዋ) በፅሁፍ ያሳውቃል/ታሳውቃለች።

3. በዋናው የስራ ኃላፊ ውሳኔ ላይ ይግባኝ መጠየቅዋናው የሥራ ኃላፊ በሰጠው ውሳኔ ላይ ተማሪው ይግባኝ ለመጠየቅ መብት አለው። ዋናው የሥራ ኃላፊ በሰጠው/ችው ውሳኔ ባለጉዳዩ/ዋ ካልተስማማ/ች ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን በ30 ቀናት ውስጥ ለሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች የትምህርት ቦርድ ([email protected] or fax to 301-279-3860) ይግባኝ ለማቅረብ ይቻላል።

ማጣቀሻዎች፡-የMCPS ደንብ KLA-RA፣ ከህዝብ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች መልስ

አሰጣጥየቦርድ መመርያ BLB፣ በይግባኞችና በችሎት የቅደም ተከተል ህጎችየቦርድ ፖሊሲ BLC፣ ስለ ልዩ ትምህርት አለመግባባቶችና ክርክሮች ምርመራና

ውሳኔ ቅደም ተከተልየMCPS የተማሪዎች ፐርሶኔል አገልግሎት ክፍል፡- 301-315-7335

Page 19: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ¡ 2017–2018 ¡ 11

ተቀጥያ—የተመረጡ የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንቦችድረ-ገጽ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/policy/

የMCPS ደንብ ABC-RA፣ የወላጅና የቤተሰብ ተሳትፎደንቡ ጠንካራ የቤት-ት/ቤት ተባብሮ መሥራትን ለማረጋገጥ ለትም/ቤት፣ መስክ/ሜዳ፣ እና የማእከል ፅ/ቤት ሰራተኞች ከወላጆች/ሞግዚቶች ጋር የሚሰሩበት መመርያዎችን ያስቀምጣል እናም የያንዳንዱ ተማሪ ተነሳሽነት፣ ፅናት፣ ክንውን፣ እና በራስ መተማመን የሚያበለፅግ አካባቢም ያራምዳል።

የMCPS ደንብ ACA-RA፣ ሰብአዊ ግንኙነቶችይህ ደንብ የሰብአዊ ግንኙነቶችን ተሞክሮዎችና ባህላዊ ብቃት በMCPS ለሚያጠናክሩ ሰብአዊ ግንኙነት ፕሮግራሞች፣ አገልግሎቶች፣ እና እንቅስቃሴዎች ምስረታ፣ መተግበር፣ እና ቀጣይነት መዋቅር/ቅርጽ ይስጣል።

የMCPS ደንብ ACF-RA፣ ፆታዊ ጥቃት ይህ ደንብ ስለ ፆታዊ ጥቃት መግለጫ ይሰጣል፣ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠርም ግለሰብ እንዴት ጥቆማ እንደሚቀርብና እርዳታና ድጋፍ የሚገኝበትን ቅደም ተከተሎች ያስቀምጣል። ተማሪዎችና ሰራተኞች የዚህ አይነት ስነምግባር ጥቃት እንዳይገጥማቸው ለማረጋገጥ MCPS መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ያመለክታል።

የMCPS ደንብ CNA-RA፣ የመረጃ ቁሳቁሶችና ማስታወቂያዎችን ለእይታ ማቅረብና ስርጭት

ይህ ደንብ ስለ ቁሳቁሶች/መገልገያዎች ማስታወቂያ እና/ወይም መግለጫዎች ፈቃድ እና ስርጭት ወይም የምርቶች አገልግሎትና ሽያጭን በተመለከተ መመርያ ይሰጣል።

የMCPS ደንብ CNA-RB፣ ማስታወቂያይህ ደንብ በሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) በሙሉ ስለስፖንሰሮች ማስታወቂያና የእውቅና/ፈቃድ መስፈርቶችን ይገልጻል። ደንቡ ማስታወቂያዎች ዬት እንደሚቀመጡና ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ ይገልፃል፣ ስለ ማስታወቂያዎች ይዘት መመዘኛ/መስፈርት ያስቀምጣል፣ የማስታወቂያ ውል ስለሚገባበት ሁኔታ መመሪያ ይሰጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ ያሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ COB-RA፣ ስለ አሳሳቢ ሁኔታ/ገጠመኝ ሪፖርት ማድረግ

ደንቡ በት/ቤት ንብረት ላይ ወይም ከት/ቤት እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ከባድ ሁኔታ ሲያጋጥም መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ቅደም ተከተል ያስቀምጣል።

MCPS ደንብ COC-RA፣ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ንብረት ላይ ጥሶ መግባት ወይም ሆን ብሎ የሚደረግ ረብሻ

ይህ ደንብ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ንብረት ላይ ጥፋት በሚያደርሱ ሰዎች ላይ የት/ቤት ሰራተኞች መውሰድ የሚገባቸውን ርምጃ ስልጣን ይገልጻል፤ ህጉንም ለማስከበር ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል። ከት/ቤት ለጊዜው የታገዱ ተማሪዎች ከርእሰ መምህር/ወይም ከተወካዩ ፈቃድ ካልተሰጣቸው በስተቀር ወደ ት/ቤት ግቢ እንዲገቡ አይፈቀድም።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ COE-RA፣ የጦር መሳሪያዎች

ይህ ደንብ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS ) ንብረት ውስጥ አደገኛ/መርዛማ ወይም ገዳይ ተብለው የሚገመቱ መሳርያዎችን መያዝ የሚከለክልና ህጉ ከተጣሰ መከተል የሚባቸውን ቅደም ተከተሎች ይገልጻል። የጦር መሳሪያዎቹ "... የአካል ጉዳት የሚያስከትሉ መሳርያዎች ተብለው ተገልፀዋል። ይህም የሚተኮሱ መሳርያዎች፣ ጩቤዎች፣ እና ማንኛውም እንደ ጦር መሳርያ የሚያገለግል።"

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ COF-RA፡ አልኮል፣ ትምባሆ፣ እና ሌሎች እፆች በ MCPS ንብረት ላይ

ይህ ደንብ በሀኪም ትእዛዝ ካልተፈቀደ በስተቀር በት/ቤት ግቢ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ የአልኮል መጠጦች ወይም ቁጥጥር የሚደረግባቸው ንጥረ ነገሮች መብላት፣ መያዝ፣ ወይም ማሰራጨት ህገ ወጥ የሚያደርገውን የስቴት ህግ ያስቀምጣል እናም እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም የት/ቤት አስተዳዳሪዎች ምን አይነት ቅደም ተከተሎችና መቀጮዎች ስራ ላይ እንደሚያውሉ ያስቀምጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ COG-RA, የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎች (Personal Mobile Devices)

ይህ ደንብ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤት ንብረት ውስጥ ወይንም የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች በሚያካሄዳቸው የእንቅስቃሴ ስፍራዎች ላይ "MCPS-sponsored activities" ስለ ተማሪዎች የግል ተንቀሳቃሽ መገልገያዎች አጠቃቀምና የቅጣት አሰጣጥ ስርአቶችን ይገልጻል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ ECC-RA፣ የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ንብረት መጥፋት ወይም መበላሸት/መጎዳት

ደንቡ፣ በአደጋና በተንኮል በሁለቱም ለደረሰ ጉዳት፣ የተሰረቀ ንብረት፣ በእሳት የጠፋ ወይም የተበላሸን ጨምሮ የጠፋ ንብረት መለየትና ማመልከት፤ የተሰረቁ ወይም የወደሙ ነገሮችን ከት/ቤት ንብረት ዝርዝር መሰረዝ፤ እናም ለጠፋ ንብረት መተኪያ ማግኘት ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS ) ደንብ ECG-RA፣ የተማሪ መኪና መንጃና ማቆሚያ መገልገያዎች፡

ይህ ደንብ ርእሰ መምህራን በየአመቱ ያሉትን መገልገያዎችና የተማሪዎችን የማቆሚያ ፍላጎቶች እንዲገመግሙ ያለባቸው ን ሃላፊነት ያስቀምጣል እንዲሁም ለተማሪዎች የማቆሚያ መገልገያዎች የመመደቢያ መስፈርቶችን ያስቀምጣል። የአካባቢ ት/ቤት ማህበረሰብ የመኪና ማቆሚያ ስርአትን መተላለፍ በተመለከተ ተገቢ የዲሲፕሊን እርምጃ የመውሰድ/የመወስን ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። በት/ቤት ግቢ ተሽከርካሪዎችን መንዳትና ማቆምን በሚመለከት ተማሪዎች ለሁሉም የአካባቢ ት/ቤት ህጎችና ደንቦች ተጠያቂ ናቸው።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS )ደንብ ECI-RA፣ የዩናይትድ ስቴትስና የሜሪላንድ ሰንደቅ አላማዎችን በሚታይበት ቦታ ማድረግ።

ደንቡ የሰንደቅ አላማዎች ማሳያ ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል የመክፈቻ/መስቀያ ተግባሮች አፈቃቀድ እና ተማሪዎች በነዚህ ተግባሮች የሚተባበሩበትን ሃላፊነት ይደነግጋል። ደንቡ ያለመሳተፍ ቅጣቶችን ይከለክላል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ EEA-RA፣ የተማሪ ትራንስፖርት/መጓጓዣ

ይህ ደንብ ለያንዳንዱ የክፍል ደረጃ የእግር ጉዞ ርቀት መጠን ያስቀምጣል እናም ተማሪዎችን በማጓጓዝ፣ ተገቢ ሪፖርቶችን በመያዝ፣ እና ተገቢ የደህንነት ጥንቃቄዎች መወሰዳቸውን በማረጋገጥ ርእሰ መምህሩ/ሯ መከተል ያለበትን/ያለባትን መርሆች ይዘረዝራል። ያውቶቡስ አሽከራካሪ የዲሲፕሊን ችግሮችን ለማመልከት መከተል ያለበትን ቅደም ተከተል ያስቀምጣል ርእሰ መምህሩ(ሯ)ም የተማሪ ዲሲፕሊን በሚገባ የመከታተል ሃላፊነቱ(ቷ)ን ይገልፃል። የልዩ ትምህርት ተማሪዎች እና ስለ አካለስንኩል ተማሪዎች ትራንስፖርትም ተመልክቷል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ EKA-RA፣ ለአስቸኳይ ሁኔታና ለአደጋ ጊዜ ቅድመ-ዝግጅት

ይህ ደንብ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ለሚገኙ ሁሉም ሰዎች ደህንነት የሚሰጡ ሁለገብ ያካባቢ ቀውስ መቋቋም እቅድ መዳበርና እንክብካቤ ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IGO-RA ተማሪዎችን የሚመለከት የአልኮል መጠጥ፣ትምባሆ፣ እና ሌሎች የእፅ መዳኒቶች ክስተቶች መመሪያ

ይህ ደንብ አልኮል፣ ትምባሆ፣ ሌሎች እፆችን በሚመለከት ከተማሪዎችና ወላጆች ጋር ስለሚካሄድ ግንኙነት ቅደም ተከተል ያስቀምጣል፤ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች መለየት፤ ተማሪዎችን የሚያካትቱ ትግባሬዎች አመዘጋገብ፤ እና የሚጠረጠሩ ቁሶች አያያዝ።

Page 20: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

12 ¡ 2017–2018 ¡ A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IGT-RA፣ የኮምፒውተር፣ የኢሌክትሮኒክስ መረጃ፣ የአውታረ መረብ ደህንነት በሚመለከት የተጠቃሚ ሀላፊነቶች

ይህ ደንብ ስለ ኮምፒውተር አውታረ መረቦች/ኢንተርኔት፣ ስለ Outlook አያያዝና አጠቃቀም ቅደም ተከተሎችና አይነተኛውን የስቴት፣ የአካባቢ፣ እና የፌዴራል ህጎች ማክበር የመሳሰሉ የሚጠበቁ ሁነቶችን ይዘረዝራል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IID-RA፣ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የትምህርት አውታሮች ስለሚሰራጩ/Cablecast/ ፕሮግራሞች

ይህ ደንብ ትም/ቤቶችና ከትም/ቤት ጋር የተያያዙ ድርጅቶችና መምርያዎች የተቀረፁ ወይም ቀጥታ-ማስተማር ፕሮግራሞች በሞንጎሞሪ ካውንቲ (MCPS) የትምህርት አውታሮች በኬብል እንዲተላለፍ (cablecast) መከተል ያለባቸውን ቅደም ተከተል ይገልጻል።

የMCPS ደንብ IGP-RA፣ አጠቃላይ የጤና ትምህርት ማስተማርያ ፕሮግራም

ይህ ደንብ በሜሪላንድ ስቴት እና የሞንጎሞሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የተቀበለው/የተስማማበት ሁለገብ የጤና ትምህርት ፕሮግራም ለሁሉም ተማሪዎች መሰጠት እንዳለበት ቅደም ተከተሎችን ይዘረዝራል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS )ደንብ IKA-RA፣ የትምህርት ውጤት/ማርክ አሰጣጥና ሪፖርት አቀራረብ

ይህ ደንብ ማርክ አሰጣጥንና-የሪፖርት አቀራረብ ሂደቶችን በተመለከተ ከሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) እና በሜሪላንድ ስቴት በደረጃ ስርአተ ትምህርትና ግምገማዎች ጋር በማቀናጀት የተማሪ ግኝትን/የምህርት ክህሎትን በትክክል የሚያንፅባርቁ ማርክ አሰጣጦችን ያንጸባርቃል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IKB-RA፣ የቤት ስራ ቅደም ተከተሎች

ይህ ደንብ ስለቤት ስራ ቅደም ተከተሎችና የሚሰጡ ስራዎች ዝርዝር መመርያ ይሰጣል። በተጨማሪም በኃይማኖት ምክንያት ተፈቅዶላቸው ትምህርት ያመለጣቸው ተማሪዎች የማካካሻ ቤት ሥራ የመስራት እድል እንደሚሰጣቸው ይገልጻል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IKC-RA፣ የክፍል ትምህርት ማርክ/ነጥቦች አማካይ ውጤት(GPA) እና Weighted Grade Point Averages/የአጠቃላይ ነጥቦች ማርክ አማካይ (WGPA)

ይህ ደንብ የክፍል ማርክ አማካይ ነጥብ እና የአጠቃላይ ማርክ አማካዮች ውጤት አወሳሰንና ለአሁንና ለወደፊት ቀጣሪዎች እንዲሁም እንደ ማመልከቻና የመቀበያ ሂደት አካል የሚጠይቁት ከ2ኛ ደረጃ በላይ ላሉ የትምህርት ተቋሞች ዘግቦ ለማስተላለፍ ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS ) ደንብ IOA-RA፣ የከፍትኛ ተሰጥኦና የላቀ ችሎታ ትምህርት

ይህ ደንብ የከፍተኛ ተሰጥኦ እና የላቀ ችሎታ ላላቸው ትምህርት መመርያ ተግባራዊ የሚደረግበትን ቅደም ተከተል ይዘረዝራል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IQA-RA፣ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በት/ቤቶች መካከል የአትሌቲክ ፕሮግራሞች (High School Interscholastic Athletic Programs) አስተዳደር

ይህ ደንብ በMontgomery County 2ኛ ደረጃ ትም/ቤቶች መካከል የሚከናወን አትሌቲክስ ካውንቲ-አቀፍ የት/ቤቶች ፕሮግራሞች አስተዳደር ስልጣን ያብራራል። የ2ኛ ደረጃ ትም/ቤት አትሌቲክስ ገፅታዎች የሚመለከቱ ፕሮግራሞች፣ ህጎች፣ እና መመርያዎች በ2ኛ ደረጃ ትም/ቤት አትሌቲክስ የመምሪያ መጽሐፍ ውስጥ (MCPS High School Athletic Handbook) ተካትተዋል፣ ይህም በርእሰ መምህሩ/ሯ ፅ/ቤት እና በእያንዳንዱ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት የሚድያ ማእከል ይገኛል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IQB-RA፣ ከስርአተ ትምህርት-ውጭ እንቅስቃሴዎች

ይህ ደንብ ከስርአተትምህርት-ውጭ እንቅስቃሴ ፕሮግራምን ለመመስረትና ለማስተዳደር/ለመምራት መስፈርቶችን ያስቀምጣል።

MCPS ደንብ IQD-RA፣ ከስርአተ ትምህርት-ውጭ እንቅስቃሴዎች ላይ ለሚሳተፉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት

በዚህ ደንብ ላይ የተመሰረተው ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ማሟላት የሚገባችውን/ብቃት ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ IQD-RB፣ ከስርአተ ትምህርት-ውጭ እንቅስቃሴዎች ለሚሳተፉ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አካዴሚያዊ ብቃት

በዚህ ደንብ መሠረት ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ብቃት ቅደም ተከተሎች ተቀምጠዋል።

MCPS ደንብ ISB-RA፣ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቅ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች

ይህ ደንብ የስቴት እና የካውንቲ ለመመረቂያ ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን እና የአፈፃፀም ቅደም ተከተሎችን ያመለክታል። በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የኮርስ መጽሔት ላይ ተጨማሪ ዝርዝር ለማግኘት ይችላሉ።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JEA-RA፣ የተማሪ በትምህርት ገበታ ላይ መገኘት

ይህ ደንብ ከት/ቤት ቀሪ የሚሆኑ ተማሪዎችን መቅረትን እንዳያዘወትሩ ክትትል ስለማድረግ፣ በይቅርታ የሚታለፉበት ሁኔታ፣ ክትትል ስለማድረግና የሚቀሩባቸውን ቀናት መዝግቦ መያዝ፣ መቅረትን ስለማሻሻል ተግባራዊ የሚሆኑ አግባብነት ያላቸውን ን/ክፍሎች ለይቶ ያስቀምጣል፣ ክትትልን ለማሻሻልና ከተማሪዎችና ከወላጆች/ሞግዚቶች ጋር ለመከታተል ቅደም ተከተሎችን ይገልጻል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JEC-RA፣ የተማሪ ከት/ቤት ማቋረጥ

ይሀ ደንብ ከሚማሩባቸው ክፍሎች ለመውጣትና ከት/ቤት ለዘለቄታው ለማቋረጥ ተማሪዎች መከተል ያለባቸው ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል። እንደዚህ ለመሳሰሉት እርምጃዎች የጊዜ ገደቦችን ይገልፃል ለትምህርት ውጤት/ማርኮችና ለክሬዲቶች አሰጣጥም መመርያዎችን ያስቀምጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JEE-RA፣ የተማሪዎች ዝውውር

በዚህ ደንብ ላይ ተማሪው/ዋ ከተመደበ(ች)በት የአካባቢ ት/ቤት ወደ ሌላ ት/ቤት ለመዛወር ስለሚቀርብ ጥያቄ ቅደም ተከተል/ስነተግባር ተገልጿል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JFA-RA፣ የተማሪ መብቶችና ኃላፊነቶች

ይህ መመርያ የቦርድ መመርያ JFA፣ የተማሪ መብቶችና ኃላፊነቶች አተገባበር ቅደም ተከተሎችን ይሰጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JGA-RA፣ የመማርያ ክፍል አስተዳደርና የተማሪ ስነምግባር እርምት እርምጃዎች

ይህ ደንብ ጤናማ እና ለመማር አመቺ ሁኔታዎችን ለማዳበር የተቀየሱ በመማርያ ክፍል እስጥ ዘላቂ የሆኑ ፅኑ የዲሲፕሊን እና የቁጥጥር ሥርአት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ቅደም ተከተሎችን ይገልጻል። ደንቡ በዚህ ሰነድ አግባብነት በሞንጎሞሪ ካውንቲ (Montgomery County) የትምህርት ማህበር እና በቦርዱ መካከል ባለው ስምምነት መስረት የርእሰ መምህሩ(ሯ)ን ኃላፊነቶች በሚመለከት ግልጽ/ዝርዝር አቅጣጫዎችን ያሳያል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS )ደንብ JGA-RB፣ ስለ እገዳና ስንብት

ይህ ደንብ በተማሪዎች ላይ ስለሚደረግ እገዳ እና ስንብት የስቴቱን ህግ በስራ ላይ ያውላል፣ ስለሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ሰራተኛ ሃላፊነቶች የሚገልፁ ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል፣ በአሰራር ሂደት ላይ የተማሪዎች መብቶችን ያብራራል፣ እና የአቤቱታ መንገዶችንም ይጠቁማል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JGA-RC፣ አካለ ስንኩልነት ያላቸው ተማሪዎች እገዳና ስንብት

ይህ ደንብ በግላዊ የትምህርት ፕሮግራሞች Individualized Education Programs (IEPs) የሚገኙ ተማሪዎችና ለRehabilitation Act of 1973/ የማገገሚያ ህግ አንቀጽ 504 የታቀፉ ተማሪዎች እገዳና ስንብትን የሚመለከቱ በፌደራል ህግ ስር የሚገኙ መመዘኛዎችን ይገልፃል/ያብራራል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JGB-RA፣ ፍተሻ ማካሄድ እና መወረስ

ይህ ደንብ ተማሪዎች የማይገባ/አደገኛ ነገር ይዘዋል ተብሎ በሚጠረጠሩበት ነገር ፍተሻ ስለማድረግና በጥርጣሬ ፍተሻ የተገኙ ነገሮችን ስለመውረስ MCPS በዝርዝርና በግልጽ የተቀመጠ መመሪያ ነው።

Page 21: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES ¡ 2017–2018 ¡ 13

MCPS ደንብ JHC-RA፣ ህፃን/ልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነት ሪፖርት አቀራርብና ምርመራ

ይህ ደንብ ህፃን/ልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነት ይገልፃል፡ ሁሉንም የሰራተኛ አባላት የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶችን በመወከል ያዩትን ሪፖርት አቅራቢዎች፣ ስለ ሃላፊነታቸው፣ የህፃን/ልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነትን ምልክቶች እንዴት ማወቅ እንደሚቻል፣ እናም የሜሪላንድ ስቴትን ህግን አለማክበር ስለሚያስከትለው መዘዝ ለማሳወቅ እና ለማሰልጠን የሚወስዳቸውን ሂደቶች ይገልፃል። ይህ ደንብ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የሰራተኛ አባለት ተፈፀመ የሚባል የህፃን/ልጅ ማጎሳቆልና ቸልተኝነት፣ ወይም ሌላ ተገቢ ያልሆነ ስነምግባር ጥቆማዎችን/ጥርጣሬዎችን ለመመርመር MCPS የሚከተላቸውን ሂደቶች በተጨማሪ ይገልፃል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JHF-RA፣ ማሸማቀቅ፣ ማዋከብ፣ ወይም ማስፈራራት

ይህ ደንብ ት/ቤቶች ለመማርያ ሰላማዊ ቦታ ይሆኑ ዘንድ ከወከባ፣ ከማስፈራራት እና ከማሸማቀቅ ነፃ የሆነ አካባቢ ለማስፈን MCPS ያለውን ቁርጠኝነት ይገልፃል። ደንቡ "ስለ ወከባ፣ ማስጨነቅ፣ እና ማስፈራራት" ይገልፃል እንዲሁም መከላከል፣ ጣልቃ-ገብነት፣ መዘዞች፣ እና የመፍትሔ እርምጃዎች፣ እናም የማሸማቀቅ፣ የወከባ፣ እና የማስፈራራት ተግባርን ሪፖርት የማቅረብ ቅደም ተከተል ደረጃዎችን ያስቀምጣል።

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንብ JHG-RA፣ ወንበዴዎች፣ የውንብድና እንቅስቃሴ፣ ወይም ተመሳሳይ አጥፊ ወይም ህገወጥ የቡድን ስነምግባር መከላከል

ይህ ደንብ የሚገልጸው የትምህርት/አካዴሚያዊ ስኬት እና ማህበራዊ እድገት የሚጎለብቱት ተማሪዎችና ሰራተኞች ሰላም እንደሰፈነ ሲሰማቸው ነው የሚለውን የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) እምነት ይገልፃል። ወንበዴዎች፣ የውንብድና እንቅስቃሴ፣ ወይም ተመሳሳይ አፍራሽ ወይም ሕገ-ወጥ የቡድን እንቅስቃሴዎች (የወሮበላነት-ስነምግባሮች) በት/ቤቶች ሰላማዊ የሥራ ሂደት ውስጥ ጣልቃ ይገባሉ። ደንቡ ወንበዴዎች፣ የውንብድና እንቅስቃሴ፣ የመከላከያ ተግባሮች፣ እና የጣልቃገብ እንቅስቃሴዎችን ይገልፃል። ለመከላከል የሚደረጉ ቅደምተከተሎች፣ ጣልቃ ገብነት፣ መዘዞቹ፣ የሪፖርት/የጥቆማ ቅደም ተከተሎች፣ የምርመራ ቅደም ተከተሎች እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ቅደም ተከተሎች ይገልጻል።

የ(MCPS) ደንብ JIA-RA፣ የላቀ ትምህርት ማህበረሰብ እና የልቀት ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች

ይህ ደንብ በመካከለኛ እና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የልቀት ትምህርት ስርአት፣ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደግሞ የላቀ ማህበረሰብ ስለማቋቋም ቅደም ተከተሎችን ይሰጣል።

የ(MCPS) ደንብ JNA-RA፣ለተማሪዎች ከትምህርት ጋር የተገናኙ ወጪዎች

ይህ ደንብ የተማሪዎች የኤኮኖሚ ሁኔታዎች ሳይገድባቸው፣ ሁሉንም ኮርሶች እንዲማሩ/እንዲያገኙ ማስቻል፣ ለኮርሶች የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ እና የትምህርት ፕሮግራም ለሁሉም ተማሪዎች የሚቀርብበትን ስርአት ይገልጻል።

የ(MCPS) ደንብ JNA-RB፣ ከተማሪ የፋይናንስ ክፍያ/ግዴታዎችን መሰብሰብ

ይህ ደንብ የተማሪ የፋይናንስ ግዴታዎች መመርያዎችን ይዘረዝራል። የ(MCPS) ንብረት በመጥፋቱ ወይም በመበላሸቱ ለመተካት ወይም ለመጠገን፣ ወይም ያልተከፈሉ የተማሪ እዳዎችን ለሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ስለመክፈል።

የ(MCPS) ደንብ JOA-RA፣ የተማሪ ማህደር/መዝገቦችይህ ደንብ ስለ ተማሪዎች መረጃ አሰባሰብ፣አያያዝ/ጥበቃ፣ እና ስርጭት ሃላፊነቶች የሚመለከት ስርአት ይገልጻል።

የ(MCPS) JPG-RA, ደህንነት/ጤናማነት:- የአካል እና የአመጋገብ ጤንነት

ይህ ደንብ በት/ቤት ደረጃ ስለ ጤናማነት አማካሪ ቡድን እና ስለ ጤና እንቅስቃሴን እንደ ስሜታዊ እና ማህበራዊ ደህንነት በቅንጅት ማስኬድ በትምህርት ቤት ስለ ጤንነት መሻሻል ከሚደረጉ ተግባሮች አንዱ ሆኖ እንዲያዝ ይደነግጋል። ደንቡ በተጨማሪም አሁን በመካሄድ ላይ ያሉ የጤና ትምህርት፣ ስነ-አመጋገብ ትምህርት፣ የአካል እንቅስቃሴ ትምህርት፣ አካላዊ እንቅስቃሴዎች፣ በተመላሽ ክፍያ የት/ቤት ምግብ ፕሮግራም፣ እና ከተመላሽ ክፍያ ምግብ ውጭ ለሚገኙ ተማሪዎች የት/ቤት ምግብና የሚጠጡ ነገሮች ፕሮግራም አሠራርን ይገልጻል።

የ(MCPS) ደንብ KBA-RB፣ የትምህርት አላማዎች እና የMCPS ድረ-ገጽ/የመረጃ መረቦች አስተዳደር

ይህ ደንብ ለሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ድረ-ገፅ ቅርፅና ይዘት መዋቅር ይደነግጋል። ድረ-ገፁ የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶችን (MCPS) ትምህርታዊ አላማ ማገልገሉን ያረጋግጣል የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶችን (MCPS) ሰራተኞችና ተማሪዎችን የግል ገመና (privacy) ስለመጠበቅ መቆጣጣርያ ስልቶችን ይደነግጋል።

የ(MCPS) ደንብ KEA-RA፣ በፖለቲካ ዘመቻ ተሳትፎ ማድረግ እና የምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት

ይህ ደንብ በፖለቲካ ዘመቻና እንቅስቃሴ ስለ ተማሪ ተሳትፎ መስፈርቶች እና ለተሳትፎ ፈቃድ ማግኛ ቅደም ተከተሎችን ይገልጻል።

የ(MCPS) ደንብ KLA-RA፣ ከህዝብ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች መልስ አሰጣጥ

ይህ ደንብ ከህዝብ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ወድያውኑ በፍትሃዊነት፣ በርትአዊነት የመያያዝና የመፍታት ቅደም ተከተሎችን ይገልፃል። ደንቡ በተቻለ መጠን ኦፊስዬላዊ/መደበኛ ያልሆነ የቅሬታ አፈታት ያበረታታል፣ እናም አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ይግባኝና ድህረ እይታ ሊደረግባቸው የሚያስችል ቅደም ተከተል ያስቀምጣል።

Page 22: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

14 ¡ 2017–2018 ¡ A STUDENT’S GUIDE TO RIGHTS AND RESPONSIBILITIES

የቃላት ፍቺ ዝርዝር እና ማስታወሻዎች

አጓጉል/መጥፎ አጠቃቀም1. ማናቸውም የአካል መቁሰል፣ በግልጽ የሚታይ ባይሆን እንኳ፣ የልጅ ወይም ለጉዳት

የተጋለጠ ጎልማሳ የአእምሮ መቁሰል/መጎዳት በማናቸውም በጊዜያዊነትም ይሁን ወይም በቋሚነት በሚያሳድግ ወይም ስለልጁ እንክብካቤ ለማድረግ ወይም ለመቆጣጠር ሃላፊነት ያለበት ጎልማሳ ሰው* የልጁ ጤንነት ወይም ደህንነቱ ወይም የተጋለጠው ጎልማሳ ተጎድቶ ቢሆን ወይም ለጉዳት በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጠ ቢሆን

2. ልጅን ወይም አቅመደካማ አዋቂ ሰው በዘላቂነት ወይም በጊዚያዊነት የመንከባከብ ወይም የመጠበቅ ሃላፊነት ያለው ማንኛውም ግለሰብ በልጅ እና በደካማ አዋቂ ሰው ላይ የተፈፀመ ማንኛውም ፆታዊ የመድፈር ተግባር ወይም ተግባሮች (አካላዊ ጉዳቶች ይድረሱም አይድረሱም) ፣ የዘመድ ፆታዊ ድፍረት/ግንኙነት፣ በማስገደድ የፆታ ግንኙነት መፈጸም፣ ወይም በማንኛውም ደረጃ የፆታ ጥቃት፣ ግብረ ሶዶም ወይም ከተፈጥሮ ውጭ የፆታ ልምዶችን የሚጨምር ነገር ግን በነዚህ ያልተወሰነ። በልጆች ላይ የሚፈጸም ፆታዊ መድፈር/የማስነወር ሁኔታዎች የሚያካትቱት፦ አባብሎ ወይም በአመፅ የጾታ ግንኙነት መፈጸም፣ ሰውነትን እርቃን ማጋለጥ፣ ብልት ማየት/ማሳየት፣ በሌሎች እየተከናወነ በሚታይ ፆታዊ ግንኙነት/አሰራር እርካታ፣ ፆታዊ ማሻሸት፣ ለፍትወት ማነሳሳት ፣ መሳም፣ መደባበስ፣ በማንኛውም ደረጃ የፆታ ወንጀል፣ አስገድዶ ግብረስጋ መፈፀም፣ ግብረ ሰዶም፣ ሽርሙጥና፣ ማቃጠር፣ ወይም አንድን ልጅ ወይም ደካማ አዋቂ ሰው ለፆታዊ ትርእይት፣ ስእል፣ ፊልም፣ ማደፋፈር ወይም ማጥመድ፣ ወይም በህግ የተከለከለ ሆኖ ሳለ ልጅን ማጋለጥ ወይም ከአንድ የተመዘገበ ፆታዊ እጥቂ ጋር አብሮ እንዲኖር ወይም አዘውትሮ እንዲቆይ በማድረግ ማገጋናኘት ወይም ማድረግን ያካትታል። * በቋሚነትም ወይም በጊዜያዊነት ልጅን ወይም አቅመደካማ አዋቂ ሰውን የመቆጣጠር/የመንከባከብ ሃላፊነት የተሰጠው ሰው የሚያካትተው፦ ወላጅ፣ አሳዳጊ፣ ቤተሰብ ወይም የቤተሰብ አባል፣ ጎረቤት፣ የ(MCPS) ሠራተኛ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭ ወይም በኮንትራት የሚሰራ፣ በኃላፊነት ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሰው ወይም ማናቸውም ሌላ ሰው

ስር የሰደደ /chronic/ በተደጋጋሚ የሚከሰት የስነምግባር መገለጫ

በመተባበርከሌሎች ጋር አብሮ በመስራት የተፈፀመ

ምረቃየትምህርት ዓመት ማብቅያ ላይ ዲግሪ የመሸለም ወይም ዲፕሎማ የመስጠት ስነስርአት

በግዴታ/በመገደድየሆነ ነገር ለማከናወን መገደድ ወይም መገፋት

ቀጣይ/ተከታታይ/continuum በተከታታይነት ቢያንስ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ አማራጮች ያሉት

አወዛጋቢበርካታ ውይይት፣ አለመግባባት፣ ወይም ጭቅጭቅ የሚያስከትል

ባህላዊ ጥበብ አንድ ሰው ስለራሱ ባህል የበለጠ ለማወቅና በጥልቀት ለመረዳት አዘውትሮ ጥረት እንደሚያደርገው ሁሉ የሌሎችንም በርካታ ባህሎች ለማወቅና ማክበር መጣር አድናቆትን፣ መረዳትን፣ እንዲሁም በአንድ ድርጅት ውስጥ በሚኖሩ ግንኙነቶች፣ ባህልን ለማስተዋወቅ/ለመግለጽ፣ ድርጀትን ለማጠንከርና ማህበረሰቡንም በበርካታ ባህል ታጅቦ እንዲጠነክር ድጋፍ ይሰጣል።

ክምችት በአብዛኛው ቀስ በቀስታ መሰብሰብ፣

የተሰየመ/ተወካይለአንድ ቦታ የተሰየመ ወይም የተመረጠ ግለሰብ

ለመወሰን መደረግ ያለበት ጥንቃቄበራስ አስተሳሰብ የመወስን ወይም እርምጃ የመውሰድ ስልጣን ወይም መብት

መድልዎበቅንዓት ወይም በምቀኝነት ምክንያት የሚነሱትን ድርጊቶች ጨምሮ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ በግላዊ ሁኔታ ወይም በይሆናል ጥላቻ፣ ረብሻ፣ ደንታቢስነት፣ ንቀት፣ ወይም በቃላት/በንግግር ማንቋሸሽ፣ ማበሻቀጥ፣ ማስፈራራት፣ አካላዊ ሁከት፣ ማወክ፣ እንቅፋት መፍጠር፣ ንብረት ማፈራረስ/ማውደም፣ ብቀላ፣ የትምህርትና ሥራ በሠላም እንዳይካሄድ ማስተጓጎል። ኣድልዎ፦ ላይላዩን አድሎኣዊነት የሌለው የሚመስል ነገር ግን ግለሰብ ባለበት ሁኔታ ወይም የተገመቱ ግላዊ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ተገቢ ያልሆነ ተፅእኖ ያላቸው ስነምግባሮችን ወይም ልምዶችን በተጨማሪ ያካትታል። ኣድልዎ፦ ዘረኝነትን፣ ፆተዊ ትእቢተኛነት/sexism፣ እና ድርጅታዊ ስር የሰደዱ ኣግባብ የሌላቸው ጥላቻዎች ከሞላ መገለጫዎቻቸው ጋር ያካትታል።

እኩልነት ማስፈንግዴታን ለመወጣት በሚደርገው ጥረት ሁሉም ተማሪ እና የሥራ ባልደረቦች ስለግላዊ ማንነታቸው ወይም በይሆናል ተፈርጀው ሳይሸማቀቁ ያሉበትን ሁኔታ አሸንፈው የተሻለ እድል ላይ ለመድረስ ጠንካራ የጋራ መስፈርት በመያዝ ለአካደሚክ እና ለሥራ ስኬታማነት መቆም አለባቸው።

መድረክስብሰባ/ሸንጎ ወይም መሰብሰቢያ ቦታ

ተገቢ ያልሆነ/ብልግናባጠቃላይ ተቀባይነት ያላቸው የመልካም ስነምግባር መለኪያዎችን የሚጻረሩ ነገሮን መፈጸም።

ህገ ወጥነትህግን ወይም መመርያን የመጣስ ተግባር

የሚያሰክሩ ነገሮችአልኮል ወይም ሌሎች እፆች

ብልግናጸያፍ-ብልግና -ስድ ወይም አሳፋሪ-አስነዋሪ

ስም አጥፊነትሆንተብሎ፣ ሃሰተኛ፣ ወይም በፅሁፍ ወይም በታተሙ ቃላት፣ ስእሎች ወይም በሌላ በአፍ ወይም በሰውነት እንቅስቃሴ የሌላን ሰው መልካም ስም የማጉደፍ ተግባር

ክፉ/ተንኮለኛ/ምቀኛሆን ተብሎ ያለምንም መነሻና ምንም ሳይነኩት/ሳይነኳት

በቁሳዊ ነገሮችበሚያሳስብ ሁኔታ፣ በሚያሰጋ ደረጃ

ቸልተኝነትልጅ ወይም ደካማ አዋቂ ሰው በጊዜያዊነት ወይም ለዘለቄታ የመጠበቅ ወይም የመንከባከብ ኃለፊነት ያለበት ግለሰብ የሚከተሉትን የእንክብካቤ ወይም የመቆጣጠር ሁኔታዎች የሚጠቁም፦ አንድን ልጅ ወይም አቅመደካማ አዋቂ ሰው ያለጠባቂ ጥሎ መሄድ፣ ወይም አግባብ ያለው እንክብካቤ ያለመስጠት፣ ወይም ጥንቃቄ አለማድረግ ጉድለት፣ ወይም ተገቢነት የሌለው አያያዝ ሁኔታ ወይም የጥንቃቄ ጉድለት፣ 1. የልጁ/የልጅቱ ወይም የደካማ አዋቂ ሰው ጤንነት ወይም ደህንነት መጎዳቱ ወይም ለጉዳት

አስጊ ሁኔታ ላይ መገኘቱ፣ ወይም2. በልጅ ወይም በደካማ አዋቂ ሰው ላይ የአእምሮ ጉዳት ወይም ለጉዳት አስጊ ሁኔታ።

ፀያፍ/ስድነትግብረገብነት የጎደለው፣ አስቀያሚ፤ ባለጌ

መለያ ባሕርያትመለያ ባሕርያት የሚያካትቱት፦ ዘር፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ የዘር ሐረግ፣ የብሔር ማንነት፣ ኃይማኖት፣ ተሰዳጅነት፣ አቋም፣ ጾታ፣ የጾታ መለያ፣ የጾታ መገለጫ፣ sexual orientation፣ የቤተሰብ/የወላጆች አቋም፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ እድሜ፣ የአካል ወይም የአእምሮ ስንኩልነት፣ ድህነት እና የማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ አቋም፣ ቋንቋ፣ ወይም በሕግ ወይም በሕገመንግስት ጥበቃ የተደረገላቸው ልዩ መብቶች ወይም ሕውነቶች.

ፀያፍ አነጋገርያልታረመ፤ ስድ፤ ምግባረ ብልሹ፤ ፀያፍ፤ ባለጌ

ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ በህብረተሰብና በአኮኖሚያዊ ታሳቢዎች መካከል ያለ ግንኙነትን የሚመለከት

በአመርቂ ሁኔታበቂ፣በርካታ፣ ወይም ልክ/መጠን፣ ብዛት

ይተካል/ተተክቷልበስልጣን፣ በሃላፊነት፣ በውጤታማነት፣ በተቀባይነት መተካት

ማባባስ/ጣልቃ መግባትማባባስ/ጣልቃ መግባት፣ በተለይ ልዩነት ለመፍጠር፣ ለመጉዳት፣ ወይም ለማበላሸት

አስነዋሪ/ፀያፍያልታረመ፤ ስድ፤ ምግባረ ብልሹ፤፤ ፀያፍ፤ ባለጌ

Page 23: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የ ፀረ-መድሎ መግለጫ

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) በዘር፣ በጎሣ፣ በቀለም፣ በዝርያ፣ በትውልድ ሃረግ፣ በዜግነት፣ በኃይማኖት፣ የፍልሰት አቋም/

ይዘት፣ በጾታ፣ በጾታ ልዩነት፣ በጾታ ማንነት መገለጫ፣ የጾታ ባሕርያት፣ በጾታ ግንኙነት፣ በቤተሰብ ይዞታ/አቋም፣ በጋብቻ፣ በእድሜ፣

በሰውነት ወይም በአእምሮ ጉዳተኝነት፣ በድኽነት፣ በማሕበራዊና ኤኮኖሚያዊ አቋም፣ በቋንቋ፣ ወይም ሌላ በሕግ እና በሕገ መንግስት

የታቀቡ ሕውነቶችን መሠረት ያደረገ ህገ-ወጥ መድልዎን ይከለክላል። መድሎ/ልዩነት የሕብረተሰባችንን በራስ የመተማመን፣የእኩልነትን

መንፈስ ለመፍጠር፣ ለማዳበርና ለመደገፍ እየተደረገ ያለውን የቆየ ልማድ/ጥረት ይሸረሽራል/ያዳክማል። ልዩነት/መድሎአዊነት የሚከተሉትን

ጥቂት ምሳሌዎችን ያካትታል፡- ጥላቻ፣ ሁከት/ረብሻ፣ ደንታቢስነት፣ ትንኮሳ፣ ጉልበተኝነት/ወከባ፣ ንቀት፣ ብቀላ/የበቀል ርምጃ፡፡

የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የሞንጎሞሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድን መርህ/ፖሊሲ ይመልከቱ (ACA), የእኩልነት፣ ሚዛናዊነት/

የፍትሕ ባህልን ማዳበር፡፡ ይህ መርህ/ፖሊሲ የቦርዱን እምነት የእያንዳንዱ ተማሪ ብቃትና ተፈላጊነት በተለይም የትምህርት ውጤት

በግለሰብ ሁኔታ የተሞረኮዞ በሚል አስተሳሰብ/ትንበያ መሆን እንደሌለበት ያረጋግጣል። መርሁ/ፖሊሲው በተጨማሪም ፍትህን/እኩልነትን

የሚያዛቡ ነገሮችን ለይቶ በማወቅ በቅድሚያ መወሰድ ያለባቸው ርምጃዎችን የተዛባ ስውር አመለካከት፣ ጭቦኛ/መሠረተ-ቢስ ልዩነት

ማድረግ፣ በተቋማት መዋቅሮች ላይ የሚፈጸሙ መሰናክሎች፣ በትምህርት እና በሥራ ላይ እኩልነት እንዳይኖር የሚገታ/የሚፃረር መሆኑን

ያስገነዝባል።

በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ሠራተኛ ላይ መድሎ/የማዳላት ጥያቄ ወይም ቅሬታ ካለዎ*

በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ተማሪዎች ላይ መድሎ/የማዳላት ጥያቄ ወይም ቅሬታ ካለዎ*

የሰራተኞች አገልግሎት እና ግንኙነት ጽ/ቤትየአፈጻጸም እና ክትትል መምሪያ/ዲፓርትመንት አድራሻ፦ 850 Hungerford Drive, Room 55Rockville, MD 20850የስልክ ቁጥር፡ [email protected]

የት/ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት የት/ቤት አስተዳደርና አፈጻጸም-ትግበራ ቡድንአድራሻ፦ 850 Hungerford Drive, Room 162Rockville, MD 20850ስልክ፦ 301-279-3444 [email protected]

* ምርመራ/ክትትል እንዲደረግ የአካል ጉዳተኛ ስለ ሆኑ ተማሪዎች መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎችን በሚመለከት (accommodations) የሚቀርቡ ጥያቄዎች፣ ክሶች፣ ቅሬታዎች እና አቤቱታዎች ወደ "የልዩ ትምህርት አፈጻጸም ቁጥጥርና ውሳኔ ሰጭ ጽ/ቤት" (Office of Special Education, Resolution and Compliance Unit), at 301-517-5864. ሊቀርብ ይችላል። ለሠራተኞች መዘጋጀት ወይም መሻሻል ያለባቸውን ነገሮች በሚመለከት የሚቀርቡ ጥያቄዎች ወደ ሠራተኛ አገግሎት እና የስራ ግንኙነት የቅሬታና ክትትል ጽ/ቤት (Office of Employee Engagement and Labor Relations, Department of Compliance and Investigations), ስልክ፦ 240-314-4899 ሊቀርብ ይችላል። በተጨማሪም መድሎ/አድልዖ ቅሬታ ለማሰማት ለሌሎች ድርጅቶች/ኤጀንሲዎች፤ ለምሳሌ የዩ.ኤስ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የስራ እድል ኮሚሽን (U.S. Equal Employment Opportunity Commission, Baltimore Field Office, City Crescent Bldg., 10 S. Howard Street, Third Floor, Baltimore, MD 21201, 1-800-669-4000, 1-800-669-6820 (TTY);ወይም ዩ.ኤስ የትምህርት ዲፓርትመንት የሰብአዊ መብት ጽ/ቤት U.S. Department of Education, Office for Civil Rights, Lyndon Baines Johnson Dept. of Education Bldg., 400 Maryland Avenue, SW, Washington, DC 20202-1100, 1-800-421-3481, 1-800-877-8339 (TDD), [email protected], ወይም www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/complaintintro.html ለማቅረብ ይቻላል።

ይህን ሰነድ ከእንግሊዝኛ በሌሎች ቋንቋዎች የውሂብ-ሕትመት ቅርጽ በአካል ጉዳተኝነት የሚኖሩ አሜሪካኖች ህግ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ

ት/ቤቶች - የሕዝብ ማስታወቂያ ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር፦ 301-279-3853፣ 1-800-735-2258 (Maryland Relay) ወይም PIO@

mcpsmd.org. በጥየቃ ለማግኘት ይቻላል። የምልክት ቋንቋ ትርጉም የሚፈልጉ ወይም በምልክት የተዘጋጀ ትርጉም ለሚያስፈልጋቸው፤

በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች MCPS የትርጉም አገልግሎት ጽ/ቤትን Office of Interpreting Services በስልክ ቁጥር፦ 240-

740-1800, 301-637-2958 (VP) ወይም [email protected].መጠየቅ ይቻላል። የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ

ት/ቤቶች (MCPS)፤ ወጣት ወንድ/ሴት ስካውቶችን እና ሌሎችም የሚመለከታቸውን ወጣት ቡድኖችን በእኩል ያስተናግዳቸዋል።

Page 24: 2017–2018 - Montgomery County Public ን በጁን 13፣ 2018 ስራ ላይ ይውላል። በ2018 ውስጥ ሌሎች ማስተካከያ ቀን ሊሆኑ የሚችሉ የሚከተሉትን

Rockville፣ Maryland

ሕትመት፦ Department of Materials Management for the

Office of Student and Family Support and Engagement

ትርጉም፦ Language Assistance Services Unit • Office of Communications

1034.17ct • Editorial, Graphics & Publishing Services • 10/17 • NP

ይህ በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ስለ ተማሪ መብቶች እና ግዴታዎች/ሃላፊነቶች

መመርያ በስፓኒሽኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በቻይንኛ፣ በኮርያንኛ፣

በቬትናምኛ፣ እና በአማርኛ በሚከተለው MCPS ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።

www.montgomeryschoolsmd.org/students/rights/