የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤...

33
የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል ንጽህና ፕሮጀክት (ኮዋሽ) በሴቶች የሚመራ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት መመሪያ ሦስተኛው የኮዋሽ የትግበራ ምዕራፍ (ከነሐሴ 2008 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2011 ዓ.ም) ነሐሴ 2009 ዓ.ም አዲስ አበባ

Transcript of የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤...

Page 1: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤

የአካባቢና የግል ንጽህና ፕሮጀክት (ኮዋሽ)

በሴቶች የሚመራ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት መመሪያ

ሦስተኛው የኮዋሽ የትግበራ ምዕራፍ

(ከነሐሴ 2008 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2011 ዓ.ም)

ነሐሴ 2009 ዓ.ም

አዲስ አበባ

Page 2: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

1

ማውጫ ገጽ

የሠንጠረዥ ዝርዝር……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………2

የእዝል ዝርዝር ……………………………………………………………………………………………………………………………………………….…………………………………………………2

የምህጻረ ቃል ዝርዝር ………………………………………………………………………………………………………………….…………………………………………………………….……4

የጽንሰ ሐሳብ ትርጓሜ……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….………………5

1. መግቢያ

1.1 የመነሻ ሀሳብ………………………………………………………………………………………………………………….………………………………………………………….…………....7

1.2 በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን የማቋቋም ዓላማ፤ ውጤት፤ ክንውንና የሥራ ዝርዝር................................….7

2. የወቅታዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ፤ የውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ዘርፍ የቢዝነስ / የስራ ፈጠራ እድሎች

2.1 የሳኒቴሽን ግብይት………………………………………………………………………………………………………………….………………………………………………………….…10

2.2 የመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፤ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ኦፕሬሽንና ጥገና …………….………………………………………………………….……………..10

2.3 ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም ተግባርና ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም…………….………………………………………………………….…….…………………..11

3. ግቦችና የአተገባበር ዘዴዎች

3.1 በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም /ለማጠናከር በኮዋሽ የታለሙ ግቦች .…….………………………………12

3.2 በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም /ለማጠናከር ኮዋሽ የሚከተለው የአተገባበር ዘዴዎች…………..14

4. በሴቶች የሚመራ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት የፕሮጀክት ኡደት

4.1 የጥ. አ. ኢን ለማቋቋም/ለማጠናከር የእቅድ / የዝግጅት ምዕራፍ …………….……………………………………………………….…….………………………15

4.1.1. የአጋር መስሪያ ቤቶችን / የባለ ድርሻ አካላትን መዘርዘር………….……………………………………………………….…….………………………….…15

4.1.2 ለአጋር መስሪያ ቤቶች ግንዛቤ መፍጠር / ማሳደግ………….…………………………………………………………….…….……………………………..…19

4.1.3 በሴቶች የሚመሩ የጥ. አ. ኢን አደረጃጀት ማስተዋወቅ፤ አባላትን መለየት…………………………………...…….………………………..……22

4.1.4 በሴቶች የሚመሩ ጥ. አ. ኢን ለማቋቋም የኢንተርፕሬነርስ /የሥራ ፈጣሪዎች መምረጫ መስፈርቶች…….………………..….……23

4.2 የጥ. አ. ኢን ለማቋቋም/ለማጠናከር የትግበራ ምዕራፍ ………..…………….……………………………………………………….…….……………..………23

4.2.1 በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም/ ማጠናከር…………………………………...…….……………….……23

4.2.2 የኢንተርፕሬነርስን / የስራ ፈጣሪዎችን የአቅም ክፍተት መለየት…………………………………...…….……………………….……….…………24

4.2.3 የኢንተርፕሬነርስን / የስራ ፈጣሪዎችን አቅም መገንባት ………….…………………………………...…….……………………….…………………24

4.2.4 ማምረት / የምርት ስራ ……………………………………………………………………………………………………………………….…….……………………..27

4.2.5 የገበያ ስትራቴጂ / ስልት ስለመጠቀም ……………………………………………………………………………………….…….……………………..………..28

4.2.6 የጥ. አ. ኢ ፈቃድ አሰጣጥ……………………………………………………………………………………….…….…………………………….……..………..……..30

4.3 የጥ. አ. ኢን ለማቋቋም/ለማጠናከር የክትትል፤ የኦዲትና ሪፖርት ምዕራፍ………………………………………...…….………………….…..…………30

5. መረጃ ማጠናከር…………………………………...…….………………………………….….……………………………………………...…….……………………………….….…..………31

6. የገንዘብ ቅብብሎሽ ፍሰት……………………………………………………………………………………….…….……………………………………………………….….…….…….…..32

Page 3: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

2

የሠንጠረዥ ዝርዝር

ሠንጠረዥ 1፤ በሴቶች የሚመራ ጥ.አ.ኢን ለማቋቋም / ለማጠናከር የተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች ዝርዝር

ሠንጠረዥ 2፤ በአምስቱ የኮዋሽ ክልሎች ሊቋቋሙ ወይም ሊጠናከሩ የሚችሉ በሴቶች የሚመሩ የጥ.አ.ኢ ዓይነት

ሠንጠረዥ 3፤ የወረዳ አጋር/ባለድርሻ መሥሪያ ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት

ሠንጠረዥ 4፤ የአሠልጣኞች ስልጠና አውደ ጥናት ላይ የተሳተፉ የክልል ባለድርሻ አካላት ገጽታ

ሠንጠረዥ 5፤ ዋና ዋና የስልጠና ርእሶችና በዚህ መመሪያ ውስጥ የተጠቀሱበት ክፍል

ሠንጠረዥ 6፤ በእያንዳንዱ የኮዋሽ ክልል ሊቋቋሙ የሚችሉ የኢንተርፕራይዞች አይነት

ሠንጠረዥ 7፤ በተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች የሚገነቡ ሼዶች (የማምረቻና መሸጫ ማዕከላት) ብዛት

የእዝል ዝርዝር

እዝል 1፡ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሳኒቴሽን ግብይትን ለማፋጠን በአጋር ድርጅቶች መካከል የተፈረመ ስምምነት፤ በአማራ ክልላዊ

መንግሥት የሳኒቴሽን ግብይትን ለማፋጠን በአጋር ድርጅቶች መካከል የተፈረመ ስምምነት፤

እዝል 2፡ (1) ስለ ኮዋሽ 3ኛው የትግበራ ምዕራፍ አጭር ማብራሪያ፤ (2) ብሔራዊ የሳኒቴሽን ግብይት መመሪያ ፤ (3) ብሔራዊ የጤናና የአካባቢ

ንጽህና ስትራቴጂ/ስልት፤ እና (4)በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን የውሃ ተቋማት ግንባታና ጥገና ሥራዎች የቁርጥ ዋጋ ኣዘገጃጀት እና

የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀት ማንዋል

እዝል 3፡ ለክልል፤ ዞን እና ወረዳ ባለሙያዎች ስልጠና በሚሰጥበት ጊዜ፤ ስለአካል ጉዳተኛነት፤ መረጃ መሰብሰቢያ መመሪያና ቅጽ

እዝል 4: በኮዋሽ ድጋፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም የወረዳ እቅድ ማዘጋጃ ቅጽ

እዝል 5፡ የኢንተርፕሬነርስን / የስራ ፈጣሪዎችን የአቅም ክፍተት መለያ ቅጽ

እዝል 6፡ የንግድ ሥራ ንድፍ ማዘጋጃ ሞዴል ማብራሪያና ቅጽ

እዝል 7፡ የቢዝነስ / የንግድ ስራ ተግዳሮትን ለመለየትና መፍትሔን ለማቀድ የሚረዳ አጋዥ ናሙና

እዝል 8፡ የቢዝነስ / የንግድ ስራ እቅድ ለማዘጋጀት የሚረዱ ዋና ዋና ርእሶች

እዝል 9፡ የሼድ ዲዛይን ፣ የግንባታ ስራ ዝርዝርና የግንባታ ዋጋ ግምት

እዝል 10፡ በወረዳ ጥ.አ.ኢ ልማት ጽ/ቤት/ ቴ.ሙ.ኢ ልማት ጽ/ቤት /የከ.ም.ዋ.የስ.እ.ፈ ኤጀንሲ እና በኢንተርፕሬነርስ / በስራ ፈጣሪዎች

መካከል የሚፈረም የመግባባያ ሰነድ ናሙና

እዝል 11፡ የመለዋወጫ እቃ መጋዘን ዲዛይን ፣ የግንባታ ስራ ዝርዝርና የግንባታ ዋጋ ግምት

እዝል 12፡ በሳኒቴሽን ግብይት ብቻ እንዲሁም የሳኒቴሽን ግብይት እና የውሃ ጣቢያዎች ጥገናን በጣምራ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች

የሚያገለግሉ የግንባታ መሳሪያዎችና የጥሬ ዕቃዎች ዝርዝር

እዝል 13፡ የሳኒቴሽን አቅርቦት ሰንሰለታዊ ትስስር

እዝል 14፡ በሴቶች የሚመራ ጥ.አ.ኢ ለማደራጀት ኮዋሽ የሚከተለው የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀት ሞዴል

እዝል 15፡ በሴቶች የሚመራ ጥ.አ.ኢ ለማደራጀት የኮዋሽ የፋይናንስ ፍሰት ስርዓት

Page 4: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

3

የዚህ መመሪያ አስፈላጊነት

ይህንን መመሪያ ማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያት በተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች ውስጥ በሳኒቴሽን ግብይትና

በውሃ ተቋማት ጥገና ሥራ የሚሰማሩ በሴቶች የሚመራ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማደራጀት

ወይም ለማጠናከር ፤ ኮዋሽ የሚያደርገውን የቴክኒክ፤ የአቅም ግንባታና የፋይናንስ ድጋፍ የተሳለጠ ለማድረግ

ነው፡፡

Page 5: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

4

የምህጻረ ቃል ዝርዝር

ማ.ፕ.ት የማህበረሰብ ፕሮጀክት ትግበራ

ቴ.ሙ.ኢ. ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ

ከ.ም.ዋ እና ስ. እ. ፈ የከተማ ምግብ ዋስትና እና የስራ እድል ፈጠራ

ኮዋሽ

የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የአካባቢና የግል ንጽህና

ፕሮጀክት

ወ.ፋ.ኢ.ት የወረዳ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር

ው.ተ.ማ የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር

ዞ.ፋ.ኢ.ት የዞን የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር

ጥ. አ. ኢ. ል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ / ኢንተርፕራይዞች ልማት

ጽ/ቤት ጽህፈት ቤት

Page 6: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

5

የጽንሰ ሃሳብ ትርጓሜ

ኢንተርፕሬነርሺፕ/የንግድ ስራ ፈጠራ - አዳዲስ የንግድ ስራዎች እንዴት እንደሚፈጠሩ ማጥናትና የተፈጠሩትም የንግድ ስራዎች ተግባራዊ

የሚሆኑበትን ሂደት የማስጀመር እንቅስቃሴ ነው፡፡ ኢንተርፕረነር/ስራ ፈጣሪ ደግሞ ሰዎች ሊገዟቸው የሚችሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን

የማቅረብ ሀሳብ የሚያመነጭና እነዚህን ለማህበረሰቡ ለማድረስ ድርጅት የሚያቋቁም ግለሰብ ነው፡፡

የቢዝነስ ሞዴል/የንግድ ሞዴል - አንድ ቢዝነስ አኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች አሴቶችን እንዴት እንደሚፈጥር እና አገልግሎቱን

እንደሚያቀርብ የሚገለጽበት ዘዴ ነው፡፡

ፍላጎት - የንጽህናና ከንጽህና አጠባበቅ ጋር የተያያዙ ምርቶችንና አገልግሎቶችን የመግዛት ፍላጎትና አቅም ማለት ነው፡፡

ኦፕሬሽንና ጥገና

ኦፕሬሽን - የውሃ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ከውሃ ተቋሙ ጥሩ አገልግሎት እንዲያገኝ፣ የውሃ ተቋሙን ብልሽት እና የጥገና ፍላጎት

እንዲቀንስ ለማድረግ የውሃ ተቋሙን በየቀኑ የማንቀሳቀስ እና የመንከባከብ ሂደት ነው፡፡

ጥገና - የውሃ ተቋም አገልግሎቱን በአግባቡና በዘላቂነት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚከናወን ተግባር ነው፡፡ የጥገና አይነቶችም የመከላከል

ጥገና ፣ የብልሽት ማስተካከያ እና የችግር ወቅት/ የአስጊ ሁኔታ ጥገና ይባላሉ፡፡

የመከላከል ጥገና - የውሃ ተቋሙን የብልሽት መጠን ለመቀነስ (ለብልሽት ከመዳረጉ በፊት) የሚከናወን ተከታታይነት ያለው የውሃ

ተቋሙን አካላት የመፈተሸ እና አንዳንድ የጥንቃቄ ስራዎችን ማከናወን ነው፡፡ የብልሽት ጥገና - አንዳንድ የተሰበሩና የተበሉ የውሃ ተቋም አካላትን የመቀየር እና አንዳንድ ቀላል ጥገናዎችን በማከናወን የውሃ

ተቋሙ አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ የችግር ወቅት / የአስጊ ሁኔታጥገና - በከፍተኛ ጥገና ፍላጎት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የውሃ ተቋማትን በመጠገን

አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡

ዘላቂነት (የመጠጥ ውሃ እና የሳኒቴሽን አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት) - ተቋማቱ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ለተከታታይ አመታት

አስተማማኝ፣ በቂና ቀጣይነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ በጥሩ ሁኔታ እንዲጠበቁ ማድረግ ነው፡፡

አገልግሎት መስጠት - የውሃ ተቋሙ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡ የውሃ ተቋሙ ሙሉ

አገልግሎት ይሰጣል የምንለው ከተቋሙ የሚገኘው የውሃ ጥራት አስተማማኝና መጠኑም ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በቂ ሲሆን ነው፡፡

ሳኒቴሽን - የሰው ዓይነ ምድር አወጋገድ፣ የግል ንጽህናን አጠባበቅ እና የውሃ ንጽህናን አጠባበቅ የሚያካትት የማህበረሰብ ጤና ዘርፍ

ነው፡፡

ሳኒቴሽን ግብይት- የተሻሻለ የንጽህና አገልግሎትን በበጎ አድራጎት / በነጻ እደላ አሰራር ከማቅረብ ይልቅ ተጠቃሚዎችን በሚያረካ መልኩ

ማህበራዊ ትስስርን ፣እንዲሁም ፍላጎትና አቅርቦትን ያማከለ ምርትና ሽያጭ ማከናወን ማለት ነው ፡፡

የሳኒቴሽን አቅርቦት ሰንሰለት -ለንጽህና አጠባበቅ የሚያገለግሉ ምርቶችን በሚያመርቱና በሚያሰራጩ አካላት መካከል የተፈጠረ የግንኙነት

ሰንሰለት ወይም የግንኙነት መረብ ነው፡፡

እጅን መታጠብ - እጅን ወሳኝ በሆኑ ወቅቶች (ከምግብ ዝግጅት በፊት፣ ከመመገብ በፊት፣ ህጻናትን ከመመገብ በፊት፣ መጸዳጃ ቤት

ከመጠቀም በኃላ፣ ህጻናትን ካጸዳዳን በኋላ እና አንዳንድ የጽዳት ስራዎችን ከሰራን በኋላ) በመታጠብ የራስን እና የቤተሰብን ጤንነት

መጠበቅ ማለት ነው፡፡

ሀይጅን - ጥሩ ጤንነትና ንጽህናን ማረጋገጥና ወሳኝ በሆኑ ወቅቶች እጅን በሳሙና መታጠብ እንዲሁም ምግብና ውሃን በንጽህና መያዝን

ያጠቃልላል፡፡

Page 7: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

6

አካል ጉዳተኛ - በቋሚነት በሚከሰቱ የአካል፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ወይም የስሜት ህዋሳት አካል ጉዳት የተነሳ በአመለካከት፣

በአካባቢና በተቋማት መሰናክልነት ምክንያትበማህበረሰቡ መካከል ሊኖራቸው የሚገባውን ሙሉ፣ውጤታማና እኩል የተሳትፎ እድል

መነፈግ ማለት ነው፡፡ስነት /ኢምፔይርመንት/ በጉዳት፣ በህመም ወይም ከውልደት ጀምሮ በሚከሰት ሁኔታ የሚፈጠር ወይም ሊፈጠር

የሚችል አካላዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ተግባርን የሚቀንስ ወይም ልዩነት የሚያመጣ ክስተት ማለት ነው፡፡ስነት የአካል ጉዳት የሚሆነው

እነዚህ ግለሰቦች በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ ወይም ባህላዊ በሆኑ ምክንያቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ሙሉ ተሳትፎ

ማድረግ ሳይችሉ/ሲነፈጉ ነው፡፡

ማብቃት - የግለሰቦችን እና የማህበረሰቦችን መንፈሳዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ ነው፡፡ ይህም

በውስጣቸው ያለውን እምቅ ሃይል ወይም ችሎታ በመረዳት በራስ መተማመን እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡

ሴቶችን ማብቃት - ሴቶች ለራሳቸውም ሆነ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ ውሳኔዎችን ማድረግ እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ማለት

ነው፡፡ ይህም ማለት የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ህጋዊ ጥንካሬያቸውን/አቅማቸውን በማሳደግና በማሻሻል የእኩልነት

መብታቸው እንዲረጋገጥ እና የሚከተሉት መብቶቻቸውን እንዲጠይቁ በራስ መተማመን እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡

• የራሳቸውን ምርጫና ውሳኔ እንዲያደርጉ፣

• በማህበራዊ፣ በሀይማኖታዊና በህዝባዊ ጉዳዮች ላይ እኩል የተሳትፎ መብት እንዲኖራቸው፣

• በማህበረሰቡ ውስጥ እኩል ደረጃ እንዲኖራቸው፣

• በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ፍትህ ላይ እኩል መብት እንዲኖራቸው፣

• ፋይናንሺያልና ኢኮኖሚያዊ በሆኑ ምርጫዎች ላይ እንዲወስኑ፣

• እኩል የትምህርት እድል የማግኘት፣

• ፆታን መሰረት ያደረገ ተጽእኖ ሳይደረግባቸው እኩል የስራ እድል እንዲያኙ፡፡

ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት - ሴቶች ሀብትን / ገንዘብን፣ ንብረትን፣ ገቢን እና ጊዜያቸውን የመጠቀምና የመቆጣጠር መብታቸውን

እንዲጠቀሙ ማድረግናአደጋን በመቋቋም የኢኮኖሚ ደረጃቸውንና ኑሯቸውን የማሻሻል አቅም እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡

Page 8: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

7

1. መግቢያ

በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞችና መለስተኛ ከተሞች ውስጥ የሥራ ዕድልን ከመፍጠር አኳያ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም ቅድሚያ ትኩረት ከሚሰጣቸው የልማት አጀንዳዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ህዝቡን ከድህነት ለማውጣትና አጠቃላይ የአገሪቱን ልማት ለማፋጠን ዋነኛ መንገድ መሆኑን እውቅና ይሰጣል፡፡ ስለዚህም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት በአገሪቱ የኢንዱስትሪና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ቁልፍ ስፍራ ይሰጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የመጀመሪያውን አምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ሁለተኛውን አምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከሐምሌ 2007 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም ያጸደቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ኢትዮጵያ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ልማት እ.ኤ.አ በ ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ያላትን ራዕይ ለማሳካት እንድትችል ሆኖ የተቀረጸ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትንና ሳኒቴሽንን በተመለከተ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በ2025 ሊደረስበት ከታቀደው ግብ ጋር ተመጋጋቢ ነው፡፡ ስለሆነም የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በስፋት ለማዳረስ እንዲቻል፤ የአገልግሎት ደረጃን ማሻሻል፤ የገጠር መጠጥ ውሃ ተቋም አስተዳደርን ማጠናከር፤ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ዘላቂነት ማረጋገጥ፤ ውጤታማና ብቃት ያለው አገልግሎት መስጠት፤ እንዲሁም የዘርፉን ሁለንተናዊ አቅም ማጎልበት ይጠበቃል፡፡ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ንዑስ ሴክተር በተቀመጠው መሠረት የገጠር መጠጥ ውሃ ሽፋንን በተመለከተ 85% ለሚሆነው የገጠር ነዋሪ ህብረተሰብ ንፁህ፣ በቂ እና ዘላቂ የመጠጥ ውሃ ማለትም በ1 ኪ.ሜ ዙሪያ ገብ ክልል ውስጥ በነፍስ ወከፍ በቀን 25 ሊትር ማዳረስ ሲሆን ፤ የገጠር መጠጥ ውሃ ተቋማት ብልሽት በ2007 ዓ.ም ከነበረበት 11% በ2012 ዓ.ም ወደ 7% ለመቀነስ ታቅዷል፡፡ የንጽህናና ሳኒቴሽን ሽፋንን ከማሳደግ አኳያ ከዓይነ ምድር የጸዱ መሆናቸው የተረጋገጠ የገጠር ቀበሌዎችን ከ18% ወደ 82% ማሳደግ ፤ እንዲሁም የእጅ መታጠቢያን ጨምሮ የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ የሚሆኑ ቤተሰቦችን ከ28% ወደ 82% ማድረስ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተጠቃለለ ነው፡፡

1.1 የመነሻ ሃሳብ

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱት የልማት አጋሮች መካከል የማህበረሰብ

መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤የአካባቢና የግል ንጽህና ፕሮጀክት (ኮዋሽ)ለሶስት ኣመት ማለትምከነሐሴ 2008 ዓ.ም እስከ

ሐምሌ 2011 ዓ.ምድረስ ተቀርጾ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ የኮዋሽ የትግበራ ስልት የማህበረሰብ ፕሮጀክት ትግበራ በሚል የሚታወቅ ሲሆን ቀደም

ባሉት ዓመታት በፊንላንድ መንግስት ድጋፍ በአማራ ክልል የገጠር መጠጥ ውሃና የአካባቢ ጥበቃ ፕሮጀክት፣ ቀጥሎም ፊንዋሽ በተባለ ፕሮጀክት

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተግባራዊ የተደረገ ስልት ነው፡፡ ኮዋሽ የመጀመሪያውን ምእራፍ ከሐምሌ 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም 2007 ዓ.ም

ድረስ ሁለተኛውን ምእራፍ ከጥቅምት 2007 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2008 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀቀ ሲሆን አሁንበሶስተኛው የትግበራ ምእራፍ ላይ

ይገኛል፡፡ ኮዋሽ በዚህ ምእራፍ በአምስት ክልሎች (በአማራ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ በኦሮሚያ ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፣ እና

በትግራይ) ውስጥ ለሚገኙ 76 ወረዳዎችድጋፍ ያደርጋል፡፡

የኮዋሽ ሶስተኛው ምእራፍ በዋናነት የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም በፕሮጀክቱ ለሚጠበቁ ክንውኖችና ግቦች ሁሉ መሰረት

ነው፡፡ የግንባታና የአገልግሎት ዘርፎች ጥራት የተጠበቀ እንዲሆን፣ ውጤትን ያማከለ እቅድና ክንውን እንዲኖር፣ እንደዚሁም የሚገኙ

ውጤቶችና ልምዶች በስፋት የሚሰራጩበትንመንገድ ማመቻቸት በአቅም ግንባታ የሥራ ዘርፍ የተጠቃለለ ነው፡፡

በኮዋሽ ሶስተኛ ምእራፍ ከተካተቱ አዳዲስ ሥራዎች መካከል በውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን ቢዚነስ/የንግድ ስራ ዘርፍ በሴቶች የሚመሩ

ኢንተርፕራይዞች መመስረት አንዱ ሲሆን ይህም ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ከማስፋፋት ጎን ለጎን የኢንተርፕራይዙ

አባላት የሆኑትን ሴቶች የኢኮኖሚ አቅማቸውን በማሳደግ ለማብቃት ያስችላል፡፡ በሴቶች የሚመራ ኢንተርፕራይዝ ማቋቋም/ማጠናከር

የሚለው ሃሳብ በፕሮጀክቱ ግብ ውስጥ እንደሚከተለው ተካቷል፡፡ በ2011 ዓ.ም ኮዋሽ በሚሠራባቸው የፕሮጀክቱ አካባቢዎች የጤናውን ዘርፍ

ማሻሻል ፣ እንዲሁም በውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን አስተዳደርናኢንተርፕሬነርሺፕ ዘርፍ ሴቶችን እኩልተጠቃሚና ተቆጣጣሪ ማድረግ የሚል

ነው፡፡

1.2 በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን የማቋቋም ዓላማ፤ ውጤት፤ ክንውንና የሥራ ዝርዝር

ከኢንተርፕሬነርሺፕ ወይም ከሥራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ከሚጠበቀው ውጤት በተጨማሪ፣ በኮዋሽ ሦስተኛ ምዕራፍ ማለትም እ.ኤ.አ

እስከ ሐምሌ 2019 ድረስ በአምስቱ ክልሎች በሚገኙት 76 ወረዳዎች ውስጥ ፕሮጀክቱትኩረት የሚያደርግባቸው ዘርፎች፤ የማህበረሰብና

የተቋማት የውሃና የንጽህና ሽፋንን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት ማሳደግ፤

እንዲሁምየአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የተገነቡ የውሃና የመጸዳጃ ተቋማት በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡

Page 9: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

8

በሦስቱ ዓመት የኮዋሽ የትግበራ ዓመታት ከኢንተርፕሬነርሺፕ ወይም ከሥራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ

በሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞችንየማቋቋምዓላማ፤ውጤት፤ክንውንናየሥራመዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ዓላማ- ኮዋሽ የውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ / የሚሰማሩኢንተርፕራይዞች ወይም የሥራ እድል ፈጠራዎች መቋቋማቸው ሁለት

መሠረታዊ ግቦችእንዳሉት ይገነዘባል፡፡ አንደኛ፣ ወቅታዊና ተደራሽ የሆነ የውሃ ተቋማት ኦፕሬሽንና ጥገና ማከናወንና የመለዋወጫ ዕቃዎች

አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ ዘላቂ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትእንዲኖር ያደርጋል፤እንዲሁም የሳኒቴሽን ግብይትን ማስፋፋት ህብረተሰቡ የተሻሻለ

መጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ አንዲሆን ያስችላል፡፡ ሁለተኛ፣ በውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን ንግድ ሥራ ዘርፍ በአመራር ቦታ ላይ የሚገኙ ፈር ቀዳጅ

ሴቶች መኖራቸው በርካታ ሴቶችና ወጣቶች በውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን ኢንተርፕራይዝ ወይም የሥራ እድል ፈጠራ ለመሰማራት ፍላጎት

እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

ውጤት - እስከ ሐምሌ 2011 ድረስ በኮዋሽ አምስቱ ክልሎች በውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን ሥራዎች ሴቶችን ማብቃት፣ የአመራር ችሎታቸውን

ማጎልበትና የአካል ጉዳት ያለባቸው ዜጎች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

ክንውን - በአምስቱ ክልሎች በሚገኙ የተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች ውስጥ በሴቶች የሚመራ የውሃ ተቋማት ጥገና፤ የመለዋወጫ ዕቃ

አቅርቦት፤ የሳኒቴሽን ግብይት እንዲሁም የግንባታ ሥራዎች ላይ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም፡፡

የስራ ዝርዝር / እቅድ - በሦስቱ ዓመት የኮዋሽ የፕሮጀክት ዘመን፣ ከአምስቱ ክልሎች በተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች ውስጥ የውሃ ተቋማት

ጥገና፤ የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት፤ የሳኒቴሽን ግብይት እንዲሁም የግንባታ ሥራዎች ላይ የሚሰማሩ በአጠቃላይ 26 በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም ወይም ማጠናከር ሲሆን ከነዚህም መካከል በአማራና በትግራይ ክልሎች በእያንዳንዳቸው 6

ኢንተርፕራይዞች፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና በኦሮሚያ ክልሎች በእያንዳንዳቸው 5 ኢንተርፕራይዞች ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 4

ኢንተርፕራይዞች የሚቋቋሙ ወይም የሚጠናከሩ ይሆናል፡፡

በፌዴራልና በክልል የሚከናወኑ ዝርዝር ሥራዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ይህም ማለት የኮዋሽ ፌዴራል የቴክኒክድጋፍ ሰጪ ቡድንበአምስቱ

የኮዋሽ ክልሎች ከየክልሉ ድጋፍ ሰጪ ክፍል ጋር በመሆን ተግባራዊ የሚያደርጓቸው ይሆናሉ፡፡

• ኦፕሬሽንና ጥገናን እንዲሁም የሳኒቴሽን ግብይትን በተመለከተ ኮዋሽ በሚሰራባቸውአምስት ክልሎች ውስጥ ያለውን ተሞክሮ ዳሰሳ

ማድረግ / ማጥናት፤

• በአምስቱ ክልሎች የኦፕሬሽንና ጥገና እንዲሁም የሳኒቴሽን ግብይት የንግድ ሥራ ዘርፍ ላይ የሚሠሩ ኢንተርፕራይዞችን በተመረጡ

የሙከራ ወረዳዎች ለማቋቋም የወረዳ መምረጫ መስፈርት ማዘጋጀት ፤ በዚሁ መሰረት የሙከራ ወረዳዎች እንዲመረጡ ክልሎችን

ማገዝ፤

• በሴቶችየሚመራየጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞችአደረጃጀት መመሪያማዘጋጀት (ለኮዋሽ ሶስተኛ ምእራፍ የስራ ዘመን

የሚያገለግል)፤

• የተዘጋጀውን የአደረጃጀት መመሪያ በኮዋሽ ክልሎች የሥራ ቋንቋ (ማለትም አማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግሪኛ) መተርጓም፤

• ለክልል ባለድርሻ አካላት በኮዋሽ ድጋፍ በኦፕሬሽንና ጥገና እንዲሁም በሳኒቴሽን ግብይት ላይ በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን

ስለማቋቋም ወይም ስለማጠናከር የአደረጃጃት መመሪያውን በመጠቀም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት፤

• ለክልል ባለድርሻ አካላት የተሰጠውን ስልጠና የኦፕሬሽንና ጥገና እንዲሁም የሳኒቴሽን ግብይት ላይ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞችን

ለማቋቋም በተመረጡትየሙከራ ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙባለድርሻ አካላት መስጠት (የተተረጓመ)፤

• በኦፕሬሽንና ጥገና እንዲሁም በሳኒቴሽን ግብይት ላይ ከሚሠሩ ኢንተርፕራይዞችአገልግሎት የሚያገኙ ደንበኞች ብድር ማግኘት

እንዲችሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድና የደንበኞች ብድር እንዲመቻች ጥረት ማድረግ፤

• በኮዋሽ ድጋፍ የሚቋቋሙ የኦፕሬሽንና ጥገና እንዲሁም በሳኒቴሽን ግብይት ላይ የሚሰሩ በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን ልምድ

ለመሰብሰብ የሚያስችል የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ ማዘጋጀት፤

• የተዘጋጀውን የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ በኮዋሽ ክልሎች የሥራ ቋንቋ (ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግሪኛ) በመተርጓም

በሙከራ ወረዳ ለሚገኙት ባለድርሻ አካላት እንዲጠቀሙበት ማድረግ፤

• የተዘጋጀውን የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ለተመረጡት የሙከራ ወረዳዎች ባለድርሻ አካላት የሥራ

ላይ ስልጠና መስጠት፡፡

Page 10: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

9

በተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች የሚከናወኑ ዝርዝር ስራዎች የሚከተሉት ናቸው

የወረዳጥቃቅንና አነስተኛኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/ የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት / የከተማ ምግብ ዋስትናና የስራ ዕድል

ፈጠራ1ኤጀንሲ ከወረዳው ውሃ፣ ጤና ፣ ሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ፣ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ እንዲሁም ከማይክሮ ፋይናንስ (ቁጠባና ብድር)

ተቋም2 ጋር በመተባበርየሚከናወን ይሆናል፡፡

• የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎችንወይም የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን ወይም በጣምራ ሁለቱን ስራዎች የሚያከናውን

በሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም፤

• የመጠጥውሃኦፕሬሽንናጥገናሥራዎችንወይምየሳኒቴሽንግብይትሥራዎችንወይምበጣምራሁለቱንስራዎችለማከናወንለተቋቋሙበሴቶ

ችየሚመራጥቃቅንና አነስተኛኢንተርፕራይዞችየኢንተፕሬነርሺፕ (የሥራዕድልፈጠራ) እናየክህሎትማሳደግሥልጠናዎችንመስጠት፤

• የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ስራዎችን ወይም የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን ወይም በጣምራ ሁለቱን ሥራዎች የሚያከናውን

በሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞችከማይክሮ ፋይናንስ (ቁጠባና ብድር) ተቋም ብድር እንዲያገኙ ማመቻቸት፤

• የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ስራዎችን ወይም የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን ወይም በጣምራ ሁለቱን ሥራዎች ለማከናወን

የተቋቋሙበሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞችየቢዝነስ እቅድ እንዲያዘጋጁ ማገዝና በእቅዱ መሠረት እንዲያከናውኑ

ክትትል ማድረግ፤

• የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ስራዎችን ወይም የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን ወይም በጣምራ ሁለቱን ስራዎች ለማከናወን

የተቋቋሙ በሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞችኦዲት እንዲደረጉ እገዛ ማድረግ፤

• የኦዲት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ ትርፋማ የሆኑ የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ስራዎችን ወይም የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን

ወይም በጣምራ ሁለቱን ሥራዎች የሚያከናውኑ በሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞችን መለየት፤

• በወረዳ ውስጥ የሚገኙ ተመሳሳይ ኢንተርፕራይዞች ሽያጭ ሥራዎች መጠን ማጠናቀር፤

• የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን የሚያከናውኑበሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞች በግለሰብ መኖሪያ ቤትና በተቋማት

ውስጥ የመጸዳጃ ንጣፎችን መግጠም እንዲችሉ ማገዝ (ሁኔታዎችን ማመቻቸት) ፤

• የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን ከሚያከናውኑ በሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞች ግዢ የፈጸሙ የውሃና ንጽህና

ኮሚቴዎችና ግለሰቦችብዛት መረጃ ማጠናቀር (ዓመታዊ መረጃ ማጠናቀር) ፤

• የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎችን ወይም የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን ወይም በጣምራ ሁለቱን ስራዎች ለማከናወን

ለተቋቋሙ በሴቶችየሚመራጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞች አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ቁሳቁሶች ግዢ መፈጸም (አስፈላጊው

የእቃና የዋጋ ተመን ዝርዝር በዚህ መመሪያ ውስጥ ተካቷል)

• የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎችን ወይም የሳኒቴሽን ግብይት ስራዎችን ወይም በጣምራ ሁለቱን ስራዎች የሚያከናውን

በሴቶችየሚመራየጥቃቅንናአነስተኛኢንተርፕራይዞች ያላቸውን ልምድ በየጊዜው ማጠናቀር (በኮዋሽ የሚዘጋጅ ቅጽ ለወረዳዎች

የሚሰጥ ይሆናል)፡፡

• የክልሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ለተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት

ጽ/ቤት የኦፕሬሽን በጀት መበጀት፤

• የሳኒቴሽን ግብይት ስራዎችን ወይም በጣምራ የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ስራዎችን ለማከናወን ለተቋቋሙ በሴቶች የሚመራ

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሼድ መገንባትና ለተወሰነ ጊዜ እንዲጠቀሙበት ማድረግ፤

• የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን ወይም በጣምራ የመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና ስራዎችን ለማከናወን ለተቋቋሙ በሴቶች የሚመራ

አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የሥራ መጀመሪያ ማቴሪያሎች እንዲያገኙ ድጋፍ ማድረግ፤

• የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበራት፣ለመጠጥ ውሃ ተቋማት ጥገና የሚያገለግል የመለዋወጫ ዕቃዎች ግዢ ሲፈጽሙ ድጎማ ማድረግና

ለመለዋወጫ እቃዎች ማስቀመጫ እንዲሁም መሸጫ የሚያገለግል መጋዘን መገንባት (ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብቻ) ፡፡

1በአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጋር በመጣመር የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በትግራይ ክልል ሁለቱ ድርጅቱ ለየብቻ ናቸው፡፡ በኦሮሚያ ክልልና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሁለቱ ድርጅቶች ለየብቻ የሚገኙ ሲሆን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ ሥራዎች በከተማ ምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ኤጀንሲ ይጠቃለላል፡፡ 2በክፍል 4.1 የባለድርሻ አካላትን መለየት በሚለው ርእሰ ሥር የተቀመጠውን የወረዳ ባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት ይመልከቱ፡፡

Page 11: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

10

2 የወቅታዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ ፤የውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ዘርፍ የቢዝነስ/የስራ ፈጠራ እድሎች

2.1 የሳኒቴሽን ግብይት

የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔራዊ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አማካኝነት እ.ኤ.አ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የማህበረሰብ መር አጠቃላይ

የሳኒቴሽንና ሃይጅን አሠራርን ተግባራዊ በማድረግ የባህሪ ለውጥ ለማምጣትእንዲቻል፣ብሎም ህብረተሰቡ መጸዳጃ ቤት በመገንባት የመጸዳጃ

ቤት ተጠቃሚ እንዲሆንለማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤተሰቦች በራሳቸው አቅም

የተሰራ የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚዎች ሆነዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ መጸዳጃ ቤቶች ያላቸው ደረጃ ሲመረመር የተሻሻለ መጸዳጃ ቤትሊኖረው

የሚገባውን ዝቅተኛ መስፈርት የሚያሟሉ አይደሉም፡፡ ስለዚህም በዓይነ ምድር አወጋገድ ምክንያት የሚመጡ የጤና ችግሮችን ለማስወገድ

አልተቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ይህንን ክፍተት ለመሙላት እንዲቻል የሳኒቴሽን ግብይትን መጀመር / ማስተዋወቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የሳኒቴሽን ግብይትን የተሳለጠ ለማድረግ እንዲቻል በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተዘጋጀ ብሔራዊ የሳኒቴሽን ግብይት መመሪያ እ.ኤ.አ ሰኔ 2013

ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል፡፡

ይህ መመሪያ የተዘጋጀበት ዓላማ፤ የሳኒቴሽን ግብይትን የአተገባበር፣የክትትል እና ግምገማ ሥራዎች ወጥነት ባለው መንገድ ለማቀድና

ለመተግበር፤ በአገሪቱ ውስጥ ለተሻሻለ የሃይጅንና ሳኒቴሽን ግብዓቶች የሚኖረውን ፍላጎትና አቅርቦት ለማሳደግ ፤ እንዲሁም የግል ባለሀብቶች

ሳኒቴሽንን እንደ ቢዝነስ ዘርፍ በመውሰድ ተሳታፊ መሆን እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው፡፡

በብሔራዊ የሳኒቴሽን ግብይት መመሪያ ከተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል፤ (1)ምቹ ሁኔታዎችን ማጠናከር (2) ለተሻሻሉ የሳኒቴሽን ምርቶችና

አገልግሎቶች አቅርቦትን ማሳደግ (3) ለነዚህ ምርቶችና አገልግሎቶች የሚኖረውን ፍላጎት እንዲጨምር ማድረግስኬታማ የሳኒቴሽን ግብይቶችን

ለማካሄድ የተዘረዘሩ ሦስት ስልታዊ መርሆዎች ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል፤ ለሳኒቴሽን ግብይት ፕሮግራም ምቹ ሁኔታዎችን ማጠናከር

የሚለውን በተመለከተ ለሳኒቴሽን ግብይት ሥራ አመቺ ሁኔታዎች በሚገኙባቸው ወረዳዎች ውስጥ (ለምሳሌ፤ ከዓይነ ምድር ነጻ የሆኑ ቀበሌዎች

በተጨማሪም የቁጠባና ብድር ተቋማትያሉባቸው ወረዳዎች)ምርትና አገልግሎቱን በአነስተኛ ደረጃ በመጀመር ቀስ በቀስ ግብይቱን ማስፋፋትና

ወደ አጎራባች ወረዳዎች ጭምር እንዲዳረስ ማድረግ እንደሚቻል ግልጽ በሆነ መንገድ ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሩ

የልማት አጋር ድርጅቶች የተሻሻለ የሳኒቴሽን ምርትና አገልግሎት አቅራቢዎችን በቴክኒክ፣በገንዘብ ፣ በስልጠናና በሌሎች የአቅም ግንባታ

ሥራዎች ለመደገፍ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ያሳስባል፡፡

በተጨማሪም ማንኛውም የሳኒቴሽን አቅርቦት ሰንሰለትን ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሳድግ / ሊያጠናክር የሚችል የቢዝነስ ሞዴል መጠቀም እንደሚቻል

በመመሪያው ተጠቅሷል፡፡ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ፣ አዋጪነታቸው የተረጋገጠ፣ ዘላቂነት ያላቸው፣ በስፋት ሊሰራባቸው የሚችሉና ተስማሚ

የሆኑ ልዩ ልዩ የቢዝነስ ሞዴሎች እንዲጎለብቱ ያበረታታል፡፡ ስለዚህም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በተለይም ልማዳዊ ክህሎትንና

የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም ደረጃውን የጠበቀ በሲሚንቶ የሚሠራ የመጸዳጃ ቤት ንጣፍ ማምረት አንዱ የቢዝነስ ሞዴል መሆኑን

ያመለክታል፡፡

2.2 የመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፣ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ኦፕሬሽንና ጥገና

የውሃ፣ የመስኖና የኤሌክትሪክ ሚኒስቴር እ.ኢ.አ በ2008 ዓ.ም የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን የውሃ ተቋማት ግንባታና ጥገና ሥራዎች የቁርጥ ዋጋ

አዘገጃጀት እና የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀት ማንዋል (መመሪያ) አዘጋጅቷል፡፡ ሆኖም መመሪያውን ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ክልሎች የተለያየ

ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ መመሪያው የተዘጋጀው የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የውሃ፣ የመስኖና የኤሌክትሪክ

ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች የተገኙትን ልምዶች በመቀመር ነው፡፡ በመመሪያው ከተካተቱ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች መካከል

የሚከተለውን መጥቀስ ይቻላል፡፡

• ለመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ሥራዎች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አደረጃጀት

• በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚከናወኑ የጥገና አገልግሎት ሥራዎች፣ የመለዋወጫና የኬሚካል

አቅርቦትና ሽያጭ

• ለመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ተቋማት ግንባታና ጥገና ሥራዎች የሚደራጁ ባለሙያዎች

• በውሃና ሳኒቴሽን ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ አባላት የሚሰጡ ስልጠናዎችና የሙያ ብቃት አሰጣጥ

• መሠረታዊ የዋጋ ትመና መርሆዎችና የቁርጥ ዋጋ አዘገጃጀት

• የቁርጥ ዋጋ ክለሳና ዋጋ ማስተካከያሥርዓት

• ለጥገና አገልግሎትና ለመለዋወጫ አቅርቦት / ሽያጭ ቁርጥ ዋጋ አተማመን

• ለጥገና የሙያ ክፍያ የቁርጥ ዋጋ አተማመን

Page 12: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

11

• መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

• የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የግንባታ ዋጋን መሠረት ያደረገ የውሃ ነክ ሥራዎች ግንባታ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ አወሳሰን

መስፈርት

ለውሃ ጣቢያዎች የሚውል የኦፕሬሽንና ጥገና የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦትን በተመለከተኮዋሽ የሚሰራባቸውአምስቱ ክልሎች የተለያየ ሞዴል

ይጠቀማሉ፡፡ ይህም ማለት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከእያንዳንዱ የውሃ ጣቢያ የውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን ኮሚቴ በተውጣጡ ተወካዮች

የሚመሠረተውየውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር፣ በክልሉ እንዲሁም በልማት አጋሮች ትብብር የሚቋቋም ሲሆንየውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር

ለመለዋወጫ ዕቃ ግዢ ከሚያበረክተው የገንዘብ መዋጮ በተጨማሪ ሽያጭ በመፈጸም በኃላፊነት ያስተዳድራል፡፡ የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር

ከክልሉ ውሃ ቢሮ በሚደረግለት የቴክኒክ ድጋፍ በመታገዝ ግዢውን ያከናውናል፡፡በኦሮሚያ ክልል ያለው ልምድ እንደሚያሳየው የክልሉ የውሃ

ቢሮ የመለዋወጫ ዕቃ ግዢን በመፈጸም በክልሉ ለሚገኙ ወረዳዎች ተደራሽ እንዲሆን ለተመረጡ የዞን የውሃ ጽህፈት ቤቶች ይከፋፈላል፡፡

የዞን ውሃ ጽ/ቤቶች ሽያጭ ካከናወኑ በኃላ ለክልሉ ውሃ ቢሮ ገቢ የሚያደርጉ ሲሆን በተመሳሳይ መንገድ የክልሉ ውሃ ቢሮ ግዢውን

ይፈጽማል(የኮዋሽ ፌዴራል የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ቡድን በጅማ ዞን ከውሃ ጽ/ቤት ሃላፊዎች ጋር ባደረገው ውይይት ፤ የውሃ ጽ/ቤትበግቢው

ውስጥ መጋዘን ያሰራ ሲሆን መለዋወጫ እቃውን በቡድን ለተደራጁ ወጣቶች በማስረከብ ለማሰራት የታቀደ መሆኑንና የመለዋወጫ ዕቃዎቹን

የመሸጫ ዋጋ ከኦሮሚያ ክልል ውሃ ቢሮ እየጠበቀ መሆኑን መረዳት ተችሏል)፡፡ በትግራይ ክልል ተዘዋዋሪ ፈንድ ኢንተርፕራይዝ የተቋቋመ

ሲሆን ኢንተርፕራይዙ የመለዋወጫ ዕቃ ግዢ በመፈጸም ለወረዳ ውሃ ፅ/ቤቶች ያቀርባል፡፡ የኦፕሮሽንና ጥገና የሚያከናውን ባለሙያ ከውሃ

ጽ/ቤት መግዛት ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የወረዳ ጽ/ቤት ሽያጩን ካከናወነ በኃላ ገቢውን ለተዘዋዋሪ ፈንድ ኢንተርፕራይዝ ገቢ

ያደርጋል፡፡በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተግባራዊ እየተደረገ ያለው አሠራር የክልሉ ውሃ ቢሮ የመለዋወጫ ዕቃ ግዢ ከፈጸመ

በኃላ ለከተማ ውሃ አገልግሎትየሚያቀርብ ሲሆን የወረዳ ውሃ ጽ/ቤትን ጨምሮ የኦፕሬሽንና ጥገና የሚያከናውን ባለሙያ ከውሃ አገልግሎት

የሚያገኝ ይሆናል፡፡የከተማ ውሃ አገልግሎት ባለው ሠራተኛና መጋዘን የሚጠቀም ሲሆን የመለዋወጫ እቃዎቹ የመሸጫ ዋጋ ከክልሉ ውሃ ቢሮ

ያገኛል፡፡ በአማራ ክልል ለውሃ ጣቢያዎች የሚውል የኦፕሬሽንና ጥገና የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦትን በተመለከተ ለግል ባለሀብቶች

/ለኢንተርፕራይዞች የተተወ ሲሆንበክልሉ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ በመለዋወጫ፤ የመገጣጠሚያና የሶላር እቃዎች አቅርቦት

ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክት፣ የመጠጥ ውሃ ተቋማት የመለዋወጫ፤ መገጣጠሚያና የሶላር እቃዎች አቅርቦትና የጥገና ማስፈጸሚያ

የአሰራር ሞዳሊቲ በሚል የተዘጋጀ መመሪያ አለ፡፡ ከመጠጥ ውሃ ተቋማት መለዋወጫ እቃበተጨማሪ የሶላርና የባዮጋዝ መለዋወጫዎችን

በተጓዳኝ ማቅረብ እንደሚቻል በመመሪያው ተጠቅሷል፡፡

የውሃ ተቋማት ጥገናን በተመለከተ ከእያንዳንዱ ውሃ ጣቢያ ስልጠና የወሰዱ የፓምፕ ጠጋኞች/ ተንከባካቢዎችየቅድመ ብልሽት ወይም

የመከላከል ጥገና የሚያካሂዱ ሲሆን ከነሱ አቅም በላይ የሆነውን ማንኛውንም የጥገና ሥራ የወረዳ ውሃ ጽ/ቤት ባለሙያዎች የሚያከናውኑት

ይሆናል፡፡ በትግራይ ክልል አራት ወረዳዎች ውስጥኤስ.ኤን. ቪ በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት አማካኝነት የተደራጁ የኦፕሬሽንና ጥገና አገልግሎት

ሰጪ ኢንተርፕራይዞች የሚገኙ ሲሆን ከአራቱ ወረዳዎች መካከል ሁለቱ የኮዋሽ ወረዳዎች ናቸው፡፡

2.3 ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም ተግባርና ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም

በኢትዮጵያ ውስጥ በፌዴራል ደረጃ የከተማ ምግብ ዋስትናና የስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም፣

ድጋፍ ለማድረግና አቅማቸውን ለማሳደግ ተግባርና ኃላፊነት የተሰጠው መሥሪያ ቤት ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና

ሕዝቦች ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች የከተማ ምግብ ዋስትናና የሥራ እድል ፈጠራ ቢሮዎች የሚገኙ ሲሆን በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ

ክልሎች ከቴክኒክ፣ ሙያና ስልጠና ተቋም ጋር በመደባለቅ የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በመባል ይጠራል፡፡ በእያንዳንዱ

ክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ለኢንተርፕራይዞች የንግድ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ በአሁኑ ወቅት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት

ፖሊሲና ስትራቴጂ (እ.ኤ.አ ማርች 2012፣ ክለሳ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2016) በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን በዚሁ ጽሑፍ

ውስጥ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚለውን ለመለየት የሚያስችል ትንተና ተካቷል፡፡ ይህም በኢንተርፕራይዝ ውስጥ የሚሠሩ

ሠራተኞች ብዛትና የካፒታል መጠንን ግምት ውስጥ በማስገባት በሁለት ዋና ዋና ማለትም ‘ኢንዱስትሪ’ እና ‘አገልግሎት ሰጪ’ ዘርፎች

የሚጠቃለል ነው፡፡ የካፒታል መጠን ስሌት ሲወጣ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚኖረውን የዋጋ ግሽበትና የምንዛሪ ተመን ግምት ውስጥ

ያስገባ ነው፡፡

የጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ትርጓሜ

ለኢንዱስትሪ ዘርፍ (የምርት አምራቾችን፣ የግንባታ ሥራዎችንና የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎችን ያጠቃልላል) -ከአምስት ያልበለጠ የሰው ሃይልና

(የድርጅቱን ባለቤትና በድርጅቱ ውስጥ የሚሠሩ የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ) እስከ ብር 100‚000 ወይም 4‚630 ዩ.ኤስ. ዲ አጠቃላይ የካፒታል

መጠን ያለው፡፡

Page 13: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

12

ለአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ (የችርቻሮ ንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴል፣ ቱሪዝም፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ፣ የጥገና ሥራዎችን ያጠቃልላል) - ከአምስት

ያልበለጠ የሰው ሃይልና (የድርጅቱን ባለቤትና በድርጅቱ ውስጥ የሚሠሩ የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ) እስከ ብር 50‚000 ወይም 2‚310 ዩ.ኤስ.

ዲ አጠቃላይ የካፒታል መጠን ያለው፡፡

የአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ትርጓሜ

ለኢንዱስትሪ ዘርፍ (የምርት አምራቾችን፣ የግንባታ ሥራዎችንና የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎችን ያጠቃልላል) - ከስድስት እስከ ሰላሳ የሚደርስ

የሰው ሃይልና ከብር 100‚001 እስከ ብር 1‚500‚000 ወይም ከ4‚630 እስከ 69‚500 ዩ.ኤስ. ዲ አጠቃላይ የካፒታል መጠን ያለው‚፡፡

ለአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ (የችርቻሮ ንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴል፣ ቱሪዝም፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ፣ የጥገና ሥራዎችን ያጠቃልላል) - ከስድስት

እስከ ሰላሳ የሚደርስ የሰው ሃይልናከብር 50‚001እስከ ብር 500‚000ወይም ከ2‚310 እስከ 23‚150 ዩ.ኤስ. ዲ አጠቃላይ የካፒታል መጠን

ያለው፡፡

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመለየት ‹የሰው ሃይል ብዛት› እና ‹አጠቃላይ የካፒታል መጠን›የሚለው መስፈርት አሻሚ ሆኖ ሲገኝ

አጠቃላይ የካፒታል መጠን እንደዋና መስፈርት ይወሰዳል፡፡

እነዚህን እድሎች በመጠቀም፣ ኮዋሽ በአምስቱ ክልሎች በሚገኙ የተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች ውስጥየውሃ፣ ንጽሕናና ሳኒቴሽን ሥራዎችን

ትኩረት ያደረገ ኢንተርፕራይዞችን /የሥራ እድል ፈጠራዎችን ለማስጀመር አቅዷል፡፡ እነዚህ ኢንተርፕራይዞች በኮዋሽ ድጋፍ አዲስ የሚቋቋሙ

ወይም በውሃ፣ ንጽሕናና ሳኒቴሽን ዘርፍ ከዚህ ቀደም የተቋቋሙ ሆነው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ የኮዋሽ እቅድ በኢትዮጵያ

መንግሥትበኩል ተቀባይነት የሚያገኝባቸውን ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡ይኸውም ተገንብተው አገልግሎት መስጠት

የጀመሩ የውሃ፣ ንጽሕናና ሳኒቴሽን ተቋማትን ዘላቂነት ከማረጋገጥ ባሻገር ፤ ከአገሪቱ የልማት አጀንዳዎች መካከል በከተሞችና ከተማ ቀመስ

በሆኑ ማእከላት የሥራ እድል መፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተጠቃሽ ነው፡፡

3 ግቦችና የአተገባበር ዘዴዎች

3.1 በሴቶች የሚመራ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም / ለማጠናከርበኮዋሽየታለሙ ግቦች

በሴቶች የሚመራ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም/ለማጠናከር የሚያስችል የእቅድ ዝግጅት ማጠቃለያ ስብሰባ እ.ኢ.አ

ከሚያዝያ 25 እስከ ሚያዝያ 26 2009 ዓ. ምድረስ በአዲስ አበባ ተካሂዶ ነበር፡፡ ኮዋሽ ከሚሰራባቸው አምስት ክልሎችየተውጣጡ

የየክልሉድጋፍ ሰጪክፍል ሀላፊዎች፣ ከየክልሉ የሚመለከታቸው የመንግሥት ቢሮዎች ማለትም ከውሃ፣ ከጤና፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞች ልማት/ ከቴክኒክ፣ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት/ ከከተማ ምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ኤጀንሲ ባለሙያዎችበስብሰባው

ላይ የተሳተፉ ሲሆን በኮዋሽ በኩል በሴቶች የሚመራ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም/ለማጠናከርየተደረገውቅድመ ዝግጅት

በስብሰባው ለተገኙ ተሳታፊዎች ተገልጿል፡፡

ከዚሁ ጋር በማያያዝ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው ነጥቦች ላይ በመወያየት በኮዋሽ የክልል ድጋፍ ሰጪ ክፍልና በአጋር መንግሥታዊ መስሪያ

ቤት ተወካዮች መካከል የጋራ መግባባት እንዲኖር ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ክልል ተኮር የሆኑ ጉዳዮች ተለይተው የተዘረዘሩ ሲሆን

እንደየክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ በማስተናገድ የእቅድ ዝግጅቱን ለማጠናቀቅ እንዲቻል እገዛ ተደርጓል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥም የመጠጥ ውሃ

ተቋማት የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦትን በተመለከተ እያንዳንዱ ክልል የሚጠቀምበት አሠራር የተለያየ እንደመሆኑ የመጠጥ ውሃ ዘርፍ

ኢንተርፕራይዞችን በተመለከተ በአራቱ ክልሎች ማለትም በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኮዋሽ

ድጋፍ ምን ሊሆን ይገባል የሚለው ሰፊ ውይይት ከተደረገባቸው ሀሳቦች መካከል ይጠቀሳል፡፡

ቀደም ብሎ በዝርዝር እንደተገለጸው በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የየክልሉ የውሃ ቢሮዎች የመጠጥ ውሃ

ተቋማት የመለዋወጫ ዕቃ ግዢን በመፈጸም የኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎችን ለሚያካሂዱ ባለሙያዎች፣ በወረዳ ወይም በዞን ውሃ ጽ/ቤት

በኩልበትግራይና በኦሮሚያ ክልሎች የሚቀርብ መሆኑ እንዲሁም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በከተማ ውሃ አስተዳደር በኩል

የሚቀርብ መሆኑ ተብራርቷል፡፡ ሆኖም በአማራ ክልል ለግሉ የሥራ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በኮዋሽ በኩል፣ በመጠጥ ውሃ ተቋማት የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት ሥራ ላይ ብቻ የሚሰማራ ኢንተርፕራይዝ ትርፋማ ሊሆን እንደማይችል

እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ይሁንና ኮዋሽ የአቅም ግንባታ ድጋፎችን በተለይም የመጋዘን ግንባታና የመለዋወጫ ዕቃ አይነቶችን ለማወቅ የሚረዳ

ስልጠና በመስጠት ሊያግዝ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ይህም የወረዳው ወይም የዞን ውሃ ጽ/ቤት የመለዋወጫ ዕቃ ግዢ ከራሱ በጀት

በመፈጸም ወይም በጽ/ቤት ውስጥ ከሚገኘው ክምችት በከፊል ለኢንተርፕራይዙ የሚሰጥ ከሆነና ከመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት በተጨማሪ

ኢንተርፕራይዙ በመጠጥ ውሃ ጥገና ወይም በሳኒቴሽን ግብይት ወይም ሁለቱንም ሥራዎች በቅንጅት ከመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት ሥራ ጋር

Page 14: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

13

በመስራት ትርፋማ ለመሆን የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ከወረዳ ወይም ከዞን ጽ/ቤት የተረከበውን የመለዋወጫ ዕቃሽያጭ

ካከናወነ በኃላ ትርፉን ለኢንተርፕራይዙ ገቢ በማድረግ ጽ/ቤቱ ዕቃውን የገዛበትን ዋጋ ከጥቂት ትርፍ ጋር ለጽ/ቤቱ ገቢ ያደርጋል፡፡የቤኒሻንጉል

ጉሙዝ ክልልን በተመለከተ የመጠጥ ውሃ ተቋማት የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት በውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር አማካኝነት የሚከናወን በመሆኑና

የመለዋወጫ እቃዎች ግዢ ላይ ከገንዘብ መዋጮ ጎን ለጎን የግዢ አፈጻጸም ሂደት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም

ኮዋሽ ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበርን ከማጠናከር አንጻር የመጋዘን ግንባታንና ለመለዋወጫ እቃ ግዢ

የሚውልየገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በእርግጥየውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት ሥራ ከሁለት ወይም ከሶስት ባልበለጡ

መደበኛ ቅጥር ሰራተኞች (በየወሩ የሚከፈላቸው) የሚሠራ በመሆኑ የኢንተርፕሬነርስ ሞዴል ያልተከተለ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በሴቶች የሚመራ ኢንተርፕራይዝን ከማቋቋም ወይም ከማጠናከር አንጻር ኮዋሽየውሃ ግንባታና ጥገና፣ የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን

ግብይት ሥራዎችን በጣምራ / በአንድነት የሚሠራ ኢንተርፕራይዝ ተመራጭ መሆኑን ያምናል፡፡ ምክንያቱም ዘርፈ ብዙና ተዛማጅ የቢዝነስ /

የንግድ ሥራዎች ላይ ከመሰማራት እንዲሁም ትርፋማነትን ከማረጋገጥ አንጻር ሰፊ እድል ያለው መሆኑ ስለሚታመንበት ነው፡፡ ይሁንና የውሃ

ግንባታና ጥገና፣ የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን በጣምራ / በአንድነት የሚሠራ ኢንተርፕራይዝ እንዲኖር ለማድረግ

በየክልሉ የሚገኙ የሚመለከታቸው የመንግሥት ቢሮ ማለትም የውሃ፣ የጤና ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት/ የቴክኒክ፣ሙያና

የኢንተርፕራይዞች ልማት/ የከተማ ምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ኤጀንሲ እንዲሁም የቁጠባና ብድር ተቋም ሃላፊዎች በጋራ የሚወያዩበትና

ከንግድ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ከንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር የጋራ መግባባት ላይ መድረስ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው(የውሃ ግንባታና

ጥገና፣ የመለዋወጫ ዕቃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን ግብይት ሥራዎችን እንደ አንድ የሥራ ዘርፍ ለመውሰድ ማለት ነው)፡፡

ኮዋሽ የሙከራ ወረዳዎችን ለመምረጥ የሚያስችል መስፈርቶችን በማዘጋጀት ለአምስቱ የኮዋሽ የክልል ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች ያሳወቀ ሲሆን

በዚሁ መሰረት በአምስቱም ክልሎች የሙከራ ወረዳዎች ተመርጠዋል፡፡ በመሆኑም በአምስቱ ክልሎች ኮዋሽ ከሚሠራባቸው 76 ወረዳዎች

መካከል በ11 ዞኖች የሚገኙ 19 የሙከራ ወረዳዎች (25%) በሁለት ዙር ለመምረጥ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ክልል የተሰጠውን

የኢንተርፕራይዞች ቁጥር ሳያልፍእንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ወረዳዎች ሊጨመሩ ይችላሉ፡፡ በሶስቱ ኣመት የኮዋሽ የሥራ ዘመን የተያዘው እቅድ

በአማራና በትግራይ ክልሎች እያንዳንዳቸው ስድስት፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እና በኦሮሚያ ክልሎች በእያንዳንዳቸው አምስት፤

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልአራት፤ በአጠቃላይ 26 ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም ወይም ለማጠናከር ነው፡፡

ሠንጠረዥ 1 ፣በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም/ለማጠናከር የተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች ዝርዝር

ቁጥር ክልል ወረዳ ዞን የሚቋቋሙ

ኢንተርፕራይዞች ብዛት

1 አማራ ጉዋጉሳ ሽኩዳድ* አዊ

6 አንከሻ አዊ

ባሶና ወራና* ሰሜን ሸዋ

አንጾኪያ ገምዛ ሰሜን ሸዋ

2. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ባምባሲ * አሶሳ 4

ኦዳ አሶሳ

3. ኦሮሚያ ቀርሳ* ጅማ

5

ጉማይ ጅማ

ኖኖ ቤንጃ ጅማ

አቢቹ ነጋአ ሰሜን ሸዋ

ጂዳ ሰሜን ሸዋ

4. ደቡብ ብሔር

ብሔረሰቦችና

ሕዝቦች

አርባምንጭ ዙሪያ* ጋሞጎፋ

5

ዱና ሃዲያ

አርቤጎና ሲዳማ

ኢሳራ ዳውሮ

ቶቻ ዳውሮ

5. ትግራይ መደብ አይዛና * ሰሜን ምዕራብ ዞን

6 ታህታይ ማይጨው ማዕከላዊ ዞን

እንዳመሆኒ ደቡባዊ ዞን

ጠቅላላ 5 19 11 26

Page 15: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

14

*ከዚህ በላይ በተገለጸው ሠንጠረዥ በዚህ ምልክት የታዩት ወረዳዎች በመጀመሪያው ዙር የተመረጡ ሲሆኑ በነዚህ ወረዳዎችና ወረዳዎቹ

ከሚገኙበት ዞኖች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ እነዚህ መሥሪያ ቤቶች ውሃ፣ ጤና፣ ሴቶችና ሕጻናት ጉዳይ፣ ጥቃቅንና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤቶች ሃላፊዎች እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን መረጃ ለማግኘት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ (ባለበት

ወረዳዎች ብቻ) ጽ/ቤት ባለሙያዎች ሲሆኑ በየወረዳዎቹ በኮዋሽ ድጋፍ ሊቋቋሙ ወይም ሊጠናከሩ የሚችሉትን ኢንተርፕራይዞች ዓይነት

ለመለየት አስችሏል፡፡ በሁለተኛው ዙር የተመረጡትን ወረዳዎች በተመለከተ በሚያዝያ 25 እና 26፣ 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው

የእቅድ ዝግጅት ማጠቃለያ ስብሰባ በተካሄደበት ወቅት ተመሳሳይ ውይይት ከየክልሉ ተሳታፊዎች ጋር ተደርጓል፡፡

ከዚህ በላይ በተገለጸው ሠንጠረዥ እንደተመለከተው 2 የሙከራ ወረዳዎች በአማራ ክልል በሌሎቹ አራት ክልሎች በእያንዳንዳቸው አንድ

የሙከራ ወረዳ በመጀመሪያው ዙር የተመረጠ ሲሆን ቀሪዎቹ የሙከራ ወረዳዎች በሁለተኛው ዙር የተመረጡ ናቸው፡፡ የሁለተኛው ዙር

ምርጫ የተካሄደው እ.ኢ.አ በሚያዝያ 25 እና 26፣ 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደውየእቅድ ዝግጅት ማጠቃለያ ስብሰባ ላይ ነበር፡፡

በአጠቃላይ፣በአምስቱ የኮዋሽ ክልሎች ሊቋቋሙ ወይም ሊጠናከሩ የሚችሉ በሴቶች የሚመሩየጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዓይነት

ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ተመልክቷል፡፡

ሠንጠረዥ 2፣ በአምስቱ የኮዋሽ ክልሎች ሊቋቋሙ ወይም ሊጠናከሩ የሚችሉ በሴቶች የሚመራ የጥ. አ. ኢ ዓይነት

3.2 በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝን ለማቋቋም/ለማጠናከር ኮዋሽ የሚከተለው የአተገባበር ዘዴ

በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም/ለማጠናከር እንዲቻል፣ ኮዋሽ በየክልሎቹ ያካሄደውን የውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን

የንግድ ሥራ ዘርፍ የዳሰሳ ጥናት ግኝቶች መሰረት በማድረግ ከዚህ የሚከተለውን የአሠራር ዘይቤ በኮዋሽ ሶስተኛ ምእራፍ ተግባራዊ ለማድረግ

ታቅዷል፡፡

• በሴቶች የሚመራጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ማቋቋም- ማንኛውም አዲስ የሚቋቋም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አባላቱ

በሙሉ ሴቶች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ኢንተርፕራይዙን ከመምራት አንጻር ሴቶች በአመራር ቦታ ላይ መሆን ይገባቸዋል

ለማለት ነው፡፡ በተለይም የሰብሳቢ ወይም የሥራ አስኪያጅና የገንዘብ ያዥ ወይም የፋይናንስ የሃላፊነት ቦታዎች በሴቶች የሚመራ ሊሆን

ይገደዳል፡፡ በተጨማሪም እንደየሁኔታው ሴቶች በኢንተርፕራዙ ውስጥ ፀሀፊ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

• አዲስ በሚቋቋም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ፣ ከጠቅላላ አባላት ውስጥ ቢያንስ 40% ሴቶች ይሆናሉ (የአመራር ቦታውን

ጨምሮ)

• የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ወንዶችም ሆኑ ሴቶችመሥራት እስከቻሉ ድረስ በማንኛውም ሁኔታ መገለል ሊደረግባቸው አይገባም፡፡ይልቁንም

ለአካል ጉዳተኛ ወንዶችና ሴቶች አስፈላጊው ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

ክልል የሳኒቴሽን ግብይት

ሥራ ላይ ብቻ

የሚሠማራ

ኢንተርፕራይዝ

ማቋቋም / ማጠናከር

የውሃጣቢያዎች ጥገና

ሥራ ላይ ብቻ

የሚሠማራ

ኢንተርፕራይዝ

ማጠናከር

የሳኒቴሽን ግብይትና

የውሃጣቢያዎች ጥገና

ሥራን በጥምረት

የሚሠራ

ኢንተርፕራይዝ

ማቋቋም / ማጠናከር

የውሃ ጣቢያዎች ጥገና፣

የመለዋወጫ ዕቃ

አቅርቦትና የሳኒቴሽን

ግብይት ሥራዎችን

በጥምረት የሚሠራ

ኢንተርፕራይዝ ማቋቋም /

ማጠናከር (የመለዋወጫ

ዕቃ አቅርቦት በወረዳ/

በዞን ውሃ ጽ/ቤት

የሚፈጸም መሆኑ

ከተረጋገጠ የሚፈጸም

ይሆናል)

የውሃ ጣቢያዎች ግንባታና

ጥገና፣ እንዲሁም

የሳኒቴሽን ግብይት

ሥራዎችን በጥምረት

የሚሠራ ኢንተርፕራይዝ

ማቋቋም / ማጠናከር

በውሃ

ተጠቃሚዎች

ማህበር አማካኝነት

የውሃ ጣቢያዎች

የመለዋወጫ ዕቃ

አቅርቦት ማቋቋም

አማራ x x x

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ x x

ኦሮሚያ X x

ደቡብ ብሔር

ብሔረሰቦችና ሕዝቦች X x

ትግራይ X x

Page 16: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

15

• በሙከራ በተመረጡ ወረዳዎች ውስጥ ከሚገኙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ማለትም ከውሃ፣ ከጤና፣ ከሴቶች ጉዳይ፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲ/ከቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት / ከከተማ ምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ፣ ከወረዳ መስተዳድር

እንዲሁም ከንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ጋር በቅርበት መሥራት ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል፡፡

• በውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራዞችን ማጠናከር የኮዋሽ እቅድ ሲሆን በዚህ ሂደት በሴቶች የሚመራና የአካል

ጉዳት ያለባቸውን ዜጎች ማካተት የሚለውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ የማይቻልበት ሁኔታ እንደሚኖር ታሳቢ ይደረጋል፡፡

• ወረዳው የአባላቱን ቁጥር ከፍ ለማድረግ በቂ ምክንያት ከሌለው በስተቀር፣ እያንዳንዱ በመጠጥ ውሃ ተቋማት በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከአምስት እስከ ሰባት አባላት ይኖሩታል፡፡

• የሚቋቋመው / የሚጠናከረው የውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን የቢዝነስ/የንግድ ዘርፍ ትርፋማ እንዲሆን ምርቱንና አገልግሎቱን በስፋት

የማስተዋወቅ ሥራ ትኩረት የሚሰጠውና፣ ሁሉም አካላት ሊረባረቡበት የሚገባ ቀጣይነት ያለው ሥራ ነው፡፡

• የሳኒቴሽን ግብይት ላይ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች በጤና ጣቢያ/ በጤና ኬላ የአገልግሎት ሽፋን ውስጥ ያሉ ቀበሌዎችን አማካኝ በሆነ

ቦታ በመገኘት መድረስ ይኖርባቸዋል፡፡ የውሃ ተቋማት ጥገናና የመለዋወጫ እቃ አቅርቦት ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በወረዳው ዋና

ከተማ ቢሆኑ የገበያ ተደራሽነታቸውን ያሰፋሉ፡፡

• የሚቋቋመውን / የሚጠናከረውንየውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን የቢዝነስ/የንግድ ዘርፍትርፋማ ለማድረግ እንዲቻል የአቅም ግንባታና የገበያ

ትስስር መፍጠር ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆን ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌም የውሃ ተቋማት የመለዋወጫ እቃ አቅርቦትና የኦፕሬሽንና

ጥገና ሥራዎችን የሚሰራን ኢንተርፕራይዝ ከውሃንጽህናና ሳኒቴሽን ኮሚቴዎች ጋር ማስተሳሰር፣ እንዲሁም የሳኒቴሽን ግብይት ሥራን

የሚሰራ ኢንተርፕራይዝ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞችን ጨምሮ ከጤና ዘርፍ ባለሙያዎችጋር ማያያዝ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ምርትና

አገልግሎትን ለማስተዋወቅ የኢንተርፕራይዝ አባላት በግላቸው የሽያጭ ሠራተኞችን ማነጋገርና ማሳተፍ ይችላሉ፡፡

• አዲስ ለሚቋቋው / ለሚጠናከረው የውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን ኢንተርፕራይዝ የክህሎት ስልጠና፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣

የኢንተርፕሬነርሺፕና የካይዘን ስልጠና መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ የቢዝነስ/የንግድ ሥራ

እቅድ ማዘጋጀትና ተዛማጅ የምርትና የአገልግሎት ዘርፍ ማበራከት /መጨመር ይኖርበታል፡፡

• የሳኒቴሽን ግብይት ግብረሃይል ሥራ በጀመረበት ክልል ከግብረሃይሉ ጋር በቅርበት በመስራት የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ

እንዲኖር በማድረግ የሳኒቴሽን ግብይት ባልተጀመረባቸው ወረዳዎች እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቃል፡፡

• አዲስ የሚቋቋው / የሚጠናከረው የውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን ኢንተርፕራይዞች የሚያመርቱት ምርትና የሚሰጡት አገልግሎት ጥራቱን

የጠበቀ እንዲሆን የክህሎት ማሻሻያ ስልጠናን ማዘጋጀት፣ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የሚቻል ሆኖ ሲገኝ ጥራት ያለው

ጥሬ እቃ አቅራቢዎች ጋር የኢንተርፕራይዙን አባላት በማገናኘት ማገዝ ተገቢ ይሆናል፡፡

4 በሴቶች የሚመራ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፐራይዞችአደረጃጀት የፕሮጀከት ኡደት

በዚህ ርእስ ስር በሴቶች የሚመራ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋምየሚሠሩ ስራዎች ቅደም ተከተል፣ የፕሮጀክት ኡደት

ደረጃዎችን በመከተል የተገለጸ ሲሆንኮዋሽ በሚሰራባቸው ክልሎች በተለይ ደግሞ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለሙከራነት

የተመረጡ ወረዳዎች የሚጠቀሙበት ይሆናል፡፡

4.1 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችንለማቋቋም/ ለማጠናከር ፣ የእቅድ / የዝግጅት ምዕራፍ

4.1.1 የአጋር መስሪያ ቤቶችን / ባለድርሻ አካላትን መለየት

የኮዋሽ የክልል ድጋፍ ሰጪ ቡድን ከየክልሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልማት ኤጀንሲ/ከየክልሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ

ኤጀንሲ/ከየክልሉ የከተማ ምግብ ዋስትናና የስራ ፈጠራ ኤጀንሲ ጋር በመተባባር ለሙከራ በተመረጡት ወረዳዎችና እነዚህ ወረዳዎች

በሚገኙባቸው ዞኖች ውስጥ በውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ተግባር ላይ የሚሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም

የሚመለከታቸውንባለድርሻ አካላት ይለያሉ፡፡

Page 17: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

16

በአሁን ሰዓት የሳኒቴሽን ግብይትን በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅና ለማስፋፋት በፌደራል ደረጃ በሚገኙ አራት ድርጅቶች መካከል የመግባቢያ ሰነድ

ተፈርሟል፡፡ እነዚህም ድርጅቶች፡ - 1) የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ 2) የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ማዕከል፣ 3) የገንዘብና ብድር ቁጠባ

ተቋም እና 4) የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት አጀንሲ ናቸው፡፡ በመግባቢያ ሰነዱ ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተግባርና ሀላፊነት

በግልጽ ተቀምጧል፡፡ በፌደራል ደረጃ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ኮዋሽ በሚሰራባቸው ሁሉም ክልሎች የተፈረመ ሲሆን በአማራ ክልል

የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የመግባቢያ ሰነዱ ፈራሚዎች መካከልአንዱሁኗል ፡፡ የየክልሎቹ የመግባቢያ ሰነድ የየክልሎቹን ነባራዊ ሁኔታ

ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ አንዳንድ መሻሻያዎች ተደርገውበታል፡፡ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተፈረሙት የመግባበቢያ ሰነዶች ቅጅ

በዚህ መመሪያ ላይ ተያይዟል (በሲ.ኤም.ፒ የመረጃ መረብ ይፈልጉ) ፡፡

እዝል 1: በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሳኒቴሽን ግብይትን ለማፋጠን በአጋር ድርጅቶች መካከል የተፈረመ ስምምነት፤ የመግባቢያ ሰነዱ

የተፈረመው በጤና ቢሮ፣ በስራ ፈጠራና የከተማ የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ቢሮ እና በኦሮሚያ

የብድርና ቁጠባ ተቋም መካከል ነው፡፡

በአማራ ክልላዊ መንግስት የሳኒቴሽን ግብይትን ለማፋጠን በአጋር ድርጅቶች መካከል የተፈረመ ስምምነት፤ የመግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው

በጤና ቢሮ፣ በቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ፣ በሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮና በአማራ ብርድና ቁጠባ ተቋም መካከል

ነው፡፡

የኮዋሽ ፕሮጀክት በሚንቀሳቀስባቸው አምስት ክልሎች የመግባቢያ ሰነዶችን በመፈረም የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ የሳኒቴሽን ግብይትን

ለመተግበር ይጠቀማል፡፡ ለሳኒቴሽን ግብይት ስኬት የመግባቢያ ሰነዱን ከፈረሙ አካላት በተጨማሪ ፤ የውሃ ቢሮን፣ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ

ቢሮን እንዲሁም የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮን የስራ አጋሮች ማድረግ ፣ በሴቶች የሚመራና አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የመጠጥ ውሃ

ዘርፍ እና የሳኒቴሽን ግብይትን የሚያከናውኑ ኢንተርፕራይዞችን በኮዋሽ ፕሮጀክት ለማቋቋም አስፈላጊ ግብዓት ነው፡፡

የዞን ውሃ፣ ጤና፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት/የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ልማት/የከተማ ምግብ ዋስትናና የስራ ፈጠራ

ልማት ጽ/ቤቶች፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ተቋም እንዲሁም የብድርና ቁጠባ ተቋማት ለሙከራነት በተመረጡት ወረዳዎች

የቴክኒክ እገዛ ሲሰጡ በሙከራ ወረዳዎች የሚገኙት ከላይ የተጠቀሱት ጽ/ቤቶች በቀጥታ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት፣

የአባላቱን አቅም የመገንባት፣ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ የማዘጋጀት፣ ከብድርና ቁጠባ ተቋም ጋር የማገናኘትና እንዲሁም ለስራ መጀመሪያ

የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እንዲያገኙ የማመቻቸት (በጥናት ላይ በተመሰረተና ኢንተርፕራይዞቹ በሚኖራቸው ፍላጎት መሰረት) ስራዎችን

ይሰራሉ / እገዛ ያደርጋሉ፡፡ ይህም የእገዛ ዓይነት የመነጨው እያንዳንዱ የሴክተር መ/ቤት በመንግስት የተሰጠውን የስራ ተግባርና ሃላፊነት

መሰረት በማድረግ ነው፡፡ የእያንዳንዱ ሴክተር ተግባርና ኃላፊነት ዝርዝር በሚቀጥለው ሠንጠረዥ ላይ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 3 ፡ የወረዳ አጋር / ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት

የጽህፈት ቤቱ ስም የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን በማቋቋም ወቅት የሚኖረው ተግባር

የወረዳ ጤና ጥበቃ

ጽ/ቤት

• የጤና ሴክተር ሰራተኞች (የጤና ጽ/ቤት፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ፣ የጤና ጣቢያና የጤና ኬላ

ሰራተኞች) ለገጠሩ፣ ለከተማ ቀመሱና ለከተሜው ማህበረሰብ የተሻሻለ የመጸዳጃ ቤት እና የንጽህና

አገልግሎት የሚሰጡ ምርቶችን የመጠቀም ፍላጎት የመፍጠር ስራውን ይመራሉ እንዲሁም

ያስተባብራሉ፤

• የጤናው ሴክተር ሰራተኞች (የጤና ጽ/ቤት፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ፣ የጤና ጣቢያና የጤና ኬላ

ሰራተኞች) ተከታታይነት ያለው የውሃ አገልግሎት ማግኘት እንዲችል የውሃ ተቋሙን በዘላቂነት

እንዲያስተዳድርና እንዲጠብቅ ህብረተሰቡን ያስተምራሉ፤

• በሳኒቴሽን ግብይት የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የስራ ፈጣሪዎችን/ኢንተርፕሬነርስን በምርት ንድፍ

ዝግጅት፣ ንድፎችን በማምረት እና የምርቶቻቸውን ደረጃ በማውጣትእንዲሁም የምርቶቹን የመሸጫ

ዋጋ ትመና ላይ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ (ምርቶቹም የመጸዳጃ ቤት ስላብ እና ለእጅ/ለገላ መታጠቢያ

አስፈላጊ የሚሆኑ ፎሴት የተገጠመላቸው ጀሪካኖችን ያካትታል)፤

• ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ወይም ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ጋር

በመቀናጀት በሳኒቴሽን ግብይት ላይ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን በቢዝነስ አቅድ ዝግጅት ማገዝና

የእቅዱን አተገባባር መከታተል፤

• ኢንተርፕሬነርስ/ስራ ፈጣሪዎችን የገበያ ትስስር በመፍጠር ማገዝ፤

Page 18: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

17

የጽህፈት ቤቱ ስም የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን በማቋቋም ወቅት የሚኖረው ተግባር

• በሳኒቴሽን ግብይት ስራ ላይ የተሰማሩት ኢንተርፕሬነርስ/የስራ ፈጣሪዎች ምርቶችና አገልግሎቶች

ጥራታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ተከታታይ የሆነ ድጋፍና ክትትል ማድረግ (ይህ በሚደረግበት ወቅት

ሌሎች በዋሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ አጋሮችን ማሳተፍ ጥሩ ነው)፤

• ደንበኞች በሳኒቴሽን ግብይት ስራ ላይ ከተሰማሩት ኢንተርፕሬነርስ/የስራ ፈጣሪዎች የሚያገኙት

ምርትና የአገልግሎት ጥራት ላይ ያላቸውን የእርካታ ደረጃ የአሰሳ ጥናት ማከናወን፤

• በሳኒቴሽን ግብይት ላይ የተሰማሩ የንግድ/የቢዝነስ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለኮዋሽ ፕሮጀክት በየሩብ

ዓመቱ ሪፖርት ማቅረብ፤ እና

• ጥሩ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በመቀመር (መመሪያው ላይ በተቀመጠው ማስታወሻ መሰረት3)

አሰራሩን ለማስፋት በሚጠቅም መልኩ ለሌሎች ማስተማሪያነትና ለቅስቀሳ እንዲውሉ ማድረግ፡፡

የወረዳ ውሃ ጽ/ቤት

• የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት (አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት) ለኢንተርፕሬነሮቹ/ለስራ ፈጣሪዎቹ

በውሃ ተቋማት ጥገና ስልጠና በሚሰጡበት ወቅት እገዛ መስጠት እና እቅማቸውን ለመገንባት የቅርብ

ክትትል ማድረግ፤

• ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ወይም ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ጋር

በመቀናጀት በውሃ ተቋማት ጥገና ላይ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን በቢዝነስ እቅድ ዝግጅት እገዛ

ማድረግና የእቅዱን ተግባራዊነት መከታተል፤

• ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቶቻቸውን ለውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን ኮሚቴዎችና፣ ለቀበሌ መስተዳድሮች

መስጠት እንዲችሉ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ፤

• የአንድ የውሃ ተቋም የጥገና ፍላጎት ከተደራጁት ኢንተርፕራይዞች የቴክኒክ አቅም በላይ ሲሆን

የወረዳው የውሃ ጽ/ቤት ጥገናዎችን ሊያከናውን ይችላል፤

• ኢንተርፕሬነርስ/ስራ ፈጣሪዎችን የገበያ ትስስር በመፍጠር ማገዝ፤

• ተጠቃሚዎች በተደራጁት የንግድ/የቢዝነስ ቡድኖች እያገኙ ያሉት አገልግሎቶች ላይ ያላቸው እርካታ

ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ከውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽን ኮሚቴዎች መረጃ የሚገኝበትን ዘዴ መቀየስ፤

• በጥገና ስራ ላይ የተሰማሩ የንግድ/የቢዝነስ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለኮዋሽ ፕሮጀክት በየሩብ ዓመቱ

ሪፖርት ማቅረብ፤ እና

• ጥሩ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን መቀመርና(መመሪያው ላይ በተቀመጠው ማስታወሻ መሰረት4)

አሰራሩን ለማስፋት በሚጠቅም መልኩ ለሌሎች ማስተማሪያነትና ለቅስቀሳ እንዲውሉ ማድረግ፣

እንደየክልሉ ተጨባጭ

ሁኔታ የሚወሰን ሁኖ፣

የወረዳው የጥቃቅንና

አነስተኛ

ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት

ወይም

የወረዳው የቴክኒክ፣

ሙያና ኢንተርፕራይዝ

ልማት ጽ/ቤት

ወይም

• በኢንተርፕሬነርስ/በስራ እድል ፈጠራ ሊሳተፉ የሚችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት በሳኒቴሽን

ግብይት እና/ወይም በውሃ ተቋማት ጥገና የሚሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ማደራጀት፤

• ኢነተርፕሬነርስ/የስራ ፈጠራ አባላት ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በማጥናት/በመለየት አስፈላጊውን

የክህሎት ማስጨበጫ ስልጠና ማዘጋጀት፤

• ኢንተርፕሬነሮቹን/የስራ ፈጣራ አባላትን የክህሎት ማሻሻያና የኢንተርፕሬነርሽፕ ስልጠና ከሚሰጡ

የስልጠና ተቋማት ጋር ማገናኘት፤

• የማምረቻ ቦታ ሼድ/መጋዘን በመገንባት5፣ለማምረቻና ለመሸጫ አገልግሎት እንዲውል

ለኢንተርፕሬነሮቹ/ ለስራ ፈጠራ አባላቱ ማስረከብ፤

• የስራ ፈጣሪዎችን/ኢንተርፕሬነርስን በምርት ንድፍ ዝግጅት፣ ንድፎችን በማምረት እና

የምርቶቻቸውን ደረጃ በማውጣት ስራ ላይ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ (አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት

ለዚህ ስራ ከውሃና ከጤና ጥበቃ ጽ/ቤቶች ጋር መመካከር ያስፈልጋል)፤

• ኢንተርፕሬነርስን/ስራ ፈጣሪዎችን የቢዝነስ እቅድ የማዘጋጀት ክህሎት ማስጨበጥ፣ በእቅድ ዝግጅቱ

ወቅት እገዛ ማድረግ (አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት የውሃና የጤና ጥበቃ ጽ/ቤቶችን ማካተት

ያስፈልጋል) እና ክትትል ማድረግ፤

3ከኮዋሽ የሚሰጥ (ወደ ትግበራ ከተገባ በኃላ) 4ከኮዋሽ የሚሰጥ (ወደ ትግበራ ከተገባ በኃላ) 5ወረዳው ለሚቋቋሙት የሳኒቴሽን ግብይት ብቻ ወይም የሳኒቴሽን ግብይትና የውሃ ተቋማት ጥገና ለሚሰጡ ኢንተርፕራይዞች ሊሰጣቸው የሚችል ሼድ/መጋዘን ከሌለ ከፊንላንድ መንግስት በጀት ድጋፍና ኮዋሽ ባዘጋጀው ዲዘይን መሰረት የሚከናወን የሼድ/የመጋዘን ግንባታ፡፡

Page 19: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

18

የጽህፈት ቤቱ ስም የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን በማቋቋም ወቅት የሚኖረው ተግባር

የወረዳው የከተማ

ምግብ ዋስትናና የስራ

እድል ፈጠራ ጽ/ቤት

• ኢንተርፕሬነርስን/ስራ ፈጣሪዎችን የገንዘብ ብድር ማግኘት እንዲችሉ ከአነስተኛ ብድርና ቁጠባ

ተቋማት ጋር ማገናኘት (ብድሩ በተቻለ መጠን በአነስተኛ ወለድ ቢሆን ጥሩ ነው)፤

• ኢንተርፕሬነርስን/ስራ ፈጣሪዎችን የገበያ ትስስር በመፍጠር ማገዝ፤

• አዲስ የተመሰረቱ ወይም ከዚህ በፊት ተመስርተው የማጠናከር እገዛ የተደረገላቸውን የንግድ/የቢዝነስ

ቡድኖች እንቅስቃሴ ለኮዋሽ በየሩብ ዓመቱ ሪፖርት ማቅረብ፤ እና

• ጥሩ ተሞክዎችንና ልምዶችን በመቀመር (መመሪያው ላይ በተቀመጠው ማስታወሻ መሰረት6)

አሰራሩን ለማስፋት በሚጠቅም መልኩ ለሌሎች ማስተማሪነትና ለቅስቀሳ እንዲውሉ ማድረግ፡፡

የወረዳው የቴክኒክና

ሙያ ትምህርት

ማሰልጠኛ ተቋም

• የክህሎት ማበልጸጊያ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የስራ እድል ፈጠራ/ኢንተርፕሬነርሺፕ እና የካይዘን

ስልጠናዎች መስጠት፤

• የስራ ፈጣሪዎችን/ኢንተርፕሬነርስን በምርት ንድፍ ዝግጅት፣ንድፎችን በማምረት እና የምርቶቻቸውን

ደረጃ በማውጣት ስራ ላይ ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ (አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት ለዚህ ስራ ከውሃና

ከጤና ጥበቃ ጽ/ቤቶች ጋር መመካከር ያስፈልጋል) ፤

• ስልጣኞች ጥራት ያለው መጸዳጃ ቤት መቀመጫ (ስላብ) የማምረት ክህሎት እንዳላቸው መመዘንና

ማስረጃ መስጠት፤

• ለእንዳንዱ ስልጠና የሰልጣኞችን መረጃ በጾታ፣ በስልጠናው አይነት እና ስልጠናው የወሰደውን ጊዜ

በመለየት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ ሪፖርት መስጠት፤ እና

• ለወደፊቱ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ (ስላብ) ለማምረት የሚያስችል የስራ ደረጃን መሰረት ያደረገ

የአጭር ጊዜ የስልጠና ይዘቶች እና የምዘና መስፈርቶች ማዘጋጀት፣ ለጊዜው ግን አሁን ያሉትን

የስልጠና ይዘቶችና መመዘኛዎችን መጠቀም7፡፡

የወረዳው የሴቶችና

ህጸናት ጉዳይ ጽ/ቤት

• በማህበረሰብ ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀቶችን (ለምሳሌ የጤና ሰራዊት፣ በመንደር ደረጃ

የሚገኙ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ወዘተ...) በመጠቀም ህብረተሰቡ በውሃ ንጽህናና ሃይጅን ተግባር

ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጡትን አገልግሎቶች እንዲያውቅና አገልግሎቱን

ከኢንተርፕራይዞቹ እንዲያገኝመረጃ መስጠት፤

• ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ/ከቴክኒክ ሞያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት

ጋር በመተባበር የስራ እድል ያላገኙ ሴቶችን መረጃ መለየትና መያዝ እንዲሁም ሴቶች በሚመሰረቱት

ኢንተርፕራይዞች ውስጥ የአመራር ቦታ እንዲኖራቸው ማድረግ፤

• በቢዝነስ/በንግድ ስራው በአመራር ላይ ያሉ ሴቶችን ማሰልጠን፤

• በስራቸው ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ የቢዝነስ/የንግድ ሴቶችን መለየት፣ መሸለምና ልምዳቸውን

ለሌሎች እንዲያካፍሉ ማድረግ8፤ እና

• ለኢንተርፕሬነርስ/ለስራ ፈጣሪዎች የገበያ ትስስር በመፍጠር ማገዝ፡፡

የወረዳው ሰራተኛና

ማህበራዊ ጉዳይ

ጽ/ቤት9

• ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ/ከቴክኒክ ሞያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት

ጋር በመተባበር የአካል ጉዳተኞች በሚቋቋሙት ኢንተርፕራይዞች ውስጥ እንዲካተቱ ማድረግ፤

• የተቋቋሙት ኢንተርፕራይዞች የሚሰሩበትን የስራ ቦታ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆናቸውን በማየት

ምቹ ካልሆኑም ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ፤ እና

• ለኢንተርፕሬነርስ/ለስራ ፈጣሪዎች የገበያ ትስስር በመፍጠር ማገዝ፡፡

የብድርና ቁጠባ

ተቋማት

• ለኢንተርፕረነርስ/ለስራ ፈጣሪዎች የገበያ ትስስር በመፍጠር ማገዝ፤

• ለኢንተርፕረነርስ/ለስራ ፈጣሪዎችን ብድር ለማግኘት አስፈላጊ ስለሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች መረጃ

መስጠት ፤

• ለኢንተርፕረነርስ/ለስራ ፈጣሪዎች የጥሬ ገንዘብ ብድር መስጠት፤

6ከኮዋሽ የሚሰጥ 7በአሁን ሰዓት የትምህርት ካሪኩለምና የምዘና ፓኬጅ ለሌላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ተቋማት የሚያገለግል ነው፡፡ 8አንዱ አማራጭ በየዓመቱ የሚከበረው ማርች 8፣ ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ነው 9በወረዳው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከሌለ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ መረጃው ከወረዳው መስተዳድር ወይም ከሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት ይገኛል፡፡

Page 20: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

19

የጽህፈት ቤቱ ስም የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን በማቋቋም ወቅት የሚኖረው ተግባር

• የኢንተርፕረነርስ/ለስራ ፈጣሪዎችን የቢዝነስ አቅድ አዋጭነትና ውጤታማነት መመርመር፤ እና

• በክትትል፣ ልምዶችን በመቅሰምና አስተያየት በመስጠት ተግባራት ላይ መሳተፍ፡፡

የተሻሻሉ ለሳኒቴሽንና ሃይጅን አገልግሎት የሚውሉ ምርቶችን ለመግዛት የተጠቃሚዎችን ፍላጎት መፍጠር፣ እንዲሁም የሳኒቴሽን

ግብይትንና የቢዝነስ ክህሎትን ማሳደግ ለጤናው ዘርፍ /ሴክተር ብቻ መተው ያለበት ተግባር ሳይሆን፤ ይልቁንም በወረዳው የሚገኙ

የተለያዩ አካላት ለምሳሌ የወረዳ አስተዳደር፣ የትምህርት ሴክተሩ (መምህራን፣ የወላጅና መምህራን ጥምረት ኮሚቴዎች) እና የወጣቶችና

ስፖርት ጽ/ቤት እንዲሁም የከተማ መስተዳድርን ተሳትፎ ይጨምራል፡፡ በወረዳው ውስጥ የሚከናወኑ/የሚከበሩ የተለያዩ በዓላት/

ዝግጅቶች (ለምሳሌ - የግንድ ትርዒት፣ ኤግዚቢሽን፣ የእጅ መታጠብ ቀን፣ የዓለም የመጸዳጃ ቤት ቀን፣ የዓለም የውሃ ቀን፣ ዓለምአቀፍ

የሴቶች ቀን እና የመሳሰሉት) የሳኒቴሽን ግብይት ስራን ለማስተዋወቅ ጠቃሚ መድረክ በመሆናቸው መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

4.1.2 ለአጋር መስሪያ ቤቶች ግንዛቤ መፍጠር / ማሳደግ

ሀ. ለክልል ባለድርሻ አካላት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት፡- የአቅም ግንባታ ስራ አካል እንዲሆን ኮዋሽ በክልል ደረጃ ለሚገኙ የተለያዩ

ባለድርሻ አካላት በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም በተዘጋጀው መመሪያ ላይ በፌዴራል ደረጃ የ3 ቀናት

የአሰልጣኞች ስልጠና ዓውደጥናት10ተካሂዷል፡፡ ስልጠናውም ለመመሪያው ዝግጅት የሚረዱ ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማሰባሰብና አንዳንድ

ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖር እድል ፈጥሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከየክልሉ የመጡት ተሳታፊዎች ለሙከራነት የተመረጡትን

ወረዳዎች ዝርዝር በድጋሚ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ ከየክልሉ የመጡት ሰልጣኞች ለሙከራ በተመረጡት ወረዳዎችና፣እነዚህ ወረዳዎች

በሚገኙባቸው ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ስልጠና ይሰጣሉ፡፡ በስልጠናዎቹም ወቅት የፌደራል የቴክኒክ አማካሪ ቡድን

የቴክኒክ እገዛና የስልጠናዎቹን ክንውን ይከታተላል፡፡

ሠንጠረዥ 4፡ የአሰልጣኞች ስልጠና ዓውደ ጥናት ላይ የተሳተፉ የክልል ባለድርሻ አካላት ገጽታ

የክልል ባለድርሻ አካላት

ሙያ ተቀራራቢ/ተመሳሳይ የስራ ልምድ

ከጤና ቢሮ የሳኒቴሽን ግብይት ባለሙያ የሳኒቴሽን ግብይት ላይ የተሰማሩ/የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን

የማቋቋምና ክትትል የማድረግ የስራ ልምድ ያለው/ያላት

ከውሃ ቢሮ (የኮዋሽ ክልል

ድጋፍ ሰጪ ክፍል አባላትን

ጨምሮ)

- የውሃ ተቋማት ኦፕሬሽንና

ጥገና ባለሙያ

- የኮዋሽ የክልል ድጋፍ

ሰጪ ክፍል

ባለሙያዎች11

የውሃ ተቋማት ኦፕሬሽንና ጥገና ስራ ላይ የተሰማሩ/የሚሰማሩ

ኢንተርፕራይዞችን የማቋቋምና ክትትል የማድረግ የስራ ልምድ

ያለው/ያላት

የጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ/

የቴክኒክ፣ ሙያና

ኢንተርፕራይዝ ልማት

ቢሮ/የከተማ ምግብ ዋስትናና

የስራ እድል ፈጠራ ቢሮ

- ቴክኒካል ባለሙያ

-የኮዋሽ ፎካል ፐርሰን

በውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ስራ ላይ የተሰማሩ/የሚሰማሩ

ኢንተርፕራይዞችን የማቋቋምና ክትትል የማድረግ የስራ ልምድ

ያለው/ያላት

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት

ማሰልጠኛ ተቋማት - የሳኒቴሽን ግብይት/የውሃ

ተቋማት ጥገና አሰልጣኝ

በውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ጉዳዮች ላይ ስልጠና ለመስጠት

ተቀባይነት ያላቸው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ

ተቋማት

የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ - የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ

አቅም አጎልባች ባለሙያ

ሴቶችን በገቢ ማስገኛ ስራዎች የማደራጀትና ክትትል የማድረግ

የስራ ልምድ ያለው/ያላት

10በቢሾፍቱ ከተማ እ.ኢ.አ ከሚያዝያ 25 እስከ ሚያዝያ 26/2009 ዓ. ምየተከናወነ 11የቡድን መሪ፣ የሲኤምፒ ባለሙያ፣ የሳኒቴሽንና ሃይጅን ባለሙያ፣ የስርዓተ ጾታና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ባለሙያ፣ የአቅም ግንባታ ባለሙያ እና የክትትልና ግምገማ ባለሙያ

Page 21: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

20

ለ. በሙከራ ወረዳዎችና እነዚህ ወረዳዎች በሚገኙባቸው ዞኖች የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ስልጠና

ስልጠና የወሰዱ የክልል ባለድርሻ አካላት (በዚህ መመሪያ 4.1.1 እንደተጠቀሰው) በሙከራ ወረዳዎች እና እነዚህ ወረዳዎች በሚገኙባቸው

ዞኖች12ውስጥ ያሉትን ባላድርሻ አካላት ያሰለጥናሉ፡፡ ስልጠናውም የሚሰጠው ለ3 ቀናት ነው፡፡ ስልጠናውም የሚሰጥባቸው ዘዴዎች በፓዎር

ፖይነት የተዘጋጀ ገለጻ ማድረግ፣ የቡድን ስራ እና የጋራ/አጠቃላይ ውይይት ናቸው፡፡ በስልጠናው የሚሸፈኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በዚህ መመሪያ

በየሚመለከታቸው የመመሪያው ክፍሎች እንዲሁም እዝሎች ውስጥ እንደሚገኝ ከዚህ በሚከተለው ሠንጠረዥ ላይ ተዘርዝሯል፡፡

ሠንጠረዝ 5፡ ዋናዋና የስልጠና ርእሶችና በዚህ መመሪያ ውስጥ የተጠቀሱበት ክፍል

ተ.ቁ. መግለጫ ጉዳዮቹ የተካተቱበት የመመሪያው ክፍሎች እና

እዝሎችን ጨምሮ

I. ንድፈ ሃሳባዊ ፍቺዎች የጽንሰ ሐሳብ ትርጓሜ

II. አጠቃላይ ጉዳዮች

• በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን አቅድ ፤ የውሃ፣ ንጽህናና

ሃይጅን ዘርፍን በተመለከተ አጭር ገለጻ -ክፍል 1

• ስለ ኮዋሽ 3ኛው የትግበራ ምዕራፍ አጭር ገለጻ (አግባብ ባለው

የክልል ድጋፍ ሰጪ ክፍል ባለሙያ የሚሰጥ)-በዚህ መመሪያ ውስጥ

ከተካተቱት ሃሳቦች በተጨማሪ አንዳንድ ክልላዊ የሆኑ መረጃዎች

በክልል ድጋፍ ሰጪ ክፍል ባለሙያ መካተት ይኖርበታል፡፡

• በኮዋሽ ምዕራፍ 3 ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ከማቋቋም

አኳያ የተቀረጸው ዓላማ፣ ውጤት፣ ክንውንና እቅድ ገለጻ

- ክፍል 1.1

- እዝል 2

-ክፍል 1.2

III. በውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ሴክተር ያሉ የንግድ/የቢዝነስ ዕድሎች

• በአገር አቀፍ ደረጃ ስላለው የብሔራዊ የሳኒቴሽን ግብይት መመሪያ

ገለጻ(በክልል ወይም በዞን የጤና ባለሙያዎች የሚቀርብ/የሚገለጽ) -ክፍል 2.1

- እዝል 2 (በሲ.ኤም.ፒ ድህረ ገጽ ይገኛል) ፡፡ http://www.cmpethiopia.org/page/2226

• በአገር አቀፍ ደረጃ ስላለው የብሔራዊ የጤናና የአካባቢ ንጽህና

ስትራቴጂ/ስልት ገለጻ (በክልል ወይም በዞን የጤና ባለሙያዎች

የሚቀርብ/የሚገለጽ)

-እዝል 2 (በሲ.ኤም.ፒ ድህረ ገጽ ይገኛል) ፡፡ http://www.cmpethiopia.org/page/2226

• የመለዋወጫ አቅርቦት፣ የውሃ ተቋማት ኦፕሬሽንና ጥገና ገለጻ -ክፍል 2.2

-እዝል 2 (በሲ.ኤም.ፒ ድህረ ገጽ ይገኛል) ፡፡ http://www.cmpethiopia.org/page/2226

• በኢንተርፕራይዞች ልማት ሃላፊነት ያለባቸው/የተሰጣቸው

አካላት/ድርጅቶች መረጃ -ክፍል 2.3

IV. እቅዶች እና የአሰራር ዘዴዎች

• በሳኒቴሽን ግብይት እና በውሃ ተቋማት ጥገና በኮዋሽ የሚደገፉ

በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን

የማቋቋምና የማጠናከር እቅድ

-ክፍል 3.1

• በኮዋሽ የሚደገፉ በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋምና ለማጠናከር ትኩረት የሚደረግባቸው

የአሰራር ዘዴዎች

-ክፍል 3.2

V. የኮዋሽ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የፕሮጀክት ኡደት ደረጃዎች -የዲዛይን ምዕራፍ

12የዞን ተሳታፊዎች የውሃ፣ የጤና፣ የጥቃቅንና አነስተኛ/የቴክኒክና ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤቶችን ያካትታል፡፡ የስልጠናውም ዓላማ በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙና ለወረዳዎች የቴክኒክ እገዛ እንዲሰጡ ነው፡፡

Page 22: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

21

• የባለድርሻ/አጋር አካላትን መለየት እና ተግባርና ሃላፊነታቸውን

መተንተን -ክፍል 4.1.1

• የአጋር አካላትን ግንዛቤ ማሳደግ -ክፍል 4.1.2

-እዝል 2ን እንደገና ማየት

(በሲ.ኤም.ፒ ድህረ ገጽ ይገኛል) http://www.cmpethiopia.org/page/2226

-እዝል 3 እና 4

• በሴቶች ስለሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት

ማስተዋወቅና አባላትን መለየት -ክፍል 4.1.3

• ኢንተርፕሬነርስ/የስራ ፈጣሪዎችን መምረጫ መስፈርቶች -ክፍል 4.1.4

የኮዋሽ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የፕሮጀክት ኡደት ደረጃዎች -የትግበራ ምዕራፍ

• የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም/ማጠናከር -ክፍል 4.2.1

• የኢንተርፕሬነርስን/የስራ ፈጣሪዎችን የአቅም ክፍተት መለየት -ክፍል 4.2.2

-እዝል 5

• የኢንተርፕሬነርስን/የስራ ፈጣሪዎችን አቅም መገንባት -ክፍል 4.2.3

-ከእዝል 6 እስከ እዝል 2

• ከሳኒቴሽን ግብይትና ከመጠጥ ውሃ ኦፕሬሽንና ጥገና

ኢንተርፕራይዞች ጋር በተያያዘ የሚኖረው ተዛማጅ የቢዝነስ/የንግድ

ስራ አይነት

-ክፍል 4.2.4

-እዝል 13

• የገበያ ስትራቴጂ/ስልት -ክፍል 4.2.5

-እዝል 14

• በሴቶች የሚመሩ የጥ. አ. ኢ ፍቃድ አሰጣጥ -ክፍል 4.2.6

የኮዋሽ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የፕሮጀክት ኡደት ደረጃዎች -የክትትል እና ድጋፍ ምዕራፍ

• ክትትል፣ ኦዲት እና የሪፖርት ምዕራፍ -ክፍል 4.3

• መረጃዎችን ማጠናቀር/መያዝ -ክፍል 5

የገንዘብ ፍሰት (ከፊንላንድ እና ከአትዮጲያ መንግሰት የሚመደቡ በጀቶች)

• የገንዘፍ ፍሰት -ክፍል 6

-እዝል 15

እዝል 2፡ (1) ስለ ኮዋሽ 3ኛው የትግበራ ምዕራፍ አጭር ማብራሪያ፤ (2) ብሔራዊ የሳኒቴሽን ግብይት መመሪያ ፤ (3) ብሔራዊ የጤናና የአካባቢ

ንጽህና ስትራቴጂ/ስልት፤እና (4)በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን የውሃ ተቋማት ግንባታና ጥገና ሥራዎች የቁርጥ ዋጋ ኣዘገጃጀት እና

የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀት ማንዋል

በኮዋሽ የሚደገፉ ስልጠናዎች በክልል፣በዞንና በወረዳ ደረጃ ሲሰጡ ከሰልጣኖቹ መካከል ምን ያህሉ የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ ማወቅ አስፈላጊ

ነው፡፡ዋና ዓላማው ምን ያህሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ምን ዓይነት የአካል ጉዳት እንዳለባቸው ማወቅ ሳይሆን ፣ በጥቅሉ የአካል ጉዳት

ያለባቸውን ተሳታፊዎች ብዛት ማወቅ ነው፡፡በስልጠና ወቅት የሚገኙት መረጃዎች ለክልል ድጋፍ ሰጭ ክፍል በሚላኩት ሪፖርቶች ላይ መካተት

አለባቸው፡፡ይህንንም መረጃ ለመሰብሰብ የሚጠቅመው መጠይቅ የእንግሊዝኛ፣ የአማርኛ እና የኦሮምኛ ቅጂዎች በዚህ መመሪያ ላይ

ተካተዋል፡፡

እዝል 3፡ ለክልል፤ ዞን እና ወረዳ ባለሙያዎች ስልጠና በሚሰጥበት ጊዜ፤ ስለአካል ጉዳተኛነት፤ መረጃ መሰብሰቢያ መመሪያና ቅጽ

የወረዳና የዞን ባለድርሻ አካላት ስልጠና ከመጠናቀቁ በፊት የእያንዳንዱ የሙከራ ወረዳ የስልጠና ተሳታፊዎች የጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞችን የማቋቋም/የማጠናከር ስራን ለማሳለጥ የሚረዳ ዝርዝር የትግበራ አቅድ ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ለእቅድ ዝግጅት

የሚያስፈልገው ቅጽ በዚህ መመሪያ ላይ ተያይዟል፡፡

እዝል 4: የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም የወረዳ እቅድ ማዘጋጃ ቅጽ

Page 23: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

22

4.1.3 በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን አደረጃጀት ማስተዋወቅና አባላትን መለየት

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞቹ አባል ሊሆኑ የሚችሉ እድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም አካል

ጉዳተኞች ይለያሉ፡፡ በተለይ ሴቶች የኢንተርፕራይዞቹ አመራር መሆን እንዳለባቸውና አካል ጉዳተኞችም የኢንተርፕራዞቹ አባላት መሆን

እንዳለባቸው ግንዛቤ በደንብ ሊፈጠር እና ሊተገበርም ይገባል፡፡የአካል ጉዳተኛ መሆን አመራር ከመሆን የማያግድ መሆኑም ሊታወቅ ይገባል፡፡

አዲሰ ለሚመሰረቱ ኢንተርፕራይዞች በወረዳው የሚሰጥ የተለየ ምክንያት ከሌለ በስተቀር የአባላቱ ቁጥር ከ 5 እስከ 7 መሆን አለበት፡፡

እንዲሁም ወሳኝ የሆኑ የኢንተረፕራይዞቹ የአመራር ቦታዎች በሴቶች መያዝ አለባቸው፡፡ እነዚህም የአመራር ቦታዎች፡- 1) ሰብሳቢ/ስራ

አስኪያጅ/ማናጀር እና 2) ፋይናንስ / ገንዘብ ያዥ ናቸው፡፡ እንዲሁም አዲስ በሚመሰረቱት ኢንተርፕራይዞች ውስጥ ከጠቅላላ አባላት ውስጥ

ቢያንስ 40% ሴቶች መሆን አለባቸው (የአመራር ቦታዎችን ጨምሮ) ፡፡

በእያንዳንዱ ዘርፍ ለሚቋቋመው ኢንተርፕራይዝ አባል ለመሆን የሚያስፈልጉት መስፈርቶች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡

ለሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ/የንግድ ስራ

▪ ከ 5 እስከ 7 የሚሆኑ ቢያንስ 45 ቀናት የተግባር የግንባታ ስልጠና የወሰዱና የስልጠና ብቃታቸው/ማስረጃቸው በሚመለከተው

የመንግስት አካል የተረጋገጠ የአካባቢ የግንባታ ባለሙያዎች/አርቴዢያንስ፡፡

ለሳኒቴሽን ግብይት እና ለውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ/የንግድ ስራ

▪ ከ 4 እስከ 6 የሚሆኑ ቢያንስ 45 ቀናት የተግባር የግንባታ ስልጠና የወሰዱና የስልጠና ብቃታቸው/ማስረጃቸው በሚመለከተው

የመንግስት አካል የተረጋገጠ የአካባቢ የግንባታ ባለሙያዎች/አርቴዢያንስ፡፡

▪ አንድ በ 10+1 እና ከዚያ በላይ በሆነ ደረጃ የተመረቀ ኤሌክትሮመካኒክ ባለሙያ

ለውሃ ተቋማት ግንባታ፣ ለሳኒቴሽን ግብይት እና ለውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ / የንግድ ስራ

▪ ከ 4 እስከ 6 የሚሆኑ ቢያንስ 45 ቀናት የተግባር የግንባታ ስልጠና የወሰዱና የስልጠና ብቃታቸው/ማስረጃቸው በሚመለከተው

የመንግስት አካል የተረጋገጠ የአካባቢ የግንባታ ባለሙያዎች/አርቴዣንስ፡፡

▪ አንድ በ 10+1 እና ከዚያ በላይ በሆነ ደረጃ የተመረቀ ኤሌክትሮመካኒክ ባለሙያ

ለውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ / የንግድ ስራ

▪ ከ 3 እስከ 5 የሚሆኑ በ 10+1 እና ከዚያ በላይ በሆነ ደረጃ የተመረቁ ኤሌክትሮመካኒኮች ወይም ኤሌክትሪሺያኖች

▪ 2 ቢያንስ 45 ቀናት የተግባር የግንባታ ስልጠና የወሰዱና የስልጠና ብቃታቸው/ማስረጃቸው በሚመለከተው የመንግስት አካል

የተረጋገጠ የአካባቢ የግንባታ ባለሙያዎች/አርቴዢያንስ፡፡

በሚቋቋሙ የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር የሚሰራ የመለዋወጫ አቅርቦት ቢዝነስ13/የንግድ ስራ

▪ የሂሳብ አያያዝ ልምድ ያለው ባለሙያ

▪ ስለመለዋወጫዎች ዓይነት ግንዛቤ ያለው፣ እንዲሁም ማንበብና መጻፍ የሚችል የሽያጭ ባለሙያ ናቸው፡፡

በኢንተርፕራይዞቹ አባላት መካከል የሚኖረው የስራ ድርሻ ለምሳሌ የሽያጭ ባለሙያ፣ መጋዘን ጠባቂ (አስፈላጊ ከሆነ) የመሳሰሉትን ጨምሮ

በአባላቱ የሚወሰን ሲሆን ይህም በኢንተርፕራይዞቹ መተዳደሪያ ደንብ ላይ መካተት ይኖርበታል፡፡

የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ/ የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና የስራ

እድል ፈጠራ ኤጀንሲ ከውሃ፣ ከጤና፣ ከሴቶችና ህጻናት ጉዳይ እንዲሁም ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር ስለ

ኢንተርፕራይዞቹ መቋቋም አስፈላጊነት የማስተዋወቅ ስራና አባላቱን የመለየት ስራ ይሰራሉ፡፡

13የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር የሙሉ ጊዜ ተቀጣሪ ሠራተኞች እንደሚኖራቸው ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የኢንተርፕራይዝ ሞዴል የግድ መከተል አይኖርባቸውም፡፡

Page 24: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

23

4.1.4 በሴቶች የሚመሩ ጥ. አ. ኢን ለማቋቋም የኢንተርፕሬነርስ/የስራ ፈጣሪዎች መምረጫ መስፈርቶች

• ሴቶች ከኢንተርፕራይዞቹ ጠቅላላ አባላት ውስጥ ቢያንስ 40% መሆን ይኖርባቸዋል፣ እንዲሁም ከአመራር ቦታዎች ውስጥ

የሰብሳቢነትና የገንዘብ ያዥነት ቦታዎችንም መያዝ አለባቸው፡፡

• በወረዳው የሚሰጥ የተለየ ምክንያት ከሌለ በስተቀር አዳዲሰ የሚመሰረቱ ኢንተርፕራይዞች አባላት ቁጥር ከ 5 እስከ 7 መሆን

አለበት፡፡

• ስራውን ለመስራት ብቁ ሆነው እስከተገኙ ድረስ አካል ጉዳተኞች የዚህ እድል ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

• በሳኒቴሽን ግብይት እና/ወይም በውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ ላይ ተሰማርተው ገቢ የማግኘት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን በውሃ፣ ንጽህናና

ሃይጅን ተቋማት ዘላቂነት ላይ አስተዋጽኦ በማድረግ የደንበኞቻቸው የኑሮ ሁኔት እንዲሻሻል ፍላጎት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

• ለቡድን ስራ / በጋራ ሰርቶ ለመለወጥ ጥሩ አመለካከት ያለው/ያላት (ከሌሎች የኢንተርፕራይዙ አባላት ጋር በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ

የሆነ/የሆነች)፣ እንደሁም ልዩነትን (ጾታን፣ አካል ጉዳተኝነትን፣ እድሜን፣ እና ሀይማኖትን) የሚቀበልና የሚያከብር /የምትቀበልና

የምታከብር መሆን አለበት/አለባት፡፡

• የጋራ እሴቶችን ለመገንባት ፍላጎት ያለው/ያላት፣ በቡድኑ አባላት ሊተገበሩ የሚገባቸውን ልዩ ልዩ ህጎችና ደንቦች የሚያከብርና ተገዢ

የሚሆን / የምታከብርና ተገዢ የምትሆን፡፡

• አዳዲስ የቢዝነስ አሰራር ዘዴዎችን ለማወቅ ፍላጎትና አቅም ያለው/ያላት፣እንዲሁም የቢዝነስ ክህሎትን የማበልጸግ፣ የቴክኖሎጂ

ሽግግር፣ ካይዘንን እና የንግድ ስራ ፈጠራ/ኢንተርፕሬነርሺፕ ስልጠናን ለመውሰድና ተግባራዊ ለማድረግ ፍላጎት ያለው/ያላት፡፡

• በአካባቢው ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ የኖረ /የኖረች፡፡

• የቡድኑን/የኢንተርፕራይዙን ንብረት ከብክነትና ከስርቆት ለመጠበቅ ቁርጠኛ የሆነ/ፍላጎት ያለው/ያላት፡፡

4.2 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም / ለማጠናከር፣ የትግበራ ምእራፍ

4.2.1 በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም/ማጠናከር

እንደየወረዳው ተጨባጭ ሁኔታ የሚመሰረት ሆኖ፣ በአንድ የሙከራ ወረዳ ከሁለት በላይ ኢንተርፕራይዞች መቋቋም አይችሉም፡፡ ኮዋሽ

በመለዋወጫ አቅርቦት ቢዝነስ/የንግድ ስራ ብቻ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም ድጋፍ እንደማደርግ ግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ

ወረዳ ላይ ሁለት ኢንተርፕራይዞች የሚቋቋሙ/የሚጠናከሩ ከሆነ “አንዱ የሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ላይ የሚሰማራ/የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ”

ሌላው ”የውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ ላይ የሚሰማራ/የተሰማራ ኢንተርፕራይዝ” የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በተቻለ መጠን ግን የሳኒቴሽን

ግብይትና የውሃ ተቋማት ጥገና ስራን ከውሃ ተቋማት ግንባታ ጋር አብሮ የሚሰራ ኢንተርፕራይዝ (ውሃ፣ ንጽህናና ሳኒቴሽንን በጥቅሉ እንደ

አንድ የቢዝነስ ዘርፍ የሚተገብር ኢንተርፕራይዝ) እንዲቋቋም ኮዋሽ ያበረታታል፡፡

በኮዋሽ ድጋፍ የሚቋቋሙትን የጥቃቅንና አነስተኛ አንተርፕራይዞች በተመለከተ እ.ኢ.አ ከሚያዝያ 25 እስከ ሚያዝያ 26/2009 ዓ. ም ድረስ

በአዲስ አበባ በተደረገው የእቅድ ዝግጅት ማጠቃለያ ስብሰባ ላይ ከተሳተፉ የክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ውይይት መሰረት

በየክልሉ ሊቋቋሙ የሚችሉት የኢንተርፕራይዝ ዓይነቶች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

ሠንጠረዥ 6፡ በእያንዳንዱ የኮዋሽ ክልል ሊቋቋሙ የሚችሉ የኢንተርፕራይዞች ዓይነት

ክልል መግለጫ

አማራ

አራት ወረዳዎች - በወረዳ አንድ ወይም ሁለት በሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ብቻ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ወይም የሳኒቴሽን ግብይትን ከውሃ ተቋማት ጥገናና ከመለዋጫ አቅርቦት ጋር አጣምረው የሚሰሩ

ኢንተርፕራይዞች (መለዋወጫዎች ከውሃ ጽ/ቤት ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ ከሆነ);

ወይም የሳኒቴሽን ግብይትንና የውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስን አጣምሮ የሚሰራ

ቤንሻንጉል ጉሙዝ

ሁለት ወረዳዎች - በወረዳ አንድ በውሃ ተቋማት ግንባታ፣ በሳኒቴሽን ግብይት እና በውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ

ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች፡፡

- ኮዋሽ በሁለቱ ወረዳዎች ውስጥ የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበራት በመለዋወጫ አቅርቦት ስራ እንዲሰማሩ

የሚያደርጉትን ጥረት ያግዛል፡፡

ኦሮሚያ አምስት ወረዳዎች - በወረዳ አንድ በሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ብቻ የሚሰማራ ኢንተርፕራይዝ ወይም የሳኒቴሽን ግብይትንና የውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስን አጣምሮ የሚሰራ ኢንተርፕራይዝ

Page 25: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

24

የደቡብ ብሔር፣

ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አምስት ወረዳዎች - በወረዳ አንድ በሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ብቻ የሚሰማራ ኢንተርፕራይዝ ወይም የሳኒቴሽን ግብይትንና የውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስን አጣምሮ የሚሰራ ኢንተርፕራይዝ

ትግራይ

ሁለት ወረዳዎች - በወረዳ ሁለት ኢንተርፕራይዞች፣ ይህም በሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ብቻ እና በውህ

ተቋማት ጥገና ቢዝነስ ብቻ የሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች(በሁለቱም ወረዳዎች በውሃ ተቋማት ጥገና የተቋቋሙ

ኢንተርፕራይዞች ስላሉ ኮዋሽ እነዚህን ኢንተርፕራይዞች ያጠናክራል)

አንድ ወረዳ- ሁለት በሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር

4.2.2 የኢንተርፕሬነርስን/የስራ ፈጣሪዎችን የአቅም ክፍተት መለየት

ከ5 እሰከ 7 የሚሆኑት የኢንተርፕራይዞቹ አባላት አንድ ዓይነት የቴክኒክና የስራ ፈጠራ ክህሎት እንደማይኖራቸው ይታመናል/ይታወቃል፡፡

ይህም የሚሆነው የተለያየ የትምህርት ዝግጅት/መስክ ስላላቸው ብቻ ሳይሆን ያላቸውንም እውቀት በተግባር ለመለወጥ የሚኖራቸው አጋጣሚ

የተለያየ ስለሚሆን ነው፡፡በዚህም ምክንያት የኢንተርፕራይዞቹ አባላት ያለባቸውን የቴክኒክና የስራ ፈጠራ ክህሎት ክፍተት የወረዳው

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ/ የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና የስራ እድል

ፈጠራ ኤጀንሲ ከወረዳው የውሃ እና የጤና ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር አሰሳ/ጥናት ማከናወን አለባቸው፡፡

እዝል 5፡ የኢንተርፕሬነርስን/የስራ ፈጣሪዎችን የአቅም ክፍተት መለያ ቅጽ

4.2.3 የኢንተርፕሬነርስን/የስራፈጣሪዎችን አቅም መገንባት

ሀ.ስልጠና - የኢንተርፕሬነርስን/የስራ ፈጣሪዎችን የአቅም ክፍተት/ውስንነት ለመለየት በተደረገው የአሰሳ/ጥናት ውጤት መሰረት በተገኘው

የቴክኒክና የስራ ፈጠራ ክህሎት ክፍተት መሰረት ኢንተርፕራይዞቹ ወደስራ ከመሰራማታቸው በፊት ለአባላቱ አስፈላጊው ስልጠና ሊሰጣቸው

ይገባል፡፡

ቴክኒካዊ ክህሎትን ማበልጸጊያ/ማሳደጊያ ስልጠና ፤በአሁኑ ወቅት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ በመሆን በየክልሉ በተመረጡ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ላይ ለሚሰማሩ የኢንተርፕራይዝ አባላት ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና መስጠት

እንዲችሉ ለተቋማቱ መምህራን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በኮዋሽ የሚቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች በእነዚህ በተመረጡ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና

ተቋማት ለ15 ቀናት ያህል በመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላብ አመራረት፣ በካይዘን፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በኢንተርፕሬነርሺፕ/በስራ ፈጠራ

የተግባር ስልጠና እንዲወስዱ ይጠበቃል፡፡

በውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ ላይ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ለዚሁ ተብሎ የሚዘጋጅ ስልጠና በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት (የወረዳ

ውሃ ጽ/ቤት ባለሙያዎችን በአሰልጣኝነት በመጋበዝ) ወይም በወረዳ/በዞን የውሃ ጽ/ቤቶች (የቴክኒክና ሙያማሰልጠኛ ተቋማትን መምህራን

በመጋበዝ) በእጅ ፓምፕ (ዩ-ሲል፣ ኦ-ሪንግ፣ ቦቢን፣ ሲሊንደር፣ ፒ.ቪ.ሲ ቧንቧ፣ ፕላንጀር፣ ሌሎች የፕምፑ አካላትን)፣ በምንጭ፣ በመለስተኛ

ጥልቅ ጉድጓዶች፣ ከምንጭ ወይም ከጥልቅ ጉድጓድ ለተዘረጉ የገጠር የውሃ ማከፋፈያ ስራዎች፣ ስለመስኖ ፓምፖች እና ሌሎች ተዛማጅ

ስራዎች የጥገና ስራ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለሚሰጡ ስልጠናዎች ሰልጣኞች በሰለጠኑበት መስክ የብቃት ማረጋገጫ/እውቅና እንዲያገኙ እንደሚያደርጉ

ይጠበቃል፡፡

የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና፤አግባብነት ያላቸው አካላት/ድርጅቶች (የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ወይም የጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት) ኢንተርፕሬነሮችን/የስራ ፈጣሪዎችን ስለ ቢዝነስ/የንግድ ስራ ክህሎት፣ ስለካይዘን፣ ስለተግባቦት እና ስለ ስራ

አመራር ስልጠና ይሰጣል፡፡ ከግብይት፣ ከሂሳብ አያያዝ እና ከፋይናንስ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በስራ ፈጠራ የስልጠና ክፍል/ምእራፍ

ውስጥ እንደሚካተቱ ይጠበቃል፡፡

ኮዋሽ የቢዝነስ ካንቫስ ሞዴል አዘገጃጀት የኢንተርፕሬነርሺፕ/የስራ ፈጠራ ስልጠና አካል በመሆን አንተርፕሬነሮች/የስራ ፈጣሪዎች ስልጠናውን

አንዲወስዱ ይፈልጋል፡፡ የቢዝነስ ካንቫስ ሜዴል 9 ብሎኮች/ክፍሎች ሲኖሩት ይህም ኢንተርፕራይዞች ቢዝነሳቸውን/የንግድ ስራቸውን እንዴት

ማካሄድ እና ዘላቂ/ትርፋማ ማድረግ እንደሚችሉ ይገልጻል፡፡ ሞዴሉ ለማንኛውም የቢዝነስ / የንግድ ስራ ዓይነት (ለጥቃቅንም ሆነ አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞች) ያገለግላል፡፡ ይህም የቢዝነስ አቅድ ከማዘጋጀት በፊት አስፈላጊ የሆኑ ሀሳቦችን ለማሰላሰልና ለማመንጨት ያገለግላል፡፡ ስለ

ቢዝነስ ካንቫስ ሜዴል ተጨማሪ መረጃና የሞዴሉ ፎርማት በዚህ መመሪያ በእዝል መልክ ተያይዟል፡፡

Page 26: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

25

እዝል 6፡ የንግድ ስራ ንድፍ ማዘጋጃ ሞዴል ማብራሪያና ቅጽ

የኢንተርፕሬነርሺፕ/የስራ ፈጠራ ስልጠናው አካል በመሆን ኢንተርፕሬነርስ/ስራ ፈጣሪዎች ቢዝነሳቸውን/የንግድ ስራቸውን ሊያጋጥሙ

የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ማወቅ ያስፈልጋል (አንድ አደጋ/እክል ሊከሰት የሚችልበትን እድል ማስላትና ይህ ክስተት በቢዝነሱ/በንግድ

ስራው ላይ ምን ያህል ተጽእኖ እንደሚኖረው መገመት)፣ አደጋዎቹ እንዳይከሰቱ ወይም ከተከሰቱ በቢዝነሱ/በንግድ ስራው ላይ የሚኖረውን

ተጽእኖ መቀነስ እንዲቻል የአደጋ መቋቋሚያ/መቀነሻ እቅድ ያስፈልጋል፡፡ የአደጋ አሰሳው/ልየታው ቢዝነስ ካንቫስሞዴል ላይ ላሉት 9ኙም

ብሎኮች/ክፍሎች ላይ መስራት ይቻላል (አደጋ አሰሳ/ልየታ ማድረግ)፣ ተጽእኖአቸውን መገመት (አደጋዎቹን በደረጃ ማስቀመጥ)፣ ምላሾችን

መግለጽ (የአደጋ መቋቋሚያ ዘዴዎችን ማስቀመጥ)፡፡ ሰፋ ባለ መልኩ ስናየው በ 9ኙ ብሎኮች/ክፍሎች ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉት

አደጋዎችን በሶስት ዋና ዋና የአደጋ አይነቶች ማጠቃለል ይቻላል፡፡ እነሱም (1)ስትራቴጂካዊ/ስልታዊ አደጋዎች፣ (2) ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ

አደጋዎች፣ እና (3) ከገበያ ጋር የተያያዙ አደጋዎች ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ ዋና ዋና የአደጋ ዓይነቶች ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎች ዝርዝር

እና አደጋዎቹን ለመቋቋም መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ለመነሻነት በሚሆን መልኩ እንዲሁም እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ

እንደተጨባጭ ሁኔታው ማሻሻያ እንዲያደርግበት በዚህ መመሪያ ላይ በእዝል ተያይዟል፡፡

እዝል 7፡ የቢዝነስ ተግዳሮትን ለመለየት እና መፍትሔውን ለማቀድ የሚረዳ አጋዥ ናሙና

የቢዝነስ እቅድ አዘገጃጃት-የቢዝነስ ክህሎትን ማበልጸጊያ/ማሳደጊያ ስልጠናው ከመጠናቀቁ በፊት ሰልጣኞች በቢዝነስ ካንቫስ ሞዴል ዝግጅት

እና የቢዝነስ አደጋዎች ትንተና ወቅት ያገኟቸውን/የሰሩባቸውን መረጃዎች በመጠቀም የቢዝነስ እቅድ ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ በዚህ መመሪያ

ላይ ሁለት የቢዝነስ አቅድ ማዘጋጃ ፎርሞች ተካተዋል፡፡ አንዱ የዓለም ባንክ ለክልልና ለተመረጡ ወረዳዎች የሳኒቴሽን ግብይት ስልጠና

በሰጠበት ወቅት ከተጠቀመበት ሞዴል ሲሆን ሌላው ደግሞ ከአማራ ክልል የቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ የተወሰደ ነው፡፡

ኢንተርፕራዞቹ ከሁለቱ አንዱን ፎርም በመጠቀም የቢዝነስ እቅዳቸውን ያዘጋጃሉ፡፡

እዝል 8 - የቢዝነስ /የንግድ ስራ እቅድ ለማዘጋጀት የሚረዱ ዋና ዋና ርእሶች

ለ.የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎችን ማመቻቸት/ማቅረብ፤የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ለተቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች

የማምረቻና የመሸጫ ቦታ የማመቻቸት ሃላፊነት አለበት፡፡በዚህም ምክንያት በሙከራነት በተመረጡት ወረዳዎች ለሚቋቋሙት የሳኒቴሽን

ግብይት ቢዝነስ/የንግድ ስራ ብቻ ወይም የሳኒቴሽን ግብይትና የውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ/የንግድ ስራ አጣምረው ለሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች

ለስራዎቹ ተስማሚ የሆነ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ እንዲኖራቸው መደረግ አለበት፡፡

በተመረጡት የሙከራ ወረዳዎች ውስጥ ለሚቋቋሙት ኢንተርፕራይዞች አመቺ የሆነ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ማግኘት ካልተቻለ የሳኒቴሽን

ግብይት ቢዝነስን ብቻ ወይም የሳኒቴሽን ግብይትና የውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስን አጣምረው ለሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች ለማምረቻና ለመሸጫ

ቦታ የሚያገልግል የሼድ ግንባታ በጀት በኮዋሽ የሚሸፈን ሲሆን ለዚህም እንዲያግዝ ኮዋሽ የሼድ ዲዛይን፣ የግንባታ ስራ ዝርዝርና የግንባታ ዋጋ

ግምት አዘጋጅቶ በዚህ መመሪያ ላይ ተያይዟል፡፡ የወረዳው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ ሙያና

ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት ከወረዳው የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የግንባታ

ቁሳቁሶችን በመግዛትና በግንባታ የስራ ልምድ ላላቸው ኢንተርፕራይዞች፣ የግል ተቋራጮች ወይም አርቴዢያኖች የጉልበት ዋጋ ውል ብቻ

በመስጠት የሼዶቹ ግንባታ ይከናወናል፡፡ የሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስን ብቻ ወይም የሳኒቴሽን ግብይትና የውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስን

አጣምረው ለሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች ለማምረቻና ለመሸጫ የሚያገልግል የሼድ ዲዛይን፣ የግንባታ ስራ ዝርዝርና የግንባታ ዋጋ ግምት

ተዘጋጅቶ በዚህ መመሪያ ላይ በእዝል ተያይዟል፡፡

እዝል 9 - የሼድ ዲዛይን፣ የግንባታ ስራ ዝርዝርና የግንባታ ዋጋ ግምት

በሚደራጁት ኢንተርፕራይዞችና በወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/ የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት

ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና የስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲመካከል ስለሼዶች አጠቃቀም ፣ ለምንያህል ጊዜ መጠቀም እንደሚችሉና

ለሚመለከተው አካል መቼ ማስረከብ እንዳለባቸው የሚገልጽ የጽሁፍ ውል ስምምነት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲና

ስትራቴጂ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው (እ.ኤ.አ ማርች 12 ተዘጋጅቶ ኤፕሪል 2016 በተከለሰው) መሰረት ተግባራዊ መደረግ አለበት፡፡

10 -በወረዳ ጥ.አ. ኢ. ልማት ጽ/ቤት/ቴ.ሙ. ኢ ልማት ጽ/ቤት/ከ.ም.ዋ እና ስ.እ. ፈ ኤጀንሲእና በሚደራጁት ኢንተርፕራይዞች መካከል የሚፈረም

የመግባቢያ ሰነድ ናሙና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በተመለከተ ኮዋሽ በውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር ለሚቀርቡ የመለዋወጫ እቃዎች ማከማቻ የሚውል የመጋዘን

ግንባታ በጀትን ይሸፍናል፡፡ የመጋዘኑ ዲዛይን በክልሉ የውሃ ቢሮ የሚወሰን ሁኖ ለመነሻነት የሚያገለግል ዲዛይን በዚህ መመሪያ ላይ በእዝል

ተያይዟል፡፡

እዝል 11 -የመለዋወጫ እቃ ማከማቻ መጋዘን ዲዛይን፣ የግንባታ ስራ ዝርዝርና የግንባታ ዋጋ ግምት

Page 27: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

26

በውሃ ተቋማት ጥገና ስራ ላይ ብቻ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና

ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት (ወይም የወረዳው የውሃ ጽ/ቤት ለተወሰነ ጊዜ) ለጽ/ቤት

አገልግሎት የሚውል ክፍል ለኢንተርፕራይዞቹ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡

ሠንጠረዥ 7፡ በተመረጡ የሙከራ ወረዳ የሚገነቡ ሼዶች (የማምረቻና መሸጫ ማእከላት) ብዛት

ክልሎች የሙከራ ወረዳዎች በሳኒቴሽን ግብይት ብቻ ወይም በሳኒቴሽን

ግብይት እና በውሃ ተቋማት ጥገና ለተሰማሩ

ኢንተርፕራይዞች የሚያገለግል ሼድ ብዛት

የመለዋወጫ

ማከማቻ መጋዘን

ብዛት

አማራ

ጓጉሳ ሽኩዳድ14 1

አንከሻ 1

ባሶና ወራና 2

አንጾኪያ ገምዛ 1

ቤንሻንጉል ጉሙዝ

ባምባሲ 1 1

ኦዳ 1 1

ኦሮሚያ

ቀርሳ 1

ጉማይ 1

ኖኖ ቤንጃ 1

አቢቹ ኛአ 1

ጂዳ 1

የደቡብ ብሔር፣

ብሔረሰቦችና ሕዝቦች

ክልል

አርባ ምንጭ ዙሪያ 1

ዱና 1

አርቤጎና 1

ኢሳራ 1

ቶጫ 1

ትግራይ

መደባይ ዛና 1

ታህታይ ማይጨው 1

እንዳመሆኒ 1

ጠቅላላድምር 20 + 115

ሐ. የመነሻ/የስራ ማስጀመሪያ ካፒታል (ቢዝነሱን ማስጀመሪያ የሚሆን በጀት ማዘጋጀት)- የስራ መጀመሪያ ካፒታል እጦት አዲስ የተቋቋሙ

ኢንተርፕራይዞች ከሚገጥማቸው ችግር መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኮዋሽ ለኢንተርፕራይዞቹ የሚሰጥ ምንም

ዓይነት ጥሬ ገንዘብ አይኖርም፡፡ ነገር ግን ኢንተርፕሬነሮቹ/የስራ ፈጣሪዎቹ ለስራ መጀመሪያ የሚሆን ምንም ሀብት/ካፒታል ከሌላቸው

የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ

ፈጠራ ጽ/ቤት ለመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላብ ማምረቻ የሚሆኑ ጥሬ እቃዎች፣ ለእጅ/ለገላ መታጠቢያ የሚሆኑ ፎሴት የተገጠመላቸውን

ጀሪካኖች (በኮዋሽ በተዘጋጀው ዝርዝር መሰረት) እና የእጅ መሳሪያዎችን በመግዛት ለኢንተርራይዞቹ በህጋዊ መንገድ ያስረክባል፡፡ ንብረቶቹን

የገዛውና ለኢንተርፕራይዞቹ ያስረከበው አካል፣ የተገዙትን ንብረቶች ከነነጠላ ዋጋቸው እንዲሁም የኢንተርፕራይዙ ሰብሳቢ ንብረቶችን

መረከቡን የሚያረጋግጥና በሰብሳቢዋ የተፈረመ ሰነድ ማስቀመጥ አለበት፡፡ የንብረት ርክክብ ሰነዱ ቅጅ በኢንተርፕራይዙ ፀሃፊ እጅ መቀመጥ

አለበት፡፡ ኢንተርፕሬነሮቹ የተገዙትን ንብረቶች ከተረከቡ በኋላ፣ ንብረቶቹ የተገዙበትን ዋጋ ለመመለስ በኢንተርፕራይዙ ስም ዝግ

አካውንት/የባንክ ሂሳብ ቁጥር በብድርና ቁጠባ ተቋም ላይ በመክፈት ክፍያውን መፈጸም የሚኖርባቸው ሲሆን በዚህ መልክ የተጠራቀመውን

ገንዘብ ለኢንተርፕራይዙ ከብርድና ቁጠባ ተቋም ብድር ለመውሰድ ይጠቀሙበታል፡፡ ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆኑ ንብረቶችን ለመግዛት

14ወረዳው በእጁ ያሉ መለዋጫዎችን ለሚቋቋሙት ኢንተርፕራይዞች የሚያስረክብ ከሆነ የሼዱ ዱዛይን መለዋወጫዎችን ለማከማቸት በሚያስችል መልኩ ሊሻሻል ይችላል፡፡ 15በእንከሻ ወይም በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ አንድ ተጨማሪ ሼድ ይገነባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እንደሚኖረው በጀት ሁኔታ የታቀዱትን ኢንትርፕራይዞች ቁጥር ለመጠበቅ በአማራ ክልል አንድ ወረዳ ሊጨመር ይችላል፡፡

Page 28: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

27

የሚስፈልገው ገንዘብ በኮዋሽ ይመደባል፡፡ የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ

ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት ኢንተርፕራይዞቹ ብድር ማግኘት እንዲችሉ ከብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር

ያገናኟቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ

ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት በሳኒቴሽን ግብይት ብቻ ወይም በውሃ ተቋማት ጥገና ብቻ ወይም በሳኒቴሽን ግብይት እና በውሃ ተቋማት

ጥገና ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች/ስራ ፈጣሪዎች የሚያገልግሉትን መሳሪያዎች (ኮዋሽ ባስቀመጠው ዝርዝር መሰረት) እና በኢንተርፕራይዞቹ

ፍላጎት መሰረት ግዢውን ያከናውናሉ፡፡ አንዳንድ የእጅ/የግንባታ መሳሪያዎች በቶሎ የሚጎዱና ሊሰበሩ የሚችሉ ከመሆናቸው አንጻር የእነዚህ

መሳሪያዎችን የግዥ ወጪ ኢንተርፕራይዞቹ ተመላሽ እንዲያደርጉ/እንዲከፍሉ አይጠበቅም፡፡በውሃ ተቋማት ጥገና ብቻ ወይም በሳኒቴሽን

ግብይት እና በውሃ ተቋማት ጥገና የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች/ስራ ፈጣሪዎች የተረከቧቸውን የጥገና መሳሪያዎች ወጪ (እንደ ትራይፖድ፣

የቧንቧ ጥርስ ማውጫ፣ የቧንቧ መቁረጫ የመሳሰሉትን) ልክ በሳኒቴሽን ግብይት እንደተሰማሩት ኢንተርፕራይዞች ንብረቶቹ የተገዙበትን ዋጋ

በመመለስ በኢንተርፕራይዙ ስም በሚከፈት ዝግ አካውንት/የባንክ ሂሳብ ቁጥር በብድርና ቁጠባ ተቋም ላይ በመክፈት ክፍያውን እየፈጸሙ

የተጠራቀመውን ገንዘብ ለኢንተርፕራይዙ ከብርድና ቁጠባ ተቋም ብድር ለመውሰድ ይጠቀሙበታል፡፡ በተመሳሳይ የወረዳው የጥቃቅንና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት

ኢንተርፕራይዞቹ ብድር ማግኘት እንዲችሉ ከብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር ያገናኟቸዋል፡፡

በስራ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የሚጠቅሙ መሳሪያዎች ለምሳሌ እንደ ጓንት፣ ቱታ፣ ሄልሜት/ባርኔጣ የመሳሰሉትን

ኢንተርፕራይዞቹ በራሳቸው ወጪ መግዛት አለባቸው፡፡

በሳኒቴሽን ግብይት እና በውሃ ተቋማት ጥገና ቢዝነስ ላይ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጉ የግንባታ መሳሪያዎች፣ ጥሬ እቃዎች እና

ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ዝርዝር በዚህ መመሪያ በእዝል መልክ ተያይዟል፡፡

እዝል 12: በሳኒቴሽን ግብይት ብቻ እንዲሁም የሳኒቴሽን ግብይትና የውሃ ተቋማት ጥገናን በጣምራ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጉ

የግንባታ መሳሪያዎች እና ጥሬ እቃዎች ዝርዝር

4.2.4 ማምረት / የምርት ሥራ

ኢንተርፕሬነሮቹ/ስራ ፈጣሪዎቹ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉላቸው (አስፈላጊውን ስልጠና ከወሰዱ፣ የቢዝነስ እቅድ ካዘጋጁ፣

የማምረቻ ቦታ ከተረከቡ እና ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን ካገኙ) ወደስራ ሊሰማሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ወቅት የወረዳው የጥቃቅንና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት፣

እንዲሁም የወረዳው የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እና የውሃ ጽ/ቤት የቅርብ ክትትል ሊያደርጉላቸው ይገባል፡፡ በሳኒቴሽን ግብይት ኢንተርፕራይዞች

የሚመረቱ ምርቶችና የሚሰጡ አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስ ምርቶች

• የተለያየ መጠን ያሏቸው ከኮንክሪት የተሰሩ መጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላብ

• የተለያየ መጠን ያሏቸው ፎሴት የተገጠመላቸው ለእጅ መታጠቢያ/ለገላ መታጠቢያ የሚሆኑ ውሃ የሚይዙ ጀሪካኖች

ከሳኒቴሽን ግብይት ጋር የተያያዙ ሌሎች ደጋፊ ተግባራት

• የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቦችን ማጓጓዝ (በሌላ አካል እንዲጓጓዝ መዋዋል አንዱ አማራጭ ነው)

• የመጸዳጃ ቤት ጉድጓድ መቆፈር

• የስላብ ማጽጃ ማቴሪያሎች (ለምሳሌ መጥረጊያ፣ መወልወያ)

• የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቦችን ማስቀመጥ

• መጸዳጃ ቤቶችን መጠገን

• መጸዳጃ ቤቶች ጉድጓድ ውስጥ ያለውን አይነምድር ማውጣት/ማስወገድ (በተለይ ለማዳበሪያነት አገልግሎት ሊውል ሲፈለግ)

• ለገላ መታጠቢያ የሚሆኑ እቃዎችን መግጠም እና የባዮ ጋዝ ፕላንት ግንባታ ማከናወን

• በቤት ውስጥ ለውሃ ማከሚያ የሚያስፈልጉ ኬሚካሎችን ማቅረብ

• አንዳንድ ለንጽህና መጠበቂያ የሚያስፈልጉ እቃዎችን መሸጥ (ሳሙናና ኦሞ፣ የወር አበባ መቀበያ ፓድ፣ የመጸዳጃ ቤት ወረቀት ወዘተ….)

Page 29: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

28

ለሳኒቴሽን ግብይት ስራዎች ቀጣይነትና ዘላቂነት ኢንተርፕራይዞቹ ቢዝነሱን በሚያከናውኑበት ወቅት የሳኒቴሽን የአቅርቦት ሰንሰለት የተጠበቀ

/ቀጣይነት ያለው መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለማገናዘብ ይረዳ ዘንድ የሳኒቴሽን የግብይት ሰንሰለት በዚህ መመሪያ ላይ

በእዝል መልክ ተያይዟል፡፡

እዝል 13፡ የሳኒቴሽን አቅርቦት ሰንሰለታዊ ትስስር

የእጅ ጉድጓድ/ፓምፕ(ዩ-ሲል፣ ኦ-ሪንግ፣ ቦቢን፣ ሲሊንደር፣ ፒ.ቪ.ሲ ቧንቧ፣ ፕላንጀር፣ ሌሎች የፓምፑ አካላት)፣ የምንጮች፣ የመለስተኛ ጥልቅ

ጉድጓዶች፣ ከምንጭ ወይም ከጥልቅ ጉድጓድ የተዘረጉ የገጠር የውሃ ማከፋፈያ ስራዎች፣ የመስኖ ቦዮች፣ የውሃ መምጠጫ ፓምፖች፣ ፎሴቶች፣

ጌት ቨልቮች፣ ቧንቧዎችና መገጣጠሚያዎች የመሳሰሉት ጥገናዎች በውሃ ተቋማት ጥገና በተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የሚሰሩ ናቸው፡፡

• መከላከል ጥገና ማከናወን

የመከላከል ጥገና የሚያካትታቸው የታቀዱና በየተወሰነ ቋሚ ጊዜ የውሃ ተቋማት አካላትን በመፈተሸና በመጠገን የውሀ ተቋሙ በጥሩ ሁኔታ

እንዲጠበቅና አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ ይህም የጥገና ዓይነት የሚያካትተው የውሃ መስመሮችን መፈተሽ፣ የውሃውን ፍሰት መጠን

ማየት፣ አንዳንድ መካኒካል የሆኑ የውሃ ተቋሙ አካላትን ማጽዳት፣ ቅባቶችን መቀባባትና የመለወጫ ጊዜያቸው የደረሱትን አካላት መለወጥን

ያካትታል፡፡ አንዳንዴም አንዳንድ በአጠቃቀም ወይም በአያያዝ ወቅት የተጎዱና የጎደሉ አካላትን የመጠገንና የመለወጥ ስራን ያካትታል ለምሳሌ

የፓምፕ እጄታ ቡሎኖችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአግባቡና በወቅቱ ከተከናወነ የመከላከል ጥገና በውሃ ተቋሙ ላይ ሊከናወኑ የሚችሉ ከፍተኛ

ወጪ የሚጠይቁ ጥገናዎችን በጣም ይቀንሳል፡፡ በቀላል አባባል የእጅ ፓምፕን በተመለከተ የመከላከል ጥገና ማለት በቶሎ አላቂ የሆኑ አራቱ

የፓምፕ አካላትን (ዩ-ሲል፣ ኦ-ሪንግ፣ ቦቢንና ቡሽ ቤሪንግ) ተበልተው የውሃ ተቋሙ አገልግሎት መስጠት ከማቆሙ ወይም አገልግሎት

የመስጠት ሁኔታው ከመቀነሱ በፊት የፓምፕ አምራቾች ባስቀመጡት የመቀየሪያ ወቅቶች/ጊዜያት ውስጥ የመለወጥ ስራ ነው፡፡ በዋነኛነት

የመከላከል ጥገና ስራ የህብረተሰቡ ሃላፊነት ሆኖ ይህም የሚከናወነው ከውሃ ተጠቃሚዎች ውስጥ በሚሰለጥኑ የፓምፕ ተንከባካቢዎች እና

ጠጋኞች ነው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያች የሰለጠኑት የፓምፕ ተንከባካቢዎች እና ጠጋኞች ጥገናውን ማከናወን ካልቻሉ በጥገና ስራ

የተሰማሩት የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጥገናውን በክፍያ ሊያከናኑ ይችላሉ፡፡

• የብልሽት ማስተካከያ ጥገና ማከናወን

ይህ ጥገና በተለያዩ ጽሁፎች የተለያየ መጠሪያዎች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ያልታቀደ ጥገና ወይም የድንገተኛ ጥገና የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ይህ ጥገና የተለያዩ የውሃ ተቋሙ አካላት ሲሰበሩ ወይም አገልግሎት መስጠት ሲያቆሙ አካላቶቹን በመጠገን ወይም በመለወጥ የውሃ ተቋሙ

አገልግሎት መስጠት እንዲችል/ወደአገልግሎት እንዲመለስ የሚደረግ የጥገና ዓይነት ነው፡፡ ብዙውንጊዜ ይህ ዓይነት ጥገና እንዲከናወን

የሚፈጥሩት ሁኔታዎች የመከላከል ጥገና በወቅቱ አለመከናወን፣ በአንዳንድ አደጋና ተፈጥሮአዊ በሆኑ ክስተቶች በውሃ ተቋሙ ላይ በሚደርሱ

ጉዳቶች እንዲሁም አካላቶቹ በማርጀታቸው የተነሳ የሚከሰቱ ሁኔታዎች ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ጥገና በሰለጠኑ የፓምፕ ተንከባካቢዎች ወይም

ጠጋኞች ለመከናወን ስለማይቻል/ስለሚያስቸግር ጥገናው መከናወን ያለበት በውሃ ጥገና ስራ ላይ በተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ

ኢንተርፕራይዞች ነው፡፡

የእጅ ፓምፕን በተመለከተ ይህ ጥገና ፓምፑን ከጉድጓድ ወስጥ አውጥቶ መጠገንን ያካትታል፡፡

4.2.5 የገበያ ስትራቴጂ/ስልት ስለመጠቀም

የውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ስራዎችን በቢዝነስ መልክ በኢንተርፕሬነሮች ማከናወን ገና በመጀመር ላይ ያለ ተግባር በመሆኑ የተለያዩ አጋራት

ቅንጅት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ቅንጅቱም የሚከተሉትን ተግባራት ለማከናወን ይረዳል፡፡

- የሳኒቴሽን ግብይት ቢዝነስን በጤና ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ (ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ሆስፒታሎች) የጤና ሴክተሩ ሰራተኞችና

ኢንተርፕሬነሮቹ በመቀናጀት ለማህበረሰቡ ማስተዋወቅ ይኖርባቸዋል፡፡በጤና ተቋማት አካባቢ ለህክምና የሚመጡ ህመምተኞችና እነሱን

ለማገዝ ለሚመጡ አስታማሚዎች የጤና ትምህርት የመስጠት ልምድ አለ፡፡ ይህም ለማህበረሰቡ ስለግል ንጽህናና የአካባቢ ጤና ጉዳዮች፣

እንዲሁም በውሃ፣ንጽህናና ሃይጅን ዘርፍ ስለ ተሰማሩት ኢንተርፕራይዞች ምርቶችና አገልግሎቶች (ደጋፊ ተግባራት) ለማስተዋወቅ ጥሩ

አጋጣሚ ይሆናል፡፡

Page 30: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

29

- የጤና ተቋማት እና የአካባቢው የገበያ ቦታዎች ቋሚ የመሸጫ ቦታዎች በመሆን ሲያገለግሉ ኤግዚቢሽኖች፣ የንግድ ትርኢቶች፣ ልዩ ልዩ

ህብረተሰቡ በመሰባሰብ የሚወያይባቸው የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረኮች ለምሳሌ ዓለም አቀፍ የመጸዳጃ ቀን፣ ዓለም አቀፍ የውሃ ቀን፣ ዓለም

አቀፍ የሴቶች ቀን የመሳሰሉትን አጋጣሚዎች መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

- የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎቸ፣ የጤና ሰራዊት እና የቀበሌ መስተዳድር በመቀናጀት ማህበረሰቡን የግል ንጽህናና የአካባቢ ጤና ጉዳዮች

ላይ ግንዛቤውን በማሳደግ የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ለመስራት የሚያስፈልገውን የመቀመጫ ስላብ የመጠቀም ፍላጎት እንዲኖረው ማድረግ

አለባቸው፡፡በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው ልምድ እንደሚያሳየው የቀበሌ መስተዳድሮች ፍላጎት ካላቸው ቤተሰቦች ገንዘብ በማሰባሰብና

ለኢንተርፕራይዞቹ በመክፈል የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቦችን እንዲያመርቱና እንዲያሰራጩ ያደርጋሉ፡፡ የወረዳው ካቢኔም በበኩሉ

አብዛኛውን ቤተሰብ የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆን ያደረጉ የቀበሌ መስተዳድሮችን በመለየት፣ እንዲሸለሙ/እውቅና እንዲያገኙ

በማድረግ ማበረታታትና ሌሎች የመስተዳድር አባላትም ይህንኑ ፈለግ እንዲከተሉ ማድረግ አለባቸው፡፡

- የኢንተርፕራይዞቹን የተለያዩ ምርቶች በማምረቻ ቦታው /ሼድ/ የውጭ ግድግዳ ላይ በመሳል ገላጭ በሆነ መልኩ ምርቶቹን ማስተዋወቅ፣

- በየአካባቢው ቋንቋ በራሪ ጽሁፎችን በማዘጋጀት ለተለያዩ ተቋማት በማሰራጨት (ለትምህርት ቤቶች፣ ለጤና ተቋማት፣ ለቤተክርስቲያኖች

እና መስጊዶች) የኢንተርፕራይዞቹን ምርቶችና አገልግሎቶች (ደጋፊ ተግባራት) ለማህበረሰቡ እንዲያስተዋወቁ ማድረግ፣

- የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቦችን በአንድ ቦታ በማምረት ተጠቃሚዎች እየመጡ እንዲገዙ ከማድረግ በተጨማሪ ኢንተርፕራይዞቹ ወደአንድ

መንደር በመንቀሳቀስና በአካባቢው የማይገኙ የግንባታ ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ ቁጥራቸው በርከት ላሉ ቤተሰቦች በመኖሪያ መንደራቸው

አካባቢ እንዲመረት ማድረግ ይችላሉ፡፡በዚህ አሰራር ወቅት ሞዴል/ምሳሌ የሚሆን አንድ ቤተሰብ የመፍጠር አሰራርን ከመከተል ይልቅ

ሞዴል/ምሳሌ የሚሆን መንደርን የመፍጠር አሰራርን ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

- የጥገና አገልግሎት ሰጪ ኢንተርፕሬነሮችን በተመለከተ የወረዳው የውሃ ጽ/ቤት ከቀበሌ መስተዳድር ጋር በመሆን አገልግሎት ሰጪዎችን

ከውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ኮሚቴዎችጋር ማገናኘት አለባቸው፡፡ የኒዘርላንድስ ተራድኦ ድርጅት /SNV/ በትግራይ ክልል ያለው ልምድ

እንደሚያሳየው ኢንተርፕሬነሮቹ በየወረዳው ያሉትን የውሃ ተቋማት ዝርዝር ከነዋና ዋና መረጃዎች ጋር (የውሃ ተቋሙ ዓይነት፣ የሚገኝበት

ቦታ፣የተጠቃሚው ህዝብ ብዛት፣ ግንባታው የተጠናቀቀበት ቀን ወዘተ...) ሲይዙ የእያንዳንዱ ውሃ ተቋም ኮሚቴ አባላት ደግሞ ችግር ሲኖር

መደወል እንዲችሉ የኢንተርፕሬነሮቹ ስልክ ቁጥር አላቸው፡፡ ኢንተርፕሬነሮቹ ጥራታቸውን የጠበቁና ተቀባይነት ባለው ዋጋ

የሚያስፈልጋቸውን የመለዋወጫ እቃ የትና እንዴት እንደሚያገኙ ማወቅ አለባቸው፡፡ የመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ ከጊዜ ወደጊዜ ስለሚለዋወጥ

ኢንተርፕሬነሮቹ ከውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ኮሚቴዎችጋር መደራደር እንዲችሉ ወቅታዊ ዋጋዎችን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ መለዋወጫዎችን

የመቀየሪያና የጥገና ማከናወኛ የጉልበት/የባለሙያ ዋጋ ግን የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር16የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን

በውሃ ስራ ለማሰማራት ባወጣው ማንዋል መሰረት በውሃ ጽ/ቤቱ የሚወሰን ነው፡፡

በተጨማሪም የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ወይም የውሃ አገልግሎት ከውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ኮሚቴዎች ጋር በመሆን የፓምፕ

ተንከባካቢዎች/ጠጋኞች የውሃ ተቋማቱን የመከላከል ጥገና እንዲያከናውኑ ማበረታታት አለባቸው፡፡ አንዳንዴ ጥገናዎቹ ከጠጋኞቹ አቅም

በላይ ከሆኑ ኢንተርፕራይዞቹ የመከላከል ጥገናውን ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡ ጎን ለጎን የውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ኮሚቴዎች ተጠቃሚው

ማህበረሰብ ለጥገናና ለመለዋወጫ ግዢ እንዲውል የውሃ ተጠቃሚዎችን ክፍያ በተከታታይ/በቋሚነት እንዲከፍሉ ማድረግና መሰብሰብ

አለባቸው፡፡ የውሃ ጽ/ቤት ባለሙያዎች በውሃ ተቋማት ጥገና የመሰማራት ሁኔታ በጣም ውስን መሆንና ይልቁንም ጥገናዎች በኢንተፕራይዞቹ

እንዲሰሩ ማድረግ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የውሃ ጽ/ቤት ባለሙያዎች የመንግስት ተቀጣሪና ደሞዝተኞች ናቸው በሚል ምክንያት/ሀሳብ

ለሚሰጡት የጥገና አገልግሎት የውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ኮሚቴዎች ክፍያ ስለማይፈጽሙ ከውሃ ተጠቃሚዎች በየወቅቱ ሊሰበሰብ

የሚገባውን ክፍያ ላይሰበስቡ ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ከማህበረሰቡ የሚሰበሰበውን ገንዘብ ከብክነት ለመከላከል የውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን

ኮሚቴዎች እና ኢንተርፕሬነሮቹ ለጥገና በሚደራደሩበት/በሚስማሙበት ወቅት የቀበሌው መስተዳድር ቢገኝ ተመራጭ ነው፡፡

- ደንበኞችን ለመሳብ ኢንተርፕራይዞቹ የምርቶቻቸውን እና የአገልግሎቶቻቸውን ዋጋ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስላት እና መወሰን

አለባቸው፡፡ ይህንንም ለደንበኞቻቸው / ለተጠቃሚዎች ማስተዋወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

- በቤተሰብ ደረጃ የመጻዳጃ ቤት መቀመጫ ስላብ አንድ ጊዜ ከተገዛ እንደገና የመገዛት እድሉ በጣም አናሳ ቢሆንም ኢንተርፕራይዞች

ስለምርቶቻቸው ጥራት ከተጠቃሚው ማህበረሰብ አስተያየት መስብሰብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ይሁን እንጂ የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙ

ቤተሰቦች ጋር በእንግድነት የሚመጡ ግለሰቦች ወደየአካባቢያቸው በሚመለሱበት ወቅት ያዩትን ነገር በአካባቢያቸው ሊያስተዋውቁ

ስለሚችሉ በየቀበሌው የሚኖሩ የተለያዩ ቤተሰቦች የተሻሻለ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቡን ሊገዙ ይችላሉ፡፡

16የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በውሃ ተቋማት ግንባታ እና ጥገና ስራ ላይ ለማሰማራት እና የግንባታና ጥገና ቁርጥ ዋጋ አዘገጃጃት ማንዋል

Page 31: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

30

በኮዋሽ ድጋፍ የሚደራጁና የሚጠናከሩ በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሞዴል በዚህ መመሪያ በእዝል መልክ

ተያይዟል፡፡

እዝል 14፡ በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የማደራጃ ሞዴል

4.2.6 የጥቃቅና እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ፈቃድ አሰጣጥ

በመንግስት ፖሊሲ መሰረት ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ በሆነ መንገድ ስራዎችን እንዲሰሩ ምዝገባ ማከናወን እና ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በኮዋሽ የሚቋቋሙት የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሚመለከተው አካል አስፈላጊዉን ምዝገባ ማከናወን እና

ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፡፡በዚህ ሂደት ውስጥ የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና

ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት ለኢንተርፕራይዞቹ ድጋፍ ሊሰጧቸው ይገባል፡፡

4.3 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም / ለማጠናከር፤የክትትል፣ የኦዲት እና ሪፖርት ማቅረቢያ ምእራፍ

ክትትል እና ኦዲት -የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚገጥማቸውን ችግሮች በወቅቱ መፍታት እንዲቻል የወረዳው የጥቃቅን እና

አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/ቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/ከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት ከሌሎች

ሴክተሮች ጋር በመተባበር የቅርብ ክትትልና እገዛ ማድረግ አለባቸው፡፡ እንደየወረዳው ሊኖር እንደሚችለው የጋራ መድረክ የሚወሰን ሆኖ

እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ በየሩብ ዓመቱ የክንውን ዘገባ ለጋራ መድረኩ ወይም ለወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት

ኤጀንሲ/ለቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/ለከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኦዲት በወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና

ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት በወቅቱ መከናወን አለበት፡፡ በሚገኘው የኦዲት ውጤት መሰረት

የእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ የቢዝነስ እቅድ በወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ድጋፍ መከለስ ይኖርበታል፡፡

ሪፖርት / ዘገባ ማቅረብ - የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሞያና ኢንትርፕራይዝ ልማት

ጽ/ቤት/የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት በየሩብ ዓመቱ በወረዳው ማ.ፕ.ት ተቆጣጣሪ በኩል ለክልሉ የኮዋሽ ድጋፍ ሰጪ ክፍል

ስለኢንተርፕራይዞቹ እንቅስቃሴ ዘገባ ያቀርባሉ፡፡

በየሩብ ዓመት ከሚቀርበው ዘገባ በተጨማሪ ኮዋሽ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ዓመታዊ ዘገባ ይፈልጋል፡፡

1. በሶስተኛው የኮዋሽ ምዕራፍ ትርፋማ የሆኑ በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብዛት

ትርጓሜ: በኮዋሽ ሶስተኛው ምዕራፍ የተመሰረቱ ወይም የተጠናከሩና በኦዲት ሪፖርት መሰረት ትርፋማ የሆኑ በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን

እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብዛት፡፡

ማሳሰቢያ: በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማለት ሴት የኢንተርፕራይዙ አባላት ዋና ዋና የአመራር ቦታዎችን

የያዙበት እና የንግድ ፈቃዱ በሴት አባል (ሰብሳቢ) ስም የሆነ ማለት ነው፡፡

2. በሶስተኛው የኮዋሽ ምዕራፍ የተመሰረቱ ወይም የተጠናከሩ በሴቶች የሚመሩ የመጠጥ ውሃ፣ የመጸዳጃ ቤት እቃዎች አቅራቢዎችና

አገልግሎት ሰጪዎች ብዛት፡፡

ማሳሰቢያ 1፡ በኮዋሽ ትርጓሜ አገልግሎት ሰጪዎች ማለት ፣ በሴቶች የሚመሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ማህበራት እና

ኮኦፕሬቲቭስ፣ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው ግለሰብ አርቴዢያኖች ወይም በሴቶች የሚመሩ በውሃ ተቋማት ግንባታ እና ጥገና የተሰማሩ

የአርቴዢያን ቡድኖችን ይይዛል፡፡

ማሳሰቢያ 2፡እቃዎች የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቦች፣ የእጅ መታጠቢያ ቁሳቁሶች፣ መለዋወጫዎች የመሳሰሉትን ይይዛል፡፡

ማሳሰቢያ 3፡አገልግሎት ማለት የውሃ ተቋማት ጥገና ወይም ግንባታ፣ ለውሃ ተቋማት ግንባታና ጥገና እንዲሁም የመጸዳጃ ቤት እቃዎችን

(ሲሚንቶ፣ ቶንዲኖ ብረት ወዘተ…) መሸጥን ያጠቃልላል፡፡

Page 32: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

31

3.በሴቶች የሚመሩ የመጠጥ ውሃ፣ የመጸዳጃ ቤት እቃዎች አቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ሰራተኞች ብዛት

ማሳሰቢያ 1፡ስለአገልግሎት ሰጭዎች፣ እቃዎች እና አገልግሎቶች ከላይ የተጠቀሱትን ፍቺዎች ይጠቀሙ፡፡

ማሳሰቢያ 2:ሰራተኞች ማለት በአገልግሎት ሰጪዎቹ የተቀጠሩ እና ደሞዝ ተከፋይ የሆኑ ማለት ነው፡፡

4.በኮዋሽ የሙከራ ወረዳዎች ባሉ አገልግሎት ሰጭዎች የተመረቱ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቦች እና የእጅ መታጠቢያ ወይም የገላ

መታጠቢያ እቃዎች (ለምሳሌ ፎሴት የተገጠመላቸው የእጅ ወይም የገላ መታጠቢያ ውሃ መያዣ ጀሪካኖች) ብዛት፡፡

ማሳሰቢያ:የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላብ ማለት በሴቶች በሚመሩ አገልግሎት ሰጪዎች የሚመረቱና ከኮንክሪት የሚሰሩ ማንኛውም

መጠን እና ቅርጽ ያላቸው ስላቦች ማለት ነው፡፡ ስላቡ ሲመረት ለሁለት የተከፈለ ከሆነ ሁለቱ ክፍሎች እንደ እንድ ስላብ ነው

የሚቆጠሩት፡፡ የእጅ መታጠቢያ ወይም የገላ መታጠቢያ እቃ ማለት ፎሴት የተገጠመለትና ለነዚህ አገልግሎቶች ለሽያጭ የተዘጋጀ

ጀሪካን ማለት ነው፡፡

5.በኮዋሽ የሙከራ ወረዳዎች ባሉ አገልግሎት ሰጪዎች ለተጠቃሚዎች የተሸጡ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላቦች እና የእጅ መታጠቢያ

ወይም የገላ መታጠቢያ እቃዎች (ለምሳሌ ፎሴት የተገጠመላቸው የእጅ ወይም የገላ መታጠቢያ ውሃ መያዣ ጀሪካኖች) ብዛት፡፡

መረጃው በስላብ ብዛት፣ በእጅ መታጠቢያ እና በገላ መታጠቢያ እቃዎች የተዘረዘረ/የተለየ መሆን አለበት

ማሳሰቢያ:የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ስላብ ማለት ማንኛውም በኮንክሪትም ሆነ በፕላስቲክ የተሰሩ ወይም አገልግሎት ሰጪዎች

ገዝተዋቸው ለተጠቃሚዎች የተሸጡ ማለት ነው፡፡ የእጅ መታጠቢያ ወይም የገላ መታጠቢያ እቃዎች (ለምሳሌ ፎሴት የተገጠመላቸው

የእጅ ወይም የገላ መታጠቢያ ውሃ መያዣ) ማንኛውም መጠን ያላቸው ጀሪካኖች ማለት ነው፡፡

6. በኮዋሽ የሙከራ ወረዳዎች በሳኒቴሽን ግብይት እና በኦፕሬሽንና ጥገና አገልግሎት ሰጭዎች አመሰራረት እና በውሃ ንጽህናና ሀይጅን

ምርቶች ግብይት የሰለጠኑ ሰዎች ብዛት፡፡

መረጃው በጾታና በአካል ጉዳተኞች የተዘረዘረ/የተለየ መሆን አለበት

ማሳሰቢያ: አካል ጉዳተኛ ማለት የመራመድ፣ የማየት፣ የመስማት፣ የተግባቦት ወይም የመረዳት ውስንነት ወይም አንዳንድ ሊረዱ

የሚችሉ መሳሪያዎች እንደ ክራንች፣ ሰው ሰራሽ እግር/እጅ የሚጠቀሙ ወይም እንደየሚጥል በሽታ የመሳሰሉ የአካል ጉዳት ያሉባቸው

ማለት ነው፡፡

5 መረጃ ማጠናቀር

በሴቶች የሚመሩ የውሃ፣ ንጽህናና ሃይጅን ኢንተርፕራይዞችን በተመረጡ ወረዳዎች የማቋቋም ዋና አላማው ከሙከራ ወረዳዎች ልምድ

በመቅሰም ወደ ሌሎች ወረዳዎች እንዲሁም አሁን ካለው የኮዋሽ ምዕራፍ በኋላም እነዚህን ስራዎች በስፋት ለመቀጠል እንዲቻል ነው፡፡

በዚህም ምክንያት በሙከራ ወረዳዎች ከሚቋቋሙት/ ከሚጠናከሩት ኢንተርፕራይዞች የተገኙ ጥሩ ተሞክሮዎች፣ ተግዳሮቶች፣ ለችግሮች

መፍትሔ የመፈለግ ልምዶችና ተዛማጅ መረጃዎች በተቀናጀ መልኩ መጠናቀር/መያዝ አለባቸው፡፡

ልምድ የመቅሰም ሂደቱን ለማቀላጠፍ ይረዳ ዘንድ ኮዋሽ ልምዶችን የመቀመርና መረጃዎችን የማጠናቀሪያ ቅጽ በማዘጋጀት እ.ኤ.አ 2017

ከማለቁ በፊት ለሚመለከታቸው አጋር አካላት የስራ ላይ ገለጻ ያደርጋል፡፡

Page 33: የማህበረሰብ መር የተሳለጠ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፤ የአካባቢና የግል … Version Guideline...የማህበረሰብ መር የተሳለጠ

32

6 የገንዘብ ቅብብሎሽ/ፍሰት

ኮዋሽ ምዕራፍ 3 የሚጠቀምበት የገንዘብ ፍሰት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማቋቋሚያ የሚያስፈልገውን የገንዘብ ግብዓትም

የሚያጠቃልል ነው፡፡ የወረዳው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/የቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/የከተማ

ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት ለኢንተርፕራይዞቹ ማቋቋሚያና ለተያያዥ ወጭዎች የሚሆነውን የኢትዮጵያ እና የፊንላንድ መንግስት

የበጀት ድርሻዎች ያስተዳድራሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የበጀት ድርሻ የሆነው የስራ ማስኬጃ በጀት ከየክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት

ቢሮዎች በክልል፣ በዞንና በወረዳ ለሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ/ለቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት

ጽ/ቤት/ለከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤቶች ይመደባል፡፡ የፊንላንድ መንግስት ድርሻ ደግሞ ለስልጠናና ለሌሎች የአቅም ግንባታ

ስራዎች (ዝርዝሩ ከላይ በክፍል 4.2.3 በተዘረዘረው መሰረት) ያገለግላል፡፡ በፊንላንድ መንግስት ድጋፍ ለስራ መጀመሪያ የሚያገለግሉ የእጅ

መሳሪያዎችና ጥሬ እቃዎች ግዢን ለመወሰን ኢንተርፕራይዞቹ ስራውን ለማስጀመር በሚኖራቸው የካፒታል አቅም ይወሰናል፡፡ ለዚህም

የሚሆነው በጀት ከፊንላንድ መንግስት ድርሻ የሚመደብ ሲሆን ገንዘቡም በወረዳው በሚገኙ የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት

ኤጀንሲ/ለቴክኒክ፣ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት/ለከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፈጠራ ጽ/ቤት ይተዳደራል፡፡ እነዚህም ጽ/ቤቶች የእጅ

መሳሪያዎች እና የጥሬ እቃዎቹን በመግዛት ለኢንተርፕራይዞቹ (የስላብ ማምረቻ ጥሬ እቃዎችን፣ ትራይፖድ፣ የቧንቧ ጥርስ ማውጫ እና

የቧንቧ መቁረጫ) በሚመለስ/በብድር መልክ ይሰጣሉ፡፡የሚመለሰው ብድር አንዳንድ አላቂ መሳሪያዎች እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ

ቁሳቀሶች የተገዙበትን ገንዘብ አይጨምርም፡፡ በሴቶች ለሚመሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከፊንላንድ እና ከኢትዮጲያ መንግስታት

የሚመደበው በጀት ፍሰት በዚህ መመሪያ በእዝል መልክ ተያይዟል፡፡

እዝል 15. በሴቶች የሚመራጥ.አ.ኢን ለማቋቋም / ለማጠናከር የኮዋሽ የፋይናንስ ፍሰት ስርዓት