የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ...

107

Transcript of የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ...

Page 1: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት
Page 2: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

i

የባለቤትነት መብት

ይህንን መጽሐፍ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል አባዝቶ ለተለያየ አገልግሎት መጠቀም የሚቻል

ሲሆን በሽያጭ የሚገኝ ገቢ ካለ ግን ለቤተ ክርስትያን ብቻ ገቢ መደረግ ይኖርበታል።

© 2007 ዓም

Page 3: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

ii

ምስጋናየዚህን መጽሐፍ መነሻ ሃሳብ በእንግሊዘኛ ያዘጋጁትና በመነሻነት እንድጠቀምበት

የፈቀዱልኝ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ታምራት ላይኔና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ፣ እንዲሁም ፓስተር ላሪ ጄ ዊክስና ፓስተር ጆኒ ዊክስ ናቸው። “ሰው ባይረዳን የጠራንና የሚመራን ጌታ አውቆን ታድጎናልና ሌላ ምን ያሻናል” ሲሉ የሚደመጡት እነዚህ ቤተሰቦች በጸሎት ምሽጋቸው ለሀገራቸው ሲማልዱና ሲያነቡ ላየ የጌታን የፍቅሩን ጉልበት መረዳት ያስችለዋል። እውነተኛው መምህር በየዕለቱ በሕይወታቸው ጣልቃ እየገባ ታማኝ ወዳጅነቱን ገልጦላቸዋልና፣ ይህ ጽሁፍ እንዲወለድና ጌታ በብዙ እንዲመለክ ስለሚተጉ እድሜያቸው ይርዘም። ስለ መልካም ፈቃዳቸው እግዚአብሔር አብዝቶ ልባቸውን፣ አዕምሯቸውን እና ጓዳቸውን ይባርክ።

ሰው በአንደበቱም ሆነ በተግባሩ በሌላው ላይ የሚያሳድረው አዎንታዊ አልያም አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖራል። ሐዋርያው ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ለጢሞቴዎስ በላከው መልዕክቱ “በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።” (1ኛ ጢሞ 4፥12) እንዳለው፣ ዶ/ር ቄስ ገመቺስ ደስታ በቅርብ በሚያውቋቸው ክርስቲያኖች ሕይወት፣ አመለካከት እና እምነት ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድሩ ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት ከጌታ ነውና በአፋችን ላይ እጅን ከመጫን በላይ ምን ልንል ይቻለናል?! በፍቅር የተሞሉ፣ ሰጥተው የማይረኩ፣ ተናግረው የማይጠገቡ መልካም መምህር መሆንዎን የሚያውቁ ሁሉ ይመሰክራሉ። ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልዎት።

በጽሁፍና በቃል በሚያስተምሩት ትምህርት ለሕይወት የሚጠቅም ምክር ለጋሽ ነዎት፤ በተለይ በግለ ታሪክዎ ላይ በማተኮር የጻፉት መጽሐፍ ላይ ስለ ዕድሜዎ ያስቀመጡት ትንቢታዊ መልእክት ይህ ጽሑፍ ፈጥኖ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ጋሽ በቄ እርሶ ወደ ጌታ ከመሄድዎ በፊት ይችህን ጽሑፍ እንዲያነቡ በመሽቀዳደም የተሰራች ናት። በእግዚአብሔር እርዳታ 75 ዓመት ሳይሞላዎ ለንባብ በመብቃቷ ምስጋና ለአምላክ ይሁን። የእግዚአብሔር ሰላምና ፍቅር ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ ሕይወትዎም እንደ ምንጭ ዳር ቄጠማ የለመለመችና ያማረች ትሁንልዎት።

Page 4: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

iii

እስከ ዛሬ ድረስ ክርስቲያኖች ወንጌልን በቤተክርስቲያንም ሆነ በግለሰብ ደረጃ፣ ለሚያምኑትም ይሁን ለማያምኑት፣ በቃላቸው እንጂ በሕይወት ኖረው ሲመሰክሩ እምብዛም አይታይም። ይህ ደግሞ ለብዙዎች እውነተኛውን ኑሮ እንዳይኖሩ መሰናክል ሲሆን ቆይቷል። በዘመናችን እንደ ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ፣ ለብዙዎች መዳን ምክንያት የሆነ የእግዚአብሔር ሰው ማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜ የተገኘህ በመሆንህ አምላክ ዘመንህን ይባርክ ለማለት እወዳለሁ። መጋቢ መስፍን ሙሉጌታ ሕይወትህ ብዙ ታስተምራለች። የምትናገረውን ሕይወት ኖረህ እውነትን ስላሳየኸን ምስጋና ይገባሀል። እግዚአብሔር የአገልግሎትህን ዘመን ይባርክ። ጸጋህንም ይጠብቅልህ።

የወንጌልን አገልግሎት፣ ከእግዚአብሔር “እንዲህ ብለህ ተናገር” የተባልነውን መናገር ነው። ሌሎችን ላለማስከፋት ወይም ተወዳጅነትን ለማትረፍ የምንቀንሰው ወይም የምንጨምረው የራሳችን የሆነ ሀሳብ ሊኖር ባልተገባ ነበር። ነገር ግን በቤተክርስቲያን አድር ባይ ሰባኪዎችና የሀሰት ነቢያት መብዛታቸው የሚያሳዝን ቢሆንም የመጨረሻው ዘመን ፍሬ ነውና አያስደነግጠንም። ውድ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁንና ፓስተር ማሙሻ ፈንታ እውነትን በታማኝነት፣ በድፍረት እና በንጽህና የመግለጽ ጸጋችሁ በጣም የሚደነቅ ነው። በተለይ እውነት በእውቀት ሲገለፅ ያለውን ውበት ማሳየት የቻላችሁ ድንቅ መምህራን ናችሁ። ለዚህ መጽሐፍ ለንባብ መብቃትም የእናንተ ቆራጥ የሆነ አቋምና እውነተኛ አስተምህሮ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው ልገልጽላችሁ እወዳለሁ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ! የነፍስ አገልግሎታችሁ ዘመን የረዘመች ትሁን።

ገንዘባችሁን፣ እውቀታችሁን፣ እንዲሁም ጊዜያችሁን ሳትቆጥቡ ለዚህ መፅሐፍ ውልደት ልዩ ድጋፍ ያደረጋቸሁ እናንተ የጌታ ውድ ስጦታዎች ድካማችሁ ለፍሬ በቅቷልና እንኳን ደስ ያላችሁ። በቅንነትና በትጋት ታዛችኋልና ብድራቱ ከእርሱ በብዙ ይከፈላችሁ።

“እውነት ለሕዝቡ በዚህ መልክ ይገለጥ ዘንድ ለወደደው ድንቅ፣ መካር፣ ኃያል እንዲሁም የሰላም አምላክ ክብርና ውዳሴ ይሁን።”

አሜን።

Page 5: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

iv

መቅድምመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ ሂደቶቹ እየዳበረ የመጣ፣ ረዥም ዕድሜን

ያስቆጠረ እና በዓለም ላይ በበርካታ ሀገራት ቋንቋ ተተርጉሞ የተሰራጨ፣ የእውቀትና ጥበብ ምንጭ የሆነ አንጋፋ መጽሐፍ ነው። ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ከማጥናት ይልቅ ከሰዎች በቁንፅል በማድመጥ ባልተሟላ መረዳት ግራ ሲጋቡ ይስተዋላል። ለዚህ ግራ መጋባት ኃላፊነቱን የሚወስደው በርካታ አካል ቢሆንም የእውቀት ሁሉ ምንጭ የሆነውን ቃል በጥልቀት ከማጥናት ይልቅ ከራስጌ መብራት ጎን በማስቀመጥ አማኝ የመምሰል አባዜ ከጥበብ አርቆናል። ሀሳቡን በትክክል ባለመረዳታችን ግራ መጋባት ውስጥ እንወድቃለን። ለዚህ ግራ መጋባት ተጠያቂው አንባቢው ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የእምነት ድርጅቶች አንዱን የአምላክ ቃል በተለያዩ መልኩ በመተርጎሙና ተከታዩንም የዚህ አስተሳሰብ ተገዢ ማድረጉ ጭምር ነው። በዚም ምክንያት በርካታ ሰው ስለ አዲሱ ፍጥረት ያለው ዕውቀት እጅግ አናሳ ከመሆኑ የተነሳ በአምላክ አምሳል መፈጠሩን ዘንግቶ በአሮጌው አዳማዊ ባህርይ ሲመላለስ ይስተዋላል። በቤተክርስቲያንም በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ ዓይነቱ ችግር በተደጋጋሚ ሲከሰት ይታያል። በዚሁ መሰረት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሊታወቁ የሚገባቸውን እውነቶች ሊያሳይ የሚችልና አነስተኛ ግንዛቤ ሊያስጨብጥ በሚችል መልኩ ይህ መጽሐፍ ተዘጋጅቶ በእያንዳንዱ ነጥቦች ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሙከራ ተደርጓል።

መጽሐፉ በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀትና መረዳት ለማደግ ለሚፈልግ ለማንኛውም ክርስቲያን፣ ለአገልግሎት ለሚዘጋጁ ወንድሞችና እህቶች፣ በግል ሕይወታቸውም ሆነ በአገልግሎታቸው ሊጠቀሙበት የሚችሉ ወገኖችን ሁሉ የሚያገለግል ቅዱሳዊ መረጃ የያዘ መጽሐፍ ነው። ስለዚህ በዋናነት በቤተክርስቲያን የሚያገለግሉ፣ በአባልነት የታቀፉ እና ገና ወደ ጌታ መጥተው የክትትልና የደህንነት ትምህርት የሚማሩ ሁሉ ይህን መጽሐፍ በመጠቀም ሕይወታቸውን ትክክለኛ አቅጣጫን ማስያዝ ይችላሉ።

የእግዚአብሔር ቃል “አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።” (ሮሜ 15፥4) እንደሚል በመጽሐፉ ውስጥ በርካታ ትምህርት ሰጪ የሆኑ ቁምነገሮች ሰፍረው ይገኛሉ። እነዚህን ቁምነገሮችና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸውን ዓበይት የሆኑ መሰረታዊ ትምህርቶችን በሚገባ ለመረዳት የዚህች መጽሐፍ ጠቀሜታ ጉልህ ነው።

የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትና ከሕይወታችንም ጋር ልናዋህደው መሞከር የእውቀት ሁሉ መጀመሪያና የበላይ ነው። ምክንያቱም በ2ኛ ጢሞ 2፥15 ላይ “የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።” በማለት ይመክራል። በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያላቸውን ትምህርቶች በራሳችን ሃሳብ ከመተርጎምና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቱን በለቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ መሰረታዊ እውነቱን ተረድተን ከሕይወታችን ማዛመድ ለግል ሕይወታችንም ሆነ ለሌሎች እውነተኛውን የሕይወት መንገድ የምናሳይበትና የምንመራበት መንገድ መሆን አለበት።

Page 6: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

v

በምድር ላይ ስንኖር እውነተኛውን ሕይወት እንዳንኖር የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች አሉ። ከእነዚህ ምክንያቶች አንዱ ለምን እንደምንኖር አለማወቅ ነው። እግዚአብሔር ወደዚህች ምድር ሲያመጣን በሕይወታችን ላይ ትልቅ ዓላማ ኖሮት ነው። ዓላማችንን አለመረዳታችን ወዴት መሄድ እንዳለብን እንዳናውቅ ያደርገናል። ተልዕኳችንን አለመረዳታችን የመኖራችንን ግብ ሳንፈጽም ሕይወታችንን በዋዛ ፈዛዛ እንድናሳልፍ ያደርገናል። ተልዕኳችንን እንድንረዳ ስለ ተልዕኮው የሚያስረዳን ያስፈልገናል። ይህንን መረዳት የምናገኘው ደግሞ ዘወትር ከእግዚአብሔር ቃል በመማር ነው። እያንዳንዱን ቀን ከትላንት ይልቅ እግዚአብሔርን የሚያስከብር ሕይወት ለመኖር ዘወትር ከቃሉ መማር አለብን። ለዚህ ደግሞ ይህች መጽሐፍ በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ያለውን ነገርና በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ የአማኝን ስልጣን በማሳየት ጉልህ ሚና ትጫወታለች።

እውነተኛ ሕይወት በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረታዊ አስተምሮዎች ላይ መመስረት አለበት። በመሆኑም በዚህ መጽሐፍ ወደ ስድስት የሚጠጉ ርዕሰ ጉዳዮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ በውስጣዊ ማስረጃዎች እየተመሳከሩ በሰፊ ርዕሰ ጉዳዮች ተዳሰዋል። ስለ አዲስ ሕይወት፣ መንፈሳዊ ውጊያ እና ለተሰበረ ልብ ፈውስ ማግኘት ስለሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች በሰፊው ማብራሪያ ስለተሰጠባቸው ይህንን መጽሐፍ የሚያነብ ሁሉ ለሕይወቱ እንዲሁም ለአገልግሎቱ ጠቃሚ አቅጣጫ ይይዛል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያንም ያገኛል ።

“እግዚአብሔር የምናነበውን እንረዳ ዘንድ መረዳቱን ይስጠን፤”አሜን!!

Page 7: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

vi

መግቢያ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከእርሱ ጋር በሕብረት እንዲኖር በመልኩና በአምሳሉ ለራሱ

ክብር እንደፈጠረው የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው ሰው በምድር ላይ እንዲበዛና ምድርን እንዲሞላ የተባረከ ሲሆን ምድርን እንዲጠብቃትና እንዲንከባከባት ኃላፊነትም ተሰጥቶት ነበር። ሰው ግን በማልማት ፈንታ በማውደም፣ የእግዚአብሔርን መልክ ከማሳየት ይልቅ ክፋትን በምድር ላይ በማምጣት ምድር እንድትረገም ምክንያት ሆነ። በነፍሱም ሟች በመሆኑ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ተለየ።

እግዚአብሔር ግን ይህ ሟች የሆነውንና ከእርሱ የተለየውን ሰው ወደ ራሱ ለማምጣት ወይም ለመመለስ አዲስ የመዳን መንገድ አዘጋጀ። ይህም የመዳን መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእግዚአብሔር ዕቅድ መሰረት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለና የሕይወቱ ጌታ አድርጎ የወሰነ ሁሉ ወደ ቀድሞ ማንነቱ እንደሚቀየር እንዲሁም አሮጌው ማንነቱ እንደሚወገድ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። መጽሐፉ በአብዛኛው የሚዳስሰው ይህንኑ እውነታ ነው። መጽሐፉ በስድስት ዋና ዋና ምዕራፍ የሚከፈል ሲሆን እያንዳንዱ ተያያዥነት ያላቸውንና ቅደም ተከተላቸውን የጠበቁ ርዕሶችን ይዟል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ውስጥ አዲሱን ሰው ስለመረዳትና ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል እንደተፈጠረ በሰፊው ያብራራል። መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ስለ አዲሱ ፍጥረት የሚናገር ቢሆንም በትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ ስለ አዲስ ፍጥረት በሰፊው የተብራራ ትንቢት ሰፍሯል። በዚህ ክፍል የተነገረው ትንቢታዊ ቃል በመጽሐፉ ውስጥ በስፋት ተዳስሶ እናገኛለን። ስለ ነፍስ፣ መንፈስ እና ስለ አካል ባህርያት በተጨማሪም ስለ አሮጌው ሰውና አዲሱ ሰው ምንነት፣ አንድነት እና ልዩነት በጥልቀት በምዕራፍ አንድ ውስጥ ተዳስሶ እናገኘዋለን።

በሽታ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ካሉ የኑሮ ሰንኮፋዎች አንዱ ነው። በምድራችን ላይ መድኃኒት የሚገኝላቸው በሽታዎች እንዳሉ ሁሉ መድኃኒት የማይገኝላቸው በሽታዎችም አሉ። መድሀኒት አልባ ከሆኑ በሽታዎች የልብ ስብራት አንዱ ነው። ይህ በሽታ ወደ ሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ የመጣው ከእግዚአብሔር በተለየባት ሰከንድ ነው። በሽታው እንደ አጥንት ስብራት በወጌሻ ወይም በሕክምና ማዳን የሚቻል አይደለም። የስብራቱ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። የዚህ መጽሐፍ ሁለተኛው ምዕራፍ ስለዚህ ስብራት እንዲሁም ስብራቱ የሚጠገንበትን ብቸኛ መንገድ በተመለከተ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ያትታል።

Page 8: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

vii

እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ በልዩ ሁኔታ የተፈጠረው ሰው ሕግን መተላለፉ ከእግዚአብሔር ከፈጣሪው ስለለየው ሰው በስጋውና በመንፈሱ ሟች ሆነ። ራሱን ማዳን የማይችል ልፍስፍስ ከመሆኑም ባሻገር በሰማይም ሆነ በምድር ሊያድነው የሚችል አካልም አልነበረውም። ምንም እንኳን እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ በመፍጠሩ የተጸጸተ ቢሆንም ለዚህ ድንቅ ፍጥረት ካለው ፍቅር የተነሳ የመዳን መንገድ ሲያዘጋጅ እንመለከታለን። ዮሐ 3፥16 “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንዲያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” ይላል። ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ታላቅ ፍቅር ነው። ከፍቅሩ የተነሳ ኢየሱስ ክርስቶስ ከገባንበት አዘቀጥ ሊያነሳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ራሱን አዋርዶ እና የሰውን ስጋ ለብሶ እኛን ነፃ አወጣን። በዚህ መጽሐፍ ምዕራፍ ሶሰት የምናገኘውም ይህንኑን እውነት ነው። ኢየሱስ ነፃ አውጪአችን መሆኑን ይገልጽና ከምንና እንዴት ነፃ እንደወጣን ያብራራል። በክርስቶስ ነፃ በመውጣታችን የልጅነት ስልጣን እንዳገኘን የዮሐ ወንጌል 1፥12 ላይ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው” በማለት ያረጋግጥልናል። በዚሁ መሰረት በክርስቶስ ነፃ አውጪነት ያገኘነውን ስልጣን በዝርዝር በማብራራት ያስረዳል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ በምዕራፍ 6፥10 ላይ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ በዝርዘር ገልጾላቸዋል። ውጊያውም ከደምና ከስጋ ጋር እንዳልሆነና በሰማይ ካለው ከርኩሳን መናፍስት ጋር እንደሆነ ይናገራል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ለተከታዮቹ “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌአለሁ” (ዮሐ 16፥33) ብሎ ሲመክራቸው እናያለን። ይህ ምክር የሚያሳየው በምድር ላይ ስንኖር ከሰይጣንና ከጭፍሮቹ ሁልጊዜ ውጊያ እንዳለብንና ዘወትር በመዘጋጀት ድል መንሳት እንዳለብን ነው። ይህንን እውነት በሰፊው ለማብራራት የውጊያን ምንነት፣ የሰይጣንና የጭፍሮቹ ባህርያት፣ ውጊያው የት እና መቼ እንደሚካሄድ በምዕራፍ አራት ላይ በዝርዘር ተቀምጧል። ይህንን ምዕራፍ በማንበብ ሁልጊዜ የተዘጋጀን እንድንሆንና የመንፈሳዊ ውጊያን ምንነት ተረድተን እንድንኖር መጽሐፏ ጠቃሚ ምክሮችንና መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረጉ አስተምህሮዎች ይዛለች።

Page 9: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

viii

እግዚአብሔር በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ የሰጠው የልጅነት ስልጣን አለ። ይህንን ስልጣን ለመቀማት ሰይጣን ሁልጊዜ በክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ ጦርነት ይከፍታል። የሚመጣውን ጦርነት ለመዋጋት ክርስቲያኑ መንፈሳዊ ጦር እቃዎችን መያዝ እንዳለበት የእግዚአብሔር ቃል ያስተምራል። የጦር ሜዳውንና የውጊያውን ስልት አውቀን መዋጋት ከክርስቲያኖች ይጠበቃል። የእውነተኛ ሕይወት ጅማሬ ውጊያን ድል በማድረግ እና የልጅነትን ስልጣን ለማንም አሳልፎ ካለመስጠት የሚጀምር ነው። የመዳን ራስ ቁር፡ ይህ ልጅ ስለሆንን እግዚአብሔርን ከማመስገን የሚጀምር ሲሆን በመዳናችን ምክንያት የክርስቶስ ልብ እንዳለን የሚያሳይ ነው። 1ኛ ቆሮ2፥16 የጽድቅ ጽሩር፡ ይህ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን እንዲመረምር ከልመና የሚጀምር ነው። መዝ 139፥23-24 የእውነት መታጠቂያ፡ ለራስና ለእግዚአብሔር እውነተኛ ከመሆን የሚጀምር ሲሆን ስሜቶችን በመቆጣጠር እውነትን መያዝን ያጠቃልላል። ያዕ4፥3 የመዘጋጀት ጫማ፡ ይህ የውጊያ መሳሪያ ከዝግጅት የሚጀምር ሲሆን ወንጌልን ለጠፉት በማካፈል መማለድንም የሚያጠቃልል ነው። 1ኛ ጢሞ 2፥1-4 የመንፈስ ሰይፍ፡ ይህ የጦር መሳሪያ ቃሉን ከማወቅ የሚጀምር ነው። በቃሉ መሰረት መጸለይ፣ በቃሉ መሰረት መኖር እና ቃሉን የሕይወት መመሪያ ማድረግን የሚያጠቃልል ነው። ዕብ 4፥12 ሌላኛው የመንፈሳዊ ውጊያ መሳሪያ ጸሎት ነው። አማኞች የሰይጣንን ጦርነት ለማሸነፍ ዘወትር በጸሎት የሚጋደሉበት ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል። ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ በእነዚህ የጦር መሳሪያዎች ዙሪያ የቀረቡ ዝርዝር ሀሳቦች በመኖራቸው መጽሐፉን የሚያነብ ሁሉ በምድር ላይ ሲመላለስ ለሚገጥመው ጦርነት በቂ ዝግጅትና ትጥቅ እንደሚኖረው ሙሉ በይታመናል።

የሰው ልጅ ዘረ-መሉ ምን እንደሆነ ማወቁ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። ዋነኛ ማንነታችንን ከሚገነቡትና ከሌሎች ሰዎችና ፍጥረታት ከሚለዩን ነገሮች የመጀመሪያው ዘረመል (DNA) ነው። በዓለም ላይ ያለን ፍጥረታት በሙሉ የራሳችን ብቻ የሆነ ዘረ-መል አለን። ይህ ዘረመል የማንነታችንን ዕድገት፣ ባህርይ እና አሠራራችን ይለያል። ዘረመል ከወላጆቻችን ከተወጣጡ የበራሂ (genes) ድብልቅ የሚመጣ ሲሆን ለእኛ የተለየ ማንነት የሚሰጥ የንድፍ መዋቅር ነው። ከእናትና አባታችን የምንወርሰው የዘረመል ክፍልፋዮች በትንሹ ቢያመሳስለንም ፍፁም የሆነ ልዩነትም ይሰጠናል። ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር አባታችን ሰውን በመጀመሪያ ሲፈጥር የተነፈሰበት የሕይወት እስትንፋስ መንፈሳዊ ዘረመላችንን በእርሱ አምሳል እንዲገነባ አድርጎታል። ይህም ማንነታችን መንፈሳዊ ዕድገታችንን፣ ስራችንን፣ የግል ባህርያችንን በአጠቃላይ ዓላማችንን የሚወስንልን ክፍል ነው። መንፈሳዊ ዘረመላችን በእግዚአብሔር አምሳል የተገነባ ነበር። ነገር ግን ይህን ዘረመል በኃጢአት ምክንያት ተበላሽቷል። ስለዚህ በኃጢአት የተበከለውን መንፈሳዊ ዘረመላችንን ለማንጻት በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን ያስፈልጋል። ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው። (2 ቆሮ 5፥17)

Page 10: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

ix

“የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።” ኢዮ 33፥4። በመሆኑም የመጽሐፉ የመጨረሻ ምዕራፍ የሚያስረዳን ይህንኑን እውነት ነው። ይህ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው ሰው እንዴት እንደተበከለና እንዴት የዓመፅ ምንጭ እንደሆነ የዓመፅ ውጤቱን በመግለጽ እንዴት ከውስጣችን አስወግደን እውነተኛውን ሕይወት መኖር እንደምንችል ያስረዳል።

በመሆኑም ይህንን መጽሐፍ በማንበብ በግል ሕይወታችንና በአገልግሎታችን እንዴት እውነተኛውን ሕይወት መኖር እንደምንችል የሚያስረዱ ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያላቸው መመሪያዎች እና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንዲሁም ማስረጃዎች ያላት መጽሐፍ መሆኗን ለማስገንዘብ እፈልጋለሁ። ሁላችንም ከመጽሐፏ ጠቃሚ የሚሆኑ ምክሮችንና ተግሳጾችን ስለምናገኝ ጌታ እስኪመጣ ድረስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎቹን ተግባራዊ እያደረግን በድክመታችን ደግሞ እርሱ እንዲረዳን በመፍቀድ እንድንኖር ወንድማዊ ምክሬን አስተላልፋለሁ። የእውነተኛ ሕይወት መንገድ ጠፍቶብን በመጨረሻው ቀን ከሕይወት መዝገብ እንዳንታጣ የአዲሱ ሰው ባህርይን ተላብሰን፣ የሚመጣውን ጦርንት በመንፈሳዊ ውጊያ ተዋግተን፣ እንዲሁም የተሰጠንን የልጅነት ስልጣን እስከመጨረሻው ይዘን መቆየት እንድንችል ተግተን እንጸልይ።

የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ፤ ይብዛልን፤ አሜን !!

Page 11: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

ርዕስ ማውጫምዕራፍ 1 አዲሱን ፍጥረት መረዳት 4

1.1 ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል 61.2 ስለ አዲስ ፍጥረት የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ቃል 91.3 ለምን እንታገላለን? 101.4 ነፍሳችንና መንፈሳችን 111.5 የነፍስ ባህርያት 111.6 የነፍስ ተፅዕኖ 111.7 የስጋ ወይም የአካል ባህርያት 121.8 አሮጌው ሰውና አዲሱ ሰው 121.9 አዲሱን ፍጥረት መረዳት 131.10 ደህንነታችንን ማስፈፀም 131.11 አሮጌውን ሰው ማስወጣት 141.11.1 ስለዚህ እንዴት አሮጌውን ማንነት ማስወገድ እንችላለን? 151.12 በክርስቶስ ያለን አዲስ ቦታ (ማንነት፥ ስለራሳችን ያለን አመለካከት) 161.13 ቃል ኪዳኑን መተግበር 171.14 ማጠቃለያ 17

ምዕራፍ 2 የተሰበረውን ልብ መፈወስ 19

2.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስብራትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ይነግረናል 192.2 ስብራት ምንድን ነው? 202.3 ልብ ምንድን ነው? 212.3.1 ልብ እንዴት ይሰበራል? 212.4 በሕይወታችን ያለውን ስብራት ማስተዋል 232.4.1 የስብራት ባህርያት 232.4.2 በሁለት ሃሳብ መሆንvv 232.4.3 በሁለት ነፍስ መሆን 232.5 ለልባችን ቁስል እንዴት ፈውስን ማግኘት እንችላለን? 252.5.1 የልብ ስብራት ፈውስን መቀበል መማር 252.5.2 ሌሎችን ማፅናናት 27

Page 12: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

ምዕራፍ 3 ኢየሱስ ነፃ አውጪያችን 283.1 በኢየሱስ ነፃ መውጣት ማለት ምን ማለት ነው? 293.2 ኢየሱስ ከምንና እንዴት ነፃ እንዳወጣን 293.2.1 ከምን ነፃ ወጣን? 303.3 በክርስቶስ ኢየሱስ ነፃ የወጣ ሰው የተሰጠው ስልጣን 32

ምዕራፍ 4 መንፈሳዊ ውጊያ 414.1 የመንፈሳዊ ውጊያ ጭብጥ 414.2 የሰይጣንና ጭፍሮቹ ማንነትና ባህርያት 424.3 መንፈሳዊ ውጊያ የት፣ መቼ እና እንዴት ይካሄዳል? 464.3.1 ጠላት ዲያብሎስ ክርስቲያኖችን ለማጥመድ የሚጠቀምባቸው ስልቶች 474.3.2 ነፍሳችን ሕይወታችንን እንድትመራ በመፍቀድ 484.3.3 ለገንዘብ ጤናማ ያልሆነ ፍቅር እንዲኖረን በማድረግ 484.4 እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች 494.4.1 በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር 544.4.1.1 መሪዎችና እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች 544.4.1.2 ዲያብሎስ የራሱን ባህርይ በመጠቀም 554.4.1.3 በዓመፅ በተያዙ ሰዎች አማካኝነት 554.4.2 የጥንቆላ መንፈስና ቤተክርስቲያን 564.4.2.1 የጥንቆላን ጥቃት መረዳትና መለየት 584.4.2.2 አስማት 594.4.3 በጥንቆላ መንፈስ ላይ ድልን መቀዳጀት 604.4.4 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማያከብሩ የሚደርስባቸው ችግሮች 634.4.5 የህቡዕ ድርጅት አደገኛነት 654.5 የዲያብሎስን ሥራ ማጋለጥና ማፍረስ 65

Page 13: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

ምዕራፍ 5 የአማኞች ስልጣንና የመውጊያ

መሳሪያዎች 5.1 የአማኞች ስልጣን 705.2 መንፈሳዊ ማሰልጠኛ 735.2.1 ክርስቶስ ከጠላት ጋር እንድንዋጋ ያሰተምረናል፤ ያሰለጥነናል 735.2.2 ክርስቶስ በማበረታታት ያግዘናል 735.2.3 መልካሙን ጦርነት እንድንዋጋ ያስችለናል 745.3 ከእግዚአብሔር የሆኑ መንፈሳዊ የጦር እቃዎች 75

ምዕራፍ 6 መንፈሳዊ ዘረመልን መረዳት (SPIRITUAL DNA) 846.4 መንፈሳዊ ዘረመል ምንድን ነው? 846.5 አሉታዊ/የተበከለ ዘረመል፥ ዓመፅ 846.2.1 የዓመፅ ፅንሠ ሀሳብ/የዓመፅ ምንነት 846.2.2 የዓመፅ ምንጭና ባህርይ 866.2.3 ዓመፅ የሚያስከትለው መዘዝ 886.6 ደህንነት/በክርሰቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን በእግዚአብሔር አምሳል ዘረመልን መልሶ መገንባት 906.3.1 ዓመፅን ማስወገድ 906.7 በደልና የሰው መንፈስ፥ 926.4.1 የሰውን መንፈስ መረዳት 926.4.2 የመንፈሳችን አዕምሮ 936.8 ሕይወትን እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ መምራት 97

Page 14: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

4 5

ምዕራፍ 1አዲሱን ፍጥረት መረዳት

♥ «ስለዚህማንምበክርስቶስቢሆንአዲስፍጥረትነውአሮጌውነገርአልፏል፤እነሆሁሉምአዲስሆኗል።»2ቆሮ5፥17

አብዛኞቻችን አዲስ ነገርን እንወዳለን። በተለይ ደግሞ ጥቅም የሚሰጥ አዲስ ነገርን። ዘወትር አዲስ መኪና፣ አዲስ ልብስ፣ አዲስ ቤት ወዘተ እንዲኖረን እንሻለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተለይ በአዲስ ኪዳን ላይ “አዲስ” የሚለው ሀረግ በተደጋጋሚ የወንጌልን የተለያዩ ፈርጆች ለማስረዳት ጥቅም ላይ ውሏል። አዲሱ ውል፣ አዲሱ ፍጡር፣ አዲስ ትዕዛዛት፣ አዲስ ገነት እና አዲስ ምድርን በአብነት መጥቀስ ይቻላል። (ኢሳ 65፥17-20፣ 66፥22፣ ዕብ 12፥26-28፣ ራዕ 21፥1-4)

† ለመሆኑ “አዲስ ፍጥረት መሆን” ማለት ምን ማለት ነው? ጳውሎስ ስለ አዲስ ፍጥረትበቆላስያስ 1፥26-27 ላይ “በእናንተ ዘንድ ያለው ክርስቶስ የሕይወታችን መሰረት ነው፤”ሲልፅፏል።ይህምለረዥምዘመናትከሰውዘርልቦናጠፍቶየነበረእውነትነበር።

አዲስ የሚለው ቃል በፊት ያልነበረን ነገር ወደ ማኖር ማምጣትን ያመለክታል። አዲስ ፍጥረትም በፊት የሌለ ህልውናን ወደ መኖር ያመጣዋል። የነበረን ነገር ወደ አዲስ ለመቀየር ደግሞ ወይም ፈርሶ መሰራት አለበት አልያም ቀድሞ የሌለውን ነገር ጨምሮ መታደስ አለበት። በእርግጥ እንደሰውኛ የሰው ልጅ አዲስ ፍጥረት መሆን አለበት ሲባል በስጋዊ አካሉ ሞቶ መነሳት ወይም ወደ እናቱ ሆድ ተመልሶ ገብቶ በድጋሜ መወለድ አለበት ማለት ሳይሆን ሲፈጠር ከነኃጢአቱ የነበረውን መንፈሱን ለክርስቶስ ተገዢ በማድረግ፣ እግዚአብሔር በላከው በአንድያ ልጁ በማመንና ከኃጢአት በመራቅ እንዲሁም ከቀድሞ የተለየ አተያይና የአኗኗር ዘዬ መከተልን የሚያሳይ ሀሳብ ነው።

♥ “ይህምቃልከዘላለምናከትውልዶችጀምሮተሰውሮየነበረምሥጢርነው፥አሁንግንለቅዱሳኑተገልጦአል።ለእነርሱምእግዚአብሔርበአሕዛብዘንድያለውየዚህምሥጢርክብርባለጠግነትምንእንደሆነሊያስታውቅወደደ፥ምሥጢሩምየክብርተስፋያለውክርስቶስበእናንተዘንድመሆኑነው።”ቆላ1፥26-27

Page 15: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

5

† እንደ አማኝ ሕይወታችን የሚመሰረተው አዲስ ፍጥረት በመሆናችን ላይ ነው፤ምክንያቱምክርስቶስበእኛዘንድአለ።

♥ “የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትንመሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱምኢየሱስክርስቶስነው።”1ቆሮ3፥10-11

† አንድ ሰው ክርስቶስን ሳይቀበል የሚያሳልፈው የሕይወት ዘመን በሙሉ ባረጀናበቆሸሸማንነትየሚጓዝበትዘመንለመሆኑአጠራጣሪአይደለም።በዮሐንስወንጌልላይ ክርስቶስን ለሚፈልጉት ሁሉ እንደመጣ በመናገር፣ ማመን የክርስቶስ ልጅ ሆኖበአዲስማንነትመገለጥማለትእንደሆነይገልፃል።

♥ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድሥልጣንንሰጣቸው፤እነርሱምከእግዚአብሔርተወለዱእንጂከደምወይምከሥጋፈቃድወይምከወንድፈቃድአልተወለዱም።”ዮሐ1፥12-13

እዚህ ጋር ለአብነት ያህል ጌታ በገሊላ ቃና ሰርግ ላይ ተገኝቶ ያደረገውን ተአምር ብናይ መልካም ነው። ውኃውን ወደ ወይን ጠጅነት ሲቀይር በመጀመሪያ ያዘዘው ከገንቦው ውስጥ ያለውን አሮጌ የወይን ጠጅ እንዲያወጡና ንፁህ (አዲስ) ውኃ እንዲጨምሩበት ነበር። በመቀጠልም ከገንቦው ውስጥ ውኃውን እየቀዱ ለእንግዶቹ እንዲያድሏቸው አዘዛቸው። አስተናጋጆቹ ወይን ጠጁን ቀድተው ለእንግዶቹ ሲሰጡ ቀድሞ ከነበረውና ለብዙ ቀናት ከተጠመቀው የወይን ጠጅ እጅግ የላቀ ጣዕም ያለው ሆነ ተገኘ። የዛኔ የቀድሞው የወይን ጠጅ መናኛ (የማይረባ) ተባለ። ጣዕም ያልነበረው ውኃ ጣዕም ተሰጠው፤ ሽታ ያልነበረው ውኃ ባለ መዓዛ ሆነ፤ መልክ ያልነበረው ውኃ ባለ ቀለም ሆነ። አዲስ ሰው መሆንም ልክ እንደዚሁ ነው። የክርስትና ሕይወታችን ጣዕም አልባ ቢሆን፣ ሽታው ቢከረፋ፣ መልከ ጥፉ ቢሆን ጌታን ስንቀበልና ውስጣችንን በመንፈሱ ሲሞላው ሁሉ ነገር ይቀየርና ተቃራኒውን ክብር እንጎናጸፋለን። ቀድሞውንም መሆን የነበረብንን ሰዎች እንሆናለን። ከራሳችን አልፎ በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ሰላም እንሆናለን። (ዮሐ 2፥1-11)

ብዙ ሰዎች በኃጢአተኛ ተፈጥሯዊ ማንነት እንደምንወለድ አያምኑም። ነገር ግን ከአዳምና ሄዋን ዘር የወጣ የሰው ልጅ ሀረግ ሁሉ የኃጢአት ውርስ እንዳለበት ቅዱስ ቃሉ ያስተምራል። እንደተወለድን ብንሞት እንኳ የውርስ ማንነታችን አብሮን አለ። ይህ ኃጢአተኛ ማንነትም ከአባታችን ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ የገደበው ነበር። ኃጢአትን ለማሰረይ በየጊዜው በሚደረግ የደም መስዋዕት የነበረው ስርዓት በአንድያ ልጁ የመጨረሻ መስዋዕትነት ሲዘጋ እግዚአብሔር ልጆቹ ወደ ፊቱ ያለመከልከል እንዲቀርቡ በማሰብ ነው። ይህንንም በማመን ልጆች ለአባታቸው ጥሪ ምላሽ ሲሰጡ የድሮ ማንነታቸውን በመግደል አዲስ ማንነትን ይቀበላሉ። ክርስቶስ የእኛን ኃጢአት ለማሰረይ የመጣ አንዱና ብቸኛ መንገድ መሆኑን ከተረዳንና ካመንን ያኔ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን።

Page 16: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

6 7

ጳውሎስ በመልዕክቱ መሰረታዊ እውነት የሆነውን ክርስቶስን፣ አዲስ ፍጥረት መሆናችንን እና አሮጌው ነገር እንዳለፈ ሁሉም ነገር አዲስ እንደሆነ ያስተምራል። በዓለም፣ በስጋ እና በሰይጣን ላይ የተቀዳጀነው የድል ምክንያቱ በክርስቶስ እንደ አዲስ መሰራታችንና መሰረታችን እርሱ መሆኑ ነው።

በመሆኑም በተፈጥሯዊ ማንነታችንና በክርስቶስ በማመናችን ምክንያት በተሰጠን የክርስቶስ ልብ መካከል ያለ ልዩነት አለ። በክርስቶስ አምነን ዳግም ስንወለድ አዲስ ማንነት፣ አዲስ ተፈጥሮ እና የክርስቶስ ልብ ተሰጥቶናል። ማንነት፥ ራስን የመሆን ሁኔታ፣ የእኛነታችን መገለጫዎች ወይም ስለራስ የሚኖር ግንዛቤ ነው። በክርስቶስ አምነን ዳግም ስንወለድ በተፈጥሮ ውርስ በሚገኝ ማንነት ውስጥ እናገኛለን። ውርስ የአንድን ነገር ወይም የአንድን ሰው ባህርይ መያዝ ሲሆን በአዲስ ተፈጥሯዊ ባህርይ እንደገና ተወልደናል፤ የእግዚአብሔር ተፈጥሯዊ ባህርይ ወራሾች ሆነናል የሚለውን እውነታ የሚያረጋግጥልን ነው። በክርስቶስ አምነን ዳግም ስንወለድ የክርስቶስ ልብ ተሰጥቶናል። እርሱ የሚያስበውን የማሰብ ብቃትና የመለኮትን ምስጢር የመረዳት አቅም አለን።

1.1 ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተፈጥሯል ♥ «እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት

አድርጎፈጠራቸው።»ዘፍ1፥27

ሁላችንም “በእግዚአብሔር አምሳል” መፈጠራችንን ከልጅነት እስከ እውቀት ስንሰማው የቆየነው ጉዳይ ነው። በእውነቱ ይህ መልካም ሀሳብ ነው። ምናልባትም የሰው ልጅ ለራሱ የሚሰጠውን ግምት ለማስታወስ ሲያስብ በአዕምሮው የሚከሰት የመጀመሪያ ሀሳብ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እኛ ሰዎች በራሳችን የፊታችን ገፅታ በመልክ ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን ጥቁር፣ አንዳንዶቻችን ነጭ፣ ገሚሶቻችን ደግሞ ጠይም ስንሆን በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶቻችን የረዘምን የተቀረነው ደግሞ አጠር ያልን፣ አንዳንዶቻችን ወፍራም ሌሎቻችንም ቀጭኖች ነን። ታዲያ እኛ ራሳችን ሳንመሳሰል ጌታን እንዴት ልንመስለው እንችላለን? እውነት “በእግዚአብሔር መልክ መፈጠር ማለት ምን ማለት ነው?”

የልጆችን ባህርይና እንዴት ቤተሰቦቻቸውን እንደሚመስሉ በመመልከት በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠር ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተሻለ መልኩ መረዳት እንችላለን። ልጆች ራሳቸውን ሆነው እያለ ወላጆቻቸውን በአካልና በባህርይ መስለው ይወለዳሉ። አብዛኛውን ጊዜ ህፃናት ከወላጆቻቸው አንዳቸውን በመልክ ሲመስሉ ድርጊታቸው ደግሞ እንደ ሌላኛው ወላጅ ሊሆን ይችላል፤ ይህንንም በማንሳት ህፃናት የቤተሰቦቻቸውን ባህርይና አገላለፅ ወርሰዋል ሲባል ይስተዋላል።

ሁላችንም ለወላጆቻችን ልዩ የሆነ የራስ ማንነት ያለን ግለሰቦች ነን። የእግዚአብሔር ልጅ ስንሆንም በተለያየ መልኩ የእርሱን ባህርይ አገላለፅ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እናሳያለን። እግዚአብሔር አዳምና ሄዋንን በአምሳሉ ሲፈጥር የሰው ዘር የእርሱን መለኮታዊ ማንነት፣ ዝንባሌና የአስተዳደሩን ስርዓት በምድር ሁሉ ላይ እንዲያሰፍን ነው።

Page 17: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

7

እኛ ሰዎች በእግዚአብሔር መልክና አምሳል ተሰርተናል። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጠር እርሱን የሚመስልበትን የዘላለማዊነትን፣ የእውቀትን፣ የመልካምነትን እና የገዢነትን መንፈስ (እስትንፋስ) እፍ አለበት። ይህ እስትንፋስ ለየትኛውም ፍጥረት አልተሰጠም (ለመላእክትም ቢሆን)። የእግዚአብሔር የሆነው መንፈስ በእስትንፋሱ ውስጥ ባህርዩን በውስጣችን አኑሮልናል። ሰውንና እግዚአብሔርን ያመሳሰለውና ያገናኘው ይህ በውስጣችን ያለው የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው። እግዚአብሔር፥ መንፈስ ነፍስና (እሳቤ፣ ስሜት እና ፈቃድ) መንፈሳዊ አካል ያለው አምላክ ነው። ሰው መንፈስ ያለው ራሱን የሚገልጥበት ነፍስ ያለው ሲሆን በስጋዊ አካል ይገለጣል።

♥ “የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ ስጋችሁምጌታችንኢየሱስበመጣጊዜያለነቀፋፈጽመውይጠበቁ።”1ኛተሰ5፥23

የሰው ልጅ ከውድቀት በፊት የእግዚአብሔርን ማንነት፣ ፍጥረት እና ስልጣን የሚገልጥ ማንነት ነበረው። በገላ 5፥22 የተዘረዘሩት የመንፈስ ፍሬ የእግዚአብሔር ባህርያት ናቸው። እነኚህን የመንፈስ ፍሬ መለማመድና ለዓለም መግለጥ ከእኛ ከአዲስ ፍጥረቶች የሚጠበቅ ነው።

♥ “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ራስንመግዛትነው።”ገላ5፥22

† በ1ኛቆሮ13የተፃፈውንየፍቅርትርጉምበማንበብስለእግዚአብሔርፍቅርምንነትናየሰውልጅከውድቀትበፊትስለነበረውማንነትበይበልጥመረዳትእንችላለን።

♥ “ፍቅርይታገሣል፥ቸርነትንምያደርጋል፤ፍቅርአይቀናም፤ፍቅርአይመካም፥አይታበይም፤የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉንያምናል፥ሁሉንተስፋያደርጋል፥በሁሉይጸናል።”1ኛቆሮ13፥4-7

ከአዳምና ከሄዋን ውድቀት በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ረገመ። ከዛን ጊዜ ወዲህ የዚህ እርግማኑ ውጤት የሆኑ ብዙ ለውጦች ተስተናግደዋል። እሾህና አሜኬላ የተባሉ የተፈጥሯችን ያልሆኑ የአኗኗርና የባህርይ ለውጦች ፍጹም ወደተለየ ማንነት መርተውናል። ንፁህ፣ ፃድቅ እና ቅዱስ የነበረው የሰው ልጅ ተፈጥሮ በኃጢአትና በዓመፅ ተበክሏል። ለዘላለማዊነት የተፈጠረው ፍጡር ለሞት ተገዢ ሆኗል። ከዚህ ማንነት የተነሳ ምድርን በመግዛት ፈንታ ለምድራዊ ነገር ተገዢ ለመሆን ተገዷል። ንፁህ ልብ ሆኖ የተፈጠረው የሰው ዘር እንደ ቃየን

Page 18: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

8 9

ወንድሙን የሚገድል (ዘፍ 4)፣ እንደ አምኖን እህቱን የሚደፍር (2 ሳሙ 13)፣ እንደ ኢዮብ ሚስት አምላክህን ስደብና ሙት የሚል (ኢዮ 2)፣ እንደ ይሁዳ ወዳጁን የሚሸጥ (ሉቃ 22)፣ እንደ አይሁድ ቅዱሱን ሰቅለህ ወንበዴውን ፍታ የሚል ሆኗል (ማቴ 27)።

♥ “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይሥልጣንእንዳለውአለቃፈቃድ፥በፊትተመላለሳችሁባቸው።በእነዚህምልጆችመካከልእኛሁላችንደግሞ፥የሥጋችንንናየልቡናችንንፈቃድእያደረግን፥በሥጋችንምኞትበፊትእንኖርነበርንእንደሌሎቹምደግሞከፍጥረታችንየቁጣልጆችነበርን።”ኤፌ2፥1-3

♥ ለ̋ሴቲቱምአለ፥-በፀነስሽጊዜጭንቅሽንእጅግአበዛለሁ፤በጭንቅትወልጃለሽ፤ፈቃድሽምወደባልሽይሆናልእርሱምገዢሽይሆናል።አዳምንምአለው፥-የሚስትህንቃልሰምተሃልናከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝኩህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ካንተ የተነሳ የተረገመች ትሁን፤በሕይወትዘመንህምሁሉበድካምከእርስዋትበላለህ።ወደወጣህበትመሬትእስክትመለስድረስበፊትህወዝእንጀራንትበላለህ፤አፈርነህናወደአፈርትመለሳለህና።”ዘፍ3፥16-19

ነገር ግን ኢየሱስ የሰው ልጆች በውስጣቸው አዲስ ባህርይ ኖሯቸውና በድጋሚ ተወልደው አዲስ ፍጥረት እንዲሆኑ መንገድ ለመክፈት ወደዚህ ምድር መጥቷል። የጠፋውንም ሊፈልግ ወደ መሬት ወርዷል። በእርሱ መምጣትም ይህች በክፋት የቆሸሸች ዓለም ተቃራኒ በሆነ ማንነትና አዲስ በሆነ ምላሽ ተቀይራለች። የኃጢአት ብርድ ላንቀጠቀጣት ዓለም እርቃኑን በመሰቀል የጸጋውን ኩታ አልብሷታል። ለማየት በሚከብድ አሰቃቂ መንገድ ለሚወግሩት አካላት “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት ቂም የነገሰበት ልብን ሰብሮ ፍቅርን አስርጾበታል፤ ሞትን ድል አድርጎ በመነሳት ዘላለማዊነቱን መልሶለታል። እነዚህም ሁሉ በኃጢአት ምክንያት መስመሩን የለቀቀው የሰዎች ማንነት በክርስቶስ አዲስ አቅጣጫ መያዙን ያመለክታል።

♥ “ስለዚህማንምበክርስቶስቢሆንአዲስፍጥረትነው።አሮጌውነገርአልፏል፤እነሆሁሉምአዲስሆኗል።”2ኛቆሮ5፥17

♥ “በክርስቶስኢየሱስአዲስፍጥረትመሆንይጠቅማልእንጂመገረዝቢሆንወይምአለመገረዝአይጠቅምምና።”ገላ6፥15

† ጳውሎስአዲስፍጥረትየመሆንአስፈላጊነትንእንዲህሲልይናገራል።ኢየሱስአዲስየሰውንዘርጅማሬሊቀይስወደዚህምድርመጣ፤በመንፈሱምየተወለዱወንዶችናሴቶችልጆቹበውስጣቸውየእግዚአብሔርባህርያዊማንነትአለ።

♥ “እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮበመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስንሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱሁለታቸውንበአንድአካልከእግዚአብሔርጋርያስታርቅዘንድነው።”ኤፌ2፥15-16

♥ “አይሁዳዊወይምየግሪክሰውየለም፥ባሪያወይምጨዋሰውየለም፥ወንድምሴትምየለም፤ሁላችሁበክርስቶስኢየሱስአንድሰውናችሁና።”ገላ3፥28-29

† ክርስቲያንመሆንማለትአንድንየእምነትአቋምማራመድሳይሆንበክርስቶስመሆንማለትነው።ዋናውጥያቄ“በክርስቶስመሆንማለትምንማለትነው?”የሚለውነው።

Page 19: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

9

1.2 ስለ አዲስ ፍጥረት የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ቃል

† በሕዝ36፥26-27ላይዳግምስንወለድስለሚሆነውነገርምስልከሳችበሆነትንቢታዊቃልአስቀምጦታል።

♥ “አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁበትእዛዜምአስሄዳችኋለሁ፥ፍርዴንምትጠብቃላችሁታደርጉትማላችሁ።”ሕዝ36፥26-27

እግዚአብሔር ከሰውነት አካላት ሁሉ ዋነኛ የሆኑትን አዲስ ልብንና አዲስ መንፈስን አጎናፅፎናል። የነገሮች ሁሉ ምንጭ ልብ (አዕምሮ) ነውና። አንዲት መኪና ሌላው አካላቷ በሙሉ አዲስ ሆነው ሞተሯ ግን ያረጀ ከሆነ ምንም አትጠቅምም። ምክንያቱም የመኪናዋ ሁለንተና በሞተሩ ጉልበት ይወሰናልና። መላ አካላቷ ቢቆሽሽ ምንም ችግር ላይኖረው ይችላል። ሞተሩ ከቆሸሸ ግን መኪናዋ መንቀሳቀስ ያቅታታል። የሰው ልጅ ልቦናም እንደመኪናዋ በመሆኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ “…ልብህን ጠብቅ፤” በማለት ይናገራል። የሰው ልብ ከቆሸሸ ወይም ካረጀ መልካም አይደለም። ምክንያቱም ልባችን የማንነታችን መገለጫ ነውና ። ነፍሳችን የምትገኘው ልባችን ውስጥ ሲሆን የአስተውሎታችንና የስሜታችን ውህድ ናት። ልባችን ደግሞ መንፈሳችንና ነፍሳችን የሚገኙበት ቦታ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል በእርግጥ እንደገና ተወልደናል ማለት ነው። አንድ ነገር ተወለደ ሲባል ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰትን ያመለክታል። የሕዝቅኤል መጽሐፍ (36፥26-27) እግዚአብሔር አዲስ ልብና አዲስን መንፈስ እንደሚሰጠን ሲናገር የቀድሞ ልባችንን እንደገና እንደሚሰራው ሳይሆን የሚያመለክተው፣ አልገዛ ያለውን ልባችንን አውጥቶ ከዚህ በፊት ያልነበረንን አዲስ ልብን እንደሚሰጠን ነው። ኃጢአታችንን ከመንፈሳችን አላጠበልንም፤ ነገር ግን መንፈሱን በውስጣችን አደረገ። ከዚህ በፊት በውስጣችን ያልነበረን አዲስን መንፈስ ሰጠን። እንደገና ተወልደናል፤ በመንፈሳችን አዲስ ሆነናል፤ አዲስ ልብ ተሰጥቶናል። ስለዚህ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ሆነናል። አዲስ ፍጥረት ስለሆንን አሁን አዲስ ማንነት አለን። (2ኛ ቆሮ 5፥17)

† ብዙ ሰዎች ስለ ልብ ሲናገሩ የኤርሚያስን መጽሐፍ በተሳሳተ መንገድ ይጠቅሳሉ።ትንቢተ ኤርሚያስ ምዕራፍ 17 ቁጥር 9 ላይ “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛናእጅግምክፉነው፤ማንስያውቀዋል?”በማለትየሰውንማንነትአስቀምጦታል።እዚህጋርአንድየተረሳውነገርመጽሐፉየተፃፈውላልተለወጠማንነትመሆኑንነው።

♥ “ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስካልተወለደበቀርወደእግዚአብሔርመንግሥትሊገባአይችልም።”ዮሐ3፥5-7

† የእግዚአብሔርአምሳያነን(2ኛጴጥ1፥4)፤በክርስቶስአንድመንፈስመሆንችለናል(1ኛቆሮ6፥17)፤የመንፈስፍሬተሰጥቶናል(ገላ5፥22-23)፤ፅድቅአግኘተናል(2ኛቆሮ5፥19፣ሮሜ5፥17-18)፤ቅዱስ፣ነቀፋየሌለውሆነናል(ቆላ1፥21-22)፤ለዘላለምፍፁምሆነናል(ዕብ10፥14)፤የክርስቶስልብተሰጥቶናል(1ኛቆሮ2፥16)፤እነዚህምከተሰጡንአዳዲስማንነቶችመሀከልመጠቀስይችላሉ።

Page 20: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

10 11

1.3 ለምን እንታገላለን?እስካሁን ያልነው ሁሉ እውነት ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እኛ የሚናገረውን መሆን ለምን

አልቻልንም? ከስጋዊ ኃጢአት ጋር ለምን በየእለቱ እንታገላለን? ሰይጣን እንዴት አካላዊና ስነ ልቦናዊ ችግር ሊፈጥርብን ቻለ? እንዴት በእኛ ውስጥ ያለውን የክርስቶስ መለኮታዊ ባህርይ ተካፋዮች መሆን እንችላለን?

ከላይ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች መልስ ሊሆን የሚችለው እኛ ዳግም የተወለድነው ከመንፈሳችን የተነሳ አዲስ ልብ ተሰጥቶናል። ነገር ግን ነፍሳችን ዳግም አልተወለደችም።

መጽሐፍ ቅዱስ ፍጥረት ስጋ፣ መንፈስ እና ነፍስ እንዳለው ያስተምራል። በአንዳንድ ቦታዎች ላይ መንፈስንና ነፍስን እየቀያየረ ቢጠቀምም በሌሎች ቦታዎች ላይ ግን እንደሚለያዩ በግልፅ አስቀምጧል። በዕብራውያን 4፥12 ላይ እንደተገለፀው ከሰው አዕምሮ በላይ ሊሆን የሚችል ነገር ግን ግልፅ የሆነ ልዩነት በመንፈስና በነፍስ መካከል አለ።

በክርስትናው ዓለም የሰው ልጅ ከምን እንደተሰራ ከሚንፀባረቅባቸው የተለያዩ አመለካከቶች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት የ“ዳይኮቶሚ”ና የ“ትራይኮቶሚ” ዶክትሪኖች ናቸው።

† የዳይኮቶሚአስተምህሮየሰውልጅበስጋናበነፍስብቻየተዋቀረነውየሚልሲሆንሰው በስጋው ከቁሳዊው ዓለም ጋር መገናኛ እንደሆነና መንፈስ ግን ከመንፈሳዊውዓለም ጋር (ከእግዚአብሔር ጋር) የሚያገናኝ የነፍስ አንድ ክፍል እንደሆነ ይገልፃል።(ዘፍ2፥7፣መክ125፥7፣ማቴ10፥28፣2ኛቆሮ5፥1-10)

† የትራይኮቶሚ አስተምህሮ የሰው ልጅ በስጋ፣ በነፍስ እና በመንፈስ የተዋቀረ ነውየሚልነው።የሰውልጅስጋዊአካልከቁሳዊውዓለምጋርሲያገናኘውነፍስደግሞየማንነት/የሀለወትምንጭእንደሆነእንዲሁምመንፈስደግሞከአምላክጋርየሚያገናኝእንደሆነይገልፃል።በዚህአስተሳሰብመሰረትሶስቱምየራሳቸውማንነትእንዳላቸውያስቀምጣል።በዚህምምክንያትያልዳነሰውመንፈሳዊሞትንእንደሚሞትይታመናል።(1ኛተሰ5፥23፣ 1ኛቆሮ 15፥44፣ሉቃ 10፥27፣ኤፌ2፥1፣ቆላ2፥13፣ሉቃ 1፥46-47፣ኢሳ26፥9)

Page 21: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

11

1.4 ነፍሳችንና መንፈሳችንበነፍሳችንና በመንፈሳችን መካከል ያለውን ልዩነት ስናውቅ እኛና ሌሎች አማኞች

ለምን ከእግዚአብሔር መንገድ የራቀ ድርጊትን እንደምናደርግ መረዳት አንችላለን። ጳውሎስ ሁላችንንም ስለሚገጥመን ስለዚህ ትግል በ ሮሜ 7፥19 ላይ እንዲህ ሲል አስፍሯል። “የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎ ነገር አላደርገውም።”

በመንፈሳችን ዳግም ብንወለድ እንኳን ነፍሳችን ዳግም ስላልተወለደች በሁለቱ መካከል ያለውን የፈቃድ ልዩነት እንድናውቅ የእግዚአብሔር ቃል እውቀትና የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ያስፈልገናል።

♥ የእግዚአብሔርቃልህያውነውናየሚሰራምሁለትአፍካለውሰይፍሁሉይልቅየተሳለነውነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለያይ ድረስ ይወጋል የልብንም ስሜትናሃሳብይመረምራል፤ዕብ4፥12-13

† ያዕቆብበመልእክቱስለነፍስናስለመንፈስልዩነትፅፏል፤(“ስለዚህርኩሰትንሁሉየክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁምየተተከለውንቃልበየዋህነትተቀበሉ።”ያዕ1፥21)

1.5 የነፍስ ባህርያት

ነፍሳችን የተፈጥሮ አካል ስትሆን የተፈጠረችበት ዓላማም የእግዚአብሔርን ማንነት፣ ባህርይውን እና ስልጣኑን ለዓለም ሁሉ እንድትገልጥ ነው። ችግሩ ግን የነፍሳችን ስሜትና ሀሳብ የተሰራው በዚህ በወደቀው ማንነት ነው። ነፍሳችን በአዕምሮ፣ በስሜት እና በፈቃድ የተዋቀረች ነች። አዕምሮ፥ መረዳታችን፣ ስሜት ፈቃድ፥ ምርጫችንን የምናውቅበት ኃይል ነው።

† የነፍስ ባህርይ የተገነባው በኃጢአት በተበከለ መንፈስ፣ መልካም ባልሆነ ማንነት፣በአምስቱየስሜትህዋሶች፣በቤተሰቦቻችንናበባህላችንወዘተ…ነው።

1.6 የነፍስ ተፅዕኖ ♥ ከእግዚአብሔርእንደሆንንዓለምምበሞላውበክፉውእንደተያዘእናውቃለን።1ኛዮሐ5፥19

† ነፍሳችንጠላትየተሳሳተአመለካከትንምሽግየሚሰራበት (2ኛቆሮ 10፥3-5)፣ስጋዊልማዶች የሚመነጩበት (ገላ 5፥19-21)፣ የሰው ጥበብ መነሻ (1ኛ ቆሮ 2፥4)፣ ራስንመፈለግ፣ ራስን መውደድ፣ ራስን ማፅደቅ የሚያድግበት “አንተ የምታደርገውን ነህ”የሚለውየተሳሳተአመለካከትየሚመነጭበትነው።

Page 22: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

12 13

1.7 የስጋ ወይም የአካል ባህርያትአካላችን አምስት ስሜቶችን የያዘ ሲሆን ማየት፣ መዳሰስ፣ መቅመስ፣ ማሽተት እና ማድመጥ

ናቸው። እነኚህ ስሜቶች በሰው ምክንያታዊነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን የሚያመጡ ከመሆናቸውም በላይ ተፈጥሯዊውን ግዛት ለመረዳት ዋና ምንጮች ናቸው። ተፈጥሯዊው ሰውና ስጋዊው ክርስቲያን የሕይወት ውሳኔን ለመወሰን በዋናነት የሚጠቀሙት ከአምስቱ ስሜቶች የሚያገኙትን መረጃ ነው።

1.8 አሮጌው ሰውና አዲሱ ሰውሐዋሪያው ጳውሎስ በክርስቶስ የሆነውን አዲሱን ሰውና አሮጌውን ሰው ያነፃፅራል።

ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ሲሆኑ ስለሚገጥማቸው የዕለት ተዕለት ተግዳሮት ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክት ላይ በምዕራፍ 4 በቁጥር 22-24 በግልፅ ጽፏል። 22- ፊተኛ ኑሯችሁን እያሰባችሁ 23- በአዕምሯችሁ መንፈስ ታደሱ፣ 24- ለእውነትም በሚሆኑ ፅድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ እያለ ተናግሯል።

በነፍስ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ነገሮች

Page 23: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

13

♥ “በእርግጥሰምታችሁታልና፥እውነትምበኢየሱስእንዳለበእርሱተምራችኋል፤ፊተኛኑሯችሁንእያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአዕምሯችሁምመንፈስታደሱ፥ለእውነትምበሚሆኑጽድቅናቅድስናእንደእግዚአብሔርምሳሌየተፈጠረውንአዲሱንሰውልበሱ።”ኤፌ4፥21-24

1.9 አዲሱን ፍጥረት መረዳት

ለበርካታ አመታት የአዲስ ፍጥረት ምንነትን አብዛኛው ክርስቲያን በጥልቀት ያልተረዳው ጉዳይ ነበር። አብዛኞቻችን የምናስበው ኃጢአተኞች እንደነበርን ነገር ግን በጸጋው እንደዳንን ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክርስቶስ ያለንን እውነተኛ ማንነት ለማወቅ ጥሩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው።

እንደ አማኝ የሚገጥመን ተፃራሪ ሀሳብ አለ። እየሆንን ያለነው የነበርነውን ነው። እንደ አማኞች ቅዱስ ወይም ፃድቅ ለመሆን ባህርያችንን በራሳችን መቀየር አንችልም። ነገር ግን ባህርያችን በበጎ መልኩ ልንቀይር የቻልነው አዲስ ፍጥረት ስለሆንንና ክርስቶስን ስንቀበል ቅዱስና ፃድቅ ተደርገን እንደገና ስለተፈጠርን ነው። ይህንን የእድገት ሂደት ለመረዳት አዲስ ከተወለደ ልጅ ጋር እናነፃፅረው።

አንድ አዲስ ለተወለደ ህፃን ልጅ ወንድነት ወይም ሴትነት፣ ማንነት፣ የመጣበት ቤተሰብ ምንም ትርጉም አይሰጠውም። ነገር ግን ወደማንነቱ ማደግና መብሰል እንዳለበት ጥያቄ የማያስነሳ ጉዳይ ነው። ዳግም ለተወለድነው ለእኛም ይህ ምሳሌ ይሰራል። ሁላችንም በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ያለው ክርስቶስን እንድንመስል በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እያሳደገን ነው። እየሆንን ያለነው የሆነውን ነው። የታየልን ማንነታችን ላይ በፅድቅ መንገድ ማደግ እንጀምራለን።

1.10 ደህንነታችንን ማስፈፀም“ማስፈፀም” ማለት በውስጥ ያለን ነገር ወደውጭ ማውጣት፣ የነበረውን ነገር ወደ መሬት

ማውረድ ወይም በተግባር ላይ እንዲውል ማድረግ ማለት ነው። በሕይወታችን ላይ የእግዚአብሔር ማንነት(ተፈጥሮ) እንዲታይ የሚያደርገው በውስጣችን ያደረው እግዚአብሔር ራሱ ነው። ይህ አዲስ የሆነ ማንነት በሕይወታችን መንሰራፋት ሲጀምር አሮጌው ፍጥረት፣ ኃጢአት፣ ቁጣ፣ ፍርሀት፣ መስገብገብ፣ የመሳሰሉት ሁሉም ስጋዊ ማንነቶች ከሕይወታችን መገፋትና መውጣት ይጀምራሉ። ይህንን ሂደት ካልተረዳን ለጠላት ክስ ተጋላጮች እንሆናለን።

♥ “ስለዚህ፥ወዳጆቼሆይ፥ሁልጊዜእንደታዘዛችሁ፥በእናንተዘንድበመኖሬብቻሳይሆንይልቁንአሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ ስለበጎ ፈቃዱ መፈለግንምማድረግንምበእናንተየሚሠራእግዚአብሔርነውና።”ፊል2፥12-13

እኛ የክርስቶስ አማኞች በክርስቶስ ዘንድ ስለፀደቅን ከፍርድ የዳንን ነን። በድካማችን ምክንያት ፈተናዎች ሊገጠሙን ወይም ወደ ፈተና ልንገባ እንችላለን። በራሳችን ምኞትና ፍላጎት ወዳልተገባ መንገድ መሳብና መታለላችን የስጋ ድካማችን መገለጫዎች ናቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ባህርያችንን እንደሞተ ሰው እንድንተወው ይፈልጋል:: በዚህ ሂደት ምሽጎች ይጋለጣሉ። በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እነኚህን ምሽጎች ማፍረስና ክርስቶስን ወደ መምሰል እናድጋለን።

Page 24: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

14 15

♥ “እግዚአብሔርበማንኛውምሁኔታአይፈትነንም።ማንምሲፈተን፥በእግዚአብሔርእፈተናለሁአይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም። ነገር ግንእያንዳንዱበራሱምኞትሲሳብናሲታለልይፈተናል።”ያዕ1፥13-14

የእግዚአብሔር ቃልኪዳንና በመንገዳችን ላይ ያሉ የጠላት ምሽጎች ♥ “ለሙሴመንገዱንአስታወቀ፥ለእስራኤልልጆችምአደራረጉን።”መዝ103፥7

1.11 አሮጌውን ሰው ማስወጣት

ንጉስ ዳዊት ልጁን ሰለሞንን ሲመክረው “ልጄ ሆይ ሰው ሁን” አለው (1ኛ ነገ 2፥2)። የአብራኩን ክፋይ “ሰው ሁን” ያለው ሰው የመሆን ትርጉሙ ምን ቢሆን ነው? መልሱ ግልጽ ሲሆን መልእክቱም እግዚአብሔር ያዘዘህን ፈፅም፤ ራስህን ከኃጢአት መንገድ አርቅ፤ ያደፈው ማንነትህን ትተህ የፈጠረህን አምላክ የሚገልፀውን አዲሱን ሰው ሁን ማለቱ ነው። ስለዚህ ሰው የመሆን ትርጉሙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ መራመድ መቻል፣ በሁለት እጅ ስራዎችን መፈጸም እና ማሰብ መቻል ብቻ ሳይሆን ሌላ ሁኔታም እንዳለ ያሳያል። አሮጌውን ማንነት አውልቀን ስንጥለው ሰው እንሆናለን። ሰው ደግሞ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው።

♥ “ከእንግዲህስወዲያለኃጢአትእንዳንገዛየኃጢአትሥጋይሻርዘንድአሮጌውሰዋችንከእርሱጋርእንደተሰቀለእናውቃለን፤የሞተስከኃጢአቱጸድቋልና።”ሮሜ6፥6

♥ “ሁሉኃጢአትንሠርተዋልና፥የእግዚአብሔርምክብርጎድሎአቸዋል፤”ሮሜ3፥23

Page 25: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

15

† የአሮጌው ሰው ልማድና አመለካከት መሰረት ያደረጋቸው ስጋዊነት፣ ራስን የመውደድዝንባሌእናባህርይናቸው።

♥ “የሥጋሥራምየተገለጠነውእርሱምዝሙት፥ርኵሰት፥መዳራት፥ጣዖትንማምለክ፥ምዋርት፥ጥል፥ክርክር፥ቅንዓት፥ቁጣ፥አድመኛነት፥መለያየት፥መናፍቅነት፥ምቀኝነት፥መግደል፥ስካር፥ዘፋኝነት፥ይህንምየሚመስልነው።”ገላ5፥19-21

♥ “መራርነትና ንዴት፥ ቁጣም፥ ጩኸትም፥ መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድይወገድ።”ኤፌ4፥31

1.11.1 ስለዚህ እንዴት አሮጌውን ማንነት ማስወገድ እንችላለን?

ሰዎች በመጀመሪያ አስተሳሰባችን፣ ስሜታችን እና ባህርያችን የፈለጉትን ቢሉን ያ አሮጌው ማንነታችን ከክርስቶስ ጋር መሰቀሉን ማመን አለብን። እኛ ደግሞ በጥምቀት አማካኝነት የሞቱ ተካፋዮች ሆነናል። ጥሩው ዜና አሮጌው ሰውነታችን ሞቷል። ይህ ማንነታችን የሞተው ልክ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል ነው። የዚህ ማንነት ኃይል የተወገደው በማመናችንና በጥምቀት አማካኝነት ነው። መሞታችን የአዲሱ ማንነታችን አካል ሆኗል። ከዚህ በኋላ የኃጢአት ባሪያ ሳንሆን የእግዚአብሔር ውድ ልጆች ነን። አሮጌው ማንነታችንን አሽቀንጥሮ ለመጣል ግን በፍጹም ልብ በአምላካችን መታመን ይገባናል። የወርቅ ቅብ የሆነ ብረት ወርቅን መሆን እንደማይችል ሁሉ “አማኝ ነኝ” የሚል ነገር ግን በልቡ ጌታን የሚክደው ቢኖር አዲስ መሆን አይችልም። ልብ በእምነት ለጌታ መንፈስ ሲከፈት መታደስ ይሆንለታል።

♥ “እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። ለኃጢአትየሞትን እኛ ወደፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድእንሆንዘንድየተጠመቅንሁላችንከሞቱጋርአንድእንሆንዘንድእንደጠመቅንአታውቁምን?”ሮሜ6፥1-3

♥ “ከክርስቶስጋርተሰቅዬአለሁ፤እኔምአሁንሕያውሆኜአልኖርምክርስቶስግንበእኔይኖራል፤አሁንምበሥጋየምኖርበትኑሮበወደደኝናስለእኔራሱንበሰጠውበእግዚአብሔርልጅላይባለእምነትየምኖረውነው።”ገላ2፥20

በውልደት የምናገኘው ማንነትና ተፈጥሯዊ ባህርይ ክርስቶስን ስንቀበል እንደሞተ እናውቃለን። ስለዚህ በአዲሱ ተፈጥሯችን መኖር እንችላለን። በዚህም የመለኮታዊ ባህርይ ተካፋዮች እንሆናለን። በቃሉ እምነት መለኮታዊ ማንነቱን እንካፈላለን።

† በክርስቶስያለንአዲስማንነት:

• ከመንፈስየተወለድንመሆኑን(ከሥጋየተወለደሥጋነው፥ከመንፈስምየተወለደመንፈስነው።ዮሐ3፥6)፣

• በመንፈሳችን ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆንን (ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።1ኛቆሮ6፥17)፣

• በክርስቶስየፀደቅንመሆኑን(ከእግዚአብሔርዘንድጥበብናጽድቅቅድስናምቤዛነትምበተደረገልንበክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው። 1ኛ ቆሮ 1፥30፤ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔርጽድቅእንሆንዘንድኃጢአትያላወቀውንእርሱንስለእኛኃጢአትአደረገው።2ኛቆሮ5፥21)፣

Page 26: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

16 17

• ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለብን፣ ምግባረ መልካም መሆናችን (እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁናቅዱሳንአድርጎበእርሱፊትያቀርባችሁዘንድ፥በፊትየተለያችሁትንክፉሥራችሁንምበማድረግበአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።ቆላ1፥21-22)፣

• ለዘላለምፍፁምመሆናችን(አንድጊዜበማቅረብየሚቀደሱትንየዘላለምፍጹማንአድርጎአቸዋልና።ዕብ10፥14)፣

• የመንፈስ ፍሬዎች ባለቤት መሆናችንን ያሳየናል። (የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ትዕግሥት፥ቸርነት፥በጎነት፥እምነት፥የውኃት፥ራስንመግዛትነው።እንደዚህያሉትንየሚከለክልሕግየለም።የክርስቶስኢየሱስምየሆኑቱሥጋንከክፉመሻቱናከምኞቱጋርሰቀሉ።ገላ5፥22)ከአዲሱ ተፈጥሯችን ጋር አዲስ የሕይወት ለውጥ ይመጣል። ከዚህ የተነሳ አዲስ የሆነ ማንነትመመስረትእንችላለን።

1.12 በክርስቶስ ያለን አዲስ ቦታ (ማንነት፥ ስለራሳችን ያለን አመለካከት)

በክርስቶስ ያለን አዲስ ቦታ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት መሸጋገር ነው። በክርስቶስ ደም የኃጢአት ስርየትን አግኝተናል። በቤዛነቱ ከእስራት ነፃ ወጥተናል። በመንግስተ ሰማይ ከእርሱ ጋር ሆነናል፤ ፀድቀናል፤ ተቀድሰናል፤ ለተለየ ዓላማ ተመርጠናል፤ በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል፤ የመንግስተ ሰማይ ዜጎች ሆነናል፤ የክርስቶስ እንደራሴዎች ሆነናል፤ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን።

♥ “እርሱከጨለማሥልጣንአዳነን፥ቤዛነቱንም፥እርሱንምየኃጢአትንስርየትወዳገኘንበትወደፍቅሩልጅመንግሥትአፈለሰን።”ቆላ1፥13-14

♥ “በውድልጁም፥እንደጸጋውባለጠግነትመጠን፥በደሙየተደረገቤዛነታችንንአገኘንእርሱምየበደላችንስርየት።”ኤፌ1፥7

♥ “ከእርሱጋርአስነሣንበክርስቶስኢየሱስምበሰማያዊስፍራከእርሱጋርአስቀመጠን።”ኤፌ2፥6

♥ “ያንመንፈስም፥በጸጋውጸድቀንበዘላለምሕይወትተስፋወራሾችእንድንሆን፥በመድኃኒታችንበኢየሱስክርስቶስበእኛላይአትርፎአፈሰሰው።”ቲቶ3፥6-7

♥ “በዚህምፈቃድየኢየሱስክርስቶስንሥጋአንድጊዜፈጽሞበማቅረብተቀድሰናል።”ዕብ10፥10

♥ “ደግሞምያተመንየመንፈሱንምመያዣበልባችንየሰጠንእርሱነው።”2ኛቆሮ1፥22

♥ “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስክርስቶስንእንጠባበቃለን፤”ፊል2፥20

♥ “እንግዲህእግዚአብሔርበእኛእንደሚማልድስለክርስቶስመልክተኞችነን፤”2ኛቆሮ5፥20

† ስለዚህአሮጌውንማንነትአውጥተንአዲሱንማንነትለብሰንእንዴትእንደአዲስፍጥረትመጓዝእንችላለን?ለሚለውጥያቄመልስእነሆ፦

♥ “እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤ በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትምበኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞትየሚጠፋውንአሮጌውንሰውአስወግዱ፥በአዕምሮአችሁምመንፈስታደሱ፥ለእውነትምበሚሆኑ

Page 27: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

17

ጽድቅናቅድስናእንደእግዚአብሔርምሳሌየተፈጠረውንአዲሱንሰውልበሱ።ስለዚህውሸትንአስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትንተነጋገሩ። ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስምፈንታ አትስጡት። የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለውየሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።መራርነትናንዴትቁጣምጩኸትምመሳደብምሁሉከክፋትሁሉጋርከእናንተዘንድይወገድ።እርስበርሳችሁምቸሮችናርኅሩኆችሁኑ፥እግዚአብሔርምደግሞበክርስቶስይቅርእንዳላችሁይቅርተባባሉ።”አፌ4፥20-32

1.13 ቃል ኪዳኑን መተግበር

የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን በሕይወታችን ውስጥ መተግበር ከምንችልባቸው መንገዶች የመጀመሪያውና ዋነኛው እግዚአብሔርን በማምለክና በማመስገን ነው።

♥ “ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩእግዚአብሔርቸር፥ምሕረቱምለዘላለም፥እውነቱምለልጅልጅነውና።”መዝ100፥4-5

በቀጣይነት የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳንና የቃሉን እውቀት በሕይወታችን ላይ ማወጅ ኪዳኑን ለመተግበር ያስችለናል።

♥ “ሞትናሕይወትበምላስእጅናቸው፤የሚወድዱአትምፍሬዋንይበላሉ።”ምሳ18፥21

♥ “ነገርንምትመክራለህ፥እርሱምይሳካልሃልብርሃንምበመንገድህላይይበራል።”ኢዮ22፥28

ምሳሌያዊ ጸሎትጌታ ሆይ በአንተ አዲስ ፍጥረት ስለሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ አከብርሃለሁ። በመንፈስ ከአንተ

ጋር አንድ ስለሆንኩ የመለኮታዊ ባህርይህ ተካፋይ ሆኛለሁ፤ ስለዚህም አመሰግንሃለሁ። ጌታ ሆይ በፊትህ ፃድቅ፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለብኝ እንድሆን ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ። ክርስቶስ በከፈለው መስዕዋትነት ለዘላለም በደሙ እንከን የለሽ ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ። የክርስቶስን ልብ ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ።

1.14 ማጠቃለያ

በሚቀጥሉት ትምህርቶች በመንፈስ እንድንጓዝና በሕይወታችን የእርሱን ማንነት እንድንለማመድ መሰናክል የሆኑብንን ነገሮች እንመለከታለን። ከመሰናክሎቹ መካከል ስብራትና የነፍስ እስራቶች፣ ከጠላት ውሸት ጋር የምንፈፅመው ስምምነትና ከጠላት ውሸት ጋር የምናደርገው በደል ይጠቀሳሉ።

♥ “የሰላምምአምላክራሱሁለንተናችሁንይቀድስ፤መንፈሳችሁምነፍሳችሁምሥጋችሁምጌታችንኢየሱስክርስቶስበመጣጊዜያለነቀፋፈጽመውይጠበቁ።”1ኛተሰ5፥23

Page 28: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

18 19

መንፈሳዊ ሰው ስጋዊ ሰው/ የሰው ምክንያታዊነት

መንፈሰ ♥ በክርስቶስአዲስ

ፍጥረትመሆን2ቆሮ5፥17

♥ አዲስግዛትቆላ1፥26-27

♥ አዲስሕይወትዮሐ6፥63

♥ ዳግምውልደትዮሐ3፥5-7

♥ መለኮታዊተፈጥሮ2ጴጥ1፥4

♥ የመንፈስፍሬዎችገላ5፥22-23

♥ ከክርስቶስጋርአንድመሆን1ኛቆሮ6፥17

♥ በክርስቶስተቀባይነትንማግኘትኤፌ1፥6

♥ ፅድቅ2ቆሮ5፥21

♥ ቅዱስ፣ነቀፋየሌለበት፣ፃድቅቆላ1፥21-22

♥ ፍፁምዕብ10፥14

♥ የክርስቶስአዕምሮ1ኛቆሮ2፥16

ነፍስ

ያዕ 1፥21

አካል

5ቱ የስሜት ህዋሳት

የስጋ ሰው ጥቂት ባህርያት • ማንነትንጉስነው፣የሰውስጋዊባህርይእኔነትዋናቦታውን

ይዟል፣

• ውሳኔዎችየሚደረጉትበሰውምክንያታዊነትነው።

• የራስንብቻመፈለግ፣ራስላይማተኮር፣ራስንመውደድ፣

• ስጋዊኑሮ፣

• በሰውልማድመመላለስ፣

• ኩራት፣ቅናት፣ምቀኝነት፣ክፉምኞት፣ቁጣ፣ፍርድ፣መታበይ፣

• ተስፋመቁረጥ፣መደንገጥ፣ደካማመሆን/መዛል

• ከእምነትጋርመታገል፣

• ስለእግዚአብሔርናስለራስየተዛባአመለካከት፣

• ጥልናቁጣየሞላበትሕይወት

• የሕይወትዋስትናማጣትናፍርሃት

Page 29: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

19

ምዕራፍ 2 የተሰበረውን ልብ መፈወስ

♥ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትምመፈታትንለዕውሮችምማየትንእሰብክዘንድ፥የተጠቁትንምነፃአወጣዘንድየተወደደችውንምየጌታንዓመትእሰብክዘንድልኮኛልተብሎየተጻፈበትንስፍራአገኘ።…”ሉቃ4፥18

† በዚህ ክፍል በሕይወታችን ያለውን የስብራት ምሽግ እንዴት እንደምናፈርስና ሌሎችምገብቷቸውእንዴትማፍረስእንደሚችሉእናያለን። • ስብራትንበተመለከተየእግዚአብሔርፈቃድ፥

• ስለልብመጽሐፍቅዱሳዊገለፃ፥

• እንዴትልባችንይሰበራል?

• ስብራትሲከሰትእንዴትማወቅእንችላለን?

• ለልባችንቁስልእንዴትፈውስንማግኘትእንችላለን?

2.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስብራትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ይነግረናል

በዓለማችን ላይ ብዙ ዓይነት የአካል ስብራት ይከሰታሉ። ቢሆንም አብዛኛው የአካል ስብራቶች በተለያዩ ባለሙያዎች የሚጠገኑ ናቸው። በሀገራችን ሊጠገኑ የማይችሉ ስብራቶች በውጪ ባለሞያዎች መፍትሔ ሊገኝላቸው ይችላል። የመንፈሳዊ ልብ ስብራት ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር በማንም ሊጠገን የማይችል ነው። “ምን ሆነህ ተሰበርክ?” ብሎ የማይጠይቅ፣ “እኔ ስላልቻልኩ ሂድና ዶክተር እገሌ ጋር ታይ” የማይል፣ “ብቸኛ ነኝና አጋዥ ዶክተር ይመደብልኝ የማይል” ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜም ልባቸው የተሰበረ ሰዎችን ሲጣራ ድምፁ ይሰማል።

♥ “እናንተደካሞችሸክማችሁየከበደሁሉ፥ወደእኔኑ፥እኔምአሳርፋችኋለሁ።”ማቴ11፥28

† ይህ ፍጹም ፍቅርን የተላበሰ ጥሪ የገባቸው እንደ መግደላዊት ማርያም ያሉ ሰዎች “ዛሬኃጢአትሽተሰርዮልሻል(ሉቃ7፥48)”፤በጎልጎታላይበቀኝእንደተሰቀለውወንበዴ“ዛሬከኔጋርበገነትትሆናለህ(ሉቃ23፥43)”ተብለዋል።

i. ኢየሱስ ሰዎች ወደ እርሱ ቢመጡ እንደሚፈውሳቸው ለደቀመዛሙርቱ ተናግሯል፤ ♥ “ከእርሱምኃይልወጥቶሁሉንይፈውስነበርናሕዝቡሁሉሊዳስሱትይሹነበር።”ሉቃ6፥19

♥ “እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ ሰምቶ ልጁ ሊሞት ስላለው ወደ እርሱ ሄደወርዶምእንዲፈውስለትለመነው።”ዮሐ4፥47

Page 30: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

20 21

♥ “በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሯቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውምእንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሯቸውም ደንቁሯል ዓይናቸውንምጨፍነዋልየሚልየኢሳይያስትንቢትበእነርሱይፈጸማል።”ማቴ13፥15

ii. ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሁ ሲመጣ የተሰበረን ልብ እንደሚፈውስ(እንደሚጠግን)

ተናግሯል። ♥ “የጌታየእግዚአብሔርመንፈስበእኔላይነው፥ለድሆችየምሥራችንእሰብክዘንድእግዚአብሔር

ቀብቶኛልናልባቸውየተሰበረውንእጠግንዘንድ፥ለተማረኩትምነፃነትንለታሰሩትምመፈታትንእናገርዘንድልኮኛል።የተወደደችውንየእግዚአብሔርንዓመትአምላካችንምየሚበቀልበትንቀንእናገርዘንድ፥የሚያለቅሱትንምሁሉአጽናናዘንድ፤እግዚአብሔርለክብሩየተከላቸውየጽድቅዛፎችእንዲባሉለጽዮንአልቃሾችአደርግላቸውዘንድ፥በአመድፋንታአክሊልን፥በልቅሶምፋንታየደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።”ኢሳ61፥1-3

† በሉቃ4፥18-21ኢየሱስከኢሳ61፥21ላይያነበበውትንቢትበእርሱበኩልእንደተፈፀመምተናግሯል። መጽሐፍ ቅዱስ የተሰበረን ልብ መጠገን (መፈወስ) የእግዚአብሔር ፈቃድእንደሆነይነግረናል።

♥ “…እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።”መዝ34፥18

♥ “…ልባቸውንየቈሰሉትንይፈውሳል፥ሕማማቸውንምይጠግናል።”መዝ147፥3

2.2 ስብራት ምንድን ነው?

I. የስብራት ምንነት

ስብራት ብለን የምንገልፀው የስሜት ዓይነት ውስጣችን ካልጠበቅነው ነገር የተነሳ በጣሙን ሲያዝን የሚሰማንና ምንም ዓይነት የማፅናኛ ቃላት ወይም ማንኛውም ዓይነት ሰው ሊያስረሳን የማይችለው የሀዘንና የመጎዳት ድብልቅ የሆነ ስሜት ነው።

† ኢየሱስ ሊፈውሰው ከመጣው የስብራት አይነቶች አንዱ በሕይወታችን በሚገጥሙንመረሳቶችናመገለሎችምክንያትየሚመጣውንስብራትነው።

II. አሳዛኝ አጋጣሚዎችና መገለሎች ልባችንን ሊሰብሩ ይችላሉ • ነውር(ከባህልናከተለመደውሁኔታውጪእንደአፀያፊተግባርየሚቆጠሩነገሮች)

• የቃል፣አካላዊና፣ፆታዊጥቃቶች

• መተው/መጣል

• አዕምሯዊናስሜታዊጥቃት

† ኢየሱስየተሰበረልባችንንሊፈውስመጣስንልምንማለታችንእንደሆነመረዳትአስፈላጊነው።

Page 31: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

21

2.3 ልብ ምንድን ነው?

የዕብራይስጥ ቋንቋ ልብን “ሌብ (labe)” ይለዋል። ይህም የህያውነታችን፣ የአዕምሯችን፣ የእሳቤያችን እና የስሜታችን መካከለኛ (inner man, mind, will, heart) ሲሆን የግሪኩ (kar-dee”-ah) - ነፍስ፣ ልብ፣ ሃሳብ፣ የስሜት መካከል ይለዋል (the heart; mind, character, inner self, will, intention, center) ። (Strong”s Concordance፣ Bible Hub)

2.3.1 ልብ እንዴት ይሰበራል?በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የህያውነታችን፣ የነፍሳችንና የአዕምሯዊ ስሜቶታችን መካከለኛ

እንደሆነ ተገልጧል። በአዲስ ኪዳንም ሆነ በብሉይ ኪዳን ላይ ብዙ ክፍሎች የልብን ባህርይ የሚገልፁ የጥቅስ ክፍሎች አሉ። ለምሳሌ ያህል ልብ ያዝናል (ሕዝ 13፥22፣ ይታለላል (ኢሳ 44፥20፣ ሮሜ 16፥18)፣ ክፋትን ያስባል (ማር 7፥21)፣ ይመኛል (2ኛ ጴጥ 2፥14)፣ ያስተውላል (ዘዳ 29፥4፣ ኢዮ 38፥36)፣ ያውቃል (2ኛ ዜና 26፥5፣ ኤር 24፥7)፣ ይፈራል (ኢሳ 35፥4) እና ሌሎች ብዙ በልብ የሚደረጉ የሕይወት ጉዞዎች ተጽፈዋል። በአብዛኛው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ልብ አድርግ” የሚለው ሀረግ ሲገኝ ይህም የማስተዋልንና አመዛዝኖ የመጓዝ ጥበብ በልብ ውስጥ እንደተቀመጠ ያሳየናል።

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የልብ ስብራት የሚመነጨው ከጠበቅነውና ካሰብነው ውጤት ውጪ ሌላ ውጤት ሲከሰትና አሉታዊ ተፅዕኖን ሲያመጣብን ነው። በተጨማሪም የልብ ስብራት ብዙውን ጊዜ በፍፁም ማንነታችን ያመንነው ነገር ፈርሶ ስናየው የሚደርስብን ከባድ የሆነ ሀዘንን ይገልፃል። ብቸኝነት፣ በሰው ዘንድ መጠላት፣ መረሳት፣ አፅናኝ ማጣት እና ሌሎችም የልብ ስብራትን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች ተርታ ተሰላፊ ናቸው።

• ከመጽሐፍቅዱስውስጥልባቸውከተሰበሩሰዎችመሀከልዳዊትአንዱነበር፤

† የእግዚአብሔር ኃያል ተዋጊ (ጦረኛ) የሆነው ንጉስ ዳዊት ሰለራሱ የተሰበረ ልብ እያሰበሲናገርእናያለን።

♥ “አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው። ነፍሴስድብንና ኃሣርን ታገሠች አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም። የሚያጽናናኝም አጣሁ።”መዝ69፥19-20

† ዳዊት ስድብ፣ እፍረትና ነውር ልቡን እንደሰበሩትና ብቸኝነት የሚሰማው፣ ሀዘንተኛ፣የተገለለ፣የተጠላ(የተተወ)በማለትራሱንይገልፃል።

† ነብዩሳሙኤልወደዳዊትቤተሰብሲመጣዳዊትበመረሳቱምክንያትእንዴትየዳዊትልብእንደተሰበረበ1ኛሳሙ16፥5-11መመልከትእንችላለን።

• ሳሙኤልእሴይንለንጉስበሚደረገውምርጫላይዳዊትከወንድሞቹጋርእንዲካተትማሳመንነበረበት። ሌላው ዳዊት በሕይወቱ የደረሰበት እፍረት ለወንድሞቹ ምግብ ለማድረስ በሄደበትወንድሙኤልያብበአደባባይበኩራቱናበብልግናውበወቀሰውጊዜነው።

♥ “ታላቅ ወንድሙም ኤልያብ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰማ የኤልያብም ቍጣ በዳዊት ላይ ነድዶ፥ለምንወደዚህወረድህ?እነዚያንስጥቂቶችበጎችበምድረበዳለማንተውኃቸው?እኔኵራትህንናየልብህንክፋትአውቃለሁናሰልፉንለማየትመጥተሃልአለው።ዳዊትም፦እኔምንአደረግሁ?ይህታላቅነገርአይደለምን?አለ።”1ኛሳሙ17፥28-29

Page 32: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

22 23

† የዳዊት መንቋሸሽና መወገዝ ጎልያድን ሊገጥም በተነሳ ጊዜም ቀጥሏል። በሌሎች ፊትበውሸት(በሃሰት)ተከሷል፤ተትቷል፤በአባቱምዘንድተቀባይነትምአጥቷል፤ስለዚህዳዊትልቡከመሰበርበላይሆኗል።

• በ2ኛ ሳሙ 13፥1-20 የዳዊት ቤተሰቦች እንዴት አስደንጋጭና አግባብ ባልሆነ

መንገድ ልባቸው እንደተሰበረ እንመለከታለን።

ለንጉስ ዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የተባለች የተዋበች እህት ነበረችው። ከሌላ የተወለደው ወንድሙም ከትዕማር ኃያል ፍቅር ይዞት ነበርና በጓደኛው ምክር ትዕማርን ወደ ቤቱ አስመጥቶ በግድ አስነወራት። ምንም እንኳን በተቻላት መጠን ብትከላከለውም ካስገደዳት በኋላ ቀድሞ ከሚወዳት ይልቅ ስለጠላት ከቤቱ አባረራት። (2ኛ ሳሙ 13፥1-18)

♥ “ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንምበራስዋላይጭናእየጮኸችሄደች።ወንድምዋምአቤሴሎም፥ወንድምሽአምኖንከአንቺጋርነበረን?እኅቴሆይ፥አሁንግንዝምበዪወንድምሽነውይህንነገርበልብሽአትያዢውአላት።ትዕማርምበወንድምዋበአቤሴሎምቤትብቻዋንተቀመጠች።”2ኛሳሙ13፥19-20

† የዳዊትልጅትዕማርበወንድሟተደፍራለች፤ተጠልታለች፤አፍራለች፤ብቻዋንተጥላለች።በዚህምክንያትበሕይወትዘመኗሁሉያለአንዳችደስታ፣በብቸኝነትእናተስፋበመቁረጥበወንድሟቤትለመኖርተገዳለች።

† በ2ኛ ሳሙ 16 ላይ ንጉስ ዳዊት ከዙፋኑ ወርዶ ስደት ላይ በነበረ ወቅት የሳዖል ዘመድየነበረየጌራልጅሳሚንጉሱንእየተከተለበሰደበውጊዜ፣ንጉሱከማዘኑየተነሳተከታዮቹእንግደለውሲሉትእንኳንፈቃደኛአልነበረም።(2ኛሳሙ16)

♥ “ዳዊትም አቢሳንና ባሪያዎቹን ሁሉ፥ እነሆ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል ይልቁንስ ይህየብንያምልጅእንዴትነዋ?እግዚአብሔርአዝዞታልናተዉት፥ይርገመኝ።ምናልባትበዚህቀንመከራዬንአይቶስለእርግማኑመልካምይመልስልኛልአላቸው።”2ኛሳሙ16፥11-12

† ልክበዳዊትሕይወትላይእንደሆነውሁሉየጠላትዓላማሕይወታችንንናከእግዚአብሔርጋርየሚኖረንንኅብረትማበላሸትነው።ጥሩውዜናግንኢየሱስየጠላትንስራለማፍረስናየተሰበረውንልባችንንለመጠገንመጥቷል።

♥ “ኃጢአትንየሚያደርግከዲያብሎስነው፥ዲያብሎስከመጀመሪያኃጢአትንያደርጋልና።”1ኛዮሐ3፥8

በሰዎች ዘንድ መጠላታችን አልያም መተዋችን በአስተሳሰባችን፣ በስሜታችንና በምንወስደው የውሳኔ እርምጃ ላይ ተፅዕኖ ያመጣል። ሆኖም ግን ከዚህ የልብ ስብራት እኛን ሊፈውስ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጣ። ኢየሱስ ይህንን የተሰበረውን ልባችንን እንዲፈውስልን መጀመሪያ ስብራታችንን ማወቅና ማስተዋል አለብን። በመቀጠልም የልባችንን ጉዳትና ስብራት እንዲፈውስልን መጠየቅ እንችላለን።

Page 33: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

23

2.4 በሕይወታችን ያለውን ስብራት ማስተዋል

2.4.1 የስብራት ባህርያት

ጳውሎስ ስብራትን የምናሰተውልበት ቁልፍ ሃሰቦችን ሰጥቶናል።

♥ “የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱንአላደርገውም። የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገርአላደርገውም። የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም፥በእኔየሚኖርኃጢአትነውእንጂ።”ሮሜ7፥15፣19-20

የስብራታችን ህመም በስሜቶቻችን እንድንመራ ሊያደርገን ይችላል። ፍርሀት፣ ቁጣ፣ ቅንአት፣ ምቀኝነት፣ የተለያዩ ችግሮች የስብራት ውጤቶች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴ ለነገሮች የምንሰጠው ምላሽ ተገቢ ላይሆን ይችላል። ጰውሎስ እንዳለው የምናደርገው የምንፈልገውን ሳይሆን ማድረግ የማንፈልገውን ነው። የማንፈልገውን ነገር ስናደርግ ለምን የምንፈልገውን ማድረግ እንደማንችል ግራ ይገባናል፤ (ውስጣችን ይወቀሳል)፤ ይህ ስብራት በሕይወታችን የሚንሰራፋበት አንዱ መንገድ ነው።

2.4.2 በሁለት ሃሳብ መሆንበልብ ስብራት ምክንያት በሁለት ሃሳብ የሚዋዥቁ ሰዎች በእሳቤአቸውና በስሜታቸው

ሲወጠሩ ራሳቸውን ያገኛሉ። እነኚህ ሰዎች በሕይወት ጉዟቸው የተረጋጉ አይደሉም። ገለባ ወደ ንፋስ አቅጣጫ እንደሚንሳፈፍና “የእኔ” የሚለው አቅጣጫ እንደሌለው ሁሉ በሁለት ሀሳብ የሚዋልሉትም ባመኑበት ነገር ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች ይመራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ አካላት ሲናገር እንዲህ ይላል፤

♥ “ሁለትአሳብላለውበመንገዱምሁሉለሚወላውልለዚያሰውከጌታዘንድአንዳችእንዲያገኝአይምሰለው።”ያዕ1፥7-8

† በሁለትሃሳብየሚዋዥቁሰዎችአንዳንድጊዜበእግዚአብሔርላይጥሩእምነትይኖራቸዋል፥ሌላጊዜደግሞእግዚአብሔርለእነርሱያለውንፍቅርይጠራጠሩታል።

† በሁለት ሃሳብ መሆን በግሪኩ dipsuchos (dip»-soo-khos) ሲሆን ትርጉሙም ሁለትነፍስ(oftwosouls,oftwoselves),double-minded,wavering)መሆንማለትነው።(ምንጭ፤Strong»sConcordance/biblehubcom)

2.4.3 በሁለት ነፍስ መሆንነፍሳችን ከአዕምሯችንና ከስሜታችን እንዲሁም ከፈቃዳችን እንደተሰራች ስንረዳ ስብራት

ሲከሰት ስለሚኖረው ሁለት ነፍስ ለመረዳት ያን ያክል ከባድ አይሆንም።

ልባችን እንዲሰበር የሚያደርግ መጠላት ሲገጥመን የተሰበረው ወይም የተጎዳው ልባችን ለሰውየውና ስብራቱ እንዲከሰት ላደረገው ሁናቴ ተገዢ ስለሚሆን በሁለት ሀሳብ መዋዠቀን ያስከትላል። ስብራቱ ውስጥ ህሊናችን እንደሚገኝ ላናስተውለው እንችላለን፤ ስለዚህ አሰተሳሰባችን

Page 34: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

24 25

ላይ፣ ከሰዎችና ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ኅብረት ላይ ተፅዕኖን ያመጣል። በሁለት ሃሳብ መዋዠቃችንም ለልባችን ስብራት ተገዢዎች የመሆናችን ውጤት ነው።

† አዕምሯችንዛሬባለውናቀድሞበነበረውእውነታበሁለትተከፍሏል።ባደገውማንነታችን(አስተሳሰባችን) እግዚአብሔርን ማመንና በእርሱ መመካት እንችላለን፤ ግን ለስብራትተገዢ በሆነው ማንነታችን ምክንያታዊነታችን እንደተጎዳ ልጅ ይሆናል። በሁለት ሃሳብየመሆንባህሪዎች፦

• ስብራትበሁለትሃሳብለመሆናችን፣በኃጢአተኛማንነትውስጥእንድንሆንእናየማንፈልገውንነገርእንድናደርግምክንያትይሆናል።

• በእግዚአብሔርናበሌሎችሰዎችላይእምነትእንዳይኖረንእንቅፋትይሆናል።

• ከእግዚአብሔርመንገድያፈነገጠሕይወትእንድንመራያደርገናል።

• ፀሎታችንእንዳይሰማያደርጋል።

በሁለት ሃሳብ የሆነ ሰው ከእግዚአብሔር ምንም ነገር አይቀበልም ማለት እግዚአብሔር ምንም ነገር ሊሰጠን ፈቃደኛ አይደለም ማለት ሳይሆን በሁለት ሀሳብ ስለሆንን እኛ ራሳችን መቀበል አንችልም ማለት ነው። ከእግዚአብሔር የሚሰጠንን ማንኛውምንም ነገር መቀበል የምንችለው በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ እምነት ሲኖረን ብቻ ነው። በልባችን ስብራትና በሁለት የሃሳብ መንገድ ተጓዥ መሆናችን ማንነታችን በእምነትና በጥርጣሬ መካከል እንዲዋልል እድል ይከፍትለታል።

በሁለት ሃሳብ የተወጠሩ ሰዎች አንድን ነገር ብቻ በትጋት ለማድረግ ሲጥሩ ይስተዋላሉ። በነገሩ መጨረሻ ግን ሀሳባቸውን ይቀይራሉ አልያም የጀመሩትን ስራ ሳይጨርሱ ያቋርጣሉ። አልበገር ባይነትና ቁጥጥር መፈለግ በሁለት ሀሳብ የሚዋልል ሰው ዋና መገለጫ ባህርያት ናቸው። እነኚህ ልባቸው በተለያየ ምክንያት የተሰበረ ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከልና በድጋሚ ላለመጎዳት የአልበገር ባይነት ባህሪን ያዳብራሉ። በተቃራኒው ደግሞ ከልብ የሚንከባከባቸውና ጥሩ የፍቅር ማንነትን የሚያሳያቸው ሰው ካገኙ የመለወጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።

• ቀጣዩ ምስል የተሰበረን ሰው ልብንና በሁለት ሃሳብ መሆን በሙላት ከመኖር እንዴትእንደሚከለክለንያሳያል።

በውስጣችን ያለው የመወሰን ብቃት በአብዛኛው በሕይወታችን ውስጥ በሚያጋጥሙን ነገሮች ላይ የተመሰረተ መሆኑ አያጠያይቅም። በፊት ካጋጠሙን ነገሮች ተነስተን ዛሬ ላይ የምንወስናቸው ጥሩም ሆነ መጥፎ ውሳኔዎች በአዕምሯችን ውስጥ የሚሰማንን የስሜት አቅጣጫ ይውስኑልናል። ያለን የመወሰን ድምፅ ሲወጣ ወደ ሀዘን ወይም ፀፀት ውስጥ የሚያስገባ ውጤትን ካመጣ ይህ ችሎታ የመጠራጠርን ስሜት ይወልዳል። ከነበረን ልምድና በድግግሞሽ ከምናውቃቸው ነገሮች የተነሳ የመጠራጠር ስሜት ይከሰታል። ልባችን በተከሰተው ነገር ማዘን ይጀምራል። በየዋህነትና በትህትና ያምን የነበረው ንፁህ ልባችን በጥርጣሬ ይደነድናል። ይህም “እንዲህ ቢሆን እንዲህ ይሆናል፤ እንዲህ ቢሆን እንደዚያ ይሆናል” የሚል አሉታዊ ስሌት ውስጥ ይከተናል። የፍርሀት ድምፅም እያደገ በመምጣት ከልባችን በመጀመር መላ አካላታችንን ያሽመደምደዋል። መልካም ፈቃዳችንንም በመንጠቅ፣ ባለማመን ተከበን የውሳኔ ሰዎች እንዳንሆን እንዲሁም በብዙ ሀሳቦች መካከል እንድንዋትት ያደርገናል።

Page 35: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

25

ፍርሀትም አዕምሯችንን ይይዛል። አዕምሯችን ደግሞ የሰውነታችንን ስሜት የሚቆጣጠርልን ክፍል እንደመሆኑ መጠን የሚሰማንን ሕመም ልክ እንደፈቀድንለት መጠን ያስተላልፍልናል። ፈቃዳችን በተስፋ መቁረጥ፣ “ሰዎች ምን ይሉኛል” በሚል ሀፍረት እና ልባችንን በማደንደን በምንይዘው መንገድ ይመራል ማለት ነው። ይህም የትኛው ምርጫ ትክክለኛ እንደሆነ ከማየት ይጋርደናል። ጠንክረን ካለንበት አረንቋ መውጣት እንዳለብን ቢሰማንም ሕመማችንን ማስታመም ይቀለናል። የተሰበርንበትን ነገር ወደ ኋላ ትተን ወደፊት ከመሄድ ይልቅ ባለንበት በሁለት ሀሳብ መካከል እንዋዥቃለን።

2.5 ለልባችን ቁስል እንዴት ፈውስን ማግኘት እንችላለን?

ለልባችን ቁስል በተለያየ መልኩ ፈውስ ማግኘት እንችላለን። የልብ ስብራት ፈውስን መቀበል መማርና ሌሎችን ማፅናናት ዋና ከሚባሉ መንገዶች መካከል ይጠቀሳሉ።

2.5.1 የልብ ስብራት ፈውስን መቀበል መማርበሀዘናችን ጊዜ መቼም የምንፅናና አይመስለንም። ይህ ደግሞ አብዛኛው ሰው የሚያስተናግደው

እንግዳ ያልሆነ ስሜት ነው። ዘለዓለም የምናዝንና የምንከፋ፣ ስብራታችን ሁሌም አብሮን የሚኖር ይመስለናል። ዳግመኛ ለመሳቅ ተዓምር የሚሆን፣ ከሀዘናችን በኋላ ምንም ነገር ሊያስደስተን እንደማይችል እናስባለን። ነገር ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው።

Page 36: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

26 27

ወደ ደስታ መንገድ ቀስ በቀስ መጓዝ፣ ተስፋ፣ ፍቅርና ደስታ በውስጣችን እንዲያድጉ መፍቀድ እንዲሁም የተጎዳንበትንና ያዘንበትን ነገር በሚገባ ማወቅ (“ምንድን ነው? ከየት መጣ? ከዚህ በኋላ ምን ላድርግ?” ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት መሞከር) ለመፈወስ የምናደርገው ጉዞ የተዋጣ እንዲሆን ያደርገዋል። የተጎዳውን ስሜታችንን የምንገልፅበት መሪር ሀዘን ከአስቀያሚ የመንፈስ ቁስል እንድንድን የሚያደርግ ተፈጥሯዊና ጤናማ ሒደት ነው። እዚህ ጋር የዳዊትን ታሪክ ማንሳት ብዙ የሚያስተምረን ነገር አለ። ዳዊት የሚወደውና የሚሳሳለት ልጁ በጠና ታመመ። በሞትና በሕይወት መካከል ሲያጣጥር አይቶ ነፍሱ እጅግ ተጨነቀች። በመሆኑም አምላኩ ልጁን ይፈውስለት ዘንድ ከንግስና ወንበሩ ወርዶ፣ የንግስና ልብሱን አውልቆ፣ ከምግብና ከውኃ ተከልክሎ፣ በራሱ ላይ ትቢያ እየነሰነሰ እና በእንባ እየታጠበ አምላኩን ልጄን አድንልኝ እየለ ይጠይቀው ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ሳይፈቅድ ቀርቶ ልጁ ሞተ። አገልጋዮቹም “ገና ልጁ ሳይሞት ራሱን እንደዚያ የጎዳ መሞቱን ስንነግረው መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል” ብለው የልጁን መሞት ይነግሩት ዘንድ እጅግ ፈሩ። እውነቱን የነገሩት ጊዜ ግን የተፈጠረው ነገር ከሃሳባቸው ተቃራኒ ነበር። ንጉሱ ከትቢያ ላይ ተነሳ፣ እንባውን ጠራርጎ ተጣጠበም፣ የንግስና ልብሱን ለብሶ የሚመገበውን እንዲሰጡት አዘዘ። የዚህ ሁኔታ ግራ የገባቸው አገልጋዮቹ አንድ ጥያቄ ጠየቁት። “ልጅህ ታሞ ሳለ አይሆኑትን ሆንክ መሞቱን ስንነግርህ በራስህ ላይ ጉዳት ታደርሳለህ ብለን ስንጠብቅህ አንተ ግን ተነሳህ፤ ፊትህንም ተጣጥበህ ተቀባባህ፤ የንግስናህን ልብስም ለብሰህ በላህ፤ ሚስጥሩ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት እሱም እንዲ ሲል መለሰላቸው፤ “ልጄ በሕይወት ሳለ ቢምርልኝ ብዬ ተጎዳሁ። ከሞተ በኋላ ግን ለምን?” አላቸው።

እግዚአብሔር ልጆቹን ያፅናናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ትዕግስተኛው ኢዮብ በዙሪያው ከነበረው ነውጥ ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቆ ነበር።

የዳዊት ቅድመ አያት የነበረችው ኑኃሚን ወደ ሞዓብ ሔዳ ያላትን ነገር ሁሉ አጥታ ስትመለስ የነበረባትን ሀዘን ለመርሳት ስሟን እስከማስለወጥ ደረጃ አድርሷት ነበር። ነገር ግን በሀዘን ጊዜ ከጎኗ ያልተለየቻት ሩት ከአፅናኝነቷ በላይ በረከት ሆናላታለች።

† በዮሐ 11 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እምነትንና ሀዘንን በአንድላይ ያዋሀደበት ምዕራፍ እንደሆነ ማየት እንችላለን። አልዓዛርን ከሞት እንደሚያስነሳውቢያውቅምከአልዓዛርእህቶችማርያምናማርታጋርከልቡአልቅሷል።(ዮሐ11፥35)

† ክርስቶስኢየሱስሀዘናችንናስብራታችንእንደሚገባውበማወቅመፅናናትእንችላለን።አዲስሰውከሆንንበኋላየእርሱመንፈስበእኛውስጥስላለናስሜታችንከስሜቱጋርየተዋሀደስለሆነ የሚሰማንንያውቃል።ማጣታችን፣መከዳታችን፣መጣላታችንንእናመሞታችንንይረዳል። እንደ አዳኛችንና እንደ ነፃ አውጪያችን ለእኛ ይጠነቀቃል። የክርስቲያንስብራትም ቀለል እንዲል ከሚያደርገው አንዱ በክርስቶስ ያለን ተስፋ ነው። በለመለመመስክ ያሳድረናል፤ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብንሔድ እርሱ ከኛ ጋር ነው፤ ብርሃናችንነውና።(መዝ23)።

♥ “ለአንዳንዶችየሚዘገይእንደሚመስላቸውጌታስለተስፋቃሉአይዘገይም፥…”2ኛጴጥ3፥9።

♥ “ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።…ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ለመሳቅምጊዜአለውዋይለማለትጊዜአለው፥ለመዝፈንምጊዜአለው…”መክ3፥1-4።

Page 37: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

27

† በስብራትወቅትምመንፈስቅዱስ፣አፅናኙየእግዚኣብሔርንሰላምይሰጠናል።(ዮሐ14፥15-16፣26)

† ወደፊልጵስዩስሰዎችየተላከውምመልእክትይህንኑያጠናክርልናል።ከሁኔታዎችይልቅወደአምላካችንይበልጥስንጠጋየእግዚአብሔርሰላምውስጣችንንያሳርፈዋል።

♥ “ጌታቅርብነው።በነገርሁሉበጸሎትናበምልጃከምስጋናጋርበእግዚአብሔርዘንድልመናችሁንአስታውቁእንጂበአንዳችአትጨነቁ።አዕምሮንምሁሉየሚያልፍየእግዚአብሔርሰላምልባችሁንናአሳባችሁንበክርስቶስኢየሱስይጠብቃል።”ፊል4፥6-7

† ስብራት ሀሳባችን፣ ባህርያችን፣ ስሜታችን፣ ግንኙነታችን እና ጤናችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖያመጣል።በሀዘንጊዜከከባድነገሮችአንዱዕክሉንካስከተለውነገርጋርተለያይቶአዲስየሚመስል ኑሮን መጀመር ነው። ነገር ግን እምነታችንን በእግዚአብሔር ላይ መጣልንመልመድለዚህሁኔታከፍተኛአስተዋዕፆአለው።

♥ “ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለነው።”ኢሳ55፥9

በእግዚአብሔር ላይ ምንም ያህል ጥያቄ ቢፈጠርም በስተመጨረሻ እሱ ስለእኛ እንደሚያስብና የሚሆነውን እንዲሁም መሆን ያለበትን እንደሚያውቅ ማመን አለብን። እንደሚረዳን በማሰብ የእርሱን ማፅናናት ለመቀበልም ዝግጁ መሆን መቻል አለብን። በጸሎትና ቃሉን በማሰላሰል ለእኛ ያለውን የእግዚአብሔርን ሰላም ተቋዳሾች መሆን እንችላለን።

• (መዝ16፣23፣34፣91፣ዮሐ14፥1-27፣2ኛቆሮ5፥1-9፣ፊል4፥6-13፣1ኛተሰ4፥13-18፣ራዕ21፥1፣22፥5)

2.5.2 ሌሎችን ማፅናናትእኛ ካለን ልምድ በመነሳት ለሌሎችም መፍትሔ መሆን እችላለን። እግዚአብሔር ያስተማረንን

ነገር ወደ ጎን ከማለትና ከማማረር አልፈን ሌሎችን መርዳት እንችላለን። ምናልባት በዛ ውስጥ ያልተቀረፈ ሀዘን ካለን ለማንሳትና ለማደግ ይጠቅመናል። ይህንንም በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር በመገናኘት፣ ሌሎች ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ በማበረታታት፣ በሰው ላይ ቀድሞ አለመፍረድና ልምድን በማካፈል (ሮሜ 12፥15)፣ በቶሎ ወደ ነበረው ሕይወታቸው እንዲመለሱ ባለመገፋፋት እንዲሁም እግዚአብሔር ለእኛ ከጎናችን እንደነበር እኛም ከነሱ ጎን መሆናችንን በትንሽ ነገር በማሳየት፣ ሰዎች ተገቢውን ሀዘን አልፈው ለፈውሳቸው እንዲዘጋጁና በጊዜው ተቀብለው ወደ ጤናማ ኑሯቸው እንዲመለሱ ማድረግ እንችላለን።

የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለ ስብራትና መፅናናት የሚናገሩት ነገር አለ።

• • መዝ 13፣ 23፥1-6፣ 30፥11-12፣56፣34፥18፣73፥26፣139፥2

• መክ3፥1-14

• ዮሐ16፥16

• 2ኛቆሮ1፥3-4

• 1ኛተሰ4፥13

• 1ኛጴጥ5፥7

• ራዕ21፥4

Page 38: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

28 29

ምዕራፍ 3 ኢየሱስ ነፃ አውጪያችን

♥ “ጌታለእርሱየሆኑትንያውቃል፥ደግሞም፦የጌታንስምየሚጠራሁሉከዓመፅይራቅየሚለውማኅተምያለበትየተደላደለየእግዚአብሔርመሠረትቆሞአል።”2ኛጢሞ2፥19

♥ “ሁሉኃጢአትንሠርተዋልናየእግዚአብሔርምክብርጎድሎአቸዋል፤በኢየሱስክርስቶስምበሆነውቤዛነትበኩልእንዲያውበጸጋውይጸድቃሉ።”ሮሜ3፥23-24

የግሪኩ ቃል ነፃ መውጣትን “አፖሉኦትሮሲስ” ሲለው ትርጉሙንም አንድን ነገር ዋጋ በመክፈል ማስለቀቅ ወይም መቤዠት ይለዋል። የዕብራይስጡ ቃል ደግሞ “ጋዋል” የሚል መጠሪያ ሰጥቶታል። ትርጉሙም መልሶ መግዛት ወይም ነፃ አውጪ ማለት ነው።

ሰው ሁሉ ነፃ መውጣት ያስፈልገዋል። ስንወለድ ጀምሮ የነበረን ማንነት በክርስቶስ መታደስ አለበት። የክርስቶስ ነፃ ማውጣት ከኃጢአትና ከጥፋት ማላቀቅ ነው።

የሰው ልጅ ሁሉ ነፃ መውጣት ያስፈልገዋል። ነፃ ለመውጣት ደግሞ ስንወለድ ጀምሮ የነበረን ማንነት በክርስቶስ መታደስ መቻል አለበት። በክርስቶስ ነፃ መውጣት ማለት ከምድራዊ ኃጢአትና ጥፋት መላቀቅን ያመለክታል። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ሰውን ሁሉ ሊያድንና ከአብ ጋር ሊያስታርቀን ሲሆን ድምፁን ለሚሰሙትም ይህ ይሆንላቸዋል። በዚህ ምዕራፍ ስር “ኢየሱስ ነፃ አወጣን” ስንል ምን ማለት እንደሆነ፣ ነፃ የወጣ ሰው ባህሪው ምን መምሰል እንዳለበት እና በክርስቶስ ውስጥ የሚኖር ሰው ያለው ስልጣንን በጥቂቱ ለመመልከት እንሞክራለን። ክርስቶስ በሞቱ ሞታችንን፣ በቁስሉ ቁስላችንን፣ በደዌው ህመማችንን እንደፈወሰልንና የመወለዱ ምክንያት በጸጋውና በፍቅሩ ኃጢአታችንን ሰርዞ የእግዚአብሔር ልጆች ሊያደርገን እንደመጣ በደንብ ማወቅና ማስተዋል ይኖርብናል።

Page 39: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

29

3.1 በኢየሱስ ነፃ መውጣት ማለት ምን ማለት ነው? ♥ “እኔንግንየሚቤዠኝሕያውእንደሆነ፥በመጨረሻምዘመንበምድርላይእንዲቆም፥ይህቁርበቴም

ከጠፋበኋላ፥በዚያንጊዜከሥጋዬተለይቼእግዚአብሔርንእንዳይአውቃለሁ።”ኢዮ19፥25-26

ነፃ መውጣት ከያዘ ባርነት መላቀቅ እንዳለ ያሳያል። እንደ ክርስቲያኖች ነፃ ወጣን ስንል በላያችን ሰልጥኖ ወይም ነግሶ የነበረን ሰይጣናዊ ግዞትና በላያችን ያኖረው ቀንበር ተወገደ ማለት ነው። ነፃ ማውጣት ማለት ደግሞ የተከፈለን ነገር መኖሩን ያሳያል። በዋጋ፣ በገንዘብ፣ በስራ፣ በመሳሰሉት ምክንያቶች አንድን ነገር ከተያዘበት ነገር ማውጣትን ወይም መለየትን ያመላክታል። በኢየሱስ ነፃ መውጣትም እንደዚሁ ሰው ከነበረበት የኃጢአት እስራት፣ በፍቅሩ ዋጋ በሞቱ ትንሳዔ መቤዠት በክርስቶስ ወደ ነፃ ዓለም መመለስን ያመላክታል።

♥ “መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡምየሚሆነውንሕዝብለራሱእንዲያነፃ፥ስለእኛነፍሱንሰጥቶአል።”ቲቶ2፥14

ከእግዚአብሔር ጋር ያለያየን ኃጢያት በክርስቶስ ስናምንና የክርስትናን መንገድ ስንከተል ይሰረዛል። በዚህም ከጌታችን ጋር አዲስ የሆነ ንፁህ ግንኙነት ያንሰራራል። የክርስቶስን ይቅርታ ለማግኘት የሚጠበቅብን ስለኃጢያታችን ስርየትን መጠየቅ ብቻ ነው። ክርስቶስን እንደግል አዳኛችን ስንቀበልና በስሙ ስንጠመቅ ዓመፃችንን ሁሉ ትተን፣ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ውኃው ውስጥ ቀብረን፣ በደሙ ታጥበን አዲስ ሰው መሆናችንን ያመለክታል። በውስጣችን መኖር በሚጀምረውም መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መታረቅ ይሆንልናል። ይህም የኢየሱስን ነፃ ማውጣት ይመሰክርልናል። ከኃጢአት ቀንበር፣ ከጨለማ ወደ ነፃነትና ወደ ብርሀን መንገዳችንን ለውጦታል። ፍቅር ወደሞላበት ወደ ቅዱስ ሕይወት ይመራናል።

ክርስቶስ እኛን ከሰይጣን አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በደሙ ዋጋ ከፍሎልናል፤ የኃጢአታችንን ቅጣት እርሱ ወስዶልናል። የመስቀሉ ሞት የትንሳዔውን ክብር እንድናስተውል አድርጎናል። በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሊቆም ራሱን በመስጠት ስለ እኛ በደል ተሰቃየ፤ ሞቱም የማስታረቂያ ድልድይ ሆነ፤ ፍፁም ሰው ስለነበረ የነበርንበትንና የምንሆነውን ያውቃል። ስለዚህም የጠፉትን በጎች መንገድ ሊያሳይ፣ ዳግመኛ ወደቤታቸው ሊመልሳቸውና ከጠላት እጅ መንጭቆ ሊያወጣ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጠ። ራሱን በመሰዋቱና በክብር ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ አማኞች ዛሬ በነፃነት በምርጫችን ወደንና ፈቅደን እንድንከተለው አድርጎናል።

3.2 ኢየሱስ ከምንና እንዴት ነፃ እንዳወጣን

ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ዋና ዓላማ በኃጢአት ምክንያት በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ እኛን ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያደርሰውን መንገድ ለማደስ ነው። ከዚህም ባለፈ ኃጢአተኞችን ሊያድን፣ በዓለም ላይ ያጠላውን ጨለማ ሊገፍ፣ ከሞት እጅ ሊያወጣን እንዲሁም የዲያብሎስን ስራ ሊገልጥ መጥቷል።

♥ “…የሰውልጅየጠፋውንሊፈልግናሊያድንመጥቷልናአለው።”ሉቃ19፥10

Page 40: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

30 31

♥ “የነቢዩንምየኢሳይያስንመጽሐፍሰጡት፥መጽሐፉንምበተረተረጊዜ፥የጌታመንፈስበእኔላይነው፥ለድሆችወንጌልንእሰብክዘንድቀብቶኛልና፤ለታሰሩትምመፈታትንለዕውሮችምማየትንእሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነፃ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድልኮኛልተብሎየተጻፈበትንስፍራአገኘ።”ሉቃ4፥17-19

3.2.1 ከምን ነፃ ወጣን?የእግዚአብሔር መንፈስ የእግዚአብሔር ልጆች መሆን ለምንወድ ሁሉ ከቀንበሮቻችን

እንዲያላቅቀን ተልኮልናል። ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተገልፀዋል።

ሀ) ከኃጢአት ♥ “ሁሉኃጢአትንሠርተዋልናየእግዚአብሔርምክብርጎሏቸዋል።”ሮሜ3፥23

የእኛ ሀጥያት የታጠበው በሳሙናና በውኃ አይደለም። ነገር ግን ለዓለም ሁሉ ያለ ምንም በደል በፈሰሰ ንጹህ ደም እንጂ። የኃጢአት መዝገብ በደልን ሁሉ ትቶ ስለበደሉት ሰዎች ራሱን መስዋዕት ባደረገ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ተዘግቷል። ያመኑበት ሁሉ ለፍርድ የሚያቆም የክስ ፋይል የለባቸውም።

♥ “ለወደደንከኃጢአታችንምበደሙላጠበን፥”ራዕ1፥4-5 ♥ በኢየሱስክርስቶስምበሆነውቤዛነትበኩልእንዲያውበጸጋውይጸድቃሉ።”ሮሜ3፥23-24 ♥ “እርሱምእስራኤልንከኃጢአቱሁሉያድነዋል።”መዝ130፥8

ለ) ከህግ ባርነት/ከህግ እርግማን ♥ “በእንጨትየሚሰቀልሁሉየተረገመነውተብሎተጽፎአልናክርስቶስስለእኛእርግማንሆኖ

ከሕግእርግማንዋጀን፤”ገላ3፥13፤

♥ “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታችየተወለደውን ልጁን ላከ፤ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።”ገላ4፥4-5

ሐ) ከባዶ ሃይማኖት ♥ “ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሯችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥

ነውርናእድፍእንደሌለውእንደበግደምበክቡርየክርስቶስደምእንደተዋጃችሁታውቃላችሁ።”1ኛጴጥ1፥18

♥ “እንዲሁእኛደግሞሕፃናትሆነንሳለንከዓለምመጀመሪያትምህርትበታችተገዝተንባሪያዎችነበርን፤”ገላ4፥3

♥ “ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴትይልቅሕያውንእግዚአብሔርንልታመልኩከሞተሥራሕሊናችሁንያነፃይሆን?”ዕብ9፥14

መ) ከሰይጣን ኃይል/ከጨለማ አሰራረርየሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማ ብሎ ከገነት ከተባረረ ወዲያ በሀሳብም ሆነ በአኗኗር

የሰይጣን ተገዢ ሆኗል። ዓለምም ለጨለማው አሰራር ተላልፋ ተሰጥታለች። ሰውም ጣዖትን የሚያመልክና ለተቀረጹ ምስሎች የሚሰግድ ሆነ። አምላኩን ረስቶ ሁለመናውን ለጨለማው ንጉስ ባርነት አስረከበ።

Page 41: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

31

ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዲያብሎስ ቀንበር ፈትቶናል። ኃይሉንም ነጥቆ በጠላት ላይ ኃይል እንዲኖረን አድርጎናል።

♥ “እርሱከጨለማሥልጣንአዳነን፥ቤዛነቱንምእርሱንምየኃጢአትንስርየትወዳገኘንበትወደፍቅሩልጅመንግሥትአፈለሰን።”ቆላ1፥13-14

♥ “የኃጢአትንም ስርየት በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስትን ያገኙ ዘንድ፥ ከጨለማወደብርሃንከሰይጣንምሥልጣንወደእግዚአብሔርዘወርእንዲሉዓይናቸውንትከፍትዘንድ፥ከሕዝቡናወደእነርሱከምልክህከአሕዛብአድንሃለሁ።”ሐዋ26፥18

♥ “ክፉከሆነከአሁኑዓለምያድነንዘንድእንደአምላካችንናእንደአባታችንፈቃድስለኃጢአታችንራሱንሰጠ።”ገላ1፥4

ሰ) ከሚመጣው ፍርድ/ቍጣ ♥ “እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና

ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስንከሚመጣውቍጣየሚያድነንንከሰማይትጠብቁዘንድ፥ከጣዖቶችወደእግዚአብሔርእንዴትዘወርእንዳላችሁይናገራሉ።”1ኛተሰ1፥9-10

♥ “ይልቁንስእንግዲህአሁንበደሙከጸደቅንበእርሱከቍጣውእንድናለን።”ሮሜ5፥9

♥ “እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነውእንጂ።”1ኛተሰ5፥9

ረ) ከሞት (ከዘላለም ሞት/ከመንፈሳዊ ሞት)የእግዚአብሔር ቃል የኃጢአት ደሞዝ ሞት እንደሆነ ይናገራል። አዳምም “ይህቺን እጸ በለስ

በበላህ ጊዜ ትሞታለህ” ተብሎ የተነገረውን ፍሬ በበላ ጊዜ በስጋው ሟች ከመሆኑም ባሻገር በመንፈሱም ሞተ። የእርሱም ኃጢአት በዘሩ ሁሉ የሚተላለፍ ነበር። ምንም እንኳን ጻድቅ ቢሆን ጽድቅ እንደ መርገም ጨርቅ ሆነ። የበጎችና የዋኖሶች ደም የማያጥበው ከባድ ኃጢአትን የሰው ልጅ ተሸከመ። (ኢሳ 64፥6)

♥ “እንግዲህልጆቹበሥጋናበደምስለሚካፈሉ፥እርሱደግሞበሞትላይሥልጣንያለውንበሞትእንዲሽር፥ይኸውምዲያብሎስነው፥በሕይወታቸውምሁሉስለሞትፍርሃትበባርነትይታሰሩየነበሩትንሁሉነፃእንዲያወጣ፥በሥጋናበደምእንዲሁተካፈለ።”ዕብ2፥14-15

♥ “ከሲኦልእጅእታደጋቸዋለሁ፥ከሞትምእቤዣቸዋለሁሞትሆይ፥ቸነፈርህወዴትአለ?ሲኦልሆይ፥ማጥፋትህወዴትአለ?…”ሆሴ13፥14

ሠ) አሁን ካለው/ከጠላት አሰራር ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ የጠላት ተቃውሞ

ያጋጥመናል። ሰይጣን አርፎ አይቀመጥም። ብዙውን ጊዜ ክርስቲያኖች ውጊያ ሲበዛብን ለጠላት ሀሳብ ቶሎ እጅ እንሰጣለን። አንድ ሁለቴ ከመጸለይ ባላለፈ ጥርጣሬንና ተስፋ መቁረጥን እናንፀባርቃለን። እግዚአብሔርም በዚህ ደስተኛ አይሆንም።

♥ “ሕዝቤእውቀትከማጣቱየተነሣጠፍቶአልአንተምእውቀትንጠልተሃልናእኔካህንእንዳትሆነኝእጠላሃለሁየአምላክህንምሕግረስተሃልናእኔደግሞልጆችህንእረሳለሁ።”ሆሴ4፥6

Page 42: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

32 33

† ይህ ደግሞ የጠላት ሀሳብ ነው። ጠላት እኛን ከእግዚአብሔር ለማራራቅና ለማጣላትየማይፈነቅለውድንጋይየለም።ለዚህነውክርስቲያኖችበጌታእንድንበረታናለጠላትሀሳብእጅእንዳንሰጥማስተዋልያለብን።

♥ “በሰይጣንእንዳንታለል፤የእርሱንአሳብአንስተውምና።”2ኛቆሮ2፥11

በአጠቃላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ለክርስቲያኖች በስሙ እንድናገለግል ስልጣን ሰጥቶናል። ልክ አዲስ ሰዎች ስንሆን ይህ ስልጣን በእጃችን ገብቷል። በስሙ ከተደረጉልን ጥቂት ነገሮች ውስጥ ኃጢአታችን ይቅር መባሉ፣ እኛን ዳግም ልጆቹ ማድረጉ፣ በጸሎት እንድናነጋግረው ስልጣን መስጠቱ፣ ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንደምንኖር መፍቀዱ ይገኙበታል። የክርስቶስ ልጆች ስንሆን ሁሉ በእጃችን አለ። አንዳንዴ ግን ይህንን እየረሳን በሽንፈት እንኖራለን።

3.3 በክርስቶስ ኢየሱስ ነፃ የወጣ ሰው የተሰጠው ስልጣን ♥ “ስለዚህየዲያብሎስንሥራእንዲያፈርስየእግዚአብሔርልጅተገለጠ።ከእግዚአብሔርየተወለደ

ሁሉኃጢአትንአያደርግም፥ዘሩበእርሱይኖራልና፤ከእግዚአብሔርምተወልዶአልናኃጢአትንሊያደርግአይችልም።”1ኛዮሐ3፥9

ሀ) ዲያብሎስንና ስራውን ለማውደም (ለማጥፋት)የክርስቶስ ኃይል ከሰይጣንና ከጨለማ መናፍስት ይበልጣል። ይህንንም ስልጣን ለኛ

ለተከታዮቹ አካፍሎናል።

♥ “አሥራሁለቱንምሐዋርያትበአንድነትወደእርሱጠርቶበአጋንንትሁሉላይደዌንምይፈውሱዘንድኃይልናሥልጣንሰጣቸው፤”ሉቃ9፥1

እግዚአብሔር የእርሱን ኃይል ስጥቶናል። በክርስቶስ አምነን መንፈስ ቅዱስን ስንቀበል ኃይልንም እንቀበላለን። እዚህ ላይ ልብ ማድረግ የሚገባን የእኛ ኃይል ሳይሆን የእግዚአብሔር ኃይል መሆኑን ነው። በእርሱ ኃይል የተሰጠንን ስልጣን መለማመድ እንችላለን። በመናፍስት ላይ ኃይልና ስልጣን ተሰጥቶናል።

• ሉቃ10፥1፣17-19፤ዮሐ14፥13-14

መፅሐፍ ቅዱስ “የተሰጠን ኃይል” ብሎ ያስቀመጠው ቃላቱን በማለት ውስጥ ሳይሆን የክርስቶስ ስም የሚያመላክተውን ነገር በመረዳትና በማመን ውስጥ ነው። ስሙም በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ፣ የእግዚአብሔርን ዓላማና ቃልኪዳን (ነፃ የማውጣት ቃል)፣ በኃጢአት ላይ ድልን መቀዳጀት፣ ሞትን እና የሰይጣንን ግዛት ድል መንሳቱን ያመላክታል። የክርስቶስ ስም ሲጠራ እግዚአብሔር በፍቅሩ የሰጠንን ስልጣን በሙሉ ይይዛል።

• (ኤፌ1፥21ፊል2፥9-10ዕብ1፥3-4፣ሉቃ10፥17፣10፥18-20፣ማር16፥17)

በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የእስራኤላውያን ሕዝብ ጠላቶቻቸውን እንዲያጠፉ ሲነግራቸው እንደነበረ እንመለከታለን። ኢየሱስም የዲያብሎስን ስራ ሊያፈርስ ወደዚህ ምድር መጣ።

♥ “መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥የዘላለም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህአውጥቶ፥አጥፋውይላል።”ዘዳ33፥27

Page 43: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

33

♥ ስለዚህየዲያብሎስንሥራእንዲያፈርስየእግዚአብሔርልጅተገለጠ።”1ኛዮሐ3፥8

† ማውደምወይምማጥፋትየሚለውቃልበአዲስኪዳንበስድስትየግሪክቃላትተተርሟል፤• Strong”s 3089-“luo” ሎ- መለቀቅ፣ ማፍረስ፣ መስበር፣ ማጥፋት

♥ ስለዚህየዲያብሎስንሥራእንዲያፈርስየእግዚአብሔርልጅተገለጠ።”1ኛዮሐ3፥8• Strong”s #2637-“Katargeo” ጥቅም የሌለው ማድረግ፣ ማስወገድ

♥ “እንግዲህልጆቹበሥጋናበደምስለሚካፈሉ፥እርሱደግሞበሞትላይሥልጣንያለውንበሞትእንዲሽር፥ይኸውምዲያብሎስነው፥”ዕብ2፥14

• Strong”s #622-“phtheiro” መጣል፣ ማፍረስ፣ ማስወገድ

♥ “ማንምየእግዚአብሔርንቤተመቅደስቢያፈርስእግዚአብሔርእርሱንያፈርሰዋል፤የእግዚአብሔርቤተመቅደስቅዱስነውና፥ያውምእናንተናችሁ።”1ኛቆሮ3፥17

• Strong”s #622-“apollumi”

♥ “ሥጋንምየሚገድሉትንነፍስንግንመግደልየማይቻላቸውንአትፍሩ፤ይልቅስነፍስንምሥጋንምበገሃነምሊያጠፋየሚቻለውንፍሩ።”ማቴ10፥28

• Strong”s #2647-“kataluo” ሙሉ ለሙሉ ማውደም፣ መሻር

♥ “እኔሕግንናነቢያትንለመሻርየመጣሁአይምሰላችሁ፤ልፈጽምእንጂለመሻርአልመጣሁም።”ማቴ5፥17

• Strong”s #1331-“diaphtheiroerio” ♥ “…ምድርንምየሚያጠፉትንታጠፋዘንድዘመንመጣ”ራዕ11፥18

እኛ ሰዎች ሰይጣንን በግላችን ማጥፋት አንችልም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ስልጣን የተረገጡትን አጋንቶች ምን ሊያደርጋቸው እንደሚፈልግ እርሱን መጠየቅ አለብን።

♥ “በቀረውስበጌታናበኃይሉችሎትየበረታችሁሁኑ።”አፌ6፥10

† በየዕለቱበክርስቶስያለንንስልጣንማስታወስአለብን።ይህስልጣንየራሳችንሳይሆንጌታኢየሱስየሰጠንስልጣንነው።

♥ “እነሆ፥እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣንሰጥቻችኋለሁ፥የሚጐዳችሁምምንምየለም።”ሉቃ10፥19

♥ “የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስክርስቶስጸጋከእናንተጋርይሁን።”ሮሜ16፥20

ለ) ጠላትን/አጋንንትን ለማስወጣት ♥ “እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር

መንግሥትወደእናንተደርሳለች።”ማቴ12፤28

Page 44: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

34 35

መናፍስት ለክርስቶስ ስልጣን አገልግሎትና ለቤተክርስቲያን ተገዢዎች ናቸው። የጠላት ሠራዊት ሁሉ በክርስቶስ ስልጣን ስር ናቸው። ለእርሱም ተገዢዎች ናቸው። እርሱ የፈቀደውን ብቻ ያደርጋሉ፤ ለእርሱም ይታዘዛሉ። ከቃሉም የተነሳ ይበተናሉ።

የክርስቶስ ስምም በመናፍስት ላይ ስልጣን አለው። ደቀ መዛሙርቱ በጠላት ላይ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ሰይጣንን ለመገሰፅ ስሙን ተጠቅመዋል። ይህ አገልግሎት በክርስቶስ ዘመን ቢጀመርም በአሁኑም ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይሰራል።

ነፃ የማውጣት አገልግሎትን በሁለቱም ጎኑ እንደተሳለ ሰይፍ መመሰል ይቻላል። የሰይጣንን ኃይል በመንፈስም በስጋም ያስወግዳል።

• ዲያብሎስ ያልተፈወሰ ስብራታችንንና ከጠላት ጋር ባደረግነው ስምምነት ላይ በመመስረትበአማኞችሕይወትላይተፅእኖሊያመጣይችላል።

• “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነፈትናችሁታውቁዘንድበልባችሁመታደስተለወጡእንጂይህንዓለምአትምሰሉ።”ሮሜ12፥2

• ጠላትበድካማችንሊገባይችላል።

♥ “ዝናውምወደሶርያሁሉወጣ፤በልዩልዩደዌናሥቃይምተይዘውየታመሙትንሁሉአጋንንትምያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ፈወሳቸውም።”ማቴ4፥24

♥ “ኢየሱስምገሠጸውጋኔኑምከእርሱወጣ፥ብላቴናውምከዚያችሰዓትጀምሮተፈወሰ።”ማቴ17፥18

† የአማኞች ስጋዊ ማንነት ከክርስቶስ ጋር ካልተሰቀለ ጠላት በስጋ ምኞት አማኞችንሊያባብልይችላል።

♥ “ከእንግዲህስወዲያለኃጢአትእንዳንገዛየኃጢአትሥጋይሻርዘንድአሮጌውሰዋችንከእርሱጋርእንደተሰቀለእናውቃለን፤የሞተስከኃጢአቱጸድቋልና።ነገርግንከክርስቶስጋርከሞትንከእርሱጋርደግሞበሕይወትእንድንኖርእናምናለን፤”ሮሜ6፥6-7

♥ “ፊተኛ ኑሯችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥በአእምሯችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔርምሳሌየተፈጠረውንአዲሱንሰውልበሱ።”ኤፌ4፥22-24

♥ “የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። በመንፈስ ብንኖርበመንፈስደግሞእንመላለስ።”ገላ5፥24-25

ከነፃ መውጣት በሚገኘው ሁሉን አቀፍ ድል ምክንያት ጠላት ይህንን ነፃ መውጣት ሊከፋፍለው ይፈልጋል። መንፈሳችን ብቻ ነፃ ወጥቶ ነፍስና ስጋችን ከተረሱ ነፃ በወጣው ሰው ላይ ጠላት ስራውን መስራት ይቀጥላል።

ሐ) ጠላትን ለማሰርና ለመፍታት ♥ “እርሱም፦እናንተስእኔንማንእንደሆንኩትላላችሁ?አላቸው።ስምዖንጴጥሮስምመልሶ፦አንተ

ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅስምዖንሆይ፥በሰማያትያለውአባቴእንጂሥጋናደምይህንአልገለጠልህምናብፁዕነህ።እኔም

Page 45: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

35

እልሃለሁ፥አንተጴጥሮስነህ፥በዚችምዓለትላይቤተክርስቲያኔንእሠራለሁ፥የገሃነምደጆችምአይችሉአትም።የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉበሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” ማቴ16፥15-19

• አለቱመሲሁየእግዚአብሔርልጅየኢየሱስክርስቶስማንነትነው።

• ይህየክርስቶስማንነትመገለጥቤተክርስቲያንየምትመሰረትበትምሰሶነው።

• ዲያብሎስሰዎችይህንንመገለጥእንዳያስተውሉያደርጋቸዋል።

• የጠላትኃይልይህንንየመገለጥእውነትሊቋቋምአይችልም።

† በዚህ መገለጥ ኃይል ለመሄድ ቁልፉ መንገድ ኢየሱስ የሰጠንን የመንግስቱን ኃይልመጠቀም ነው፤ ይህም ማለት በሰማይ የታሰረውን በምድር ማሰር በሰማይ የተፈታውንበምድርመፍታትነው።

መ) ኃይለኛውን አስሮ ኃይለኛውን ለመበዝበዝሰይጣን በተለያዩ ወጥመዶች የእግዚአብሔርን ሕዝብ ወደ ሲኦል በምታመራ መንገድ ላይ

አሰማርቷቸዋል። ቅንና ዘላለማዊ በምትመስል ነገር ግን ወደ ሞት የምታመራ መንገድ ላይም ለዓላማው አሰልፏቸዋል። (ምሳሌ 14፥12፣ 16፥25) ምርኮውንም አፅንቷል። እኛ የክርስቶስን ስምን የያዝን ግን በሚያበረታንና ጉልበት በሚሆነን በእርሱ የእግዚአብሔር የሆኑትን ከኃይለኛው እጅ ላይ ፈልቅቀን እንድንወስድ ስልጣኑን ተቀብለናል። ይህን የሚያደርገው በውስጣችን የሚሰራው ቅዱስ መንፈሱ እንጂ እኛ አይደለንም።

♥ “ያለእኔምንምልታደርጉአትችሉምናበእኔየሚኖርእኔምበእርሱ፥እርሱብዙፍሬያፈራል።”ዮሐ15፥5

• ክርስቶስ ባለሙሉ ስልጣን እንደሆነ ማመን ማለት ለሰይጣን እኛ ራሳችን

ስልጣን ካልሰጠነው በስተቀር ምንም ስልጣን እንደሌለው ማመን እንደሆነ

ከስር የተቀመጡት ጥቅሶች ያለመክታሉ።

♥ “ኢየሱስምቀረበናእንዲህብሎተናገራቸው።ሥልጣንሁሉበሰማይናበምድርተሰጠኝ።”ማቴ28፥18

♥ “አለቅነትንናሥልጣናትንገፎ፥ድልበመንሣትበእርሱእያዞራቸውበግልጥአሳያቸው።”ቆላ2፥15

• ከኢየሱስ ከተቀበልነው ስልጣን የተነሳ በሰይጣን ላይ ብርቱ መሆናችንን

መቀበል። ♥ “በእርሱየመለኮትሙላትሁሉበሰውነትተገልጦይኖራልና።ለአለቅነትናለሥልጣንምሁሉራስ

በሆነበእርሱሆናችሁሞልታችኋል።”ቆላ2፥9-10

• መንፈስ ቅዱስ ሰይጣን የሚጠቀምባቸውን ማንነቶች ማለትም ኃጢአት፣

በደል፣ ይቅር ማለት፣ አመፀኝነትና ስብራት እንዲሁም የነፍስ እስራት ላይ

ከሰይጣን ጋር የተስማማነውን ስምምነት እንዲገልጥልን መጠየቅ።

Page 46: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

36 37

♥ “በቁጣችሁላይፀሐይአይግባ፥ለዲያብሎስምፈንታአትስጡት።”አፌ4፥27

• ማናቸውም መወገድ፣ መጥፋት ያለባቸውን የዲያብሎስ አሰራሮችን

እንዲገልጣቸው መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ።

• ሰይጣን በውስጣችን ባስቀመጣቸው ማንነቶች ፈንታ ምን ማስቀመጥ

እንሚፈልግ መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ

♥ “ቃሉንላከፈወሳቸውም፥ከጥፋታቸውምአዳናቸው።”መዝ107፥20

• እግዚአብሔርን ስላደረገልን ነገር ማመስገንና ማክበር።

♥ “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉንለእግዚአብሔርክብርአድርጉት።”1ኛቆሮ10፥31

ለመሆኑ ኃይለኛው ሰው ማነው? ♥ “ወይስሰውአስቀድሞኃይለኛውንሳያስርወደኃይለኛውቤትገብቶእቃውንሊነጥቀውእንዴት

ይችላል?ከዚያምወዲያቤቱንይበዘብዛል።”ማቴ12፥29

† በኃይለኛ ሰው የተመሰለው ሰይጣን ነው። (ኢሳ 49፤ 24-25) ይህንንም የተባለበትምክንያትየድካምመንፈስካልተፈጠረባቸውናየረሀብመንፈስከሌላቸውመላእክትአንዱከመሆኑምባሻገርበሰዎችላይበተለይምባላመኑትላይጠንካራተፅዕኖማድረግየሚችልበመሆኑነው።በመጽሐፍቅዱስውስጥየተጠቀሱትስሞቹምይህንኑያሳያሉ።

† እንደሚያገሣ አንበሳ (1ኛ ጴጥ 5፥8)፣ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶእርሱም የቀደመው እባብ (ራዕ 12፥9)፣ ሌዋታን (ኢሳ 27፥1)፣ ጥልቅ መልአክ (ራዕ 9፥11)፣የብርሃንን መልአክ የሚመስል (2ኛ ቆሮ 11፥14)፣ ክፉ (ማቴ 13፥39)፣ የዚህ ዓለም አምላክ(2ኛቆሮ4፥4)፣

ኢየሱስ ግን ብርቱ ስለሆነ አሸንፎታል። ከእጁ ሰዎችን አስለቅቋል። ሲኦልን መዝብሮ ነፍሳትን ነፃ አውጥቷል። ሰዎችን በማንቃት፣ አይኖቻቸውን በመክፈት ቅድስና እና ሞገስን በልብ በማስቀመጥ ለእግዚአብሔር መንፈስ ምቹ ማደሪያ እንዲሆን በማዘጋጀት ጠላትን ድል ነስቷል።

ማቴ 12፥29ን ስናነብ በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ አንድ ጠንካራና ልጓም ሊበጅለት የሚያስፈልገው ሰው እንዳለ ኢየሱስ ሲናገር ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን ኢየሱስ ምን ማለት ፈልጎ እንደሆነ ሰፋ ያለ ጥናት ያስፈልጋል። ፈሪሳውያን ኃይለኛ ሰው የሚለውን አባባል በኢሳ 49፥24-25 ባለው አገባብ ይረዱታል።

♥ “በውኑብዝበዛከኃያልእጅይወሰዳልን?ወይስየጨካኙምርኮኞችያመልጣሉን?እግዚአብሔርግንእንዲህይላል።በኃያላንየተማረኩይወሰዳሉ፥የጨካኞችምብዝበዛያመልጣልከአንቺጋርየሚጣሉትንእጣላቸዋለሁ፥ልጆችሽንምአድናለሁ።”ኢሳ49፥24-25

ኃይለኛው ሰው የሚለው ቃል ኃያል ተብሎ በኢሳ 49፥24 በተገለፀው ቃል መረዳት እንችላለን። ኃያል የሚለው ቃል በዕብራይስጥ የሚገልፀው መለኮታዊ ወይም አጋንንታዊ ኃይልን ሲሆን

Page 47: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

37

የሚያመለክተው ደግሞ ብዙ ኃይላትን ነው። በኢሳ 49 ላይ ያለው ቃል በሰዎች እስራት ምክንያት ከሰብዓዊ ባህርይ ውጭ የሆነ ግጭትን ያመለክታል። እዚህ ጋር ኢየሱስ እየተናገረ ያለው አንድ ኃይለኛ ሰው በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ እንዳለ ሳይሆን አንድን ሰው የሚያስሩ ብዙ ማንነቶች በሕይወቱ ውስጥ እንዳሉ ነው።

• አጋንንት የሚሰሩት በስልጣን ተዋረድ ነው፤ ♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ

ዓለምገዦችጋርበሰማያዊምስፍራካለከክፋትመንፈሳውያንሠራዊትጋርነውእንጂ።”አፌ6፥12

ከዚህ ማየት የምንችለው በአንድ ሰው ውስጥ ያለ ጠንካራ (ኃይለኛ ማንነት) በስልጣን ስርዓት ውስጥ እንዳለ ነው። ይህ ማለት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ካለው አጋንንት እስከ ዝቅተኛ ስልጣን ያለው አጋንንት ድረስ መስራት ይችላሉ ማለት ነው። አንድ ሰው ሙሉ ለሙሉ ነፃ ለመውጣት እነኚህ ሁሉ መወገድ አለባቸው።

የኃይለኛው ሰው ቤት ምንድን ነው ?

“የሱ ቤት”- የሚለው ቃል በእርሱ ስር የሚገዛቸውን በሙሉ ይገልፃል። ዓለምን፣ የአየር ላይ ልዑል፣ ከስራው አንፃር በሰዎች ላይ ያለው ተፅዕኖና መንፈሳዊ ፈቃድ በተሰጠው ላይ እንዲሁም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ባለው ሰው ላይ ያለውን ስልጣን ያሳያል።

በማቴ 12፥29 “ቤት” የሚለው ቃል ከሁለት የግሪክ ቃላት የመጣ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ኦኪያ (oikia) ወይም ኦኪዮሰ የሚለው ቃል የሚያመለክተውም መኖሪያን፣ ቤተሰብን፣ ቤትን፣ መጠለያንና መቅደስን ነው። የጥቅሶቹን አገባብ በመመልከት ኢየሱስ የሰውን አካል የኃይለኛው ሰውና በእርሱ ስር ያሉት መኖሪያ ቤትነት ለመግለፅ እንደፈለገ እንረዳለን። የሁለቱን የግሪክ ቃላት ሙሉ ትርጉም በጥምረት በመመልከት ኢየሱስ በተጨማሪ ለመግለፅ የፈለገው አንድን ቤተሰብ መሆኑን መረዳት ይቻላል። የእግዚአብሔር በረከት ወይም እርግማን ለግለሰብ ብቻ ሳይሆን ለትውልድም ነው ።

♥ “ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለምኪዳንአቆማለሁ፥ለአንተናከአንተበኋላለዘርህአምላክእሆንዘንድ።”ዘፍ17፥7

♥ “ሰባትቀንበዳሶችውስጥትቀመጣላችሁከግብፅምድርባወጣኋቸውጊዜየእስራኤልንልጆችበዳስውስጥእንዳስቀመጥኋቸውየልጅልጆቻችሁያውቁዘንድ፥በእስራኤልያሉትየአገርልጆችሁሉበዳስውስጥይቀመጡእኔእግዚአብሔርአምላካችሁነኝ።”ዘሌ23፥43

♥ “አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።”ዘፀ20፥5-6

የኃይለኛው ሰው እቃዎች ♥ “ሌዋውያንሆይ፥ስሙኝተቀደሱ፥የአባቶቻችሁንምአምላክየእግዚአብሔርንቤትቀድሱርኩሱን

ነገርሁሉከመቅደሱአስወግዱ።”1ኛዜና29፥5

Page 48: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

38 39

ከዚህ ጥቅስ አኳያ የኃይለኛው ሰው እቃዎችን አጋንንታዊ እቃዎች ብለን ልንጠራቸው የምንችል ሲሆን የሰው ልጅ ኢየሱስን ከማወቁ በፊት ጠላት በሰው ሕይወት ውስጥ የሚያስቀምጣቸው ቆሻሻዎች ናቸው። ይህንንም የሚያደርገው አጋንንት በአማኞች ሕይወት ውስጥ ያለውን መልካም ገፅታ በጠላት ቆሻሻ እንዲነትብና በእርሱ ተፅዕኖ ውሰጥ እንዲወድቁ ከመሻት ነው። ኢየሱስ እንዳለው ከኃይለኛው ሰው ቤት መውጣትና መፍረስ ያለባቸው ማንነቶች አሉ። (ማቴ 12፥29)

♥ “ስለዚህምእርሱብዙዎችንይወርሳል፥ከኃያላንምጋርምርኮንይከፋፈላልነፍሱንለሞትአሳልፎሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለዓመፀኞችምማለደ።”ኢሳ53፥12

የአጋንንት ባህርይ መስረቅ፣ መግደልና ማጥፋት ነው። በዚህ ምክንያት ኢየሱስ በግልፅ የሚናገረው የኃይለኛውን ሰው እቃ መውረስ አንደኛው የነፃ ማውጣት አካል ነው።

♥ “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸውእንዲበዛላቸውምመጣሁ።”ዮሐ10፥10

አጋንንት በእያንዳንዱ የሰው ሕይወት ላይ የሚያመጣው ማንኛውም ነገር ለሰውየውና ከሰውየው ጋር የደም ትስስር ባላቸው ሰዎች ላይ ጥፋት የሚያመጣ ሲሆን ሰውየውም ቢሆን ቤተሰቦቹ በአጋንንት ስልጣን ስር እንዲወድቁ በር ይከፍትላቸዋል። በዚህ መንገድ የሚመጡ የባዕድ መንፈሳዊ መሳሪያዎች፣ ሰዎች በራሳቸው ኃጢአትና በጣዖት አምላኪነታቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ ያደርጋሉ።

ለጠላት መጠቀሚያ እቃዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች፦• የጨለማው አሰራር

የጨለማ አሰራር ማለት ሰዎች በተገለጠ ብርሃን እንዲጓዙ ከማድረግ ይልቅ በድቅድቅ ጨለማ እንዲደናበሩ ማድረግን የሚመለክት ሲሆን ከሌሎች ተሸሽጎ እንደ ዘረፋ፣ ድብደባ እና ዝሙት ያሉ ድብቅ ኃጢአቶችን መስራት ማለት ነው።

ማንም በጨለማ የሚጓዝ ቢኖር ውስጡ በፍርሀት ይጨነቃል። በጉዞውም ደህንነት አይሰማውም። በጨለማ ውስጥ የተደበቀ ጠላት ክፉ ተግባር ይሰነዝርበታልና። ከጨለማ ወደ ብርሀን ስንወጣ ግን በግልፅ እናያለን። ስለዚህ ደህንነትም ይሰማናል። በመንፈሳዊ ሕይወታችንም የጽድቃችን ፀሃይ በሆነው ጌታ ባበራልን ብርሃን ልንጓዝ ይገባናል።

♥ “ከጨለማናከሞትጥላአወጣቸው፥እስራታቸውንምሰበረ። ”̋መዝ107፥14

• ቀንበር

ሰይጣን የሰው ልጆች በኑሯቸው እንዳይደሰቱና አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር እንዳያደርጉ ብዙ ቀንበሮችን አድርጎባቸዋል። ስለዚህ ስለ ዘላለማዊ ሕይወታቸው ከማሰብ ይልቅ በሕይወታቸው ውስጥ የሚያጠነጥነውን ችግር በመፋቅ ብኩን እንዲሆኑ አድርጎዋቸዋል።

♥ “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍርትለቅቁዘንድ፥የተገፉትንስአርነትትሰድዱዘንድ፥ቀንበሩንስሁሉትሰብሩዘንድአይደለምን?”ኢሳ58፥6

♥ “ባሪያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ

Page 49: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

39

የባርነታችሁንቀንበርሰብሬአለሁቀናብላችሁእንድትሄዱአድርጌአችኋለሁ።”ዘሌ26፥13

እነኚህንና እነኚህን የመሳሰሉ መንፈሳዊ መሳሪያዎች ከሰው ሕይወት ካልተወገዱ ጠላት በሰው ሕይወት ውስጥ ስልጣኑን ያሰፋል። አጋንንታዊ እቃዎችንና መጠቀሚያዎች መለየት የምንችለው መንፈስቅዱስ እንዲገልጣቸውና ከተገለጡ በኋላ ምን መደረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔርን ስንጠይቅ ብቻ ነው።

• አይነ-ርግብ

♥ ስለአይነ-ርግብ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባትበመከዳችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀድዳታለሁ፥ እንደ ወፍም የምታጠምዱአቸውንነፍሳትእለቅቃለሁ።ሽፋኖቻችሁንደግሞእቀድዳለሁሕዝቤንምከእጃችሁአድናለሁ፥ከዚያምወዲያ በእጃችሁ ለመታደን አይሆኑም እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። እኔምያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገድእንዳይመለስየኃጢአተኛውንእጅአበርትታችኋልና።”ሕዝ12፥20-22

ሰ) ሰዎችን ከእስራት ነፃ ለማውጣት ♥ “ብቻውንአምላክለሚሆንለማይጠፋውለማይታየውምለዘመናትንጉሥምስጋናናክብርእስከ

ዘላለምድረስይሁን፤አሜን።”1ኛጢሞ1፥17

ሰዎችን ከእስራት ነፃ የማውጣት ዓላማ ኢየሱስ እንዲከብርና ስላደረገልን ነገር እንዲመሰገን ነው። ሰዎች ነፃ እንዲወጡ የምንፀልየው ኢየሱስ የሰው ልጆችን ስለሚወድና ለነፃነታችን እስከ ሞት ድረስ ዋጋ ስለከፈለ ነው። የእርሱ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን ደግሞ የእርሱን ፈለግ ልንከተል ይገባል። በመሆኑም በሞት ጥላ ስር ላሉ መፈታትን፣ በባእድ አምልኮ ለተጠመዱ የሕይወት መንገድን፣ በጨለማው አሰራር ተሰናክለው ለወደቁት ዳግም መነሳትን፣ በተስፋ መቁረጥ ረመጥ ውስጥ ላሉ ተስፋን፣ መንፈሳዊ አይናቸው ታውሮ በስጋ መንፈስ ብቻ ወደሞት የሚጓዙትን የወንጌሉን ብርሃን እየሰበክን ከዲያብሎስ ምርኮ ነፃ ማውጣት ከጌታ የተቀበልነው ኃላፊነታችን ነው።

† የመጽሐፍቅዱስአዲሱትርጉምሉቃ4፥18በሚከተለውመንገድይተረጉመዋል።

♥ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው ለድሆች ወንጌልን እንድሰብክ ቀብቶኛልና ለታሰሩት መፈታትንለታወሩትማየትንእንዳውጅየተጨነቁትንነፃእንዳወጣየተወደደችውንየጌታአመትእንዳወጅልኮኛል።”

Page 50: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

40 41

ምዕራፍ 4መንፈሳዊ ውጊያ

መንፈሳዊ ውጊያ ለክርስቲያኖች የሕይወት አንዱ ክፍል ነው። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን ከተጠመቅንባት ጊዜ አንስቶ የመንፈስ ውጊያ ወታደሮች ነን። በምድራዊው ዓለም ላይ ሳለን ሀገራችንም ሀሳባችንም ሰማያዊ ነው። ሰይጣን የምድራዊው መንግስት ገዢ ነውና ሰማያዊ ዜግነትን ሽተን የምድራዊ ዜግነትን መናቃችን ለእርሱ ሕመሙ ነው። በመሆኑም በእኛና በሰይጣን መካከል “ከግዛቴ አትወጡም”ና “እንወጣለን” በሚል ምክንያት ጦርነት ይፈጠራል። ይህ በጠላት ጭፍሮችና በክርስቶስ ኢየሱስ አማኞች መካከል የሚደረገው ውጊያ መንፈሳዊ ውጊያ የሚል መጠሪያ አለው። መንፈሳዊ ውጊያ ሰው በራሱ ፈልጎ የሚያመጣው ሳይሆን ክርስቲያን በመሆኑና የጠላትን መንገድ አልፈልግም ብሎ በመካዱ ምክንያት የሚመጣ የሰይጣን የበቀል እርምጃ ነው። መንፈሳዊ ውጊያ አንድ አማኝ ጌታን ከተቀበለ በኋላ የሚያጋጥመውን እንቅፋት የሚወጣበት ስልትም ነው።

ይህ ምዕራፍ አንድ አማኝ ጌታን ከተቀበለ በኋላ የሚያጋጥመውን ከጠላት የሆነ እክል በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እንዴት የጠላትን ግዛት በራሱ ሕይወትም ሆነ በአካባቢው ላይ ማፈራረስ የሚችልበትና ከጠላት ስልታዊ ጥቃቶች እንዴት መከለል እንዳለበት በጥቂቱ በመግለፅ የሚያዘጋጅ ነው።

4.1 የመንፈሳዊ ውጊያ ጭብጥ

በወደቀው ዓለም ውስጥ እስካለን ድረስ መንፈሳዊው ውጊያ እየተፋፋመ የሚቀጥል እንጂ ማቆሚያ ያለው አይደለም። ሰይጣንና የወደቁት ተከታዮቹ ግዛታቸውን ከእግዚአብሔር ግዛት ለማስጠበቅ ሌት ተቀን ይተጋሉ። ይህም ተጋድሎ ሰዎች የመዳንን ነፃነት እንዳያገኙ በማሳወር የጠፉ

Page 51: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

41

ነፍሳትን ለራሱ መንግስት በማስገዛትና ቅዱሳን ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግስት እንዳያስፋፉ በዓላማና ዕቅድ የሚያሰናክልበት መንገድ ነው።

ለአዲስ አማኞች መንፈሳዊው ውጊያ ይበረታባቸዋል። በእምነት የጎለበቱትም ቢሆኑ ከውጊያው የሚያመልጡ አይደሉም። በክርስቲያኖች ላይ ውጊያ የሚበረታው ከእግዚአብሔር ወገን በመሆናችን ነው። ሁልጊዜም ውጊያ ሲካሄድ ሁለቱ አካላት ከአንድ ወገን እንዳልሆኑ የታወቀ ነው። ከዲያብሎስና ከወገኖቹ ጋር የሚካሄደው ውጊያም የዚህ ልዩነት መገለጫ ነው። ከተማረከ ሰራዊት ጋር ማንም እንደማይዋጋ ሀቅ ነው። ጌታ ይህን አስቀድሞ ስለተናገረን ተዘጋጅቶ መቆም ተገቢ ነው። በመንፈሳዊ ውጊያ ሂደት ውስጥ ነፃ የወጣን ሰዎች በየጊዜው እንፈተናለን፤ በጌታ መታመናችንና በእርሱ ላይ ብቻ መደገፍ እንድንጀምር እንማርበታለን።

የመንፈሳዊ ውጊያ ውጤት በገሃዱ ዓለምም የሚታዩ ተግዳሮቶች አሉት። በቅዱሳን መላእክትና በጠላት ጭፍራዎች መካከል የሚደረገው ትግል ፈለግነውም አልፈለግነውም እኛን ይመለከታል። በተለይ አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን የጠላት ጠላት ስለሚሆንና ሰይጣንም የአማኝ ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ ስለሚያውቅ ይህ ተጋድሎ ይበልጥ ይበረታል።

♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”ኤፌ6፥12

የጠላትን ስራ ለማጋለጥ በመጀመሪያ ማወቅ ያለብን ነገሮች አሉ፤ መንፈሳዊ ውጊያ በእግዚአብሔር ኃይላት (ማለትም ቅዱሳን መላእክትና የዳኑ ሰዎች) እንዲሁም በሰይጣንና በተከታዮቹ መካከል የሚደረግ ውጊያ ነው። ይህም ውጊያ የጠፉትን ነፍሳት ወደ መዳን እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። ሰይጣን ብዙ ሰዎች እንደጠፉ እንዲቀሩ ይፈልጋል። የክርስቲያኖች ዓላማ ደግሞ በጠላት ግዛት ላይ ሕይወትን በሚለውጠው ወንጌል አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር መንግስት የጠፉትን መሰብሰብ ነው።

4.2 የሰይጣንና ጭፍሮቹ ማንነትና ባህርያት ♥ “በእነርሱምላይንጉሥአላቸውእርሱምየጥልቅመልአክነው፥ስሙምበዕብራይስጥአብዶን

በግሪክምአጶልዮንይባላል።”ራዕ9፥11

• ሰይጣን አፈጣጠሩ እንደ መልአክ ነበር። የተፈጠረበትም ዓላማ እንደሌሎቹ ቅዱሳን መላእክትየእግዚአብሔርአገልጋይእንዲሆንነበር።

♥ “አንተልትጋርድየተቀባህኪሩብነበርህበተቀደሰውበእግዚአብሔርተራራላይአኖርሁህበእሳትድንጋዮችመካከልተመላለስህ።”ሕዝ28፥14

ነገር ግን ሰይጣን ለፈጠረለት ዓላማ ከመኖር ይልቅ ባልተፈጠረለት ዓላማ ጌታ መሆንን ሻተ። ጌትነቱንም መላእክቱ ያምኑለት ዘንድ ሰበካቸው። በመሆኑም ያመኑት ሌሎች መልአክትም ነበሩት። ሰይጣን የነበረው የመላእክነት ስልጣኑ ተገፎ ወደ ምድር ሲጣል ያመኑበት ሁሉ አብረውት ተጥለዋል። ከዛን ጊዜ የጀመረ ክፋቱ ዛሬም ድረስ በሰዎች ሕይወት ውስጥ መሰናክሎችን እያስቀመጠ እንዲወድቁ ያደርጋል።

Page 52: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

42 43

♥ “ጅራቱምየሰማይንከዋክብትሲሶእየሳበወደምድርጣላቸው።ዘንዶውምሴቲቱበወለደችጊዜሕፃንዋንእንዲበላልትወልድባላትሴትፊትቆመ።”ራዕ12፥4

♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”ኤፌ6፥12

♥ “እርሱከመጀመሪያነፍሰገዳይነበረ፤እውነትምበእርሱስለሌለበእውነትአልቆመም።ሐሰትንሲናገርከራሱይናገራል፥ሐሰተኛየሐሰትምአባትነውና።”ዮሐ8፥44

† ጠላታችንይህሰይጣንሲሆንእርሱምየወደቀውመልአክ፣ሲሶ(1/3)መላእክትያሳተናፈጣሪያቸውን ትተው እርሱን የመረጡ ተከታዮች ያሉት፣ እግዚአብሔርን ባለመታዘዙምክንያትበወደቀውየሰውማንነትላይጥፋትንየሚያመጣማንነትያለውመንፈስነው።በመጽሐፍቅዱስውስጥሰይጣንንሊገልፁከሚችሉስሞችመካከልጥቂቶቹእነሆ፦

ሌባ፤ አጥፊና ገዳይሰይጣን ብዙ ጊዜ የሚጠራባቸው ስሞች ምግባሩን የሚገልፁ ናቸው። ከመጥፎ ምግባሮቹ

መካከል ሌብነት አንዱ በመሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሌባ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት እናገኘዋለን።

♥ “ሌባውሊሰርቅናሊያርድሊያጠፋምእንጂስለሌላአይመጣም፤እኔሕይወትእንዲሆንላቸውእንዲበዛላቸውምመጣሁ።”ዮሐ10፥10

ሰይጣን ከሰዎች ላይ የሰረቃቸው አካላዊ ነገሮች እንዳሉ ሆነው የሰረቃቸው መንፈሳዊ ነገሮች ግን በሰዎች ላይ ይበልጥ ጉዳትን አስከትለዋል። ሰዎች ከተሰረቁባቸው መንፈሳዊ ነገሮች መካከልም ሰላም፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ ጤና፣ አንድነት፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ ንጹህ ልብ፣ የገዢነት ስልጣን፣ ጥንካሬ እና ሌሎች ቆጥረን የማንጨርሳቸው ነገሮች ናቸው። የሰው ልጆች ጸጋ የነበሩ እነዚህን ሁሉ መንፈሳዊ ሀብቶች አጥፍቷቸዋልና አጥፊ የሚለው ስያሜም ተሰጥቶታል።

ውሸታምና ወንጀለኛውሸት የሰይጣን መገለጫ ነው። ይህ ውሸት የሰው ልጆችን ከገነት ያባረረና ብዙ መላእክትንም

ወደ ጥልቁ ያስጣለ ሲሆን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንም ጭምር በኃጢአት ለመጣል በፈተና መልክ የቀረበ ነው። በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሲሉ የሀሰት መዓት ይደረድራሉ። ይህንንም ሲያደርጉ ዕቅዳቸውን ከመፈፀም ባሻገር የሰይጣናዊ ባህርይ እያጎለበቱ እንደሆነ አይገነዘቡትም።

♥ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱከመጀመሪያነፍሰገዳይነበረ፤እውነትምበእርሱስለሌለበእውነትአልቆመም።ሐሰትንሲናገርከራሱይናገራል፥ሐሰተኛየሐሰትምአባትነውና።”ዮሐ8፥44

ተንኮለኛና አታላይተንኮል የሚሰራው በሌላው ስህተትና ውድቀት ለመደሰት ሲሆን ተንኮሉ ለተሰራበት አካል

ጉዳት በተቃራኒው ደግሞ ተንኮሉን ላደረገው አካል መዝናኛ ነው። ሰይጣን በሰራው ተንኮል የሰው

Page 53: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

43

ልጆች ከገነት ሲባረሩ ማየቱ ደስታው ነበረ። የሰይጣን ተንኮል አሁንም ቢሆን የሰው ልጆችን እየጣለ፣ ከእውነተኛው መንገድም እያሳታቸው ይገኛል። ዓለም አወቅኩ የምትላቸው ነገሮች በእግዚአብሔር ዘንድ ያላዋቂነት ምልክቶች ናቸው፤ ዓለም ሰለጠንኩ የምትልባቸው መንገዶችም ከእግዚአብሔር የሚያርቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ዓለም የምትነግረን በምንም ሁኔታ ቢሆን ትርፍ እንድናተርፍ ሲሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ኪሳራ ነው። ለዚህም ነው ክርስቶስ “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል” ማር 8፥36 ያለው። እነዚህ ሁሉ ሰይጣን ዓለምን ወደ ስህተት የሚመራባቸው የተንኮል ወጥመዶቹ ናቸው። በተጨማሪም አዳምንና ሄዋንን አታሎ ከጌታ መንግስት ከማባረሩም ባሻገር አሁንም ዓለምንና አሸንክታቦቿን የሚያምሩ በማስመሰል ወደሞት የሚመራ ነውና አታላይ ተባለ።

♥ “ነገርግንእባብበተንኮሉሔዋንንእንዳሳታት፥ሀሳባችሁተበላሽቶለክርስቶስከሚሆንቅንነትናንጽሕናምናልባትእንዳይለወጥብዬእፈራለሁ።”2ኛቆሮ11፥13

♥ “ዓለሙንምሁሉየሚያስተው፥ዲያብሎስናሰይጣንየሚባለውታላቁዘንዶእርሱምየቀደመውእባብተጣለ፤ወደምድርተጣለመላእክቱምከእርሱጋርተጣሉ።”ራዕ12፥9

ከሳሽ ♥ “ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም

የክርስቶስምሥልጣንሆነ፥ቀንናሌሊትምበአምላካችንፊትየሚከሳቸውየወንድሞቻችንከሳሽተጥሎአልና።”ራዕ12፥10

የሚያገሳ አንበሳ ♥ “በመጠንኑሩንቁም፥ባላጋራችሁዲያብሎስየሚውጠውንፈልጎእንደሚያገሣአንበሳይዞራልና”

1ኛጴጥ5፥8

የፍርሃት መንፈስየሰው ልጅ ሲፈጠር የሚፈራው አንዳች ነገር አልነበረውም። ታዲያ የፍርሃትን ስሜት በሰው

ልጆች ሕይወት ውስጥ ማን ዘራው? ሀሳቡስ እንዴት ተሳካለት? የፍርሃት ስሜትን ወደ ሕይወታችን ያስገባው የሰው ልጅ ሁሉ ጠላት የሆነው ዲያብሎስ ነው። ሀሳቡ ሊሳካለት የቻለውም የሰው ልጅ በአምላኩ ላይ የነበረውን እምነት ከውስጡ ሸርሽሮ ስለወሰደበት ነው። የሚያምን አይፈራም፤ አይጠራጠርምም። የሚያምን ቢኖር ግን እንደ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ወደ እሳት ቢጣል እንኳን በፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ሳይሆን እስከሞት ድረስ በመታመን ነው። እንደ ሰማዕቱ እስጢፋኖስም ከሚወረወርበት ድንጋይ ይልቅ ነፍሱ የምታርፍበትን የሰማይ ደጅ ተከፍቶ ያያል። ስለዚህ አይፈራም።

♥ “ፍጹምፍቅርፍርሃትንአውጥቶይጥላልእንጂበፍቅርፍርሃትየለም፥ፍርሃትቅጣትአለውና፤የሚፈራምሰውፍቅሩፍጹምአይደለም።”1ኛዮሐ4፥18

የብርሃን መላእክት መሰልየዲያብሎስ አሰራር ሰዎች በስህተት መንገድ እንዲሰለፉ ያደረገ ነው። ማንም ሰይጣንን በጸብና

በክርክር ብቻ የሚገለጽ ነው ብሎ የሚያምን ከሆነ ስህተት ነው። ሰይጣን አማኞችን የሚዋጋው ጦርን በመሰበቅ ብቻ ሳይሆን የብርሀን መልአክ በመምሰል የክርስቲያኖች ስብስብ መካከል

Page 54: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

44 45

ላይ በመገኘት ነው። እንደ አገልጋይም በመሆን መድረክ ላይ በመውጣትና የሌሎች ኃጢአትን በመዘርዘር ለሌሎች መሰናክል ይሆናል። የጌታን ቃል ገልጦ የአሮጊቶችን ተረት ተረት ያወራል። የኢየሱስ ክርስቶስን ቃልና ትምህርት በማጣመም የሀሰት ትምህርትን በማሰራጨት ብዙዎችን ወደ ስህተት መንገድ ይመራል። ለእምነታቸው የቀኑ መስሏቸው የሚያመልኩትን አምላክ ሳያውቁት እንዲክዱ ያደርጋቸዋል።

♥ “ይህምድንቅአይደለም፤ሰይጣንራሱየብርሃንንመልአክእንዲመስልራሱንይለውጣልና።”2ኛቆሮ11፥14

♥ “የበግለምድለብሰውከሚመጡባችሁበውሥጣቸውግንነጣቂዎችተኵላዎችከሆኑከሐሰተኞችነቢያትተጠንቀቁ።”ማቴ7፥15

ፈታኝየሰይጣን ፈተና ትኩረት የሚያደርገው ሰዎችን ከትክክለኛው መንገድ በማሳት ላይ ነው።

ብዙ ጊዜ የሚፈትነን ደግሞ ከሁሉ አብልጠን በምንወዳቸው ነገሮች ነው። ይህ ደግሞ ለብዙ ሰዎች ፈተናውን እንዳናልፍ ምክንያት ይሆናል። ገንዘብን አብልጠን የምንወደውን በገንዘብ፣ ዝናን የምናፈቅረውን በዝና፣ ቤተሰባችንን አብልጠን ለምንወድ ደግሞ በቤተሰብ ፈተናውን ያዘጋጃል። እንደ ልቤ የተባለው ንጉስ ዳዊት የተሸነፈበት ፈተና በሴት ልጅ ውበት ነበር። የጌታ ደቀመዝሙር የነበረው ይሁዳ ደግሞ የተሸነፈው አዕምሮውን ጠፍሮ በያዘው የገንዘብ ፍቅር ነበር።

ትዕግስተኛው ኢዮብ ግን ምንም እንኳን በምንወዳቸው ነገሮች የሚመጡብን ፈተናዎች ቢበዙብንም ከአምላካችን ጋር እንዳይስተካከሉብን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባን ያሳየናል። ኢዮብ አምላኩን እንዲክድ በሚወዳቸውና በሚያፈቅራቸው ነገሮች በሙሉ ተፈትኗል። ከተፈተነባቸው ነገሮች መካከል ያሉት ንብረቶች በሙሉ ወደሙበት። ይህ በመሆኑ ግን በአምላኩ ላይ የስድብም ሆነ የማማረር ቃል አልተናገረም። ቀጥሎም የተፈተነው ከንብረቱ በላይ በሚሳሳላቸው ውድ ልጆቹ ነበር። እነዚህ ልጆች የቤቱ ማዕዘን ተደርምሶባቸው በአንድ ላይ ማለቃቸውን ሲነገረው እንኳን የማማረር ቃል አልተሰማበትም ነበር። ይልቁኑም “እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ነሣ፤ (ኢዮ 1፥21)” በማለት ለአምላኩ ያለውን ፍቅር በቁስ አካላት እንደማይለካ አረጋገጠ እንጂ። በመቀጠልም በጤናው፣ ከዛም በገዛ በሚስቱና ጓደኞቹ ተፈተነ። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ቢያፈቅራቸውም ነገር ግን ከአምላኩ ጋር ሊስተካከሉለት አልቻሉም። በመሆኑም ፈታኙ ሰይጣን በፈተናው ተሸነፈ። እኛም በምን አይነት ፈተና እየተፈተንን እንዳለን መገንዘብ አለብን። እምነታችን የሚለካው በሱ ነውና።

♥ “ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ። ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋልድካማችንምከንቱሆኖአልብዬእምነታችሁንለማወቅላክሁ።”1ኛተሰ3፥5

ክፉ ክፉ የምንለው በሌሎች ላይ እኩይ የሆነ ድርጊትን የሚፈጽም አካልን ነው። የክፋቱ ዓላማም

በሌሎች ሀዘን ለመደሰት እንዲሁም መሰናክልን በማድረግ ካሰቡበት ስፍራ ለማስቀረት ሊሆን ይችላል። ሰይጣን በፈጣሪው ላይ በማመጽ የጀመረው ክፋት የሰው ልጆችንም ትእዛዝ አለማክበርን በመስበክ ባህሪያቸው እንዲቆሽሽ፣ የጸጋ ልብሳቸው እንዲገፈፍና ከገነት ወደ ምድር እንዲጣል፣ በኑሮው ውስጥም እሾክና አሜኬላ እንዲያበቅል አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪም አዳምን ከገነት እንዲባረር ያደረገ፣ ለቃየን ድንጋይ በማቀበል በወንድሙ ላይ ግድያ እንዲፈጽም፣ በአሁኑም ጊዜ

Page 55: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

45

ጎሳ በጎሳ ላይ፣ ሀገርም በሀገራት ላይ ጦር እንዲሰብቁ በማድረግ የክፋትን ባህርይ ከራሱ አልፎ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠረው የሰው ዘርም አውርሶታል።

♥ “የመንግሥትንቃልሰምቶበማያስተውልሁሉ፥ክፉውይመጣል፥በልቡየተዘራውንምይነጥቃልበመንገድዳርየተዘራውይህነው።”ማቴ13፥19

♥ “…እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለምመጨረሻነው፥አጫጆችምመላእክትናቸው።”ማቴ13፥39

† አዳምን እና ሄዋንን አታሎ ከጌታ መንግስት ከማባረሩም ባሻገር አሁንም ዓለምን እናአሸንክታቦቿንየሚያምርበማስመሰልወደሞትየሚመራነውናአታላይተባለ።

♥ “ዓለሙንምሁሉየሚያስተው፥ዲያብሎስናሰይጣንየሚባለውታላቁዘንዶእርሱምየቀደመውእባብተጣለ፤ወደምድርተጣለመላእክቱምከእርሱጋርተጣሉ።”ራዕ12፥9

ዘንዶ ♥ “ሌላምምልክትበሰማይታየ፤እነሆምታላቅቀይዘንዶ፤ሰባትራሶችናአሥርቀንዶችምነበሩት

በራሶቹምላይሰባትዘውዶችነበሩ፥”ራዕ12፥3

የዚህ ዓለም ገዢሰይጣን የዚህ ዓለም ገዢ ተብሏል። ገዢ የተባለበትም ምክንያት ሰዎችን ከእግዚአብሔር

መንገድ ውጪ በማድረግ ለገዛ ሀሳቡ ተገዢ ስለሚያደርጋቸውና ለፍላጎቱም ስለሚያሰልፋቸው ነው። የአገዛዝ ስርዓቱ ደግሞ “በምድር ላይ ሳለህ አንተን ብቻ ደስ ይበልህ” የሚል መርህን ይከተላል። ይህንንም ደስታ ለማግኘት ስረቅ፤ ዝረፍ፤ ዘሙት፤ ጨፍር፤ ደንስ፤ ሌላውን አሸንፈህ አንተ ብቻ የበላይ ሁን እንጂ ማንም ካንተ የበላይ አይሁን፤ አንተ ለማለፍ ከፈለግክ ሌሎቹን ጣል፤ መከበርንም ከፈለግክ ሌሎቹን አዋርድ የሚል ነው። ነገር ግን ክርስቲያኖች የምንመራው በዚህ ዓለም ገዢ ሳይሆን በእግዚአብሔር ነው። በመሆኑም እነዚህን የጠላት አገዛዝ ስርዓቶችን በሙሉ እንቃወማለን።

♥ “ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይምአንዳችየለውም”ዮሐ14፥30

4.3 መንፈሳዊ ውጊያ የት፣ መቼ እና እንዴት ይካሄዳል?(ኤፌ 6፥12፣ 1ኛ ቆሮ 4፥14)

እግዚአብሔር በሚሰራበት በማንኛውም ቦታ መንፈሳዊ ውጊያ አለ። የክፉ ሀሳብ የእግዚአብሔርን ልጆች ከመልካም መንገድ መመለስና ወደ ጥፋት መንገድ ማስገባት ነው። በማይታየው መንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ይህ ውጊያ በቤታችን ውስጥ፣ በስራችን ቦታ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሉ ይካሄዳል። መንፈሳዊ ውጊያ በሰማያዊ ግዛት ላይ የሚካሄድ ሲሆን የጦር ሜዳውም የሰዎች አዕምሮ ውስጥ ነው።

Page 56: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

46 47

መንፈሳዊ ውጊያ መቼ ይካሄዳል?ይህ ውጊያ የጀመረው መላእክት ሲወድቁ ሲሆን ወደ ምድር የመጣው ደግሞ አዳምና ሔዋን

ከገነት ሲባረሩ ነው። ሰዎች ወደ ክርስቶስ መንገድ ሲመጡ ከሰይጣን ቁጥጥር ውጪ ይሆናሉ። የዚህን ጊዜ ጠላት ታላቅ ውጊያ ይጀምራል። ሰይጣን ለመንፈሳዊ ውጊያ የሚሰጠው ቦታ እጅግ ከፍተኛ ነው። ወደ ዓለም ፍፃሜ እየተቃረብን በመጣን ቁጥር ኃይሉን እያጠናከረ ይገኛል። ኃጢአትን ለማድረግ ስናስብ፣ የስጋ ባህርያትን ስናሳይ፣ ከሰው ጋር ተጣልተን ልባችን ሲሰበር፣ መንፈሳችን ሲወድቅ፣ በእነዚህ ሁሉ ጊዜ መንፈሳዊ ውጊያን እየተዋጋን ነው። ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ወጥተን ጌታ ወደሚፈልገው ቦታ ለመድረስ ከፍተኛ ትግል ሊጠብቀን ይችላል። እግዚአብሔርን መታመናችንና የዳንበትን ዓላማ በደንብ ማወቅ አሸናፊዎች ያደርገናል።

• መንፈሳዊውጊያእንዴትይካሄዳል?(ኤፌ6፥12፣ዳን10)

ሰይጣን በመንፈሳዊና በገሃዱ ዓለም ጦርነት ይከፍታል። በመንፈሳዊው ዓለም በሰዎች ልብና አዕምሮ ውስጥ ይህ ውጊያ ሲካሄድ በተጓዳኙ በገሃዱ ዓለም ደግሞ የመሬትን ይዘት በመያዝ በሚታዩ ዕንቅፋቶች በጭፍራዎቹ አማካኝነት ያካሄዳል። ሰይጣን ኃይሉን በሙሉ አሟጦ ክርስቲያኖችን ሊያጠፋና ዓላማቸውንም ሊያስት ይታገላል። ነገር ግን መንፈሳዊ ውጊያን ስንዋጋ መጠንቀቅ ያለብን ነገር ብቻችንን አለመሆናችን ማረጋገጥ ነው። የክርስቶስን ስም ስለጠራን ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል። ከኢየሱስ ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ሲኖረን ስሙን ስንጠራ ኃይልና ስልጣን ይኖረናል።

ብላቴናው ዳዊት በእስራኤላውያን ዘንድ ይፈራ የነበረውን ጎልያድን መትቶ የጣለው በወንጭፍ በተወረወረች አንዲት ጠጠር መስሎ ከተሰማን ተሳስተናል። ዳዊትም ያለው “አንተ በኃይልህ እና በጉልበትህ ስትመጣ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሀለሁ (1ኛ ሳሙ 17፥45)” ነው። እንደዚህ በእግዚአብሔር ኃይል ላይ ለመደገፍ ደግሞ እርሱን ማወቅ ይገባናል።

4.3.1 ጠላት ዲያብሎስ ክርስቲያኖችን ለማጥመድ የሚጠቀምባቸው ስልቶች

አንዳንድ ሰዎች ዲያብሎስን የሚስሉት መልኩ ጥቁር፣ ጥፍሮቹ የሾሉ፣ ጥርሱ ያገጠጠ፣ አይኑ ደም የመሰለ እና እርቃነ ስጋውን እደሚጓዝ ፍጡር አድርገው ነው። የብርሃን መልአክ እስከሚመስል ድረስ ራሱን እንደሚለውጥ አይገነዘቡም። ስለዚህ ራሱን ቆንጆ አድርጎ ከመጣ በውጊያ ላይ መቆየት ይሳናቸዋል። ሁለመናቸውን ለሀሰተኛው አባት ምርኮኛ አድርገው ያስገዛሉ። ከዚህም ሌላ ልናውቅ የሚገባን ነገር መልካም ሆኖ እንዲሁም ተለሳልሶ በመቅረብ ብዙ ክርስቲያኖችን ራሳቸውን ምርኮኛ አድርገው እንዲያስገዙለት የማድረግ መንገድም መከተሉን ነው። ጠላታችን ዲያብሎስ ለውጊያው የሚጠቀምበት የተለያዩ ስልቶችና የጦር ሜዳዎች ሲኖሩት በዋነኛነት ሶስት የጦር ሜዳዎችን ይጠቀማል፤ እነሱም የነፍስ የጦር ሜዳ፣ የዲያብሎስ የጦር ሜዳ እና የሰዎች የጦር ሜዳ ስልቶች ናቸው።

Page 57: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

47

4.3.2 ነፍሳችን ሕይወታችንን እንድትመራ በመፍቀድነፍሳችን የአዕምሯችን፣ የፈቃዳችን፣ የስሜታችን ውቅር ናት። የነፍስ ትስስር የማይታይ

ነገር ግን የአንድ ሰው ነፍስ ከሌላ ሰው ነፍስ ጋር ሲዋሃድ (ሲጣጣም) የሚፈጠር ነው። ነፍሳችን ሃሳባችንን፣ ስሜታችን እና ፈቃዳችንን አካታለች። ለምሳሌ ያህል ዳዊትና ዮናታን በ 1ኛ ሳሙኤል በምዕራፍ 18 ቁጥር 1 ላይ እንደተገለፀው ነፍሳቸው እንደተሳሰረና እስከሞት ድረስ ይዋደዱ እንደነበር ይታወቃል። የነፍስ ትስስር ከጥልቅ ፍቅር የሚመነጭ ሲሆን ማንኛውንም መሰናክል የሚያሳልፍ ኃይል ይሰጣል።

የነፍስ የጦር ሜዳ በነፍሳችን ውስጥ የሚካሄደውን ሙግት ያመላክታል። የሰዎችን ባህርይ የነፍስ ሙግት ውጤት ነው ልንለው እንችላለን። በጎው ጎናችን ከስጋዊ ፍላጎታችን ጋር ይዋጋሉ፤ ከዛም አንዱ ያሸንፋል። ስጋ ሲያሸንፍ ሰዎች ክፋት የነገሰባቸው፣ በሌሎች ሃዘን የሚደሰቱ፣ ራስ ወዳድ እና በሁለት ሀሳብ ወላዋይ ይሆናሉ። በወንድሞቻቸው ላይ እንኳን ሳይቀር የክፋት ሰይፋቸውን ይመዛሉ። ነገር ግን ሰላም ከሕይወታቸው ይርቃል። በመሆኑም የሚኖሩባት ዓለም የምታሳድዳቸው እስኪመስላቸው ድረስ ጥላቸውን እንኳን ማመን ይሳናቸዋል። (ዘፍ 4)

በጎ ጎናችን ሲያሸንፍ ደግሞ የእግዚአብሔር ሰላም በውስጣችን ይሞላል። ለወንድሞች አዛኝ፣ ቅን፣ ደስተኛ እንሆናለን። የዲያብሎስን አሰራር አሸንፈን እንደ እግዚአብሔር ውጥን መኖር ይቻለናል። እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ ለመኖር የጦርነቱ ውጤት በመልካሙ ጎናችን አሸናፊነት መጠናቀቅ አለበት።

♥ “ስለሥጋማሰብሞትነውና፥ስለመንፈስማሰብግንሕይወትናሰላምነው።ስለሥጋማሰብበእግዚአብሔርዘንድጥልነውና፤ለእግዚአብሔርሕግአይገዛምና፥መገዛትምተስኖታል፤”ሮሜ8፥6-7

♥ “በእኔማለትበሥጋዬበጎነገርእንዳይኖርአውቃለሁና፤ፈቃድአለኝና፥መልካሙንግንማድረግየለኝም።የማልወደውንክፉንነገርአደርጋለሁናዳሩግንየምወደውንበጎውንነገርአላደርገውም።”ሮሜ7፥18-19

♥ “ነገር ግን በብልቶቼ ከአዕምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግየሚማርከኝንሌላሕግአያለሁ።እኔምንኛጎስቋላሰውነኝ!ለዚህሞትከተሰጠሰውነትማንያድነኛል?”ሮሜ7፥23-24

4.3.3 ለገንዘብ ጤናማ ያልሆነ ፍቅር እንዲኖረን በማድረግገንዘብ ለሰው ልጆች መገልገያ ተደርጎ የተፈበረከ ቢሆንም በተቃራኒው ብዙ ጊዜ ሰዎች ገንዘብን

ሲያገለግሉ ይታያሉ። ሰይጣን የሰው ልጆችን ከሚያጠምድበት ወጥመዶች መካከል ዋነኛው ገንዘብ ነው። ይህንን ስትራቴጂ በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንም ቢሆን ለመፈተን ተጠቅሞበታል። በረሃቡ ጊዜ በእንጀራ ሊያጓጓው ያልተሳካለትና አምላኩን እንዲፈታተን ያቀረበው ሀሳብ ውድቅ የሆነበት ዲያብሎስ በመጨረሻ ግን ዋናውን ፈተና ፈተነው። ወደ ተራራ ወስዶ የተዋበ ዓለምን አሳየው። እናም ለኔ ከሰገድክልኝ ይህንን የምታየውን ዓለም እሰጥሀለው አለው። ብዙውን ጊዜ እኛ ሰዎች ይቺን ፈተና ማለፍ ከባድ ይሆንብናል። ለዛም ነው ሰይጣን ዋናውንና የመጨረሻ ከባድ የሚለውን ፈተና በጌታ ላይ የተገበረው። “ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና” ብሎ ሲመልስለት እንደማይሸነፍ አወቀ። በጌታ ፊት መቆምም ተሳነው። (ማቴ 4፥1-10፤ ሉቃ 4፥1-13)

Page 58: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

48 49

በገንዘብ የሚመጣብንን ውጊያ ማሸነፍ ትልቅ ድል ነው። ምክንያቱም ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነውና (1ኛ ጢሞ 6፥10)። ወንድም ወንድሙን የሚያስገድልበት፣ የሚዋደዱ ጓደኛሞችን ፍቅር የሚያስፈትንበት፣ ሀገርና ወገንን አስክዶ የራስን ጥቅም ብቻ የሚያሳድድበት፣ ክብርን አሳልፎ ሰጥቶ ስጋን የሚያሸጥ፣ ሰብዓዊነት ተዘንግቶ ድሆችን እንደ ርኩስ የሚያስቆጥርበት የገንዘብ ልክፍት እውነትም የኃጢአት ሁሉ ስር ነው።

የእግዚአብሔር ቃል ለሁለት ጌቶች ልትገዙ አትችሉም ብሎ ወይ አምላክን አልያም ደግሞ ገንዘብን እንድንመርጥ ይነግረናል (ሉቃ 16፥13)። እዚህ ጋር የሚገርመው ነገር ገንዘብም እንደ አምላክ ጌታ መባሉ ነው። በአንዳንድ ሰዎች ሕይወት ላይ ከአምላክም በላይ ገዝፎ ይታያል። ስንት ዘማሪ የነበሩ ወንድምና እህቶቻችን ለገንዘብ ሲሉ በዘመሩበት አንደበታቸው ዘፈኑበት? ስንቱ ቃሉን ለዓለም እንዲሰብኩ የተሰጣቸው ለገንዘብ ሲሉ ጸጋቸውን ችላ አሉ? ስንት የቃሉን ማዕድ አብረውን ይቋደሱ የነበሩ ዛሬ ቃሉን ለመቋደስ ጊዜ አጡ? ታዲያ በላያችን ላይ ገንዘብን ከጌታም በላይ ጌታ አደረግነው ማለት አይደለምን?

የጌታ ደቀመዝሙር የነበረው ይሁዳ ከአልባሌ ቦታ አንስቶ ለክብር ያበቃውን ጌታውን የሸጠው ለገንዘብ ሲል ነው። አዎ! ገንዘብ አብዛኛው ክርስቲያን ተወግቶ የወደቀበት የሰይጣን ዋነኛው የውጊያ መሳሪያ ነው። ለዛም ነው ባለጸጋ ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል የተባለው (ማቴ 19፥24፤ ማር 10፥25፤ ሉቃ 18፥25)። የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ገንዘብ አይጠቅምም ለማለት አይደለም። ባለጸጋ አትሁኑ ለማለትም አይደለም። ነገር ግን በፍቅረ ነዋይ ተወግተን የሰይጣናዊ አሰራር ምርኮኛ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን።

4.4 እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች ♥ “አጥብቀህልብህንጠብቅ፥የሕይወትመውጫከእርሱነውና።”ምሳ4፥23

• እግዚአብሔራዊያልሆኑየነፍስትስስሮችእንዴትይፈጠራሉ?

♥ እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች የሚፈጠሩት ከሚጎዱና በኃጢአት የተሞላ ኅብረትከሌሎችጋርስናደርግነው።“ራሳቸውየጥፋትባሪያዎችሆነው፥አርነትትወጣላችሁእያሉተስፋይሰጧቸዋል፤ሰውለተሸነፈበትለእርሱተገዝቶባሪያነውና።”2ኛጴጥ2፥19

በእኛ ላይ የሚደረጉ ኃጢአታዊ ስራዎች ለምሳሌ የንግግር፣ የፆታዊና አካላዊ ጥቃቶች ሲገጥሙን እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ ወይንም ጤናማ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች ሊገጥሙን ይችላሉ። በሕይወታችን የሚገጥሙን እነኚህ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ከሚጎዱን ሰዎች ጋር በነፍስ እንድንተሳሰር ያደርጉናል። ሰዎች እንደማንረባና እንደማንጠቅም ሲነግሩን ወይንም በሌሎች መገለልና መጣል ሲደርስብን የሚፈልጉን ከሚመስሉን አጉል ነገሮች ጋር ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስርን ሊፈጥርብን ይችላል። በጣም ልንገለል ወይንም ብቸኝነት ሊሰማን ይችላል። ይህንን ለመከላከል በስሜታዊነት ለሌሎች ሰዎች ባሮች ወይንም ተገዢዎች ልንሆን እንችላለን። ከሰዎች ጋር የተለማመድናቸው መጥፎ የሆኑ የነፍስ ትስስሮች አሁን ልንመሰርት ያለውን አዲስ ኅብረት እነኚህ መጥፎ በሆኑት ልምምዶች መነፅር እንድንመለከት እንገደዳለን።

• እግዚአብሔራዊያልሆኑየነፍስትስስሮችእንዴትይጠነክራሉ?

Page 59: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

49

ምንም እንኳን ጥቃቱ ቢቆምም፣ ኃጢአታዊ ማንነቶች ቢያበቁም የነፍስ ትስስር በቀላሉ ላይወገድ ይችላል። በተለያዩ ምክንያቶች ለሌሎች ተገዢ ልንሆን እንችላለን፥ ለምሳሌ በጥቃት፣ በኃጢአት፣ በቤተሰብ ችግር፣ ሀሺሽ፣ ይቅር አለማለት፣ ቁጣ፣ በአስማት መሳተፍ፣ ዝሙት፣ ማመንዘር፣ ስካር እና ሌሎች በገላ5፥19-21 የተጠቀሱት የስጋ ሥራዎች ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።

ግጭትና ብስጭትአንድ ሰው ከትዳር አጋሩ ጋር ከእግዚአብሔር ያልሆነና ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር

በመካላቸው ሊኖር ይችላል። ይህ ትስስር ሊፈጠር የሚችለው የትዳር ጥንዶች በተለያየ የሕይወትና መንፈሳዊ ልምምድ ስለሚኖራቸውና አመለካከታቸውም ያንኑ ያህል የተለያየ ሊሆን ስለሚችል ነው። ይህንን ልዩነት ባለመረዳትና አቻችሎ ለመሄድ ፈቃደኛ ባለመሆን ጥንዶቹ እርስ በእርሳቸው ልብን የሚጎዱ ንግግሮችን ሊነጋገሩ ይችላሉ። ይህ ሁኔታ በጊዜው በመነጋገርና በይቅርታ ሊፈታ ካልተቻለ ግን በመካከላቸው ከእግዚአብሔር ያልሆነ ትስስርን ይፈጥራል። ይህንን ከእርሱ ያልሆነውን ትስስር እንዲበጥስ በጸሎት ካልጠየቁ በቀር በብስጭት ይሞላሉ። ዲያብሎስም በሕይወታቸው ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እድል ፈንታ ያገኛል። የክፋት ምክሩንም ለሁለቱም ማማከሩን ይጀምራል። “እንዲህ፣ እንዲህ በይው፤ እንዲህ በላት፤ እንዲህ አድርጊው፤ እንዲህ አድርጋት፤” በማለት የሚሰጣቸውን የክፋት ምክር በመቀበል ሰብዓዊ ያልሆኑ ስራዎችን እስከ መስራት ድረስ ያደርሳቸዋል። ይህ ሁሉ ጉዳት ሊመጣ የሚችለው ሁለቱም ወይም ከሁለቱ አንዱ ልባቸውን እልከኛ በማድረጋቸው ነው። ሰይጣን እድል ያገኘበት ትዳር ውስጥ “የትዳር ጓደኛዬ አትወደኝም” ወይም “አይወደኝም” የሚል ዕሳቤን እንዲያዳብሩ ያደርጋቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን መጽሐፍ እንዲህ ይገልፀዋል፦

♥ “ተቆጡኃጢአትንምአታድርጉ፤በቁጣችሁላይፀሐይአይግባ፥ለዲያብሎስምፈንታአትስጡት።”ኤፌ4፥26-27

ይህ ካልሆነ ልብ በይቅር ባይነትና በእረፍት ፋንታ በሚቀጥለው ጊዜ ግጭት ሲፈጠር ትዕግስት ማጣት ይከሰታል። ይህ የነፍስ ትስስር ስህተትን የምንቀበል ሳይሆን ፈራጆች እንድንሆን ያደርገናል። በዚህ ጊዜ ችግርን ተቀብሎ ይቅር ከመባባል ይልቅ የእርስ በእርስ አልበገር ባይነት ይዳበራል፥ ምክንያቱም ሰይጣን የልብን ዙፋን ይቆናጠጣል። ከእግዚአብሔር የሆነ የነፍስ ትስስር ቢኖረንም እንኳን ጠላት እኛን ለመከፋፈልና ለትዳር አጋሮቻችን የሚኖረንን አስተሳሰብ በጎ ባልሆነ መልኩ እንድንቀይር ሊፈትነን ይችላል። ከጠላት ሃሳብ ጋር ስንስማማ ጠላት ትዳራችንን እንዲበጠብጥ ህጋዊ ፈቃድ ሰጠነው ማለት ነው።

ቀድሞ የነበረን መልካም ያልሆነ የጓደኝነት(የእጮኝነት) ጊዜ አሁን ባለንበት እጮኝነት ላይ ተፅዕኖ የሚያመጣ ከሆነ ጠላት ቀድሞ የነበረብንን ብስጭት አሁን ባለው ሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ እንዲያመጣ እድልን ሰጥተነዋል ማለት ነው።

ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት ከሌሎች ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ከነበራቸው በሚመሰርቱት ትዳር ላይ ተፅዕኖ እንደሚያመጣ የታወቀ ነው። ስለዚህ ከእነኚህ ሰዎች ጋር የነበራቸው የነፍስ ትስስር መሰበር አለበት። እግዚአብሔር ምህረት እንዲያደርግና ይህንን የነፍስ ትስስር እንዲሰብረው ካልጠየቁ በስሜታቸው ብስጭት ይከማቻል።

Page 60: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

50 51

ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር ቀላል በሚመስሉ ስምምነቶች ሊፈጠር ይችላል። ከእግዚአብሔር ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች በፍቅር የተሞላን ከእግዚአብሔር የሆነን የነፍስ ትስስር አያጠፋም። ነገር ግን ብስጭት በሕይወት እንዲሆን በማድረግ ለወደፊቱ የሚጎዳ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋሉ።

ማሽኮርመምና መዳራት አብዛኛው ሰው ማሽኮርመምን ሰይጣን ሰዎችን በዝሙት ለመጣል የሚጠቀምበት መሳሪያ

መሆኑን ሳያውቁ እንደጨዋታ ይቆጥሩታል። ማሽኮርመም ማለት የወሲብ ስሜትን ለማነሳሳት የሚደረግ የንግግር ወይም የእንቅስቃሴ ድርጊት ነው። ለእንደዚህ አይነቱ ድርጊት ተመሳሳዩ መዳራት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ማሽኮርመም የሚናገር ሲሆን ምን ማለት እንደሆነና ፍሬዎቹን በግልፅ ያስቀምጥልናል። ምሳ 6፥24-26 እና ምሳ7፥5 ስለ ማሽኮርመምና የሚዳሩ ሰዎች ስለሚጠቀሟቸው ቃላት ይገልፃል። ወንዶችና ሴቶች እርስ በራሳቸው ሲሽኮረመሙ የተዳሪዎችን ተግባር ያደርጋሉ። የከፋው ነገር የመዳራትና የማሽኮርመም ፍሬ የነፍስ ትስስርን ያስከትላል። ይህም ያንን ሰው እንድንመኝ ያደርጋል፤ በትዳር ውስጥ ችግር ካለ የተሻለ ነገር ለማግኘት መመኘት ይጀመራል።

† መዳራት ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስርን ያመጣል። በመጀመሪያ አስተሳሰብንያስራል።በመቀጠልስሜትንበመጨረሻምፈቃድንያስራል።ጠላትበኢንተርኔትበሚታዩወስባዊ ምስሎችና ወሲብን በተመለከተ የሚደረጉ የአጫጭር መልእክት ልውውጦችእግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች በሰዎች ላይ ለማድረግ ይጠቀምበታል። በዚህቅፅበት ልባችን ይረታል። ለዚህ ነው ኢየሱስ ማንም ወደ ሴት ያየ በልቡ አመንዝሯልየሚለው(ማቴ5፥28)።

ፆታዊ የስጋ ትስስር ኃጢአትበኃጢአት ከሌሎች ሰዎች ጋር መሳተፍ ከእግዚአብሔር ያልሆነ የመንፈስ መተሳሰርን

ያመጣል። አዲስ ኪዳን ፆታዊ ኃጢአትን በሁለት ይከፍለዋል። እነሱም ማመንዘርና መዘሞት (ዝሙት መፈፀም)ናቸው።

ማመንዘር ማለት አንድ ባለትዳር የሆነ ሰው ከትዳሩ ውጪ ወሲብ ሲፈፅም ወይም አግባብ ያልሆኑ ፆታዊ ባህርይዎችን ሲለማመድ ነው። መዘሞት ማለት አግባብ ያልሆነ ፆታ ባህርይ ሲሆን ማመንዘርንም ያካትታል። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ሁለቱም ድርጊቶች የስጋ ስራ ናቸው።

♥ “የሥጋሥራምየተገለጠነውእርሱምዝሙት፥ርኵሰት፥መዳራት፥ጣዖትንማምለክ፥ምዋርት፥ጥል፥ክርክር፥ቅንዓት፥ቁጣ፥አድመኛነትመለያየት፥መናፍቅነት፥ምቀኝነት፥መግደል፥ስካር፥ዘፋኝነት፥ይህንምየሚመስልነው።”ገላ5፥19

ጊዜው ይለያይ እንጂ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥረው ወንድና ሴት አድርጎ ነው። ይህንን ያደረገበትም ምክንያት እርስ በእርስ እንዲረዳዱ፣ አብረው ደስ እንዲላቸው እንዲሁም ዓለምን እንዲሞሏት ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሀሳብ ወይም ዓላማ እውን የሚሆነው የሰው ልጅ ከተፈቀደለትና በትዳር ከተሳሰረው አንድ ሰው ጋር ብቻ ነው። ለዚህም ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤” ዕብ 13፥4 በማለት የሚናገረው። ማንኛውም ከትዳር ዉጪ የሚደረግ ፆታዊ ግንኙነት (ወሲብ) ኃጢአት ሲሆን ይህንን ከምናደርገው ሰው ጋር ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስር እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል። እንዲህ ዓይነት

Page 61: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

51

ፆታዊ ኃጢአት በጣም የጠነከረ የነፍስ ትስስርን ሲፈጥር በተጨማሪም ለጠላት ስቃይ ያጋልጣል። ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ 6፥18 ላይ በማንኛውም የፆታዊ ኃጢአት ላይ ስንሳተፍ በገዛ አካላችን ላይ ኃጢአት እንደምንሰራ ይነግረናል።

♥ “ከዝሙትሽሹ።ሰውየሚያደርገውኃጢአትሁሉከሥጋውጭነው፥ዝሙትንየሚሠራግንበገዛሥጋውላይኃጢአትንይሠራል።”1ኛቆሮ6፥18

ሌላው ከእግዚአብሔር ያልሆነ ጾታዊ ትስስር ግብረ ሰዶማዊነት ነው። ይህ ተግባር እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሙሉ ለሙሉ በመቃወም የሚደረግ ርኩሰት ነው። ቃሉም “ስለዚህ እርስ በእርሳቸው ስጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኩሰት አሳልፎ ሰጣቸው።” ሮሜ 1፥24 እንዳለ ይህ ተግባር ቅጣትን የሚያስከትልና ክፉ የሆነ የስጋ ትስስር ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰዶምና ገሞራ ሰዎች በዚህ ኃጢአት የተበከሉ እንደነበሩ እናውቃለን። እርስ በእርሳቸው የሚያደርጉት በደል አልበቃ ብሏቸው ሎጥ ቤት እንግዳ መስለው በመጡ መላእክት ላይ እንኳን ይህንን ድርጊት ለመፈጸም ተሰባስበው እንደመጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ዘፍ 19፥1-25) በአሁኑ ወቅትም ቢሆን ይህ ድርጊት በድብቅ ከመሰራትም አልፎ በአንዳንድ ሀገራት ላይ እንደ መብት ተደርጎ በህጋቸው አጽድቀውት ይገኛሉ። ነገር ግን ይህ የኃጢአት ተግባር ለሰዶማውያን ሕዝብ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር እንደሆነ ዓለማችን የተረዳች አትመስልም። በስመ ስልጣኔ ጠላት ይህንን አፀያፊ ልማድ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ እየዘራ ይገኛል። ሀገራችንን ጨምሮ “ክርስቲያን ነን” በሚሉ ሀገራት ውስጥ ይህ የጥፋት መንገድ ከምንጊዜውም በላይ በፍጥነት እየተገነባ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ማንነታችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆነ ይነግረናል። በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚገባቸው ነገሮች ሁሉ ለአምላክ መታጠንና መቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። ለዚህም ነው የአማኞች አካል የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንጂ ኃጢአት የሚፈፀምበት አይደለም የሚባለው። ፆታዊ ኃጢአት በሕይወታችን ሰይጣን እንዲገባ መንገድ ይከፍትለታል። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሆናችን ቀርቶ የሰይጣን ማረፊያ እስክንመስል ድረስ ለበለጠ የድፍረት ኃጢአት የተለማመድን እንድንሆንም ያደርገናል። በመሆኑም ከዳንን በኋላ የሚኖረንን ነፃነት ለማጣጣም በፊት በነበሩን ፆታዊ ግንኙነቶች አማካኝነት የነበሩን የነፍስ ትስስሮች መቆም አለባቸው። ነገር ግን እነኚህ ትስስሮች በጸሎትና ከጠላት ጋር ያለ ስምምነት ካልፈረሰ በትዳር አልጋ ላይ በሀሳብ፣ በስሜት፣ በመንፈስ ሊገለጡ ይችላሉ። ይህ ደግሞ አካላዊና መንፈሳዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ ጠላት እነኚህን የነፍስ ትስስሮችን ትዳርን ለማፍረስ መሰረት አድርጎ ይጠቀምባቸዋል።

ፖርኖግራፊየግሪኩ ቃል ፖርኒያህ ሲለው ትርጓሜውም ዝሙት ወይም ማመንዘር ማለት ነው።

ፖርኖግራፊ የወሲብ ስሜትን የሚያነሳሱ ነገሮችን ማለትም ፎቶግራፎች፣ የተለያዩ እርቃነ-ስጋን የሚያሳዩ ስዕሎች እንዲሁም ቪዲዮችን (ከትዳር አጋር ውጪ የሚደረጉ ግንኙነት፣ ሰዶማዊ ግንኙነት ወዘተ) በመመልከት ትክክለኛ ወዳልሆነ ፆታዊ ግንኙነቶች እንድናመራ የሚያደርግ፣ የሰውን አዕምሮ የሚይዝ መንፈስ ነው። በአሁኑ ጊዜ ፖርኖግራፊ በወንድም በሴትም እየጨመረ ያለ ችግር ነው። በዚህ ጊዜ የነፍስ ትስስር የሚኖረው ሰዎች ከማያውቋቸው ሰዎች፣ በልብወለድ፣

Page 62: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

52 53

በኢንተርኔት በሚታይ ለወሲብ በሚያነሳሱ ፊልሞች፣ በመጽሐፍት እና መፅሄቶች ላይ አንድን ገፀ ባህርይ ወክለው ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ነው። ሰይጣን ፖርኖግራፊን በተለያዩ የዓለም ክፍል ያሉ ወጣቶችን የስጋዊ ፍላጎታቸውን በማነሳሳት በምክንያታዊነት ሳይሆን በጭፍን ስጋዊ ስሜት እንዲመሩ ያደርጋቸዋል። ብዙ ተፈጥሯዊ ያልሆኑና ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ እንደ ሰዶማዊ ያሉ ተራክቦዎችን ያስተምራቸዋል። ያስተማራቸውንም ተግባር ላይ እንዲያውሉ በመገፋፋት ርካሽ ለሆነ ድርጊት ይዳርጋቸዋል። በድርጊታቸው እንዳይጸጸቱ እንኳን የስልጣኔ ትርጉም ይህ ነው ይላቸዋል።

በሁለተኛ ቆሮንቶስ 10፥3-5 የጠላት ምሽግ በውስጣችን የሚፈጠረው በአዕምሯችን ካሉ መጥፎ እሳቤዎች እንደሆነ ተገልጿል። ጠላትም አሁን ከምንጊዜውም በላይ ፖርኖግራፊን እንደ አንድ መሳሪያ ይጠቀማል።

♥ “በሰውልማድምንምእንኳየምንመላለስብንሆን፥እንደሰውልማድአንዋጋም፤የጦርእቃችንሥጋዊ አይደለምና፥ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን፤ ለክርስቶስም ለመታዘዝአዕምሮንሁሉእንማርካለን፥”2ኛቆሮ10፥3-5

አዕምሯችንና እሳቤአችን በምንመለከታቸው ወሲባዊ ስዕሎች ይበከላል። ፖርኖግራፊ ወንዶችና ሴቶችን ለፆታ ግንኙነት የተፈጠሩ እቃዎች ያደርጋቸዋል። ይህንን ፖርኖግራፊ የተመለከቱ ሰዎች ከእግዚአብሔር ያልሆነ የነፍስ ትስስርን የፈጠሩ ሲሆን ከዲያብሎስ ጋር ሰዎችን ለራስ እርካታ ሲባል መጠቀም ምንም ችግር እንደሌለው ስምምነት አድርገዋል። ከእግዚአብሔር ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች መበጠስ አለባቸው። በተጨማሪም ከዲያብሎስ ጋር የተደረጉ ስምምነቶች መፍረስ አለባቸው።

የልብ ወዳጅ ምርጫየልብ ወዳጅ ስንመርጥ መጠንቀቅ አለብን። ሰይጣን ከአማኞች መልካምን ነገር ለመስረቅ

አንዱ የሚጠቀመው መንገድ እኛን ለመጉዳትና ለመጠቀም የሚፈልጉ ሰዎችን በማምጣት ነው። እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች ትክክለኛ ካልሆኑ ጓደኞች ጋር በምናደርገው የተመቻቸ ግንኙነት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ አምኖን ከኢዮናዳብ ጋር የመሰረተው ያልተገባ ጓደኝነት ነው። አንዳንድ ጓደኞች ያለብንን መንፈሳዊ ድክመት እንድንቀርፍ ከማገዝ ይልቅ ስህተት በሆነ መንገዳችን እንገፋበት ዘንድ በል በል ይሉናል። አምኖንም በእህቱ ፍቅር መጠመዱን ለጓደኛው ኢዮናዳብ በነገረው ጊዜ ይህ ሃሳብ ካንተ ይራቅ ብሎ እንደመምከር አሞኛል ብለህ ወደ ቤትህ ጥራት እሷም ወንድሟ ነህና ስትሮጥ ትመጣለች። የዛኔ ስሜትህን ንገራት። አምኖንም የተባለውን ፈጸመ። ለእህቱ ልብ መሰበር ምክንያትም ሊሆን በቃ (2ኛ ሳሙ 13)። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው መልካም ባልሆነ ጓደኛነት ምክንያት ነው። ከቀድሞም ቢሆን ከአሁን የሚኖሩን እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮች ካልተወገዱ ሁልጊዜ ወደ ስህተት ማምራታችን አይቀርም። ለዛም ነው የእግዚአብሔር ቃል “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?” 2ኛ ቆሮ 6፥14 ያለው። ምንም እንኳን በመጥፎ ጓደኛችን መጥፎ አካሄድ ተፅዕኖ ስር አንወድቅም ብለን ብናስብም ቀስ በቀስ ባላወቅነው መንገድ በመጥፎ ስራቸው ልንወሰድ እንችላለን።

♥ “አትሳቱ፤ክፉባልንጀርነትመልካሙንዓመልያጠፋል።”1ኛቆሮ15፥33

Page 63: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

53

ነገር ግን መልካም ጓደኛ ወደ ሕይወት መንገድ እንድናቀና ያደርጋል፤ ለችግር መፍትሔ ይኖረዋል። ለመንፈሳዊ ሕይወት መጎልበት ይረዳል። ያለብንን ድክመት እያረመ ለሰይጣናዊ ስራ የማንመች ያደርጋል።

♥ “ጻድቅለባልንጀራውመንገዱንያሳያልየኀጥኣንመንገድግንታስታቸዋለች።”ምሳ12፥26

♥ “ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥በዋዘኞችም ወንበርያልተቀመጠ።”መዝ1፥1

4.4.1 በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስርበአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር ማለት አንዳንድ ሰዎች በተለየ መንገድ የማይገባንን ቦታ

ሲሰጡን የሚፈጠር ነው። ማንኛውም ሰው በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር ሊገጥመው ይችላል፤ ነገር ግን በአመራር ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ስለዚህ የነፍስ ትስስር ንቃት ሊኖራቸው ይገባል።

በአንድ በኩል የሆነን የነፍስ ትስስር መለየትትክክለኛ ባልሆነ መልኩ በሌሎች ሰዎች የምንፈለግ ከሆነ ይህ ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር

መሆኑን መረዳት እንችላለን። አንዳንድ ጊዜ ዝሙትን ያካተተ የነፍስ ትስስር ካለባቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ስናሳልፍ ወቃሽ ስሜት ሊሰማን ይችላል። ማለትም በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር መንፈሳችንን ሊያወርድ ይችላል። እነኚህ ሰዎች በእጃችን ቢሆኑም እንኳን እነሱን ከሕይወታችን ለማስወገድ ልንቸገር እንችላለን። የሚፈጁብን ጊዜ ግድ ሳይላቸው ሙሉ አትኩሮት እንድንሰጣቸው ይፈልጋሉ። በሕይወታቸው ለሚፈልጉት ነገር እግዚአብሔርን ከመጠየቅ ይልቅ እኛን ጣዖታቸው አድርገው ፍላጎታቸውን እንድናሟላ ይፈልጋሉ። በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስሰር ምሳሌ፦ጥገኞች የሆኑ ሰዎች፣ ፍርሃት ያለባቸው፣ ሰውን እንደ ራሳቸው ጀግና የሚቆጥሩ፣ ለፆታዊ ግንኙነት ሰዎችን የሚፈልጉ ወዘተ…ይጠቀሳሉ።

አንድ ሰው የራሱን መንፈሳዊና ስሜታዊ ፍላጎት ለማሟላት ጥገኛነትን የሚያዳብር ከሆነ ይህ ጤናማ ያልሆነ የነፍስ ትስስር መወገድ አለበት። በተጨማሪም ራሳችንን ከዚህ እስራት ነፃ ለማውጣት በሕይወታቸው የማይገባንን ቦታ ከሰጡን ሰዎች ነፃ ለመውጣት መጸለይ ያስፈልጋል።

4.4.1.1 መሪዎችና እግዚአብሔራዊ ያልሆኑ የነፍስ ትስስሮችበአመራር ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች በአንድ በኩል የሆነ የነፍስ ትስስር ሊገጥማቸው ይችላል። ይህንን

አይነት የነፍስ ትስስር ሊፈጥሩ የሚፈልጉት አካላት በስራቸው ሳይሆን ከመሪው ጋር በሚኖራቸው የኃጢአት ግንኙነት ብቻ ተቀባይነትንና ስልጣንን የሚያገኙ በሚመስላቸው ክፍሎች ናቸው። መሪዎቻቸውን ከማክበርም ባለፈ ማምለክ ደረጃ ይደርሳሉ። ስለዚም አድርጉ ለተባሉት ማንኛውም መጥፎ ስነምግባር ራሳቸውን ከማሰለፋቸውም ባሻገር መሪውንም ጭምር ወዳላሰበው መጥፎ ድርጊት የመምራት ዝንባሌ አላቸው። ከዚህም በተጨማሪም ቅናተኞችና ተፎካካሪ ሰዎች መሪዎች የያዙትን ስልጣን በመፈለግ ከእግዚአብሔር ያልሆነን የነፍስ ትስስር ሊፈጥሩ ይችላሉ። በአንዳንድ ሰዎች አካባቢ ስንሆን የማይመች ወይንም ጥሩ ስሜት የማይሰማን ከሆነ ሰዎቹ ከእግዚአብሔር ያልሆነን የነፍስ ትስሰር ከእኛ ጋር ሊኖራቸው ይችላል።

Page 64: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

54 55

4.4.1.2 ዲያብሎስ የራሱን ባህርይ በመጠቀምቀደም ብሎ ያየናቸው የውጊያ ስልቶች በሌሎች አካላት አማካኝነት የሚደርሱብን የሰይጣን

ፈተናዎች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ከውጪ መልካምና አስደሳች የሚመስሉ ናቸው። ስለዚም በጦርነት ውስጥ እንዳለን እንኳን ሳንረዳ እንዲሁም ራሳችንን ለውጊያው ዝግጁ ሳናደርግ የሚጥሉ ክስተቶች ናቸው። ይህኛው የዲያብሎስ የጦር ሜዳ ግን የጠላት ባህርይ በጣሙን የሚታይበት ሲሆን ራሱ በሕይወት መንገዳችን ላይ መሰናከያዎችን እያስቀመጠ አምላክን እስከምናማርር ድረስ ወይም መኖሩን እስከምንጠራጠር ድረስ የሚዋጋበት መንገድ ነው። በኑሯችን ውስጥም ምንም አይነት ምቾት እንዳይሰማን እያደረገ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ሳይሆን በሚኖሩብን የዕለት ችግር ላይ ብቻ ትኩረት እንድናደርግ ማድረግ የዚህ የውጊያ ስልት ዋነኛ ዓላማ ነው። ይህም ከአሕዛብ በላይ በአማኞች ላይ ይበረታል። ለዛም ነው የእግዚአብሔር ቃል “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤” 1ኛ ጴጥ 5፥8 እያለ የሚመክረን። እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ ሁሌም በጸሎት መትጋት ይገባናል። እንደ ትእግስተኛው ኢዮብም በነገሮች ሁሉ “እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን” በማለት ከደረሱብን ችግሮች ይልቅ የሚደርስልን አምላክ እንደሚበልጥ ማሳየት አለብን። መብለጡንም በአንደበታችንና በህሊናችንም ልንመሰክር ይገባናል።

የዲያብሎስ የጦር ሜዳ የጠላት ባህርይ በጣሙን የሚታይበት ሲሆን ራሱ የሚያስቀምጣቸውን ዕንቅፋቶች ያካትታል። የዲያብሎስ ባህርይ መግደል፣ መዋሸት፣ ማጭበርበር፣ መክሰስ፣ መስረቅና ማጨንገፍ ነው። ይህም ከአሕዛብ በላይ በአማኞች ላይ ይበረታል።

♥ “በመጠንኑሩንቁም፥ባላጋራችሁዲያብሎስየሚውጠውንፈልጎእንደሚያገሣአንበሳይዞራልና፤”1ኛጴጥ5፥8

♥ “ደግሞም፦ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሓን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱንለማድረግበዲያብሎስሕያዋንሆነውከተያዙበትወጥመድወጥተው፥ወደአዕምሮይመለሳሉብሎየሚቃወሙትንበየዋህነትይቅጣ።”2ኛጢሞ2፥25-26

4.4.1.3 በዓመፅ በተያዙ ሰዎች አማካኝነት (አስማተኞች፥ መተተኞች፥ መናፍስት ጠሪዎች፥ ጠንቋዮች፥ …)

ይህ ወጥመድ በክርስቲያኖች ላይ በኃጢአት ተፅዕኖ ስር ባሉ ሰዎች በኩል የሚደረግ ውጊያን የሚያመላክት ሲሆን አስማት፣ ጥንቆላ፣ የመሳሰሉትን የኤልዛቤል መንፈሶችን ያካትታል። በዚህም ጠላት ዋነኛ ተጠቃሚ ነው። ሶስተኛው የጦር ሜዳ ውስጥ በዓመፅ ተፅዕኖ ስር ያሉ ሰዎች የክርስቲያኖችን ሕይወት ለመቆጣጠር ዓላማ ካደረጉ ጋር የሚደረግ ጦርነት ይካሄድበታል። እግዚአብሔር ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋር ኅብረት እንዳናደርግ አጥብቆ ያዘናል።

♥ “ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።”1ኛዮሐ3፥8

♥ “ለእውነትእንዳትታዘዙማንከለከላችሁ?”ገላ5፥7

♥ “የማታስተውሉየገላትያሰዎችሆይ፥በዓይናችሁፊትኢየሱስክርስቶስእንደተሰቀለሆኖተሥሎነበር፤ለእውነትእንዳትታዘዙአዚምያደረገባችሁማንነው?”ገላ3፥1

Page 65: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

55

♥ “አምላክህእግዚአብሔርወደሚሰጥህምድርበገባህጊዜእነዚያአሕዛብየሚያደርጉትንርኵሰትታደርግ ዘንድ አትማር። ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔርፊት የተጠላ ነው ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል። አንተ ግንበአምላክህበእግዚአብሔርዘንድፍጹምሁን።የምትወርሳቸውእነዚህአሕዛብሞራገላጮችንናምዋርተኞችንያዳምጣሉአንተግንእንዲሁታደርግዘንድአምላክህእግዚአብሔርከልክሎሃል።”ዘዳ18፥9-14

4.4.2 የጥንቆላ መንፈስና ቤተክርስቲያንአብዛኛው ሰው ወዶ የጥንቆላን ስራ ላይከተል ይችላል። ነገር ግን ሁሌም ከጌታ መንገድ

ሊያወጣን የሚተጋው ሰይጣን በብዙ መልኩ በማስጨነቅ ወደ አሰራሩ ስርዓት እንድንገባ ግፊት ያደርግብናል። ራሱ ለፈጠረው ችግር መፍትሔው እሱ ጋር ያለ በማስመሰል ይጠራቸዋል። ጥሪውን ሰምተው ለሄዱ ሰዎች ደግሞ ዳግም እንዲመጡ የሚገፋፋ መንፈስን አስርፆ ከመላኩም ባሻገር ሌሎችም ወደእርሱ እንዲመጡ መንገዱን ጠራጊ ያደርጋቸዋል። በእምነት ያሉትንም ቢሆን “አምላካችሁ መቼ ይሰማችኋል? እርሱ ይዘገያልና ዛሬውኑ መፍትሔ የሚሰጣችሁ አካል ጋር ሂዱ፥ ዳግም በዚህ ችግር መጨነቃችሁ ይብቃ፤” በማለት እግዚአብሔርን ተንበርክከው የልባቸውን ባማከሩት ማግስት ለጥንቆላ እንዲንበረከኩ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን እኛ እንደ ክርስቲያን በገባን እውነት እግዚአብሔርን ከመታዘዝ በቀር በማንኛውም የጥንቆላ ስራ ውሰጥ መሳተፍ የለብንም።

በሀገራችን ለጥንቆላ መንፈስ የተሰጠች አንዲት ስም አለች። እሷም “አዋቂ” የምትል ናት። እዚህ ጋር አንድ ክርስቲያን ወንድም ሲናገር የሰማሁትን ገጠመኝ ባስገባት ለሁላችን መማሪያ ልትሆን የምትችል ታሪክ ትመስለኛለች። ነገሩን ሲያጫውተኝ፣ “በሰፈራችን ያለ አንድ ጠንቋይ ነበረ። ታዲያ አንዲት ሴትዮ ዝናውን ሰምታ ከሌላ ሀገር ትመጣለች። እኔንም ከቤት ስወጣ ታገኘኝና “እባክህን የአዋቂውን ቤት ታሳየኛለህ?” በማለት ጠየቀቺኝ” አለ። “ሴቲቱ ልትጠይቀኝ የፈለገችው ምን እንደሆነ ቢገባኝም “አዋቂ” በማለት ስለጠራችው ግን ቅሬታ ተሰማኝና ጣቴን ጌታን እንድታስታውስ ወደ ሰማይ እያሳየዋት “የአዋቂው ቤት እዛ ነው አልኳት”።” እኔም “ለምንድን ነው አዋቂ ስላለችው ቅሬታ የተሰማህ? ስሙ ማንም ቢሆን ስራውን እኮ ነው ልንቃወመው የሚገባው” ባልኩት ጊዜ የመለሰልኝ መልስ እንዲ የሚል ነበር። “ለምን አዋቂ እንለዋለን? የእርሱ ትክክለኛ ስሙ ጠንቋይ ነው። ይህ ስም ትክክለኛ ምግባሩን ይናገራል። ትርጉሙም ስለ ጠንቅ ወይም ስለ ክፋት የሚውል ማለት ነው” አለኝ። የዛን ጊዜም “ሰዎች ወደዚህ አካል የሚሄዱት ስሙ እንኳን ስለ ጠንቅ የሚውል መሆኑን እንደሚናገር ገብቷቸው ይሆን?” ብዬ ራሴን ጠየቅኩ።

ሙሴ በትሩን እባብ ባደረገ ጊዜ የግብፅ አስማተኞችና ጠንቋዮችም ከእርሱ እኩል በትራቸውን እባብ ማድረግ መቻላቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ነገር ግን ሰይጣናዊ ድግምት በእግዚአብሔር ሰው ፊት ለፊት ምንም አቅም የለውም። ለዚህም ነው የሙሴ እባብ የመተተኞቹን እባብ መዋጥና ስፍራ እንዳይገኝላቸው ማድረግ መቻሏ። ስለዚም እኛ እንደክርስቲያን በገባን እውነት እግዚአብሔርን ከመታዘዝ በቀር በማንኛውም የጥንቆላ ስራ ውሰጥ መሳተፍ የለብንም።

Page 66: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

56 57

ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔር የሆነው ዓይን ሲበራላቸው በጥንቆላ መንፈስ የተነዱበት እድሜ ምን ያህል የባከነ እንደነበር ይረዱታል። ቤታቸው አስቀምጠው ቅቤ የሚያጠጧትን ጨሌ አውጥተው ጥለው ሁለመናቸውን ለጌታ ያስገዛሉ።

♥ “አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውምቢታሰብአምሳሺህብርሆኖተገኘ።”ሐዋ19፥18-19

በጥንቆላ መንፈስ ውስጥ ያሉ ክርስቲያን ነን ባዮች በክፉ መንፈስ ስለመያዛቸው እውቀቱ አይኖራቸውም። እውነታውን እንዳያውቁ ታውረዋል። ጥንቆላዎች በሕይወታችን ቦታ የሚያገኙት ራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ከመስጠት ይልቅ ከአጋንንት ጋር ስምምነት ስናደርግ ነው።

♥ “ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደማምለክ ነውየእግዚአብሔርንቃልንቀሃልናእግዚአብሔርንጉሥእንዳትሆንናቀህአለ።”1ኛሳሙ15፥23

የጥንቆላ መንፈስ ራስ ወዳድና ዋጋ የሚያስከፍል ነው። በዚህ መንፈስ የሚሰሩ ሰዎች አዛዦች፣ በዝባዦችና ጥቅም ፈላጊዎች ሲሆኑ እነርሱ ከማንም በላይ ራሳቸውን እንደ ጥሩ መንፈሳዊያን ሰዎች በመቁጠር በትዕቢት የተሞላ መንፈሳዊ የበላይነትን ለማግኘት ይሞክራሉ። ጸሎት እንዳንፀልይ፣ ከአማኞች ጋር በኅብረት እንዳንሆን፣ ወደ ቤተክርስቲያን በሰዓት እንዳንሄድ እና ከነጭራሹም እንድንቀር ሊያደርጉን ይችላሉ። ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን መንፈሳዊ ኅብረት እንድናዳብር ከማበረታታት ይልቅ ለመንፈሳዊ ምሪትና ለጸሎት ወደ እነርሱ እንድንሄድ ይፈልጋሉ። እግዚአብሔራዊ ያልሆነ የመንፈስ እስራት በውስጣችን እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ከእነዚህ አብዛኞቹ በራሳቸው ሐዋሪያት ወይም ነብያት እንደሆኑ ያወጁ ናቸው፤ ነገር ግን ትንቢታቸው ከመንፈስ ቅዱስ ያልሆነ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚፃረር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለን ትንቢቶችን መርምረን ከእግዚአብሔር እንደሆኑና እንዳልሆኑ ማወቅ አለብን።

♥ “ነቢያትምሁለትወይምሦስትሆነውይናገሩሌሎችምይለዩአቸው፤”1ኛቆሮ14፥29

ትንቢት የሚናገሩ ጠንቋዮች ከላይ ተገልፀዋል። በዚህ መንፈስ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን በኃጢአት ተፅዕኖ ውስጥ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። ይህ መንፈስ የሚቆጣጠራቸው ሰዎች ዘመናቸው በከንቱ ያልቃል፤ ምክንያቱም ሰዎች ኃጢአታቸውን አውቀው ነፃ ለመውጣት እንዲሞከሩ አያበረታታም።

♥ “በሰማርያ ነቢያት ላይ ስንፍናን አይቻለሁ በበኣል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤልያስቱነበር።”ኤር23፥13

የጥንቆላ መንፈስ ቤተክርስቲያንና ከቤተክርስቲያን ጋር የሚኖረንን ግንኙነት የሚያጠቃ የቅንዓት፣ የፉክክር እና ነፍስ የማጥፋት መንፈስ ነው። የሚሰራውም በስጋ ነው። የጥንቆላ መንፈስ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠንን ቅባትና ስጦታ አይወድም። ይህ መንፈስ በእኛ፣ በመጋቢዎች፣ በአገልጋዮች እንዲሁም በቤተክርስቲያን ውስጥ በአመራር ቦታ ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ቅባት ሊያጠፋና ሊገድል ይፈልጋል።

Page 67: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

57

4.4.2.1 የጥንቆላን ጥቃት መረዳትና መለየትጥንቆላ ምስጢራዊ ሲሆን ዋና ስራውም በድብቅ ወይም በጨለማ የሚሰራ ነው። በሰዎች

የሚሰሩ የሚመስሉ ነገር ግን በአምስቱ ስሜቶቻችን ልንረዳቸው የማንችላቸው በሰይጣናዊ ኃይሎች የሚሰሩትን ስራዎች ያጠቃልላል። ከጥንቆላ በስተጀርባ ያለው ኃይል እግዚአብሔርን የማይወድ ሰይጣናዊ ኃይል ነው። ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ካለማወቅ የተነሳ ለችግሮቻቸው ሌሎች አማራጮችን ይፈልጋሉ። በደመነፍስ ዝም ብሎ ከመኖር አዋቂ የሚመስሉ ስዎች ጋር ይጠጋሉ። ከእነዚህም መካከል ጠንቋዮች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ። እነርሱም ከጠላት በመሆናቸው እውቀት የላቸውም።

♥ “ሕዝቤእውቀትከማጣቱየተነሣጠፍቶአልአንተምእውቀትንጠልተሃልናእኔካህንእንዳትሆነኝእጠላሃለሁየአምላክህንምሕግረስተሃልናእኔደግሞልጆችህንእረሳለሁ።”ሆሴ4፥6

የሰዎች ሕይወት በሀሜት፣ በረሃብ፣ በበሽታ፣ በመከፋፈል እና በጭንገፋ ምክንያት እየጠፋ ነው። ይህም የሚሆነው ጠንቋዮች በሰው ሕይወት ላይ የሚያደርጉት ተፅዕኖ ችላ ስለሚባል ነው። በአስማት ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች የሰይጣንን ዓላማ በድግምትና በእርግማን በመሳሰሉት አጋንንታዊ ተልዕኮዎች ቀውስን ያመጣሉ። ይህ ደግሞ አለመስማማትን፣ መከፋፈልንና ጭንገፋን ያስከትላል።

† የጠንቋይ ወይም የመተተኛ ስራዎች ሁሉ ከሰይጣን መሆናቸውን ሊያሳዩ የሚችሉ ብዙምልክቶች አሉ። ከምልክቶቹም መካከል ለሰዎች እርስ በእርስ መባላት ትልቁ ምክንያትመሆናቸው ነው። “ያንቺ ጠላት/ያንተ ጠላት እከሌ ነው፤ ስለዚህ ይህንን ድግምትወስደህ እንደዚህ አድርግ። እኔ ሕይወቱ እንዲበጠበጥ አደርጋለሁ” ይላሉ። የሰዎችንሕይወትመበጥበጥደግሞየሰይጣንባህሪነው።ከዚህምበተጨማሪምወደእርሱሄደውፍላጎታቸውንእንዲያሟላላቸውየሚጠይቁሰዎችራሳቸው“እከሌንግደልልኝ፤አጥፋልኝ፤አሳብድልኝ፤ ደሀ አርግልኝ፤ አፍዝልኝ” እና የመሳሰሉትን የክፋት ጥያቄዎች መጠየቃቸውየቦታውንሰይጣናዊነትበግልጽየሚያሳይነው።በዚምምክንያትሰይጣንበሰዎችሕይወትእያመጣያለውችግርእጅግብዙነው።ስንቱየአልጋቁራኛሆነዋል?በቤታቸውስሰላምአጥተው ስንቱ የፍቺ ጥያቄ ለፍርድ ቤት ያስገባል? ስንቱስ በአፍዝ አደንግዝ በሕይወትካሉትበታችከሞቱትበላይሆነዋል?ሳዖልበክፉመንፈስተጠቅቶእንደነበረበ1ኛሳሙ16፥14ተገልጿል።በዳዊትላይየእግዚአብሔርቅባትስለነበርሳዖልከዳዊትጋርመፎካከርናበዳዊትላይመቅናትጀመረ።ሳዖልከቅናቱየተነሳዳዊትንበተደጋጋሚሊገድለውእንደፈለገእንመለከታለን።ከዚህምበተጨማሪሳዖልየእግዚአብሔርንድምፅችላበማለትጠንቋይጋር በመሄድ እግዚአብሔርን ይበልጥ አሳዝኗል። በዚህም ምክንያት ሕይወቱ አልፏል።(1ኛዜና10፥13-14)

ስለዚህ ሰይጣን ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖራቸውን ቅርበት ለማዳከም ጥንቆላን ይጠቀማል። ክርስቲያን የሆኑ ሰዎች በጥንቆላ ተፅዕኖ ውስጥ ሲሆኑ ሊገጥማቸው ከሚችሉ ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተገልፀዋል። (ዘዳ 28፣ ዘዳ 32 ይነበብ።)

Page 68: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

58 59

• ግጭትና ሰላም ማጣት፥ ይህ ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ካለማወቅና ካለማመን የሚመጣነው።

♥ “እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተክርስቲያናትሁሉእንዲህነው።”1ኛቆሮ14፥33

• ቀርፋፋናድንጉጥመሆን

♥ “እኔን ስለ ተውኸኝ፥ ስለ ሥራህ ክፋት፥ እስክትጠፋ ፈጥነህም እስክታልቅ ድረስ በምትሠራውሥራሁሉእግዚአብሔርመርገምን፥ሽሽትን፥ተግሣጽንይሰድብሃል።…እግዚአብሔርበዕብደት፥በዕውርነት፥በድንጋጤምይመታሃል።”ዘዳ28፥20-28

• ከእግዚአብሔርለመስማትመታገል

• በዚህተፅዕኖውስጥያለሰውበአካላዊምበመንፈሳዊምሁኔታከወደፊትራዕያቸውጋርመገናኘትአይችሉም።ለአትኩሮትይቸገራሉ።

• ለነገሮችየሚኖራቸውተነሳሽነትዝቅያለወይንምእስከአለመኖርሊደርስይችላል።

• ራሳቸውንያገልላሉ።

• ኃጢአተኛእንደሆኑናትክክለኛእንዳልሆኑይሰማቸዋል(ተስፋአስቆራጭየሆነመጥፎወቀሳ)።

• ክርስቲያን የሆኑ ሰዎች በእርግማን ሲያዙ ስሜታቸው እጅጉን ይጎዳል ወይንም በስሜታቸውደካማይሆናሉ።

• በመንፈሳዊእርግማንየተያዙሰዎችጨለማናድብርትበገፅታቸውላይይነበባል።ከመገኘታቸውየተነሳመንፈሳዊውአየርይለወጣል።

• በጭንቅላታቸውአካባቢየሚሰማቸውስሜትይኖራልይህንልክእንደራስምታትልንመስለውእንችላለን።

• ጠላትበሚያጠቃቸውጊዜአካላዊህመምለምሳሌድንገተኛማቅለሽለሽ፣ራስምታት፣አፍንጫላይ የሚኖር ችግር፣ ድብርት፣ መንቀጥቀጥና የትንፋሽ ችግር የመሳሰሉት በአጠቃላይ አካላዊበሽታዎችሊገጥማቸውይችላል።

• በተጨማሪም ድብርት፣ ተስፋ ማጣት፣ ልፍስፍስነት፣ ፍርሀት፣ ሃዘን፣ ቁጣ እና ከልክ በላይማውራትሊገጥማቸውይችላል።

• በብዛት ከጥንቆላ ጋር የተያያዙ እርግማኖች ትክክለኛ ያልሆኑ አዕምሮን የሚረብሹ ፍርሃቶችእንዲከሰቱሊያደርጉይችላሉ።

እኛ ክርስቲያኖች ግን ለዚህ ክፉ ስራ ተባባሪ አይደለንም። እንዲሁም እነርሱ ጋር ካለው እኛ ጋር ያለው ይበልጣልና የድግምትና የመተት ስራ በእኛ ላይ አንዳች የለውም። ይልቁኑም በዚህ መንፈስ የተያዙትን ስለ እውነተኛው መድሀኒትና ስለ እውነተኛው አዋቂ በመስበክ ካሉበት ሰይጣናዊ እስራት ነፃ ልናወጣቸው ይገባል።

4.4.2.2 አስማትበማንኛውም የአስማት ስራ ውስጥ መሳተፍ ከጠላት ጋር የነፍስ ትስስርን ሊፈጥር ይችላል።

ጥንቆላ ሰይጣን ሰዎችን ለመማረክና ነፍሳትን ለማደን የሚጠቀምበት አንዱ መንገድ ነው።

Page 69: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

59

♥ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፥ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና?ብርሃንምከጨለማጋርምንኅብረትአለው?”1ኛቆሮ6፥14

♥ “እንዲህምበል፥ጌታእግዚአብሔርእንዲህይላል፦ነፍስንለማጥመድለእጅድጋፍሁሉመከዳለሚሰፉለሰውምሁሉራስእንደእየቁመቱሽፋንለሚሠሩሴቶችወዮላቸው!የሕዝቤንምነፍስብታጠምዱበውኑነፍሳችሁንታድናላችሁን?”ሕዝ13፥18

♥ “የማታስተውሉየገላትያሰዎችሆይ፥በዓይናችሁፊትኢየሱስክርስቶስእንደተሰቀለሆኖተሥሎነበር፤ለእውነትእንዳትታዘዙአዚምያደረገባችሁማንነው?”ገላ3፥1

4.4.3 በጥንቆላ መንፈስ ላይ ድልን መቀዳጀትክርስቲያኖች የጥንቆላ ስራ መኖሩን አንክድም። ነገር ግን ይህ ሰይጣናዊ ድርጊት በእኛ ላይ

ምንም ስልጣን ይኖረው ዘንድ የተገባ አይደለም። ምክንያቱም እኛ ጋር ያለው ከእልፍ አእላፋት መናፍስት ይበልጣል። ሰዎች በተለይም ለዚህ ክፉ መንፈስ ስራ ተገዢ የሚሆኑት ከእግዚአብሔር ጋር ካላቸው የላላ ግንኙነት ምክንያት ነው። የሚሰራባቸውም ድግምትና ማንኛውም ክፉ ድርጊት የሚደርስባቸው መከላከያ የሚሆንላቸውን መንፈሳዊ ጋሻ ባለመያዛቸው እንዲሁም “እጠቃለሁ” በሚል ፍራቻቸው ነው። ይህ ፍራቻ ሰዎች በአምላካቸው ላይ ያላቸውን መተማመን ስለሚቀንሰው ለሰይጣናዊ ስራ መግቢያ ቀዳዳን ያበጁለታል። ክርስቲያኖች ሁሉ ለእሳት ተላልፈው ከተሰጡት ከነሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ ትምህርት መውሰድ ይገባናል።

ትምህርት አንድ፥ በእኛ ሕይወት ውስጥ የሚመላለሱ የተለያዩ አካላት (ናቡከደነጾር) ምስልን ወይም የባእድ አምልኮ መገለጫን ፊት ለፊታችን አቁመው “ስገዱ፤ ካለበለዚያ ግን በሚንቀለቀል እሳት ውስጥ ትጣላላችሁ” ይሉናል። ይህ ሁለት የተለያዩ ጽንፍ የያዘ ምርጫ ነው። አንደኛው ምርጫ “አምላክህን ክደህ ለቆመልህ ምስል ስገድ፤ በሰላምም ትኖራለህ” ሲሆን ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ “አምላኬን አልክድም፤ ላቆማችሁትም ምስል አልሰግድም” በማለት የሚመጣብንን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ራስን ዝግጁ ማድረግ ነው።

ትምህርት ሁለት፥ ከእነዚህ ሰዎች የምንማረው ሁለተኛው ትምህርት ደግሞ በአምላካችን ላይ ያለንን ፍጹም የሆነ መተማመን በአንደበታችን መግለጽ ይሆናል። ስለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ካነደድከው እሳት የምናመልከው አምላክ ያድነናል” በማለት ነበር። ይህ እምነት በሁላችንም ማንነት ወስጥ ሊገነባ የሚገባ እምነት ነው። የምናመልከው አምላክ ሰይጣን የሚቃጣብንን መከራ ሁሉ በመመከት ያድነናል። እዚህ የእምነት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ብዙ ሰዎች ለሰይጣን ፉከራና ሸለልቶ ድንጉጥ ይሆናሉ። በመጨረሻም አምላካቸውን በመካድ ለቆመላቸው ምስል ይሰግዳሉ።

ትምህርት ሶስት፥ እነዚህ ሶስት ሰዎች በአምላካቸው ላይ ያላቸውን ሙሉ እምነት ከገለጹ በኋላ የተናገሩት አንድ ነገር ነበረ።” አምላካችን ከዚህ እሳት ባያድነን እንኳን አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም።” አምላካችንን የምናመልከው በሰዓቱ ከተቃጣብን መከራ ስለሚያድነን ብቻ ሊሆን አይገባውም። ምክንያቱም በደረሰብን ትንሽ ችግር “አምላክ ለካ የለም” ወደሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሰናልና። እምነታችን ላይ ቅድመ ሁኔታ ልናስቀምጥ አይገባንም። የቀረበልንን ሰይጣናዊ ማስፈራሪያ ችላ ብለን “አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም” በማለት እምነታችንን ማፅናት አለብን። እነዚህ ሶስት ሰዎች ምርጫው በቀረበላቸው ጊዜ የትርዒቱን ታዳሚዎችን በሙሉ ያስገረመና ያስተማረ መልስ መልሰዋል። ለእኛም ምሳሌ የሚሆን ውሳኔን ወስነዋል።

Page 70: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

60 61

ትምህርት አራት፥ እነ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ እና አብድናጎ በተጋረጠባቸው ፈተና ላይ ድልን ተቀዳጁ። የተቀዳጁትን ድል በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን። አንደኛ በራሳቸው ላይ የተቀዳጁት ድልና ሁለተኛ “ለባእድ አካል ስገዱ” እያሉ በሚያስገድዱት አካላት ላይ የተቀዳጁት ድል ናቸው። በመጀመሪያ በራሳቸው አካል ላይ የተቀዳጁትን ድል እንመልከት። ማንም ሰው ትሞታለህ ሲባል የማይፈራ የለም። ላለመሞት የማያምንባቸውን ብዙ ነገሮች ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም። እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች የነፍስና የስጋ ሙግት የሚካሄዱባቸው አጣብቂኝ ጊዜ ናቸው። በዚህ አጣብቂኝ ጊዜ አብዛኛውን ጊዜ ስጋ ነፍስን ታሸንፋታለች። እነዚህ ሰዎች ግን ዘላለማዊ ሕይወትን በማስቀደም “ከፈለክ ግደለን” ማለታቸው አምልኮታቸውን እንከን አልባ አድርጎታል። ሁለተኛው ድል ደግሞ በሌሎቹ ላይ ያስመዘገቡት ድል ነው። ንጉሱን “አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም” በማለታቸው በብዙ ታዳሚዎች ፊት ለሌሎቹ መቀጣጫ ይሆኑ ዘንድ ወደ እሳቱ ተጣሉ። ነገር ግን ሶስት ሆነቀው ተጥለው አራት ሆነው ይታዩ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ መልአኩን ልኮላቸው እሳቱ ቢንበለበልም አላቃጠላቸውም ነበር። ይህንን ሁኔታ የተመለከቱ ሁሉ ልባቸው ተሰበረ። ሰዎች ለዘረጉት የአምልኮ ስርዓት ተገዝቶ በሕይወት ከመኖር ይልቅ በአምላክ ተማምኖ ወደ እሳቱ መጣል የበለጠ መሆኑን ተረዱ።

ጥንቆላ መኖሩን የማናውቅ ወይም የማንቀበል ከሆነ በመንፈሱ ላይ ድልን መቀዳጀት አንችልም። ጳውሎስ በቆሮንቶስ መጽሐፍ ላይ የሰይጣንን ስራ ችላ ማለት እንደሌለብን ይነግረናል። እውነታን ካልተቀበልን የምንታለልበትን መንገድ እንከፍታለን። ሁላችንም በበጎ መልኩ ተፅዕኖ እንድናደርግ በእግዚአብሔር የተሰጠን ስልጣን አለ። ተፅዕኖ የምናደርገው ቤተሰቦቻችን ላይ፣ አገልግሎታችን ላይ እና ማናቸውም ተፅዕኖ ማምጣት የሚገቡን ቦታዎች ላይ ሊሆን ይችላል።

♥ “እኛግንእግዚአብሔርእንደወሰነልንእስከእናንተእንኳእንደሚደርስእንደክፍላችንልክእንጂያለ ልክ አንመካም። ወደ እናንተ እንደማንደርስ አድርገን ከመጠን አናልፍምና፥ የክርስቶስንወንጌልበመስበክእስከእናንተእንኳደርሰናልና፥በሌሎችድካምያለልክአንመካም፥ነገርግንእምነታችሁሲያድግከእናንተወዲያባለውአገርእስክንሰብክሥራችንንእየጨመርን፥በክፍላችንበእናንተዘንድእንድንከብርተስፋእናደርጋለን፤በሌላውክፍልስለተዘጋጀውነገርአንመካም።”2ኛቆሮ10፥13-16

እግዚአብሔር እኛን የጠራን ድል አድራጊዎች እንድንሆን እንጂ ተጠቂዎች (ድል ተደራጊዎች) እንድንሆን አይደለም። እኛ የሰይጣን ወይም በእርሱ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥገኛ አይደለንም። በእነኚህ መናፍስት እንድንታለልና እንድንገዛ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም። መልካሙ ዜና በጥንቆላ መንፈስ ላይ ሙሉ ስልጣን አለን። እግዚአብሔር የጥንቆላን መንፈስ የምንዋጋበት ስልጣን ሰጥቶናል።

♥ “በሰውልማድምንምእንኳየምንመላለስብንሆን፥እንደሰውልማድአንዋጋም፤የጦርእቃችንሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብበእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስምለመታዘዝ አዕምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉልንበቀልተዘጋጅተናል።”2ኛቆሮ10፥3-6

† ጥንቆላእግዚአብሔርየሰጠንመንፈሳዊየጦርእቃእውነትእንዳልሆነሊነግረንይችላል።በዚህምክንያትእኛንበጠላትላይያለንንስልጣንሙሉለሙሉእንዳንጠቀምሊያደርገንይችላል።እግዚአብሔርየጥንቆላንመንፈስየምናሸንፍበትቃሉንናቅባቱንበመንፈስቅዱስአማካኝነትሰጥቶናል።

Page 71: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

61

ጥንቆላን የሚቃወም ምሳሌያዊ ጸሎትጥንቆላና ከጠላት ጋር የተያያዙ ነገሮች ከእግዚአብሔር እንደሚያጣሉን ካወቅን ቀጣዩ እርምጃ

መሆን ያለበት ከጠላት እጅ ፈልቅቆ ያወጣንን አምላክ መታመንና በእርሱ ትዕዛዛት መንገድ መጓዝ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ በመሰጠት በጸሎት ፊቱ መቅረብ አለብን። እግዚአብሔርን ከተማመንን ደግሞ እንደ እርሱ ፈቃድ በስሙ የምንጠይቀውን ሁሉ ሊያደርግልን የታመነ ነው። ከዚህ በታች ያለው ምሳሌያዊ ጸሎት እንዴት መጸለይ እንደምንችል ያሳያል።

“ነገርንም ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።” ኢዮ 22፥28 ♥ “የመንግሥተሰማያትንምመክፈቻዎችእሰጥሃለሁ፤በምድርየምታስረውሁሉበሰማያትየታሰረ

ይሆናል፥በምድርምየምትፈታውሁሉበሰማያትየተፈታይሆናል።”ማቴ16፥19

† በሰማይ ያለህ አባት ሆይ በአጋንንት ላይና በጥንቆላ መንፈስ ለይ ስለተሰጠኝ ስልጣንአመሰግንሃለሁ። በሕይወቴ ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም የጥንቆላ አሰራሮች በክርስቶስኢየሱስ ስም አስወግዳለሁ። የክርስቶስን ደም በስሜቴ ላይ፣ በፈቃዴ ላይ፣ በአካሌ ላይአውጃለሁ።ኢየሱስክርስቶስአምላኬእንደሆነናማንምበእኔላይጌታሊሆንእንደማይችልአውጃለሁ። በቃልህ እንደተናገርከው “በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንምበፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር” ኢሳ 54፥17) ርስቴ አንተነህና ከአንተ ውጪ ማንም አይገዛኝም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ መላእክትህን ልከህ መልካምያልሆነ መንፈስን ወደ እኔ የሚያስተላልፉትን እንድታስወግዳቸው እፀልያለሁ። በእኔላይ የተደረጉትን አስማቶች ሁሉ እሰብራለሁ። በእኔ ላይ የሚደረገውን የጥንቆላ ኃይልበክርስቶስ ደም ሰብሬዋለሁ። በጥንቆላ መንፈሰ የተያዘውን አዕምሮዬን አስለቅቃለሁ።በቃሉእንደተጻፈውከማንኛውምየጥንቆላኃይልነፃእንደሆነኩአውጃለሁ(እንግዲህልጁአርነትቢያወጣችሁበእውነትአርነትትወጣላችሁ።ዮሐ8፥36)።አንተብቻበእኔላይጌታእንደሆንክናማንምበእኔላይጌታሊሆንእንደማይችልአውጃለሁ።

† በዙሪያዬምያሉትሰዎችበእኔላይአንተብቻስልጣንእንዳለህእንዲያውቁእርዳቸው።በታመነውቃልህመሰረትበእነኚህሰዎችየተደረገማንኛውምሕይወቴንየሚያበላሸውንነገር ሁሉ በክርስቶስ ስም አፈርሳለሁ። ወደ እኔ መንፈስን ሊያስተላልፉ ያሉ ሰዎችንከልክላቸው። የክርስቶስን ደም በእኔና መንፈስን ሊያስተላልፉ ባሉ ሰዎች መካከልአደርጋለሁ። እነኚህ ሰዎች በማንኛውም መንገድ ወደ እኔ እንዳይመለሱ እከለክላለሁ።በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ስልጣንና በደሙ ጉልበት በሕይወቴ ላይ የተደረጉ የኮከብቆጠራስራዎችንእደመስሳለሁ።በሰዎችአማካኝነትበእኔላይአስማትንወይምጥንቆላንሊያደርጉየተነሱአጋንንትስልጣናቸውንአስወግዳለሁ።እነኚህንአጋንንትበደሙጉልበትአጠፋቸዋለሁ። የክርስቶስን ደም በእኔና በእነርሱ መካከል አደርጋለሁ። የሰይጣንንማንነትናአንተለእነርሱያለህንፍቅርገልጠህላቸውከአጋንንትመንፈስነፃይወጡዘንድእፀልያለሁ።

Page 72: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

62 63

† በሕይወቴ ያለውን ማንኛውም ትምክህት፣ ዓመፅ፣ ኃጢአት፣ አለመታዘዝ እናዘዛለሁ።ከዲያብሎስ ጋር በማንኛውም ሁኔታ ስምምነት አድርጌ ከሆነ ይቅር እንድትለኝናስምምነቶቹከሚያመጡትችግርእንድታነፃኝእፀልያለሁ።

† አባትእግዚአብሔርሆይበማንኛውምሁኔታየአንተካልሆኑናመንፈስንከሚያስሩሰዎችጋርኅብረትአድርጌከሆነይህንንእንድትገልጥልኝእፀልያለሁ።በሕይወቴጤናማባልሆነመንገድከሌሎችጋርስምምነትፈጥሬከሆነይቅርበለኝ።

† የተሰጠኝንመብራትአበራለሁ።ይህንንመብራትከፍአድርጌበማብራትጨለማንሁሉእንዲያስወግድአደርጋለሁ።ወደምድርወርደህየሰይጣንንስራስላፈረስክአመሰግንሃለሁ።ጉልበትሁሉበሰማይምበምድርምሊንበረከክለት፣ሁሉምምላስክርስቶስጌታእንደሆነሊመሰክርእንደሚገባአውጃለሁ።አሜን!!

4.4.4 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የማያከብሩ የሚደርስባቸው ችግሮችመታዘዝ ከሰነፎች መስዋት እንደሚሻል የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። በመሆኑም

ሕይወታችን ሙሉ የበረከት ፍሬዎችን እንድንለቅም የመታዘዝን አስፈላጊነት መገንዘብ አስፈላጊ ነው። በመውጣታችን እንባረካለን፤ ስንገባም እናባረካለን፤ በአህዛብ መካከል የተደሰተ ሕዝብ አድርጎ ያቆመናል። ለተቸገሩ እንድናበድር ኪሳችንን ሙሉ፣ እጃችንንም ለመርዳት የተፈታ ያደርገዋል። እርሱ ከሚሰራልን መስመር ቀኝም ግራም አንልምና ኑሯችን ሁሌም በለመለመው መስክ ይሆናል። (ዘዳ 8)። ነገር ግን እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ልቡንም ስለክፋት የሚያደነድን ቢኖር የሚከተሉት እርግማኖች ይደርሱበታል።

ሀ) ድህነትድህነት ከቁሳዊነቱ ይልቅ መንፈሳዊነቱ ያመዝናል። አንዳንድ ሰዎች እጅግ ብዙ የሚባል ገንዘብ

በካዝናቸው ውስጥ ቢኖር እንኳን የድህነት መንፈስን ከውስጣቸው ይፍቁት ዘንድ ይሳናቸዋል። እነዚህ ሰዎች የቁስ ባለጸጋ ቢሆኑም እንኳን ሁሌም ገንዘብን ይጠሟታል። በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ያገለግሏታል እንጂ አይገለገሉባትም። በመሆኑም በኑሯቸው ውስጥ ምንም እርካታ ከማጣታቸውም ባሻገር ገንዘባቸው የሚያተርፍላቸው ጭንቀትን ብቻ ነው።

♥ “ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙንሁሉባትጠብቅባታደርግም፥እነዚህመርገሞችሁሉይመጡብሃልያገኙህማል።በከተማርጉምትሆናለህ፥በእርሻምርጉምትሆናለህ።እንቅብህናቡሃቃህርጉምይሆናል።”ዘዳ28፥15-17

እንዲሁም ሃብቱ ሁሉ የተረገመና ወዳሚ ይሆናል። ይህ ቃል የሚያሳየን ቁም ነገር የሌማት መሙላት ብቻ የህሊናን ፍላጎት አያጠግበውም። ስለዚህ ኃጢአተኞች ምንም እንኳን ባለጸጋ ቢሆኑ የእግዚአብሔር ክብር ጎሏቸዋልና ፍሬውን እንዳይበሉ ይሆናሉ። ቢበሉ እንኳን የማይረኩ ይሆናሉ። ብዙ ጊዜ በየሆስፒታሎቹ የተለያዩ ባለጸጋዎች ከምግብ አንፃር እንኳን “ከአንድ ምግብ ዓይነት ውጪ ከበላህ ትሞታለህ” ሲባል ይሰማል። እንደዚህ የተባሉ ሰዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር አልታዘዝ ያሉ ናቸው ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር ያዘነባቸው ሰዎች እንደዚህ አይነት ችግርን ሊያስተናግዱ ይችላሉ።

Page 73: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

63

♥ “የምድርህንፍሬድካምህንምሁሉየማታውቀውሕዝብይበላዋልአንተምሁልጊዜየተጨነቅህየተገፋህምትሆናለህ።እጅግዘርወደእርሻታወጣለህአንበጣምይበላዋልናጥቂትትሰበስባለህ።”ዘዳ28፥33ና38

ለ) አቅመ ደካማነትሰዎች በራሳቸው ደካማ ናቸው። ነገር ግን በሚያበረታን በእግዚአብሔር መከራንም ቢሆን፣

ችግርንም ቢሆን የምንወጣበት አቅም ይኖረናል። ማዕበል የሚያላጋው የባህር ዳር ድንጋይ እንደሚያብረቀርቅ ሁሉ ለአማኞች ፈተና በበለጠ ድል የሚያንጸባርቁበት አጋጣሚ ይሆንላቸዋል እንጂ ወድቀው አይቀሩም። መሰናክሎችንም ቢሆን በጥንካሬ ያልፋሉ። ነገር ግን ማንም ከጌታ ፈቃድ ቢያዘነብል “እንደራሴ ፈቃድ እንጂ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አልኖርም” ቢል የጥንካሬው መንፈስ ከእርሱ ጋር አይደለምና ደካማና ልፍስፍስ ይሆናል። በማያልቅ የችግር ውርጂብኝ ውስጥ ይኖራል። በመከራዎቹ ውስጥ አብሮት የሚቆምና አይዞህ የሚለው ክፍልም አይኖርም።

♥ “እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።በቀትርም ጊዜ ዕውር በጨለማ እንደሚርመሰመስትርመሰመሳለህ፥ መንገድህም የቀና አይሆንም በዘመንህም ሁሉ የተጨነቅህ የተዘረፍህምትሆናለህ፥የሚያድንህምየለም።”ዘዳ28፥22ና29

ሐ) ዕብደትዕብደት ማለት መደበኛ ሁኔታ ላይ አለመሆንና የህሊና ክፉ እና ደጉን የማመዛዘን አቅምን

ማጣትን ያሳያል።እነዚህ ሁኔታዎች የሚሳዩት ደግሞ ዕብደት ማለት የግድ ጨርቅን መጣል ብቻ አለመሆኑን ነው። ነገር ግን በህብረተሰብ ዘንድ አሳፋሪ የሚባሉና የተናቁ ስራዎችን መስራት፣ ግራ መጋባት፣ ጭንቀት፣ መርሳት፣ ደግ እና ክፉን አለመለየት፣ ያለምክንያት ከሰዎች ጋር መጣላት፣ ራስን መጥላት፣ የልብ አለመረጋጋት እና የመሳሰሉት የዚህ እርግማን ውጤቶች ናቸው።

♥ “እግዚአብሔርበዕብደት፥በዕውርነት፥በድንጋጤምይመታሃል።”ዘዳ28፥28

በምሳሌ 26፥2 ላይ እንደሚታየው እርግማን ያለምክንያት ሰው ላይ ተፅዕኖ ሊያመጣ አይችልም። በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ እንዲያመጣ የሚያደርጉት ይቅር አለማለት፣ ኃጢአት፣ በዘር ውስጥ ያለ በደል፣ እምነት ማጣት፣ ፍርሃት፣ አለመታዘዝ፣ ስርቆት እና ከሰይጣን አገልጋዮች የሚመጣ እርግማን ምክንያቶች ይሆናሉ።

ሕዝቅኤል በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደረገው ጥንቆላ ይናገራል፤ (ሕዝ 13)። ጠንቋዮች አማኞችን እንዲወጉ ወይም እንዲያጠፉ መንገድ ከሚከፍትላቸው ዘዴዎች መካከል እጅን በመጫን የሰይጣንን መንፈስ ማስተላለፍ፣ የሰዎችን የወደፊት ሕይወት ለማወቅ የሚደረግ ኮከብ ቆጠራ፥ አስማት (ከሰው አዕምሮ በላይ የሆነን ነገር ማድረግ)፣ የደረቅ መርፌ ህክምና፣ እኛ ወይም ዘሮቻችን ዓለም አቀፍ ህቡዕ ድርጅት አባል መሆንና መሳተፍ ተፅዕኖ እንዲያመጡ ሊያደርጋቸው ይችላል።

(ህቡዕ ድርጅት ምስጢራዊ ድርጅት ሲሆን ከላይ ሲታይ የሚጎዳ የማይመስል ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር ያለው እምነትና አስተምህሮ ከትክክለኛው አስተምህሮ የሚፃረር ነገር ያለበት ድርጅት ነው። ህቡዕ ድርጅት የሚያሰተምረው አንድ እግዚአብሔር እንዳለና በሁሉ ሃይማኖት የሚገኝ ሰው አንድ እግዚአብሔርን በተለያየ ስም እንደሚያመልክ ነው።)

Page 74: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

64 65

♥ “ስለዚህም ጌታ፥ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።” 2ኛ ቆሮ 6፥17-18

በህቡዕ ድርጅት ውስጥ አባላት የሆኑ ሰዎች አባልነታቸውን በውጪ ካሉ ሰዎች መደበቅ አልያም መካድ እንዳለባቸው አንዳንድ ፅሁፎች ያስረዳሉ። የድርጅቱን ምስጢር በመሀላ እንዲጠብቁም ይደረጋሉ። ህቡዕ ድርጅቶች በውስጣቸው የተለያዩ ዓይነት ስርዓታዊ አከባበር ሲኖራቸው ጉዳት ከማያመጣው የቡድን ስብስብ በዓለም ሁኔታ ላይ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እስከሚችሉ የሰዎች ስብስብ ሊደርስ ይችላል። በአብዛኛው ጊዜም እነዚህ ትልልቅ የሚባሉ ድርጅቶች የሰይጣን አስተሳሰብንና አምልኮትን እንደሚከተሉ የተለያዩ ማስረጃዎች አሉ።

ህቡዕ ድርጅት የሀይማኖት ድርጅት እንዳልሆነ ሲነገር፣ ነገር ግን የራሱ የሆነ መመሪያ መጽሐፍ ያለው፣ የተለያዩ አማልክትን የሚያመልኩ እና በጥምቀት የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ ነው። መጽሐፉም እንደሚገልፀው ዘላለማዊ ሕይወት አንዱ የሃይማኖቱ መሰረት እንደሆነ ነው። አብዛኛው የህቡዕ ድርጅቶች አባላት በለጋ እድሜአቸው ሲሞቱ ቤተሰቦቻቸው ደግሞ ለመናፍስት በሚያደርጉት ስለትና መሃላ በተለያዩ በሽታዎች እንዲሰቃዩ አድርጓቸዋል።

አብዛኞቹ የህቡዕ ድርጅቶች አባላት የሆኑ ሕዝብ ጥሩ ሰዎች ቢሆኑም በእርግማን የታሰሩ ናቸው። ብዙ ሰው በዙሪያቸው ያሉ የህቡዕ ድርጅት አባላት በባህርያቸው ጥሩ ስለሆኑና ጥሩ ነገር ስለሚያደርጉ ስለድርጅቱ ማንነት በትክከል አይረዱም። በዚህ ምክንያት ይህን ቡድን መቀላቀል መልካም እንደሆነና እንደማይጎዳቸው ያስባሉ። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ሲሆን የህቡዕ ድርጅት መሰረቱ የተለያዩ ጣዖቶች በመሆኑ ይዞት የሚመጣው መዘዝ ከፊት ለፊት አይታወቅም። እነኚህ የትውልድ በደሎች የደም ትስስር ባላቸው ሰዎች ያልፋሉ፤ በደሎቹ ለትውልድ እርግማን በር ይከፍታሉ። ከህቡዕ እምነትና እርግማን ለመውጣት ሰዎች በክርስቶስ ደም መታጠብና መንፃት አለባቸው።

4.4.5 የህቡዕ ድርጅት አደገኛነት † ደህንነትን ለመቀበል ወደ ፈጣሪ የሚያደርሱ ብዙ መንገዶች አሉ የሚለው የማታለል

አስተምህሮ † ጥሩስራበመስራትብቻደህንነትይገኛልየሚለውአስተምህሮ † ለአማልክቶችየሚደረግስለትናመሀላ † ወደፊትየሚመጡትውልዶችለእጅስራየተሰጡናቸው

† የድርጅቱመሰረትጥንቆላመሆኑ

4.5 የዲያብሎስን ሥራ ማጋለጥና ማፍረስ

የዲያብሎስ ስራዎች ጨለማ ውስጥ ባሉ ሁኔታዎች ይመሰላሉ። ፍራቻ፣ ተንኮል፣ የሚሄዱበትን አለማወቅ፣ ደባ፣ ርኩሰት፣ መሰናክል፣ ዝሙት፣ ስርቆት እና የመሳሰሉት የሚሰሩት በጨለማ

Page 75: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

65

ነው። እነዚህን ስራዎች ስናፈራርስበት ግን የሰይጣን ምሽግ የሆነው የጨለማ ሕይወት በብርሀን ይጥለቀለቃል። ለዲያብሎስም ራሱን የሚያስጠጋበት ስፍራ አይገኝለትም።

♥ “ፍሬምከሌለውከጨለማሥራጋርአትተባበሩ፥ይልቁንግለጡትእንጂ፥እነርሱበስውርስለሚያደርጉትመናገርእንኳነውርነውና፤ሁሉግንበብርሃንሲገለጥይታያል፤የሚታየውሁሉብርሃንነውና።”ኤፌ5፥11-13

• ጌታኢየሱስክርስቶስወደዚህዓለምየመጣውእነዚህንየጨለማአሰራርበሕይወትቃሉናወደርአልባበሆነፍቅሩሊያፈርስነው።

♥ “ስለዚህየዲያብሎስንሥራእንዲያፈርስየእግዚአብሔርልጅተገለጠ።”1ኛዮሐ3፥8-9

ጸሎትጸሎት የግል ስሜት ብቻ የምናንጸባርቅበት ሁኔታ አይደለም። አንዳንድ ክርስቲያኖች

የእግዚአብሔርን ቃል ባለመረዳት የሚጸልዩት ችግር ሲደርስባቸውና የዲያብሎስ ውጊያ ሲበረታባቸው ብቻ ነው። በመሆኑም ጸሎት ብሶትንና ሀዘንን ብቻ ማካፈያ መንገድ አድርገው ያስቡታል። ለምስጋና የሚሆን ጊዜ የላቸውም። የዕለት ቆይታን ሪፖርት የሚያቀርቡ ይመስል ስለደረሰባቸው ችግርና ስላጋጠማቸው ፈተና ብቻ ይናገራሉ። ስለዚህ በጸሎት ውስጥ ከመናገር በቀር መስማትን አይለማመዱም። ነገር ግን ስንጸልይ ከጌታ ጋር አብረን እንደሆንን ልናስብ ይገባናል። ለጸሎት ስንንበረከክ አባታዊ ምክሩና ቡራኬውን ለመቀበል ከእግሩ ስር እንዳለን ሊሰማን ይገባል። አጥንትን የሚያለመልም እንዲሁም ውስጥን በሀሴት በሚሞላ ቃላት ሲያናግረን በጥሞና መስማት ይኖርብናል። የዛኔ ሰይጣን ከእኛ ጎን መቆም ተስኖት ሲርቅ ውስጣችንም በመንፈሳዊ ጉልበት ሲታደስ ይሰማናል። ይህ ነው ዲያብሎስን ድል እንድንነሳው የሚያስችለን የመውጊያው ጦር፤ ይህ ነው ከሚቃጡብን የዲያብሎስ ፈተናዎች የምንሻገርበት ድልድይ።

♥ “በጸሎትናበልመናምሁሉዘወትርበመንፈስጸልዩ፤”አፌ6፥18

በሕይወታችን ላይ የክርስቶስ ኢየሱስን ደም ማወጅየጌታችን ደም መድኃኒት ሊሆነን እንጂ እንዲሁ በከንቱ የፈሰሰ አይደለም። የሰው ልጆችን

ኃጢአት ሊያነፃ የሚችል፣ መድኃኒትም የሆነ በነፃ የሚገኝ ውድ ፈሳሽ ነው። ለዛም ነው “የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” የተባለው። ይህ ደም መድኃኒት የሚሆነው ለተቀበሉት ብቻ ነው እንጂ ለማያምኑት አይደለም። ሰይጣን በክርስቶስ ደም መዋጀታችንን አይወደውም። ምክንያቱም ይህ ደም ግዛቱ የሆነችውን ሲኦልን ባዶ ያስቀረ፣ የማረካቸውንም ነፍሳት የነጠቀ ነውና። ዛሬም “እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት (ራዕይ 12፥11)” በማለት በክርስቶስ ደም ዲያብሎስን ድል እንደምንነሳ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል።

በእግዚአብሔር ቃል መበርታትና መቆምየእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና መስማት በመጀመሪያ በትዕቢትና በሰይጣናዊ ስሜት የደነደነ

ልብ ይሰብራል፤ ይቀድስማል። ቃሉን ከሕይወታችን ጋር በማዋሀድና እንደ ሃሳቡም በመኖር አሸናፊዎች እንሆናለን።

Page 76: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

66 67

♥ “በሁሉምላይጨምራችሁየሚንበለበሉትንየክፉውንፍላጻዎችሁሉልታጠፉየምትችሉበትንየእምነትን ጋሻ አንሡ፤የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔርቃልነው።በጸሎትናበልመናምሁሉዘወትርበመንፈስጸልዩ፤በዚህምአሳብስለቅዱሳንሁሉእየለመናችሁበመጽናትሁሉትጉ፤”አፌ6፥16-18

♥ “የእግዚአብሔርቃልሕያውነውና፥የሚሠራም፥ሁለትምአፍካለውሰይፍሁሉይልቅየተሳለነው፥ነፍስንናመንፈስንምጅማትንናቅልጥምንምእስኪለይድረስይወጋል፥የልብንምስሜትናአሳብይመረምራል፤”ዕብ4፥12

እግዚአብሔርን ከማወቅ የሚያግዱ ሃሳቦችን ማስወጣት (መተው)ያወቅነውንና የተቀበልነውን አምላክ እግዚአብሔርን እንድንረሳ የሚያደርጉንን ሁኔታዎች

መተው መቻል አለብን። እግዚአብሔርን እንድንረሳ ከሚያደርጉን ሁኔታዎች አንዱ ለሰዎች የምንሰጠው ትክክል ያልሆነ ግምትና ክብር ነው። የምናደርጋቸውን ነገሮች በሙሉ “ሰዎች ይደሰቱበታል ወይስ አይደሰቱበትም?” ማለት እንጂ “እግዚአብሔር ይደሰትበታል ወይስ አይደሰትበትም?” የሚል ሀሳብ ውስጥ እንድንገባ እንሆናለን። ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች ዝሙትን ለመስራት፣ ጉቦ ለመቀባበል፣ ሰውን ለመግደል፣ እንዲሁም ሌሎች የኃጢአት ስራዎችን ለመስራት ማንም ሰው የማያይበትን አሳቻ ቦታና ጨለማን የሚመርጡት። “ሰው አየኝ አላየኝ” ከማለት ባሻገር “እግዚአብሔር አየኝ አላየኝ” የሚለው ሀሳብ በህሊናቸው ውስጥ አይመላለስም። ብላቴናው ዮሴፍ በዚህ ረገድ ሊያስተምረን የሚችል ታሪክ አለው። ይህ ሰው የእግዚአብሔር ክብር አብሮት ስለነበር በባእድ ሀገር በንጉሱ ዘንድ ክብርን ተጎናጽፎ ነበር። በመሆኑም ንጉሱ ወደ ሌላ ቦታ በሄደ ጊዜ በስልጣኑና በንብረቱ ላይ ወክሎት ሄዶ ነበር። ታዲያ የዚያ ንጉስ ሚስት በዮሴፍ ላይ የዝሙት መንፈስ አድሮባት ነበርና “አብረኸኝ ተደሰት፤ ከአልጋዬም ላይ ውጣ በማለት” ትጋብዘዋለች። ዮሴፍ ግን “በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?” (ዘፍ 39) በማለት መለሰላት። ይህንን አይነት ልምምድ እኛም ብንሆን ማዳበር ያለብን ነገር ነው። ከሰዎች ተደብቀን የምንሰራቸው ኃጢአቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ግልጽ መሆናቸውን ማወቅ መልካም ነው። በመሆኑም “ይህንን አስጸያፊ ድርጊት በአምላኬ ፊት አልፈጽምም” በማለት መተው አለብን።

♥ “የጦር እቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤የሰውንምአሳብበእግዚአብሔርምእውቀትላይየሚነሣውንከፍያለውንነገርሁሉእናፈርሳለንለክርስቶስምለመታዘዝአዕምሮንሁሉእንማርካለን፥”2ኛቆሮ10፥4-5

ቃል ኪዳንን የራስ ማድረግ ♥ “የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ

ታጠፋላችሁ፥ቀልጠውየተሠሩትንምምስሎቻቸውንሁሉታጠፋላችሁ፥በኮረብታላይያሉትንመስገጃዎቻቸውንምታፈርሳላችሁምድሪቱንምለእናንተርስትአድርጌሰጥቼአችኋለሁናምድሪቱንትወርሱአታላችሁትቀመጡባታላችሁም።”ዘኁ33፥52-53

♥ ራስንአለማግለልናበቤተክርስቲያንውስጥመሳተፍ

እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ሰጥቶናል። ለአንዳንዶቻችን በዝማሬና በምስጋና እንድናገለግል፣ ለሌሎቻችን ቃሉን እንድንሰብክ፣ ለአንዳንዶቻችን እንድንመክር፣ ለአንዳንዶቻችን እንድንመራ፣ ለአንዳንዶቻችን በጽሁፍ እንድናገለግል የተለያዩ ጸጋዎች

Page 77: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

67

ተሰጥተውናል። በእነዚህ በተሰጡን መክሊቶች ልናተርፍባቸው እንጂ ልንቀብራቸው አይገባም። ምክንያቱም በትንሹ መታመን በትልቁ ለመሾም ምክንያት ነውና። በመሆኑም ራስን ከማግለል ይልቅ የተሰጡንን ጸጋዎች ለመተግበር ዘወትር መትጋት ይገባናል።

♥ “ለፍቅርናለመልካምምሥራእንድንነቃቃእርስበርሳችንእንተያይ፤በአንዳንዶችምዘንድልማድእንደሆነው፥መሰብሰባችንንአንተውእርስበርሳችንእንመካከርእንጂ፤ይልቁንምቀኑሲቀርብእያያችሁአብልጣችሁይህንአድርጉ።”ዕብ10፥24-25

የሰዎችን የጸጋ ስጦታ ሳይሆን የሕይወታቸውን ፍሬ መመልከትምልክትን እያዩ መጓዝ ብዙ ችግሮች አሉት። ሰዎች ስለፈወሱና ድንቅ ድንቅ ነገሮችን

ስላደረጉ ብቻ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አስማተኞችም ድንቅ ድንቅ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉና። ሙሴ በትሩን እባብ ሲያደርግ አስማተኞቹም ይህንን ማድረግ እንዳልተሳናቸው ማስታወስ ይገባል። በመሆኑም የሕይወታቸውን ፍሬ ማየት ተገቢ ነው። የእግዚአብሔር ቃልም እንድንጠነቀቅ ይመክረናል። የጌታ የሆኑት ግን ነገሮችን ሁሉ በፍቅር ያደርጋሉ።

♥ “የበግለምድለብሰውከሚመጡባችሁበውሥጣቸውግንነጣቂዎችተኵላዎችከሆኑከሐሰተኞችነቢያትተጠንቀቁ።ከፍሬያቸውታውቋቸዋላችሁ።ከእሾህወይንከኩርንችትስበለስይለቀማልን?”ማቴ7፥15-16

♥ “እርስበርሳችሁፍቅርቢኖራችሁ፥ደቀመዛሙርቴእንደሆናችሁሰዎችሁሉበዚህያውቃሉ።”ዮሐ13፥35

እጅን ጭኖ ስለሚፀልይልን ሰው በሚገባ ማወቅ(መጠንቀቅ)ተአምራትን ሲሰሩ ስላየናቸው ብቻ ሰዎችን በላያችን ላይ እጃቸውን ጭነው እንዲጸልዩ

ልንፈቅድላቸው አይገባም።

♥ “በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፥ በሌሎችም ኃጢአት አትተባበር፥ ራስህን በንጽህናጠብቅ።”1ኛጢሞ5፥22

እኛን ለመቆጣጠር የሚፈለጉ ነገሮችን ማስወገድከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ምንም ነገር ቢሆን ሊቆጣጠረን አይገባም። እንደ ሲጋራና

መጠጥ ያሉ ሱሶች ውስጥ ካለን ፈጥነን መውጣት ይገባናል። ሰው ለዛውም የእግዚአብሔር ድንቅ ስራ ነውና አካልንም መንፈስንም በሚያቆሽሽ ግዑዝ ነገር ቁጥጥር ውስጥ መውደቅ አይገባውም። ካልገዛው እያለ ፈተናውን በሚያበዛብን የስጋ ፍላጎትም ቁጥጥር ስር መውደቅ የለብንም። ስጋችንን እየጎሸምን ልንኖር ግድ ነው፤ አለበለዚያ እንደስጋ ፈቃድ ወደ ፈለግንበት አቅጣጫ ስንነዳ እይታችን ከአምላካችን ላይ ይነቀላል። ልባችንን ሕይወት ለሚሆናት ከእግዚአብሔር ሀሳብ በቀር ለጊዜያዊ ምቾትና ደስታ ተገዢ አናድርጋት። ሌሎች በእኛ ላይ የሚተገብሩት ሰይጣናዊ ተግባርም ቢሆን እንዳይሰራ እንዲሁም መሰናክል እንዳይሆንብን ልባችን በአምላካችን ላይ ፍጹም የሆነ እምነት ሊኖረው ይገባል።

♥ “አጥብቀህልብህንጠብቅ፥የሕይወትመውጫከእርሱነውና።”ምሳ4፥23

Page 78: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

68 69

♥ “በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉትፈርጂበታለሽ።የእግዚአብሔርባሪያዎችርስትይህነው፥ጽድቃቸውምከእኔዘንድነው፥ይላልእግዚአብሔር፦”ኢሳ54፥17

አመፀኛ ሰዎችን መለየትዓመፀኞችን በእግዚአብሔር ቃል ልንለውጣቸው ከቻልን መልካም ነው። የክርስትና ሕይወት

ትርጉሙ በዓመፃ ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎችን መልሶ ለእግዚአብሔር ተገዢ ማድረግ ነው። በጸሎታችን ማሰብ፣ የሕይወት ቃልንም ልንመሰክርላቸው ይገባል። የምንሄድበትን የሕይወት መንገድ ለእነርሱም ይሆን ዘንድ ሰላማችንንና ፍቅራችንን እንግለጽላቸው። ነገር ግን አንዳንዶች የምንነግራቸውን ቃል እንደ ሞኝነት ይቆጥሩታልና ሰምተው ለመቀበል ይከብዳቸዋል። ይልቁንም እኛም የጊዜውን ፍልስፍና ተከታይ እንድንሆንና የክርስቶስን ሞትና ትንሳዔ ዜና እንዳናወራ ማሰናከያዎችን ይፈጥራሉ። በመንገዳቸው ተስበን እንዳንቀር ሊቀየር የማይፈልግ የዓመፅን ሰው መለየት አለብን።

♥ “ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነውየእግዚአብሔርንቃልንቀሃልናእግዚአብሔርንጉሥእንዳትሆንናቀህአለ።”1ሳሙ15፥23

♥ “እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ወደእግዚአብሔርቅረቡወደእናንተምይቀርባል።እናንተኃጢአተኞች፥እጆቻችሁንአንጹ፤ሁለትአሳብምያላችሁእናንተ፥ልባችሁንአጥሩ።”ያዕ4፥7-8

Page 79: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

69

ምዕራፍ 5የአማኞች ስልጣንና የመውጊያ መሳሪያዎች

♥ “እነሆ፥እባቡንናጊንጡንትረግጡዘንድ፥በጠላትምኃይልሁሉላይሥልጣንሰጥቻችኋለሁ፥የሚጐዳችሁምምንምየለም።”ሉቃ10፥19

ሰው ክርስቶስ አዳኙና ጌታው መሆኑን አምኖ ከተቀበለ በኋላ ለሚኖረው ሕይወት ምሉዕነት የእግዚአብሔር ኃይል በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ደጋፊው ይሆናል። ይህም በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሕይወቱ ውስጥ ሊያጋጥመው የሚችለውን መንፈሳዊ ውጊያ ለመቋቋም እንዲችል ያደርገዋል።

† ይህ ምዕራፍ አንድ አማኝ የተሰጠውን ስልጣን ምን እንደሆነ እንዲያውቅና ስልጣኑንበእምነትተቀብሎእንዴትመጠቀምእንዳለበትበጥቂቱያሳያል።

5.1 የአማኞች ስልጣንሀ ፍጥረታትን በሙሉ እንዲያስተዳድሩ አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ባህርይ በእስትንፋሱ አማካኝነት አስተላልፎልናል። በመሆኑም

ፍጥረታትን የመምራት ባህርይን ከእግዚአብሔር ተጋርተናል። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የነበረው የመጀመሪያው ዓላማ ምድርን እንዲገዛ ነበር። ወንድና ሴት አድርጎ ከፈጠራቸው በኋላ የሰጣቸው ትእዛዝ በምድር ላይ ያሉትን ፍጥረታት በሙሉ እንዲያስተዳድሩ ነበር። እግዚአብሔር ሰውን በአምሳሉ ሲፈጥር የእግዚአብሔርን ምስል እንዲያሳይ ብቻ ሳይሆን በተሰጠው ስልጣን በተፅዕኖ ምድርን እንዲመራ ነበር። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመስማታቸው ግን የዘላለም ሞት ሲፈረድባቸው ዳግመኛ ወደነበሩበት ቦታ እንዲመልሳቸው ተሰፋን በመስጠት ነበር። ይህም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣቱና ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት ራሱን መስዋዕት በማድረጉ ሲፈፀም የሰው ልጆች የተቀማነውን ስልጣን በእርሱ በማመን መልሰን ማግኘት እንችላለን። ከእነዚህም ስልጣናት መካከል አንዱ ጠላታችን ዲያብሎስንን የምንወጋበት ነው። እንደ ቃሉ በእምነት ከክርስቶስ ጋር በመንግሰተ ሰማይ በስልጣኑ ከእርሱ ጋር ተቀምጠናል፤ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ምድርንም እንመራለን።

Page 80: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

70 71

♥ “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንናየሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።እግዚአብሔርምሰውንበመልኩፈጠረበእግዚአብሔርመልክፈጠረውወንድእናሴትአድርጎፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንምሙሉአት፥ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉግዙአቸው።”ዘፍ1፥26-28

ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለመስማቱ ግን የዘላለም ሞት ተፈርዶበታል። ከእርግማኑም የተነሳ ምድርና ሌሎች ፍጥረታት ከሰው ልጆች ጋር የነበራቸው ተፈጥሯዊ መስተጋብር ልዩ የሆነ አቅጣጫን ለመያዝ በቅቷል። የምድር እሾህና አሜኬላን ማብቀልና የእንስሳትም በሰው ልጆች ላይ ማመጽ የዚህ እርግማን ነጸብራቅ ናቸው። የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታይ ማንነት ባይኖረነም እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ የበደሉን እዳ በልጁ ሞት ተክቶልናል።

♥ “የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው። መሬታዊው እንደሆነመሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው፥ ሰማያዊው እንደሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞእንዲሁናቸው።”1ኛቆሮ15፥47-49

♥ “የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ታስበውዘንድሰውምንድርነው?ትጐበኘውምዘንድየሰውልጅምንድርነው?ከመላእክትእጅግጥቂትአሳነስኸውበክብርናበምስጋናዘውድከለልኸው። በእጆችህምሥራሁሉላይሾምኸውሁሉንከእግሮቹበታችአስገዛህለት፥”መዝ8፥3-6

♥ “የሰማያትሰማይለእግዚአብሔርነውምድርንግንለሰውልጆችሰጣት።”መዝ115፥16

♥ “ኢየሱስምቀረበናእንዲህብሎተናገራቸው።ሥልጣንሁሉበሰማይናበምድርተሰጠኝ።እንግዲህሂዱናአሕዛብንሁሉበአብበወልድናበመንፈስቅዱስስምእያጠመቃችኋቸው፥ያዘዝኋችሁንምሁሉእንዲጠብቁእያስተማራችኋቸውደቀመዛሙርትአድርጓቸውእነሆምእኔእስከዓለምፍጻሜድረስሁልጊዜከእናንተጋርነኝ።”ማቴ28፥18-20

♥ “ክርስቶስንምከሙታንሲያስነሣውከአለቅነትናከሥልጣንምከኃይልምከጌትነትምሁሉበላይናበዚህዓለምብቻሳይሆንነገርግንሊመጣባለውዓለምደግሞከሚጠራውስምሁሉበላይበሰማያዊስፍራበቀኙሲያስቀምጠውበክርስቶስባደረገውሥራየብርታቱጉልበት ይታያል።”ኤፌ1፥20-21

♥ “በሚመጡዘመናትምበክርስቶስኢየሱስለእኛባለውቸርነትከሁሉየሚበልጠውንየጸጋውንባለጠግነትያሳይዘንድ፥ከእርሱጋርአስነሣንበክርስቶስኢየሱስምበሰማያዊስፍራከእርሱጋርአስቀመጠን።”ኤፌ2፥6

• ክርስቶስበማንኛውምነገርላይሙሉስልጣንናሙሉኃይልአለው።

♥ “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይምጌትነትወይምአለቅነትወይምሥልጣናት፥በሰማይናበምድርያሉትሁሉበእርሱተፈጥረዋልናከፍጥረትሁሉበፊትበኵርነው።ሁሉበእርሱናለእርሱተፈጥሯል።እርሱምከሁሉበፊትነውሁሉምበእርሱተጋጥሞአል።”1ኛቆላ1፥15-17

♥ “ልጆችሆይ፥እናንተከእግዚአብሔርናችሁአሸንፋችኋቸውማል፥በዓለምካለውይልቅበእናንተያለውታላቅነውና።”1ኛዮሐ4፥4

Page 81: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

71

ለ) በአጋንንት ሁሉ ላይ ስልጣንና ደዌንም ይፈውሱ ዘንድአጋንንትና ጭፍሮቻቸው በሰዎች ልጆች ላይ ምንም ዓይነት ስልጣን የላቸውም። የአጋንንት

አሰራር በእኛ ላይ ምንም ጉልበት የለውም። ይልቁኑም እኛ በክርስቶስ ስም ለምናምን እንደ ሀሳቡም ለተጠራን የአጋንንትና የጭፍሮቻቸውን ስራ እናፈራርስ ዘንድ ስልጣኑ ተሰጥቶናል። ዳንኤል በበደሉ ሳይሆን በጸሎት ከአምላኩ ጋር በመተዋወቁ ጠላቱ ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል ቢያስፈርድበትም ይህ የእግዚአብሔር ሰው ግን ከአንበሶቹ ጋር ያለምንም ችግር ማደር መቻሉ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው።

♥ አሥራ ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤ ሉቃ 9፥1

እኛ የክርስቶስ አካሎች ነን። ለዛም ነው ራሱ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎቼ ናችሁ (ዮሐ 15፥5)” ብሎ የተናገረው። የታላቁ ንጉስ አካላት መሆናችን የእርሱን ኃይል እንድንላበስ ያደርገናል። የጌታ ኃይል በመስቀል ላይ ተገልጿል።

♥ “እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል። አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድልበመንሣትበእርሱእያዞራቸውበግልጥአሳያቸው።”ቆላ2፥14-15

እኛንም በጠላት ኃይል ላይ ድልን እንድንጎናጸፍ ሲነግረን እንዲህ ይላል፤ ♥ “እነሆ፥እባቡንናጊንጡንትረግጡዘንድ፥በጠላትምኃይልሁሉላይሥልጣንሰጥቻችኋለሁ፥

የሚጐዳችሁምምንምየለም።”ሉቃ10፥19

♥ “በእርሱየመለኮትሙላትሁሉበሰውነትተገልጦይኖራልና።ለአለቅነትናለሥልጣንምሁሉራስበሆነበእርሱሆናችሁተሞልታችኋል።”ቆላ2፥9-10

እርግጥ ነው ኃይላችንና ጉልበታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። እኛ በራሳችን ምንም ጉልበት የሌለን ልፍስፍሶችና ደካማዎች ነን። አንድ ቅርንጫፍ ከዋናው ግንድ ተለይቶ እሳት ማቀጣጠያ ከመሆን በቀር ምን እርባና አለው? መልሱ ምንም ነው። እኛም ከወይኑ ግንድ የተለየን ቅርንጫፎች ከሆንን እንደዚሁ ነው። በጠላት ኃይል ላይ ድልን ልንጎናጸፍ አንችልም። ይህ እውነታ የተገለጠለት ነብዩ ዳዊት “አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሀለሁ (መዝ 18፥1)” ብሎ አመሰገነ። የእኛ ጉልበትና ኃይል የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ነው።

♥ “የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስክርስቶስጸጋከእናንተጋርይሁን።”ሮሜ16፥20

♥ ይህ ጸጋ ከእኛ ጋር ሲሆን ጦራችንና ጋሻችን ይሆናል። “በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜአትቃጠልም፥ነበልባሉምአይፈጅህም።”ኢሳ43፥2

Page 82: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

72 73

ሐ ማሰርና መፍታት ♥ “ወይስሰውአስቀድሞኃይለኛውንሳያስርወደኃይለኛውቤትገብቶእቃውንሊነጥቀውእንዴት

ይችላል?ከዚያምወዲያቤቱንይበዘብዛል።”ማቴ12፥29

♥ “የመንግሥተሰማያትንምመክፈቻዎችእሰጥሃለሁበምድርየምታስረውሁሉበሰማያትየታሰረይሆናል፥በምድርምየምትፈታውሁሉበሰማያትየተፈታይሆናል።”ማቴ16፥19

5.2 መንፈሳዊ ማሰልጠኛ

አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወቱ ውስጥ የሚያጋጥመውን ችግሮችና ውጊያዎች በድል ለማለፍ መበርታት አለበት። ለመበርታት ደግሞ ከማን ጋር እንደምንዋጋና እንዴት እንደምንዋጋ ማወቅና መሰልጠን አለብን። ይህም ጌታን በመስማትና ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ነው።

♥ “እግዚአብሔርአምላኬይባረክ፥ለእጆቼሰልፍን፥ለጣቶቼምዘመቻንየሚያስተምር…፤”መዝ144፥1

5.2.1 ክርስቶስ ከጠላት ጋር እንድንዋጋ ያሰተምረናል፤ ያሰለጥነናልየሰይጣን ውጊያ ስልት ልዩ ልዩ ነው። የራሳችንን ስጋዊ ስሜት በመቀስቀስ፣ ጓደኞቻችንን

በክፋት በማስነሳት፣ በስራ ቦታ በመቃወም፣ በመንገዳችን መሰናከያ በማስቀመጥ እና በምንወዳቸው ነገሮች ሁሉ ይዋጋናል። ምናልባትም እየተዋጋን መሆኑ ሳይገባንና እየጣለን መሆኑን ሳናውቅ ወደ ሀሳቡ ሊወስደን ይችላል። ነገር ግን በአሸናፊው በክርስቶስ በመማርና በመሰልጠን፣ አካሄዱን ሁሉ በመረዳት ድልን እንቀዳጃለን። ለዛም ነው መዝሙረኛው ዳዊት “እግዚአብሔር ይባረክ፣ ለእጆቼ ሰልፍን፣ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር…(መዝ 144፥1)” ብሎ ያመሰገነው።

♥ “ይሄዱባት ዘንድ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ወይም አይጠብቁ እንደ ሆነ እስራኤልንእፈትንባቸውዘንድ፥ኢያሱበሞተጊዜከተዋቸውአሕዛብአንዱንሰውእንኳከእንግዲህወዲህከፊታቸው አላወጣም። እግዚአብሔርም እነዚህን አሕዛብ አስቀረ፥ ፈጥኖም አላወጣቸውም፥በኢያሱምእጅአሳልፎአልሰጣቸውም።”መሳ2፥21-23

♥ “ከከነዓናውያንም ጋር መዋጋት ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ፥ በፊትምሰልፍን ያልለመዱ የእስራኤል ልጆች ትውልድ መዋጋትን ያውቁና ይማሩ ዘንድ እግዚአብሔርያስቀራቸውአሕዛብእነዚህናቸው።”መሳ3፥1-2

5.2.2 ክርስቶስ በማበረታታት ያግዘናልእግዚአብሔር የሰይጣን ውጊያ ሲበረታ እንዳንደክም የሚያበረታን መንፈሱን ልኮልናል። ንስር

ያረጀ አካሉን በአዲስ እንደሚተካ እኛም ዘወትር በእርሱ ቅዱስ መንፈስ እንበረታለን፤ ጉልበታችንንም እናድሳለን። የሚከብደንም ነገር አይኖርም።

♥ “ኃይልንበሚሰጠኝበክርስቶስሁሉንእችላለሁ።”ፊል4፥13

Page 83: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

73

እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው ወደ ከነዓን ሲጓዙ የእግዚአብሔር እርዳታ ተለይቷቸው ቢሆን ኖሮ ተመልሰው ራሳቸውን ለፈርዖን አሳልፈው በሰጡ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን እውነታ ስለሚያውቅ ከፊት ለፊታቸው ጥልቅ የሆነና በሰፊው የተንጣለለ ውኃ በገጠማቸው ጊዜ ውኃውን ልክ እንደ ግድግዳ ለሁለት ከፍሎ በደረቅ እንዲሻገሩ በማድረግ እንዲሁም የፈርዖንን ሰራዊት በዚያ ውኃ ውስጥ በማስጠም ሲያድናቸው፣ በዚያ እልም ባለው በረሀ ከደረቅ ድንጋይ ውስጥ ውኃ እያፈለቀ እያጠጣቸው፣ መናን እያወረደ እየመገባቸው፣ ወደፊት ይጓዙ ዘንድ እያበረታቸው፣ እሱን ብለው የወጡ ሕዝቡን በሰላም እንዲሄዱ አስችሏቸዋል።

♥ “እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ፥ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።እጆቼንሰልፍያስተምራል፤በክንዴምየናስቀስትእገትራለሁ።”2ኛሳሙ22፥34-35

በክርስቶስ ስናምንና ከእርሱ ጋር አንድ ስንሆን በሰማያዊ ቦታ በስልጣን እንቀመጣለን። ሁሉ ነገራችንን በአዲስ ሁኔታ መመልከት እንጀምራለን። የደከሙ የሚመስለን ማንኛውንም አካላት ያበረታልናል። ለአብነት ያህል እጆች፥ ጥንካሬን ይወክላሉ፤ ነሀስ ደግሞ የእግዚአብሔርን ፃድቅ ፈራጅነት ይወክላል። ኢየሱስ በጠላት ስራ ላይ በሙሉ ስልጣን እንድንፈርድ ስልጣን ሰጥቶናል። እርሱን በምንታዘዝበት ጊዜ ደግሞ ይህ ስልጣን መስራት ይጀምራል። በክርስቶስ በኩል ትክክል ባልሆኑ ነገሮች ላይ በፅድቅ እንድንፈርድ ስልጣን ተሰጥቶናል።

♥ “ከኃጢአትበቀርበነገርሁሉእንደእኛየተፈተነነውእንጂ፥በድካማችንሊራራልንየማይችልሊቀካህናትየለንም።”ዕብ4፥15

5.2.3 መልካሙን ጦርነት እንድንዋጋ ያስችለናልእርግጥ ነው በዓለም ላይ መልካም ጦርነት እንዲሁም መጥፎ ሰላም ኖሮ አያውቅም። ለዛም

ነው ሀገራት ሁሉ ወደ ጦርነት ላለመግባት የሚደራደሩትና አስታራቂ መፍትሔን የሚያፈላልጉት። ከሰይጣን ጋር ጦርነት ላለማድረግ ግን መደራደሪያው አንድና አንድ ብቻ ነው። እሱም የጥፋት ልጅ መሆን። እኛ የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችን ወደ ጦርነት መግባት አማራጭ የሌለው ነው። የዚህ ጦርነት መልካም የመባሉም ምክንያት የጦርነቱ አካል መሆን ነፍስን የሚያጠፋ ሳይሆን የሚያተርፍ በመሆኑ፣ የሚሰብር ሳይሆን የሚጠግን በመሆኑ፣ የሚያከስር ሳይሆን የሚያተርፍ በመሆኑ፣ የሚያደክም ሳይሆን የሚያበረታ በመሆኑ እና መሸነፊያ ሳይሆን ድልን መቀዳጃ በመሆኑ ነው።

♥ “ጢሞቴዎስልጄሆይ፥አስቀድሞስለአንተእንደተነገረውትንቢት፥በእርሱመልካምጦርነትትዋጋዘንድይህችንትእዛዝአደራእሰጥሃለሁ።”1ኛጢሞ1፥18

ስለዚህ ማንም ቢሆን ለዚህ መልካም ጦርነት ታጥቆ መነሳት ይኖርበታል። ነገር ግን “እኔ ደካማ ነኝ፥ ሰይጣንን ታግዬ መጣል አይቻለኝም” አይበል። ምክንያቱም የመውጊያ ጦራችን ስጋዊ አይደለምና። አዎ! እኛ የምንዋጋው የሰይጣንን ስራ ልክ እንደ ሸክላ የሰባበረው ሲኦልንም መዝብሮ ባዶ ማድረግ በቻለው በክርስቶስ ደምና ጸጋ ነውና።

♥ “የጦር እቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉእናፈርሳለንለክርስቶስለመታዘዝአዕምሮንሁሉእንማርካለን፥”2ኛቆሮ10፥4-5።

♥ “እነርምከበጉደምየተነሣከምስክራቸውምቃልየተነሣድልነሡት፥ነፍሳቸውንምእስከሞትድረስአልወደዱም።”ራዕ12፥11

Page 84: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

74 75

በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በመመስረት ብዙውን ጊዜ ስለ መልካሙ ውጊያ ስናወራ ይበልጥ ስለ እምነት አብሮ ይነሳል። ክርስቶስ የጴጥሮስን የልብ እምነት በማየቱ ጴጥሮስ ካሰበው በላይ ባርኮታል። አማኞች እግዚአብሔርን ባመንን ልክ ስልጣናችንም ያንን ያህል ነው። የክርስትና ሕይወት እረፍት የለሽ የትግል ኑሮ በሆነበት በዚህ ዘመን እምነት የክርስቶስ ወታደሮች ሆነን በፅናት እንድንቆም፣ ሊለካ የማይችል ቦታ ይይዛል። ተስፋ መቁረጥና የክርስቶስ ቅንዓት አለመኖር ከኢየሱስ ቤተሰቦች መካከል መወገድ ስንፍናዎች ናቸው። በመጨረሻ ወደ ሰማያዊው ቤታችን ብንሔድ ከመቆጨት ያድነናል። ክርስቶስ እምነታችን ነው። እምነታችንን በሙሉ በእርሱ ላይ ከጣልን እንደ እርሱ ፍላጎት ትግላችንን በድል እንጨርሳለን።

5.3 ከእግዚአብሔር የሆኑ መንፈሳዊ የጦር እቃዎች

የእግዚአብሔርን የጦር እቃዎች (ክርስቶስንም ጨምሮ) በመልበስ ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን። በተጨማሪም እኛ የእግዚአብሔር መሳሪያዎች ነን፤ እግዚአብሔር ጠላትን የምንዋጋበት ሙሉ ትጥቅ ሰጥቶናል። መንፈስ ቅዱስ የሰይጣንን ስራ ለማፍረስ ቃሉን ወደ ሚያስፈልገው መሳሪያ መቀየር ይችላል።

♥ “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማዓለምገዦችጋርበሰማያዊምስፍራካለከክፋትመንፈሳውያንሠራዊትጋርነውእንጂ።”ኤፌ6፥11-12

♥ “አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ በአንቺም መንግሥታትንአጠፋለሁ።”ኤር51፥20

♥ “በውኑቃሌእንደእሳት፥ድንጋዩንምእንደሚያደቅቅመዶሻአይደለችምን?ይላልእግዚአብሔር፦”ኤር23፥29

† በኤፌ6፥14-18እንዲሁምበተለያዩየመጽሐፍቅዱስክፍሎችውስጥእንደጦርእቃዎችልንጠቀምባቸውየምንችላቸውንነገሮችተፅፎልናል፦

i. የእውነት ቀበቶ፥

እውነትን ተናጋሪዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው። ከሀሰተኛ ጋር አይተባበሩም። ጌታ ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። (ዮሐ 14፥6)” ብሏል። በተቃራኒው ዲያብሎስ የሀሰት አባት ተብሏል (ዮሐ 8፥44)። ስለዚህ እውነትን የታጠቀ ዲያብሎስ የካበውን የሀሰት ካብ የሚያፈራርስበትን መዶሻ ይዟል ማለት ነው። ከአምላካችን ከእግዚአብሔር በቀር ማንንም አምላክ ነው ቢሉን ይህንን የእውነት ቃል በእምነት መናገር እንችላለን።

♥ “እኔእግዚአብሔርነኝከእኔምሌላማንምየለምከእኔምበቀርአምላክየለምበፀሐይመውጫእና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግንአላወቅኸኝምእኔእግዚአብሔርነኝ፥ከእኔምሌላማንምየለም።”ኢሳ45፥5

ii. የፅድቅ ጥሩር፦ ኢየሱሰ ፅድቃችን ነው።

Page 85: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

75

iii. እኛ በራሳችን ጽድቅ የለንም። ♥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የሚያስመካ ስራን አልሰራንም። ነገር ግን ከነጉድለታችን የሚቀበለን

የጽድቃችንን መመኪያ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም የፈሰሰልን ንጹህ ደሙ የጽድቃችንማህተምነውናእሱንመያዝአለብን።“እግዚአብሔርየጽድቅጋሻዬነው…”መዝ7፥10

♥ “ጽድቅንምእንደጥሩርለበሰ፥በራሱምላይየማዳንንራስቍርአደረገየበቀልንምልብስለበሰ፥በቅንዓትምመጐናጸፊያተጐናጸፈ።”ኢሳ59፥17

iv. በሰላም ወንጌል መጫማት፥

† ወንጌልን ስንጫማ ጥሩ ተዋጊዎች መሆን እንችላለን። ነገር ግን ወንጌልን መጫማትቃሉን ማወቅን የሚያካትት ቢሆንም ቃሉን ልንለብሰው ወይም ልንዋሀደው ካልቻልንግን ጥቅም አልባ ይሆንብናል። ምክንያቱም ቃሉንማ ሰይጣንም ቢሆን ጌታን ለማሳሳትሲሞክርተጠቅሞበታል።ዛሬምቢሆንእኛንለማሳትናለመጣልይጠቀምበታል።ስለዚህቃሉበውስጣችንእንዲሰራመፍቀድይኖርብናል።ለዛምነውቃሉ“ይህንንመጽሐፍብላ“ያለው።

♥ “ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድያቀናል።”ሉቃ1፥79

v. የእምነት ጋሻ

† ብዙ ጊዜ ሰዎች እምነት የሚለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ይተረጉሙታል። ለመሆኑእምነት ምንድነው? እምነት ማለት የድርጅት አባል መሆን ማለት አይደለም። ክርስቶስለእኛበመስቀልላይያፈሰሰውንደምመቀበልማለትነው።ሕይወትየሚጀምረውከዚህነው።በሰማይምበምድርምእናምንበትዘንድያለንአንድብቻነው።ከእርሱበቀርሌላእምነትንየሚያመጣቢኖርእርሱየሞትአገልግሎትንያገለግላል።

♥ “እምነትህበእግዚአብሔርይሆንዘንድለአንተዛሬእነሆአስታወቅሁህ።”ምሳ22፥19

♥ “በሰላምእተኛለሁአንቀላፋለሁምአቤቱ፥አንተብቻህንበእምነትአሳድረኸኛልና።”መዝ4፥8

♥ እምነትበአንደበትብቻየሚገለጥሳይሆንየምናምንበትንነገርወደውስጣችንማስረጽነው።ይህእምነታችን ከዲያብሎስ ፍላጻ የምንሸሸግበት ጋሻችን፣ ራስ ራሱን የምንቀጠቅጥበት ጫማችን፣ከክርስቶስ ቤተሰቦች ጋር አንድነትን የምንመሰርትበት ማህበር፣ ከአምላካችን ጋር የምንገናኝበትመስመር፣ከውድቀታችንየምንነሳበትምርኩዝ፣ያላየናትንመንግስተሰማይየምናይበትመነጽር፣የዲያብሎስንስራየምናፈራርስበትመሳሪያችንነው።“በሁሉምላይጨምራችሁየሚንበለበሉትንየክፉውንፍላጻዎችሁሉልታጠፉየምትችሉበትንየእምነትንጋሻአንሡ።”ኤፌ6፥16

♥ “የእግዚአብሔርቃልቅንነውናሥራውምሁሉበእምነትነውና።”መዝ33፥4

♥ ማንምዓለምንሁሉቢያተርፍኑሮውምየምድራዊስኬትንጫፍቢነካነገርግንእምነትአልባቢሆን ምን ይጠቅመዋል? ጠቢቡ ሰለሞን እንደተናገረው “ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደመከተልነው።”መክ1፥14

♥ “በዓለምያሉትወንድሞቻችሁያንመከራበሙሉእንዲቀበሉእያወቃችሁበእምነትጸንታችሁተቃወሙት።”1ኛጴጥ5፥9

Page 86: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

76 77

vi. የመዳን ራስ ቁር

† የራስ ቁር ሰዎች በተለያየ ምክንያት ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸውለመከላከያተብሎየሚሰራ፣ጭንቅላትንከጉዳትየሚጠብቅብረትለበስመከላከያነው።የክርስትናው የራስ ቁርም ይህንን ገላጭ ምሳሌ በመከተል መንፈስ ለሆነው ጠላታችንመንፈሳዊ የራስ ቁር መከላከያ እናጠልቃለን። ይህ መንፈሳዊ መሳሪያ የዲያብሎስ ጦርቢወጋንእንኳንእንዳይጥለንይጠብቀናል።

♥ “እኛግንከቀንስለሆንን፥የእምነትንናየፍቅርንጥሩርየመዳንንምተስፋእንደራስቁርእየለበስንበመጠንእንኑር፤”1ኛተሰ5፥8

vii. የመንፈስ ሰይፍ፥-

† ዲያብሎስመንፈስእንደመሆኑመጠንየሚዋጋንምበመንፈስእንጂስጋዊጦርበማዝመትአይደለም።ስለዚህየእኛምየጦርእቃቁሳዊጋሻናቁሳዊጦርአይደሉም።ረቂቅየሆነውንየዲያብሎስንጦሮችየሚያይመነጽር፣ወደእኛየሚወነጨፉትንየርኩሳንመናፍስትጦሮችየሚመክት መንፈሳዊ ጋሻ እንዲሁም ድል የምናደርግበት መንፈሳዊ ጦር ያስፈልገናል።እሱምየእግዚአብሔርቃልነው።

♥ “የእግዚአብሔርቃልሕያውነውና፥የሚሠራም፥ሁለትምአፍካለውሰይፍሁሉይልቅየተሳለነው።”ዕብ4፥12

viii. የእግዚአብሔር ክብር

† ክብር ከማፍቀር ይጀምራል። ያለ ፍቅር ግን ክብር የለም። ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅርየሚገለጸውደግሞአብረውንያሉእህትወንድሞቻችንንበማፍቀር፣መጠጊያአልባለሆኑሰዎች መጠጊያ በመሆን፣ ለፍጥረት ርህራሄ ሲኖረን፣ ጭካኔንን ከሕይወታችን ስናርቅነው። “ሰው አያየንም” ብለን የምንሰራቸውን የክፋት ስራዎችና ኃጢአት “በአምላኬበእግዚአብሔርፊትእሰራዘንድይህከእኔይራቅ”በማለትነው።ይህክብርየሰይጣንደባበእኛላይአቅምእንዳይኖረውዋስትናችንነው።

♥ “የእግዚአብሔርምክብርበኋላህሆኖይጠብቅሃል።”ኢሳ58፥8

♥ “እግዚአብሔርይቀድማችኋልና፥የእስራኤልምአምላክይከተላችኋልና…”ኢሳ52፥12

ix. የብርሃን ጋሻ ጦር

† ጨለማበብርሀንይገፈፋል።ስለዚህየጨለማውንአሰራርልንገልጥእንዲሁምበመንፈሳዊብርሃንልንተካውየብርሃንንጋሻመያዝይገባናል።ጌታኢየሱስ“እኔየዓለምብርሃንነኝያለእኔምንምልታደርጉአትችሉም(ዮሐ8፥12፣9፥5)”እንዳለየጨለማንስራየምናፈራርስበትየብርሃንየጦርእቃችንጌታነው። ♥ “በእኔየሚያምንሁሉበጨለማእንዳይኖርእኔብርሃንሆኜወደዓለምመጥቻለሁ።”ዮሐ12፥4

Page 87: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

77

♥ “እግዚአብሔርብርሃንነውጨለማምበእርሱዘንድከቶየለምየምትልይህችናት።”1ኛዮሐ1፥5

♥ “ሌሊቱአልፎአል፥ቀኑምቀርቦአል።እንግዲህየጨለማውንሥራአውጥተንየብርሃንንጋሻጦርእንልበስ።”ሮሜ13፥12

♥ “ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥጌታእስኪመጣድረስጊዜውሳይደርስአንዳችአትፍረዱበዚያንጊዜምለእያንዳንዱምስጋናውከእግዚአብሔርዘንድይሆናል።”1ኛቆሮ4፥5

♥ “ከእርሱምየሰማናትለእናንተምየምናወራላችሁመልእክት፥እግዚአብሔርብርሃንነውጨለማምበእርሱዘንድከቶየለምየምትልይህችናት።”1ኛዮሐ1፥5

x. የእግዚአብሔር ቃል (ኢየሱስ)

† ቃሉ ለመንገዳችን መብራት፣ የሕይወት እንጀራ፣ መዶሻ፣ እሳት እና ሰይፍ በመባልተገልጿል። እግዚአብሔር በቃሉ አማካኝነት ጠላት ላይ አዋጅ እንድናወጣና ጠላትንእንድናዝስልጣንሰጥቶናል።

♥ “ነገርንምትመክራለህ፥እርሱምይሳካልሃልብርሃንምበመንገድህላይይበራል።”ኢዮ22፥28

(1) ቃሉ ሕይወት ነው

† የእግዚአብሔርቃልእንደዓለማዊመጽሐፍበምድርላይስለሚቀርናስለሚያልፍእውቀትየሚነግረንአይደለም።ልብወለድተብለውእንደሚጻፉትምጊዜያዊደስታወይምሽብርእንዲሰማን አድርጎ የሚያልፍም አይደለም። እንደ ነገስታትና መሳፍንት ቃልም በሹመትዘመን የሚከበር ሲወርዱ ደግሞ አብሮ የሚወርድ አይደለም። ሕይወት ነው፤ ለዛውምዘላለማዊ የሆነ። የሚያምኑበትና እንደ ሊድያ (ሐዋ 16) ልቦናቸውን ክፍት አድርገውየሚሰሙትሁሉሕይወትንያገኛሉ።

♥ “ሕይወትንየሚሰጥመንፈስነውሥጋምንምአይጠቅምምእኔየነገርኋችሁቃልመንፈስነውሕይወትምነው”ዮሐ6፥63

(2) የሚያጠግብ እንጀራ

† የእግዚአብሔር ቃል የሚያጠግብ እንጀራ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው? የዚህ አባባልትርጉም ስጋ የሚያመጣብንን ውጊያ እንድንንቅ ያደርገናል ማለታችን ነው። ብዙ ሰዎችየሚወድቁበት የውጊያ ስፍራ ሆድ ነው። ከአዳም ጀምሮ የነበረው መሰናክል ዲያብሎስኢየሱስ ክርስቶስንእንኳንሳይቀር በራበውሰዓትበእንጀራፈትኖታል። ኢየሱስ ክርስቶስግን የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቃል ሲኖር የስጋ ጊዜያዊ መራብ ምንም እንዳልሆነተናግሯል።የእግዚአብሔርቃልበመንፈሳዊእርካታናጥጋብያኖረናል።ቃሉንለሚቀበሉትሁሉለዓለማዊምግብናመጠጥብለውአምላካቸውንእንዳይተዉየሚያደርግመንፈሳዊእርካታነውልንለውእንችላለን።በሰማርያሊያልፍግድየሆነበትናለሳምራዊቷሴትበቃሉስለሚገኝዘላለማዊየሕይወትውኃየነገራትእረፍትንእንድታገኝነበር።

♥ “ኢየሱስም፦ሰውበእግዚአብሔርቃልሁሉእንጂበእንጀራብቻአይኖርምተብሎተጽፎአልብሎመለሰለት።ዲያብሎስምረጅምወደሆነተራራአውጥቶየዓለምንመንግሥታትሁሉበቅጽበትአሳየው።ዲያብሎስም፥ይህሥልጣንሁሉክብራቸውምለእኔተሰጥቶአልለምወደውምለማንም

Page 88: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

78 79

እሰጠዋለሁናለአንተእሰጥሃለሁ ስለዚህአንተበእኔፊትብትሰግድ፥ሁሉለአንተይሆናልአለው።ኢየሱስምመልሶ፦ለጌታለአምላክህስገድእርሱንምብቻአምልክተብሎተጽፎአልአለው።”ሉቃ4፥4-8

♥ “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”ዮሐ1፥1

♥ “የመዳንንምራስቁርየመንፈስንምሰይፍያዙእርሱምየእግዚአብሔርቃልነው።”ኤፌ6፥17

(3) ሰይፍ ነው

† የእግዚአብሔር ቃል ሰይፍነቱ በሁለት መልኩ ነው። የመጀመሪያው ሰይፍ ራስንከዓለማዊነትና ከረከሰ መንገድ በመቁረጥ የሚነጥል መሆኑ ነው። ክርስቲያኖች ምንምእንኳንበዓለምላይየምንኖርብንሆንምዓለምከምታሰናዳውየዓመፅድግስግንየተለየንነን። ከማያምኑና ለስጋቸው ብቻ ከአደሩ አካላት የለየንና ወደ እግዚአብሔር ማህበርያሰባሰበን የቃሉ ሰይፍ ነው። ሰይፍ የተባለበት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሰይጣንንተዋግተንአሸናፊየምንሆንበትበመሆኑነው።

♥ “የእግዚአብሔርቃልሕያውነውና፥የሚሠራም፥ሁለትምአፍካለውሰይፍሁሉይልቅየተሳለነው፥ነፍስንናመንፈስንምጅማትንናቅልጥምንምእስኪለይድረስይወጋል፥የልብንምስሜትናአሳብይመረምራል”ዕብ4፥12

♥ “በደምምየተረጨልብስተጐናጽፎአል፥ስሙምየእግዚአብሔርቃልተብሎአል።”ራዕ19፥13

xi. የእግዚአብሔር ስም

† የእግዚአብሔር ስም ከስሞች ሁሉ የበላይ የሆነ ስም ነው። ይህ ማለት በስሙ ብቻታላቅና ድንቅ የሚሰራበት የተመረጠ ስም ነው። ብቸኛና ታላቅ ስም ነው። የታዋቂሰዎችምስምምሆነየነገስታትስምምንምያህልገናናቢሆንእንኳንስማቸውምንምነገርሊያደርግአይችልም።የገናናውአምላክስምግንአጋንንትንአቅማቸውንየሚሰልብነው።የእግዚአብሔርስምለሚደገፉትደጋፊነው፤ለሚያምኑትሰላምነው፤ተስፋለሚያደርጉትእረፍትነው፤ለሚጠሩትሁሉንቻይነው።

♥ “ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፥ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት።”ሉቃ10፥17

† ይህስምጎባጦችንያቀና፣ዕውራንንምያበራ፣ሙታንንምያስነሳስምነው።በሐዋ3፥6ላይስናነብጴጥሮስመንገድዳርቁጭብሎየሚለምነውንሰው“የምሰጥህገንዘብየለኝምበጌታስምተነስናተመላለስ”ብሎከተወለደጀምሮሽባየነበረውንሰውዘሎእንዲቆምአስችሎታል።ቃሉእንደሚናገረውወዲያውቁርጭምጭሚቱምበረታ፤ዘሎምቀጥብሎቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ወዲያና ወዲህም እየሄደ እየዘለለም የእግዚአብሔርን ስምእንዳመሰገነእንረዳለን።ይህንንያክልታላላቅተአምራትንየሚያደርግስምአንድብቻነው፤እሱምየጌታችንየኢየሱስክርስቶስስምነው።

♥ “በአንተጠላቶቻችንንእንወጋቸዋለን፥በስምህምበላያችንየቆሙትንእናዋርዳቸዋለን።”መዝ44፥5

♥ “ያመኑትንምእነዚህምልክቶችይከተሉአቸዋልበስሜአጋንንትንያወጣሉበአዲስቋንቋይናገራሉ

Page 89: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

79

እባቦችንይይዛሉ፥”ማር16፥17

♥ “ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥”ፊል2፥10

xii. የኢየሱስ ደም ♥ “እነርሱምከበጉደምየተነሣከምስክራቸውምቃልየተነሣድልነሡት፥ነፍሳቸውንምእስከሞት

ድረስአልወደዱም።”ራዕ12፥11

♥ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው።እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል። አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድልበመንሣትበእርሱእያዞራቸውበግልጥአሳያቸው።”ቆላ2፥14-15

xiii. የእግዚአብሔር እሳት

† እሳት ለሰው ልጆች ሕይወት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት ግኝቶች አንዱ ነው። እሳትከብርሃንነት አንስቶ ምግብን እስከማብሰል ድረስ ጥቅም ይሰጣል። ሲበዛም ያቃጥላል።ማቃጠሉምበሁለቱምጎኖች፣በጥቅምምበጉዳትምሊገለፅይችላል።በዓለምአብዛኛውክፍል ላይ ሰዎች እሳትን ቁስል እንኳን እንዲድን ይጠቀሙበታል። የእግዚአብሔርምእሳት እንደዚሁ ነው። የእግዚአብሔር እሳት ለእኛ ክርስቲያኖች ብርሃን ከመሆን ባሻገርፍቅሩን፣አዳኝነቱን፣ጥበቃውን፣ሁሉንቻይነቱን፣ልጆቹንማንፃትናመቀደሱንሲያመላክትለኃጢአተኞችደግሞማስፈራቱን፣ቁጠኝነቱንእንዲሁምቅጣቱንይገልፃል።

♥ “የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ፥ እጄም ፍርድን ትይዛለች፥ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ለሚጠሉኝምፍዳቸውንእከፍላለሁ።”ዘዳ32፥41

♥ “እሳትበፊቱይሄዳል፥ጠላቶቹንምበዙሪያውያቃጥላል።”መዝ97፥3

♥ “እነሆ፥ፍሙንበወናፍየሚያናፋለሥራውምመሣሪያየሚያወጣብረትሠሪንእኔፈጥሬአለሁየሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ። በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንምበፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ጽድቃቸውምከእኔዘንድነው፥ይላልእግዚአብሔር፦”ኢሳ54፥16-17

♥ “ስለዚህምየሠራዊትጌታእግዚአብሔርእንዲህይላል፦በዚህቃልተናግራችኋልናእነሆ፥በአፍህውስጥቃሌንእሳትይህንምሕዝብእንጨትአደርጋለሁ፥ትበላቸውማለች።”ኤር5፥14

♥ “በውኑቃሌእንደእሳት፥ድንጋዩንምእንደሚያደቅቅመዶሻአይደለችምን?ይላልእግዚአብሔር፦”ኤር23፥29

♥ “እኔበዙሪያዋየእሳትቅጥርእሆንላታለሁ…”ዘካ2፥5

xiv. አምልኮና ምስጋና

† ዓለማችንበፍላጎቶችየተሞላችናት።አንዱንስናሳካሌላውይጎድልብናል።ስለሆነምያሉንንወይምየተሰጡንብዙነገሮችሳሉትኩረታችንየሌለንነገሮችላይይሆናል።ስለዚህጸሎትሰንፀልይ ከልመና በቀር የማመስገን ልምድ እንዳናዳብር እንሆናለን። እዚህ ጋር ማንሳትያለብንጥያቄዎችአሉ።“ጌታንተመስገንልንልምንምክንያትአለን?ጤነኛእጅናእግርአለን? ውስጣችን ጤናማ ነውን? ሕይወታችንስ እጅግ የተጎሳቆለ፣ ለእኛ የሚሆን ትንሽ

Page 90: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

80 81

ነገር ያጣን ነን? የሚወዱን ቤተሰቦችና ጓደኞችስ አሉን? የምንበላው አጥተን ጾማችንንእናድራለን?የምንለብሰውአጥተንራቁታችንንእየሄድንነውን?የሚጠለሉበትንአጥተውየጎዳና ተዳዳሪ የሆኑትን ስናይ ምን ይሰማናል? የዓይናቸውን ብርሃን አጥተው ቀኑጨለማየሆነባቸውንስናይስስለራሳችንምንእናስባለን?በእውኑእግዚአብሔርንይህንንአድርገህልኛልና አመሰግንሃለሁ ለማለት ምክንያት እናጣለን? ከቃላት ባለፈ ማመስገንናመዘመርበራሱበጠላቶቻችንላይድልንእንድንቀዳጅእንደሚያስችልእናውቃለን?”

♥ “ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞዓብ ልጆችበሴይርምተራራሰዎችላይእግዚአብሔርድብቅጦርንአመጣባቸውእነርሱምተመቱ።”2ኛዜና20፥22

♥ “ቅዱሳን በክብር ይመካሉ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። የእግዚአብሔር ምስጋናበጕሮሯቸውነውሁለትአፍያለውምሰይፍበእጃቸውነው፥በአሕዛብላይበቀልንበሰዎችምመካከልቅጣትንያደርጉዘንድንጉሦቻቸውንበሰንሰለት፥አለቆቻቸውንምበእግርብረትያስሩዘንድየተጻፈውንፍርድያደርጉባቸውዘንድ።ለቅዱሳንሁሉይህችክብርናት።ሃሌሉያ።”መዝ149፥5-9

xv. የመንፈስ ቅዱስ ቅባትና ስጦታዎች

† የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የተለያዩ ናቸው። በመድረክ ላይ ቆሞ የሚሰብክ ሰባኪ፣ግለሰብን ቀርቦ የሚመክር መካሪ፣ ተስፋ በመቁረጥ ላይ ላለ ሰው የተስፋን መንገድየሚያሳይ ምእመን፣ ባለው ጸጋ ቤተክርስቲያንን የሚመራ ምሁር፣ እንደ ልድያ የልቡንደጅ ወለል አድርጎ ከፍቶ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ግለሰብ፣ ዘወትር ለአገልግሎትራሳቸውን የሚሰጡ ዲያቆናት፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ጸጋን ተቀብሏል። ከስጦታዎችምመካከልየተሸበረናያዘነልብንማጽናናትአንዱነው።ምንምእንኳንጠላትየሚውጠውንፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችን ቢዞርም መንፈስ ቅዱስ ያጽናናናል፤ ያበረታታናል።ሌላውበመንፈስቅዱስየምናገኘውስጦታፈተናንየምናልፍበትናጠላትንየምናሸንፍበትኃይልንነው።

♥ “መልሶም፥ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልናበብርታትአይደለም፥ይላልየሠራዊትጌታእግዚአብሔር፦”ዘካ4፥6

♥ “እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴምመንፈስንናኃይልንበመግለጥነበረእንጂ፥በሚያባብልበጥበብቃልአልነበረም።”1ኛቆሮ2፥4

♥ “…መንፈስቅዱስበእናንተላይበወረደጊዜኃይልንትቀበላላችሁ፥”ሐዋ1፥8

♥ “እንዲሁምደግሞመንፈስድካማችንንያግዛል፤እንዴትእንድንጸልይእንደሚገባንአናውቅምና፥ነገርግንመንፈስራሱበማይነገርመቃተትይማልድልናል፤”ሮሜ8፥26

† ሌሎችድንቅድንቅነገሮችንየምናደርግበትንጥበብምይሰጠናል።

♥ “ለአንዱጥበብንመናገርበመንፈስይሰጠዋልና፥ለአንዱምበዚያውመንፈስእውቀትንመናገርይሰጠዋል፥ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤”1ኛቆሮ12፥8-10

Page 91: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

81

♥ “እናንተግን፥ወዳጆችሆይ፥ከሁሉይልቅበተቀደሰሃይማኖታችሁራሳችሁንለማነጽእየተጋችሁበመንፈስቅዱስምእየጸለያችሁ፥…”ይሁ1፥20

xvi. ጾም

† ጾምስጋንእያደከምንሕይወታችንንየምንገነባበትመሳሪያነው።በመንፈሳዊሕይወታችንውስጥ የሚታየውን መዛል በአዲስ ጥንካሬ የምናድስበት ነው። ስለዚህ መጾማችንከምግብና ከውኃ ብቻ ሳይሆን ከክፋትም ጭምር ሊሆን ይገባል። ነገር ግን የኃጢአትንሃሳብ ሳናጠፋ ጾም እስኪያልቅ ብቻ በይደር ማቆየት የለብንም። አንዳንድ ሰዎች “አሁንጾምላይስላለሁነውእንጂአንተንፈርቼእንዳይመስልህ”በማለትእየጾሙእንኳንየጸብመንፈስንእንዳላስወገዱአመላካችንግግርንይናገራሉ።ይህንንዓይነቱንሁኔታጾምሳይሆንየረሃብአድማብንለውየተሻለይገልፀዋል።ለነፍስየሚሆንበረከትምአይገኝበትም።

♥ “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍርትለቅቁዘንድ፥የተገፉትንስአርነትትሰድዱዘንድ፥ቀንበሩንስሁሉትሰብሩዘንድአይደለምን?”ኢሳ58፥6

† ጾም ጸሎት ይዘን በምንፀልይ ጊዜ ፀሎታችን ከምድራዊ መረዳት ያለፈና በጠላት ላይመለኮታዊሽብርንያመጣል።ጾምጸሎትመንፈሳዊመረዳታችንንበማሳደግከእግዚአብሔርቃልጋርጊዜእንድንወስድናድምፁንመስማትእንድንችልይረዳናል።ጾምለችግሮቻችንሁሉመፍትሔየምናገኝበት፣በጠላቶቻችንላይሁሉድልንየምንቀዳጅበት፣ዲያብሎስንናጭፍራዎቹንጅራፍሳናነሳየምንገርፍበትነው።በመጽሐፍቅዱስውስጥበ2ዜና20፥1-30ላይንጉስኢዮሳፍጥጠላቶችሊወሩትበመጡጊዜበሀገሩይሁዳሁሉጾምአውጆነበር።በመጨረሻምሰይፍንሳያነሳጠላቶቹእርስበእርስእንደተገዳደሉእናያለን።

† በአስቴር መጽሐፍ አይሁዶች ላይ የወጣውን ፍርድ ለማስቀየር ንግስት አስቴርእግዚአብሔር እንዲያግዛት ጾም አውጃ ነበር። በመጨረሻም አይሁዳውያን እንደዳኑናየአይሁድጠላትሀማራሱባዘጋጀውመስቀያላይእንደተሰቀለይናገራል።

† በማቴ 4፥1-11 ኢየሱስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከፆመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦሲፈትነውፈተናውንያለፈውየእግዚአብሔርንቃልበመናገርነበር።

† ጾም ጠላትን ለመውጋት ኃይል ያለው መሳሪያ ሲሆን በጠላት ላይ ድልን እንድንቀዳጅይረዳናል።ጾምስለሕዝብሰላምንለመለመንእንዲሁምራስንምልክእንደመቅደላዊቷሴትከጌታእግርበታችዝቅአድርጎምህረትለመለመንያገለግላል።ከዚህበተጨማሪምበጉዟችንውስጥየእግዚአብሔርንሀሳብናፍላጎትለመረዳትምይጠቅማል።ሰውከዓለምየኃጢአትጉዞጋርእንዳይተባበርናእንዳይረክስምጭምርበጾምመትጋትይገባዋል።ነገርግንበጾምጊዜየምንሰራውመልካምስራውጤታማሊሆንየሚችለውድርጊታችንበጾምጊዜብቻየተወሰነካልሆነብቻነው።ከአሰብነውየጾምጊዜቀጥሎበሚኖሩትጊዜያትምውስጥድርጊታችንንመቀጠልከቻልንብቻነው።ጾማችንንእግዚአብሔርእንደሚያየውያለነቀፋ የምንጾም ከሆነ ከመብልና መጠጥ ብቻ ሳይሆን ከሚያረክሰው ክፉ መሻትናከዓለማዊነትሕይወትልንርቅይገባናል።ዛሬላይጾማችንመጨከንካልቻለጾማችንገናሌላእውነተኛጾም፣ሌላእውነተኛጸሎት፣ሌላእውነተኛንስሐያስፈልገዋል።ዋጋቸውንበሰውፊትእንደተቀበሉትግብዞችጸሐፍትናፈሪሳውያንሳይሆንሙሉዋጋቸውንበሰማያት

Page 92: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

82 83

ባለውአባታችንፊትእንደተቀበሉቅዱሳንተግተንከጸሎትጋርጾማችንንበመንፈስቅዱስጉልበትመጾምአለብን።

“አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎና!!”የውጊያ ጸሎት

† በጌታበኢየሱስክርስቶስስልጣንናበደሙጉልበትበቃሉበተጻፈመሰረትቤቴእንደተባረከአውጃለሁ።

♥ “የእግዚአብሔርመርገምበኃጥእቤትነው፥የጻድቃንቤትግንይባረካል።”ምሳ3፥33

♥ “ኀጥኣንይገለበጣሉ፥ደግሞምአይገኙምየጻድቃንቤትግንጸንቶይኖራል።”ምሳ12፥7

♥ “በጻድቅሰውቤትብዙኃይልአለየኃጥእሰውመዝገብግንሁከትነው።”ምሳ15፥6

♥ “ሕዝቤምበሰላምማደሪያበታመነምቤትበጸጥተኛማረፊያይቀመጣል።”ኢሳ32፥18

† በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣንና በደሙ ጉልበት በቃሉ በተፃፈው መሰረት ልጆቼመባረካቸውንአውጃለሁ።

♥ “በተጠማ ላይ ውኃን በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና መንፈሴን በዘርህ ላይበረከቴንምበልጆችህላይአፈስሳለሁ፥”ኢሳ44፥3

♥ “ልጆችሽምሁሉከእግዚአብሔርየተማሩይሆናሉ፥የልጆችሽምሰላምብዙይሆናል።”ኢሳ54፥13

♥ “የእግዚአብሔርምሕረትግንከዘላለምእስከዘላለምበሚፈሩትላይ፥ጽድቁምበልጅልጆችላይነው።”መዝ103፥17

♥ “ክፉሰውእጅበእጅሳይቀጣአይቀርምየጻድቃንዘርግንይድናል።”ምሳ11፥21

Page 93: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

83

ምዕራፍ 6መንፈሳዊ ዘረመልን መረዳት (SPIRITUAL DNA)

6.4 መንፈሳዊ ዘረመል ምንድን ነው?

ዋነኛ ማንነታችንን ከሚገነቡትና ከሌሎች ሰዎችና ፍጥረታት ከሚለዩን ነገሮች የመጀመሪያው ዘረመል (DNA) ነው። በዓለም ላይ ያለን ፍጥረታት በሙሉ የራሳችን ብቻ የሆነ ዘረመል አለን። ይህ ዘረመል የማንነታችንን ዕድገት፣ ባህርይና አሠራራችን ይለያል። ዘረመል /DNA/ ከወላጆቻችን ከተወጣጡ የበራሂ (genes) ድብልቅ የሚመጣ ሲሆን ለእኛ የተለየ ማንነት የሚሰጥ የንድፍ መዋቅር ነው። ከእናትና አባታችን የምንወርሰው የዘረመል ክፍልፋዮች በትንሹ ቢያመሳስለንም ፍፁም የሆነ ልዩነትም ይሰጠናል። ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር አባታችን ሰውን በመጀመሪያ ሲፈጥር የተነፈሰበት የሕይወት እስትንፋስ መንፈሳዊ ዘረመላችንን በእርሱ አምሳል እንዲገነባ አድርጎታል። ይህም ማንነታችን መንፈሳዊ ዕድገታችንን፣ ስራችንን፣ የግል ባህርያችንን ባጠቃላይ ዓላማችንን የሚወስንልን ክፍል ነው። መንፈሳዊ ዘረመላችን በእግዚአብሔር አምሳል የተገነባ ነበር። ይህ በእግዚአብሔር አምሳል የተገነባው ዘረመላችን በኃጢአት ምክንያት ተበክሏል፤ በኃጢአትና በበደል ተሸፍኗል፤ ወደ አሉታዊ ዘረመል ተቀይሯል። ስለዚህ በኃጢአት የተበከለውን መንፈሳዊ ዘረመላችንን ለማንጻት በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆንን የግድ ይላል። ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው። (2 ቆሮ 5፥17)

♥ “የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።”ኢዮ33፥4።

6.5 አሉታዊ/የተበከለ ዘረመል፥ ዓመፅ6.2.1 የዓመፅ ፅንሠ ሀሳብ/የዓመፅ ምንነት

ዓመፅን ማወቅና እንዴት በሕይወታችን እንደሚሰራ መረዳት እንደ አማኝ ልናውቀው የሚገባ አስፈላጊ እውነት ነው። በሕይወታችን ያለ የበደልን ምሽግ ማፈራረሳችን የሰይጣንን የጭቆና አገዛዝ ከሕይወታችን ለማስወገድና ከስጋ ፈተናዎች ነፃ ለመውጣት ይረዳናል።

Page 94: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

84 85

የዕብራይስጡ ቃል ዓመፅን መርድ /marad/rebel፣ ፓሻ /pasha/transgression/ እንዲሁም arown በሚባሉት ቃላት ሲገልፀው የግሪኩ ደግሞ አፖስትሬፎ /apostrepho /turn away፣ አኑፖትአክቶስ /anupotaktos /rebellion ወይም anomia ይለዋል። ትርጉሙም ጠማማ፣ መጥፎ ተነሳሽነት፣ የተቆላለፈ፣ የማይታዘዝ፣ መተላለፍ እና የተረገመ የሚሉትን ቃላት ይወክላል። ዓመፅ ለጠላት እስራትና ለሰይጣናዊ አገዛዝ በር ይከፍታል። ይህንን ዘረመል በሰው ልጆች ንጹህ ማንነት ውስጥ ያስቀመጠው ጠላት ዲያብሎስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ከዓመፅ እንድንርቅ ይመክረናል። ዓመፅ የሚያስከትለው መዘዝም እጅግ የከፋ ነው።

† እግዚአብሔር አዳምና ሄዋንን ሲፈጥር ዓላማው ፍሬያማ እንዲሆኑና በእግዚአብሔርአምሳል የተፈጠረውን የሰው ዘር በምድር ሁሉ ላይ እንዲያበዙ እንዲሁም ቤተሰብእንዲሆኑ ነው። የእስራኤልን ነገዶች ስንመለከት ለእያንዳንዱ ነገድ እግዚአብሔር ዓላማነበረው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገድ ዓላማ እንደነበረው ለቤተሰባችንም በስጋለምንገናኝ ዘመዳሞችም ዓላማ አለው። ነገር ግን በቤተሰብ ውስጥ በሚኖረው ጣዖትአምላኪነትናበዓመፅምክንያትየእግዚአብሔርፈቃድተቀይሯል።(ዘፍ49ያንብቡ።)

ስለ ዓመፅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ የተነገረ ሲሆን በመጀመሪያው የሳሙኤል መጽሐፍ ላይ ከሟርተኝነት ጋር አንድ ያደርገዋል። በተጨማሪም ጥንቁልናንም የሚያጠቃልል ቃል ነው። ሁለቱም ከፍተኛ የጠላትን ኃይል በመጠቀማቸው አደገኞች ናቸው። የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ከሚያቀርቡት መስዋዕትና መባ ይልቅ ልባቸውን ንጹህ ማድረጋቸው የበለጠ የተወደደና የተመረጠ ነው።

♥ “ሳሙኤልምበውኑየእግዚአብሔርንቃልበመስማትደስእንደሚለውእግዚአብሔርበሚቃጠልናበሚታረድመሥዋዕትደስይለዋልን?እነሆ፥መታዘዝከመሥዋዕት፥ማዳመጥምየአውራበግስብከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምንእንደማምለክነውየእግዚአብሔርንቃልንቀሃልናእግዚአብሔርንጉሥእንዳትሆንናቀህአለ።”1ኛሳሙ15፥23

♥ “ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙትርፍታመጣየነበረችአንዲትገረድአገኘችን።”ሐዋ16፥16

በዓመፅ መንፈስ የተያዘ ማንነት ብዙ ነገሮችን አያገናዝብም። ለማይጠቅምና ለማይረባ አዕምሮም ተላልፎ ይሰጣል። በሕይወቱ ውስጥ ምንም ጥቅም በሌላቸው ነገሮች ላይ ጊዜውንና ኑሮውን ያባክናል። ከእርሱ በታች ለሆነ ቢጮህ ለማይሰማው የተቀረጸ ምስል ያወራል። ድርጊቱንም ለማይመለከተው ግዑዝ ነገር ጉልበቱን ያንበረክካል።

♥ “ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ምሕረትህ ስለ እውነትህምምስጋናን ስጥ።አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? አይበሉ። አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነውበሰማይም በምድርም የፈቀደውን ሁሉ አደረገ። የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር፥ የሰው እጅሥራናቸው።አፍአላቸውአይናገሩምም፤ዓይንአላቸውአያዩምም፤ጆሮአላቸውአይሰሙምም፤አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፤ እጅ አላቸው አይዳሰሱምም፤ እግር አላቸው አይሄዱምም፤በጕሮሯቸውም አይናገሩም። የሚሠሯቸውም የሚያምኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።”መዝ115፥1-8

Page 95: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

85

የምናምናቸውና የሚያገለግሉን ነገሮች እንደ ጣዖት ሊሆኑብን ይችላሉ። በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ጣዖት የሆኑ የተቀረጹ ምስሎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ሕይወቱን የተቆጣጠሩ ማንኛውንም ነገሮች ያጠቃልላል። አንዳንድ ሰው የያዘው ስልጣን ጣዖት ይሆንበታል። ነገሮቹን ሁሉ የሚያስበው ከእግዚአብሔር ሀሳብ አንጻር ሳይሆን ከስልጣኑ አንጻር ነው። በመሆኑም ስልጣኑን ተገን አድርጎ በበታቾቹ ላይ በደልን ይፈጽማል። ሌላውም ደግሞ አምላኩ የፈጠረለት ውበት ጣዖት ይሆንበታል። ውበቱን በመጠቀም ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት በመጣር ሂደት ውስጥ አምላክን የሚያሳዝን እንደ ዝሙትና መዳራት ያሉ ኃጢአቶችን ይፈጽማል። ሌላው ደግሞ ያለው ሀብትና ንብረት ጣዖት ይሆንበታል። አምላኩንም ፈጽሞ እንዳያስብ አዕምሮው በገንዘብ በሚገኙ ገጸ በረከቶች ላይ ብቻ ትኩረት ያደርጋል። የኃጢአትና የበደል መፍለቂያም ይሆናል። ስለዚህ የበለጠ ያልተገባ ገንዘብ ለማግኘት ብሎ መዋሸት፣ ማጭበርበር እንዲሁም መግደል ውስጥ ይገባል። ይህ ድርጊት አምላክን አስክዶ ወደራሱ መሳብ ችሏልና ጣዖት ሆኖበታል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለመዝናናት ብለው በቀልድ የጀመሩት አልኮል ጣዖት ይሆንባቸዋል። ቀስ በቀስ በተደረገ ልምምድ ሱስ ይሆንባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ አጉል ባህርያት ቁጣ፣ ፍርሃት፣ ማመንዘር፣ በአስማት መሳተፍ፣ እንዲሁም ማናቸውም የሥጋ ሰራዎች ባህሪው ሊሆኑ ይችላሉ።

ክርስቲያኖች ሕይወታችን ውስጥ ጣዖት ሊሆኑ የሚችሉ ማንኛውንም ነገሮች ማስወገድ ይኖርብናል። ጣዖትን ማምለክ ለዲያብሎስ በር ከፍቶ መንፈሳችንን እንዲበክል ፈቃድ መስጠት ነው። የዲያብሎስ የሀሰት ማታለያዎቹ ናቸውና። ክርስቶስ እኛን መቅደሶቹ እንሆን ዘንድ የቀባን ስለሆንን ከእነዚህ ክፉ ጣዖታት እንድንለይ የእግዚአብሔር ቃል ይመክረናል።

♥ “እንግዲህምንእላለሁ?ለጣዖትየተሠዋምናምንነውእላለሁን?ወይስጣዖትምናምንእንዲሆንእላለሁን?”1ኛቆሮ10፥19-20

♥ “ለእግዚአብሔርቤተመቅደስምከጣዖትጋርምንመጋጠምአለው?እኛየሕያውእግዚአብሔርቤተመቅደስነንና”2ኛቆሮ6፥16

♥ “እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹምእያደረግንሥጋንናመንፈስንከሚያረክስሁሉራሳችንንእናንጻ።”2ኛቆሮ7፥1

6.2.2 የዓመፅ ምንጭና ባህርይየዓመፅ ምንጩ የሉሲፈርን ሀሳብ ማስተናገድና መቀበል ነው። አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ

ተላልፎ መልካምና ክፉውን የሚያሳውቀውን የዛፍ ፍሬ በበላ ጊዜ ዓመፅ (እርግማን) ወደ ሰው ልጆች ገባ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሰው ተፈጥሮ ተለወጠ፤ ሰው ከዲያብሎስ ጋር መስማማትና መጓዝ ጀመረ። ዓመፅ የእርግማንና የክፉ ተነሳሽነት መገኛ ነው። ሰዎች ከመዳናቸው በፊትም ሆነ ከዳኑ በኋላ በእግዚአብሔር መንገድ እንዳይጓዙ የሚያደርግ ነው።

♥ “አንተልትጋርድየተቀባህኪሩብነበርህበተቀደሰውበእግዚአብሔርተራራላይአኖርሁህበእሳትድንጋዮችመካከልተመላለስህ።ከተፈጠርህበትቀንጀምረህበደልእስኪገኝብህድረስበመንገድህፍጹምነበርህ።”ሕዝ28፥14-15

♥ “በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራበታላቅምበብርቱምሰይፍይቀጣል፥በባሕርምውስጥያለውንዘንዶይገድላል።”ኢሳ27፥1

Page 96: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

86 87

† የዓመፅምባህርይይህንይመስላል።በውስጣችንያለውንየድሮማንነትበማስታወስወይምካለንማንነትውስጥከአዲሱማንነታችንባህርይውጪናባልተለመደመንገድእንድንኖርያደርገናል። ይህም ዓመፅ እየሰፋና እያደገ በሄደ ቁጥር ትርምስን፣ ረብሽን፣ ብጥብጥንእና በመጨረሻም ሞትን ያስከትላል። ሰው እግዚአብሔር ለርሱ ያለውን ዓላማ መረዳትሲያቆም ወይም ሳይረዳ ሲቀር ማመፅ ይጀምራል። በዚህም ምክንያት ከመንፈስ ቅዱስቁጥጥርውጪመሆንይጀምራል።”

♥ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”ኤፌ6፥12

ዓመፅ የኃጢአት ስር ነው። ዳዊት በመዝሙር 51፥5 እናቱ በዓመፅ እንደፀነሰችው ይናገራል። ኃጢአትን ስናደርግ የኃጢአቱ ምንጭ የሰው ልጅ ልብ ከአምላኩ መንገድ ውጪ መሆኑ ነው። ልብንም በማደንደን ለእግዚአብሔር ምክር ልቡን ማደንደን ይጀምራል። በዚህም ዓመፅ የክፋት መሰረት ይሆናል። ዓመፅ ለኃጢአት ከትውልድ ወደ ትውልድ የመተላለፍ መሰረታዊ ምክንያት ነው። የዘር ሀረግን ይረብሻል። ከእግዚአብሔር ባልሆኑ ምርጫዎች፣ ጤናማ ባልሆኑ ባህርይዎች ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻችን ይገባል። የክርስቶስን አዳኝነትና በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ እንዳናስተውልና እንድንክድ ያደርጋል። ለምሳሌ ያህል በስርቆት፣ በስግብግብነት፣ በዝሙት፣ በአስማት በመሳተፍ በመሳሰሉት ስራዎች ዓመፅ ይበልጥ ያድጋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ዓመፅን የኃጢአት ስጋ ይለዋል። ዓመፅ በሁሉም በሰው ዘር መንፈሳዊ አካል ውስጥ አለ። የኃጢአት ስጋ መነሻው የሰው ውድቀት ሲሆን የሰውን አዕምሮ፣ ስሜት፣ ፈቃድ እና አካላዊ ማንነቱን በክሏል። በዓመፅ ምክንያትም ጠላት ሰዎችን በእርግማንና በበሸታ ለመምታት የሚጠቀምበት መንገድ ተከፍቶለታል።

♥ “ከእንግዲህስወዲያለኃጢአትእንዳንገዛየኃጢአትሥጋይሻርዘንድአሮጌውሰዋችንከእርሱጋርእንደተሰቀለእናውቃለን፤የሞተስከኃጢአቱጸድቋልና።”ሮሜ6፥6

♥ “ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውንበውስጣችሁምየተተከለውንቃልበየዋህነትተቀበሉ።”ያዕ1፥21

ዓመፅ አሉታዊ የሆነ መንፈሳዊ ዘረመል ሲሆን በቤተሰብ የዘር ግንድ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል ነው።

♥ “እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥በደለኛውንምከቶየማያነፃ፥የአባቶችንምኃጢአትበልጆችእስከሦስትናእስከአራትትውልድምበልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ። ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህእግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። በላይ በሰማይካለው፥በታችምበምድርካለው፥ከምድርምበታችበውኃካለውነገርየማናቸውንምምሳሌ፥የተቀረጸውንምምስልለአንተአታድርግ።አትስገድላቸው፥አታምልካቸውምምበሚጠሉኝእስከሦስተኛናእስከአራተኛትውልድድረስየአባቶችንኃጢአትበልጆችላይየማመጣ…”ዘፀ20፤1-5

Page 97: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

87

6.2.3 ዓመፅ የሚያስከትለው መዘዝዓመፅ ወደ ሰዎች ሕይወት ከሚገባባቸው ምክንያቶች እንደዋና ከሚጠቀሱት መካከል የሰው

ልብ እልከኝነትና ትምክህተኝነት ሲሆኑ ልብ እንዲጠጥር ደግሞ የተለያዩ መንስዔዎች መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ ሌሎች ሰዎች የሚጎዳን ነገር በሚያደርጉብን ጊዜ በምንሰጠው ምላሽ፣ አካላዊና ፆታዊ የቃላት ጥቃት፣ ሰው ስለ እኛ በሚያወራው ነገር፣ የእምነት ማጣት የመሳሰሉት ናቸው። በእነዚህም ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር የነበረን ግንኙነት ይቋረጣል። ዓመፅ እግዚአብሔርን ያስቆጣዋል፤ እግዚአብሔርም ዓመፅን የሚያደርጉትን እንደጠላቶቹ ይቆጥራቸዋል፤ ጨካኝ መልአክ ይላክበታል፤ በምድረ በዳ ለብቻ ያስቀራል።

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲወስዳቸው የገባላቸው አንድ ቃል ነበረ። እሱም በአርባ ቀናት ውስጥ ወደ ስፍራው እንደሚደርሱ ነው። ነገር ግን ሕዝቤ የሚላቸው እስራኤላውያን በየቦታው በእግዚአብሔር ላይ ያምፁ ነበር። ሙሴ ከአምላኩ ጋር ሊነጋገር እንዲሁም የቃል ኪዳኑን ታቦት ሊያመጣ ወደ ተራራ በወጣ ጊዜ እስራኤላውያን ግን ከወርቅና ከነሀስ የተቀረጸ ምስል አቁመው እየጮሁ ያመልኩ ነበር። በዚህ ድርጊታቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እጅግ አዝኖ ተቆጥቶም ነበር። ሙሴም ያመጣውን ታቦት ወርውሮ እስኪሰብረው ድረስ በሚመራቸው ሕዝብ ድርጊት ተቆጥቶ ነበር (ዘፀ 32)። እስራኤላዊያን በየመንገዱ የዓመፅና የትዕቢት ቃላት ይናገሩ ነበር። ከሰማይ መናን እያወረደ ቢመግባቸው “መና ሰለቸን፤ የግብፅ ሽንኩርት ደግሞ ናፍቆናልና እንመለስ” ብለውትም ያውቃሉ (ዘፀ 16፣ 17)። በግዞት ለብዙ ዘመናት ያሳለፉት የችግርና የስቃይ ጊዜ ተረስቷቸው በበረሀ ማለቅ አንፈልግምና ወደ ግብፅ እንመለስ በማለትም አጉረምርመዋል። ታዲያ ለዚህና ላልተጠቀሱት በደሎች እግዚአብሔር ሲቀጣቸው እንመለከታለን። ከቅጣታቸውም መካከል ብዙዎቹ ሕዝብ በበረሀ በሞት ተቀጥተው አልቀዋል። በመሆኑም ከግብፅ ከወጡት ሕዝብ ሁለት ሰው ብቻ ወደ ተስፋይቱ ምድር ገቡ። በረከታቸውን በመታዘዝ በአርባ ቀን መቀበል እየቻሉ በዓመፃቸው ምክንያት አርባ ዓመት ተራዝሞ ሳያዩት እንኳን አልፈዋል (ዘኁ 14)። እግዚአብሔር ጣዖትን የሚያመልኩ ሰዎችን እንደ ጠላቶቹ ይቆጥራቸዋል።

♥ “የሰውልጅሆይ፥እነዚህሰዎችጣዖቶቻቸውንበልባቸውአኑረዋልየበደላቸውንምመቅሠፍትበፊታቸው አቁመዋል እኔስ ከእነርሱ ልጠየቅን? ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ሁሉምበጣዖቶቻቸውከእኔተለይተዋልናየእስራኤልንቤትበልባቸውእይዝዘንድከእስራኤልቤትጣዖቶቹንበልቡየሚያኖር፥የበደሉንምመቅሠፍትበፊቱየሚያቆምሰውሁሉወደነቢዩበመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ ብለህ ንገራቸው።” ሕዝ14፥3-6

♥ “በእጃቸውሥራሁሉሊያስቈጡኝትተውኛልና፥ለሌሎችምአማልክትዐጥነዋልናቍጣዬበዚህስፍራይነድዳል፥አይጠፋምም።”2ኛዜና34፥25

በቀላሉ ጣዖትን ማምለክ ማለት ከአንዱ እግዚአብሔር ሌላ በሰዎች፣ በእቃና በመሳሰሉት ዋስትናን መፈለግ ነው። አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር ከእግዚአብሔር አብልጠን ስንታመንና ፍላጎታችንን ለማሟላት ራሳችንንም ጨምሮ በሰዎች መመካትና በሌላ ነገር መደገፍን ያመላክታል። አንድን ነገር ያለማቋረጥ ማሰላሰል/obsession/ ጣዖት ሊሆንብን ስለሚችል መጠንቀቅ አለብን።

Page 98: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

88 89

♥ “አትስገድላቸው፥አታምልካቸውምምበሚጠሉኝእስከሦስተኛናእስከአራተኛትውልድድረስየአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህትውልድድረስምሕረትንየማደርግእኔእግዚአብሔርአምላክህቀናተኛአምላክነኝና”ዘፀ20፥5

♥ “ተመልከተኝ ስማኝም፤ በኀዘኔ ተቅበዘበዝሁ ተናወጥሁም ከጠላት ድምፅ ከዓመፀኛም ግፍየተነሣ ዓመፃን በላዬ ጥለውብኛልና፥ በቁጣም ጠልተውኛልና።ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞትድንጋጤምወደቀብኝ።”መዝ55፥2-4

♥ “ክፉሰውዓመፃንብቻይሻልስለዚህጨካኝመልአክይላክበታል።”ምሳ17፥11

† ዓመፅሰውንከእግዚአብሔርያቆራርጠዋል።በምድረበዳለብቻያስቀራል።

♥ “እግዚአብሔርብቸኞችንበቤትያሳድራቸዋል፥እስረኞችንምበኃይሉያወጣቸዋልዓመፀኞችግንበምድረበዳይኖራሉ።”መዝ68፥6

መጽሐፍ ቅዱስ አመፀኛ ሰው ልቡና አረማመዱ ከእግዚአብሔር ጋር እንዳልሆነ ይናገራል። በዚህም ምክንያት ፍርድ ይመጣበታል። ዓመፅ ልብን ያሸፍታል፤ ያደነድናል። ሰይጣንም ይህንን በመጠቀም መንፈሳዊ ዓይንን ያሳውራል። የልብ ዓይን ሲታወር ደግሞ ምርጫችንን በጣም ያበላሸዋል። የምርጫ መበላሸት ለወደፊት ሕይወት መመሳቀልና የፀፀት ኑሮ እንዲመራ ያደርጋል።

♥ “እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ጠማማና የምታስመርር ትውልድ፥ ልብዋን ያላቀናች ትውልድ፥ነፍስዋበእግዚአብሔርዘንድያልታመነች።”መዝ78፥8

አታድርጉ የተባልነውን ማድረግ የዓመፅ መገለጫ እንደሆነ ሁሉ አድርጉ የተባልነውንም አለማድረግ የዓመፅ አንዱ ክፍል ነው። በትንቢተ ዮናስ ላይ እንደ ምንመለከተው እግዚአብሔር ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ሲልከው ዮናስ ግን ይህንን ጥያቄ አለመቀበሉን እንመለከታለን። ከእግዚአብሔርም ፊት ኮብልሎ ወደ ተርሴስ በመርከብ ሲሄድ እግዚአብሔር በባህሩ ላይ ታላቅ ማዕበልን እንዳስነሳ፣ መርከቢቱን እጅግ እንዳንገላታት፣ ዮናስም ወደ ባህሩ እስኪጣል ድረስ ከፍተኛ ጭንቅን በመርከቢቱ ላይ እንደሆነ እናያለን። ዮናስ ባህር ውስጥ በተጣለ ጊዜ ታላቅ አሳ እንደዋጠው ሳያኝከው ሶስት ቀን ሙሉ በሆዱ ይዞ አቆየው። በመጨረሻም በባህሩ ዳርቻ ወስዶ ተፋው። (ዮና 1፣ 2)

የዮናስ ታሪክ እኛንም ብዙ ያስተምረናል። እግዚአብሔር አድርጉ ያለንን ባለማድረግ ስንት ጊዜ የዓመፅ ተግባር ፈፀምን? እግዚአብሔር በተለያዩ መንገዶች እናደርግ ዘንድ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሲያዘን ኖሯል። በውስጣችን ካለው መንፈስ ቅዱስ ድምፅ አንስቶ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በሰባኪያን እና በተለያዩ አገልጋዮች በኩል ትእዛዝን አስተላልፎልናል። ነገር ግን እነዚህን ትዕዛዛት በእንቢተኛነት ካልፈጸምን የዓመፅ አንዱን አይነት በሕይወታችን ላይ እየተገበርን መሆኑን መረዳት አለብን።

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እያመፁ መሆናቸው ሳይገባቸው በተደጋጋሚ በዚህ ክፉ ተግባር ተሳታፊ ይሆናሉ። ይህኛው አይነት ዓመፅ ደግሞ ቀናኢ የሆኑ መስሏቸው ነገር ግን ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዳይገቡ ደንቃራ መሆንን ያመለክታል። ክርስቲያኖች የምናምነው አምላክ እግዚአብሔርን ነው። የሀይማኖታችን መሰረት ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህንን ቃል “አልቀበልም” የሚል ወይም “ለእምነቴ በሚመች መንገድ ይህንን ቃል እተረጉማለሁ” የሚል ማንም ቢኖር ዓመፅን እየተገበረ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል።

Page 99: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

89

ሐዋርያው ጳውሎስም በአንድ ሰሞን በዚህ ሆን ተብሎ በማይተገበረው ወይም ከእውቀት ማነስ የተነሳ በሚመጣው የዓመፅ ተግባር ላይ ተሳትፎ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ሐዋ 7፣ 8)

አመፀኛነት የሰይጣንን ሀሳብ ወደ ሕይወታችን ከምንጋብዝበት መንገድ አንዱ ነው። ነገር ግን ንሰሀ በመግባትና ኃጢአትን በመናዘዝ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ይቻላል። ዓመፅ ከሰይጣን የጀመረ ነው። እግዚአብሔር ምድርን ከመፍጠሩ በፊት መላእክትን ፈጥሮ ነበር። የራሳቸውም ምርጫ ነበራቸው። ከእነሱም አንዱ በእግዚአብሔር ላይ አመፀ (ኢሳ 14፥12-14፣ ሕዝ 28፣12-19)። ከእሱም ጋር የነበሩትን አሳምፆ ከተፈጠሩበት ዓላማ ወደ ራሱ ፈቃድ አስወጣቸው። ወደ ምድር ከተጣለ በኋላም የሰዎችን ሕይወት የማመሳቀልና የመበጥበጥ ስራውን በትጋት እየተወጣ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎችን ወደ ራሱ ሀሳብ እያፈለሰ እንደሚጠቀምባቸው ይታያል። ይህንንም ስራውን በአሁኑ ጊዜ በግልፅ ሁኔታ በሰፊው እያከናወነ ነው።

ሉሲፈር ትምክህተኝነቱ አሸንፎት ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቷል። ከእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መባረሩም ሌሎች የዓመፅ ፍሬዎችን ከማፍራት በላይ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑትን ሁሉ ለማጥፋትና ከእጁ እንዲገቡ አድርጎታል።

♥ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱከመጀመሪያነፍሰገዳይነበረ፤እውነትምበእርሱስለሌለበእውነትአልቆመም።ሐሰትንሲናገርከራሱይናገራል፥ሐሰተኛየሐሰትምአባትነውና።”ዮሐ8፥44(በተጨማሪራዕ12፥4-9ይነበብ።)

6.6 ደህንነት/በክርሰቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን በእግዚአብሔር አምሳል ዘረመልን መልሶ መገንባት

ከላይ ያየናቸውን የእግዚአብሔር የሆነውን ዘረመል ያቆሸሹና በኃጢአት የተበከለ ዘረመልንም ወደ ሕይወታችን የጋበዙ ድርጊቶችን በሙሉ ከማንነታችን ውስጥ አውጥተን መጣል ይኖርብናል። እርግጥ ነው የሰው ልጅ ከኃጢአት የነፃና ፍጹም ይሆን ዘንድ አይቻለውም። ይህንን እውነታ መረዳት በተለያዩ ጊዜያት ሳናውቅ በምንፈጽማቸው ስህተቶች ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል። ሁልጊዜም የቆሸሸው ማንነታችንን የምናጠራው በተሰበረ ልብና በንስሀ ዘወትር ወደ አምላካችን በመቅረብ እንጂ ፍጹም በመሆን አይደለም። እስከ አሁን ስለ ዓመፅ ስናይ ደህንነታችንን ለማስፈፀም እየሞከርን እንዳልሆነ መረዳቱ ተገቢ ነው። መዳናችን የተፈፀመው በክርስቶስ ነው።

6.3.1 ዓመፅን ማስወገድዓመፅን ስናስወግድ በእግዚአብሔር ሀሳብ ውስጥ የታየልንን ማንነታችን በውስጣችን መስራት

ይጀምራል። ይህ የቀድሞ ማንነት ፍቅር፣ ሰላም፣ መታዘዝ፣ መከባበር፣ መተጋገዝ፣ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብና በፍጹም ሀሳብ መውደድ እንዲሁም ሌሎች መልካምነትን የሚያሳዩ ተግባራትን መፈጸምን ያጠቃልላል። ሌላው ከዓመፅ ነፃ ስንሆን በመንጋ ማሰባችንና ከመንጋው ጋር ለኃጢአት ማበራችን ይቀራል። ራሳችንንም ለክርስቶስ የተለየ አድርገን ማቅረብ እንችላለን።

Page 100: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

90 91

አብዛኛውን ጊዜ በኃጢአትና በዓመፅ ምክንያት የሚመጡ ባህሪዎች ተመሳሳይ ሊመስሉ ይችላሉ። ዓመፃችንን ለመናዘዝ መንፈስ ቅዱስ ዓመፃችንንና ኃጢአታችንን እንዲለይልን መጸለይ ያስፈልጋል። ኃጢአታችንን ብቻ ተናዘን ዓመፃችንን ካልተናዘዝንና ካልተውን ሰይጣን በሕይወታችን ስራውን መስራቱን ይቀጥላል።

ምሳሌ የሚሆነን ፖርኖግራፊ ነው፤ በፖርኖግራፊ በመሳተፋችን ኃጢአታችንን መናዘዝና እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በመጸለይ ከኃጢአት ልንነፃ እንችላለን። ነገር ግን ዓመፃችን ከነ ሰንኮፉ ስላልተነቀለ ተመልሰን ወደ ነበርንበት እንመለሳለን። ብዙ ጊዜ በደል ወይም ዓመፅ በቤተሰብ ሊደበቅ ወይም ግልፅ ላይሆን ስለሚችል መንፈስ ቅዱስን መጠየቁ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው።

† በደልን ለማወቅ መጀመሪያ የምንሰራውን ኃጢአት ማወቅ አለብን። ስለ ኃጢአት ያለንእውቀትናግንዛቤመመርመርአለበት። • ምንዓይነትኃጢአትየመስራትልማድአለን? • በቤተሰባችንያለውኃጢአትምነድነው?

• ወደእኛየተሸጋገረውምንድነው?

† በተጨማሪምመጽሐፍቅዱስምንእንደሚልመመልከትአለብን።

♥ “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ትዕቢተኛዓይን፥ሐሰተኛምላስ፥ንጹሕንደምየምታፈስስእጅ፥ክፉአሳብንየሚያበቅልልብ፥ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልምጠብንየሚዘራ፤”ምሳ6፥16-19

† እነኚህበአዳምናበሄዋንውድቀትምክንያትወደሰውዘርየገቡማንነቶችናቸው።ስለዚህከሕይወታችንእንዲወገዱመጸለይአለብን።

† መጽሐፍቅዱስኃጢአትንእንዴትማስወገድእንዳለብንበግልፅአስቀምጦልናል።

† ኃጢአትንስንናዘዝከኃጢአታችንእንነፃለን።በደልናመናዘዝናድካማችንንከሕይወታችንማስወገድአስፈላጊነው።

♥ “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅነው።”1ኛዮሐ1፥9

♥ “በእኔምላይበእንቢተኝነትስለሄዱብኝየበደሉኝንበደል፥ኃጢአታቸውንም፥የአባቶቻቸውንምኃጢአትይናዘዛሉ።”ዘሌ26፥40

† ከበደልና ከበደል ኃይል ለመላቀቅ የራሳችንንና የዘርማንዘሮቻችንን በደል እንድንናዘዝእግዚአብሔርይፈልጋል።

ኃጢአት እንዳለብን አውቀን ኃጢአታችንን መናዘዝ ከእኛ አልፎ ትውልዳችንን ያድናል። ከጠላት እስራት ለመፈታት ማንነታችንን ለሱ ማቅረብ አለብን። እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳችን እኛን ለማውጣት ሁሌም ዝግጁ ነው። ወደ እቅፉ በመግባት የሰላም ኑሮን መምራት እንችላለን ለሌሎችም መዳን ምክንያት እንሆናለን።

Page 101: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

91

† በመጽሐፍቅዱስስለበደልየተፀለዩፀሎቶችመልስአግኝተዋል

• ሙሴለእስራኤልይቅርመባልየፀለየውጸሎት፤

♥ “አቤቱበፊትህስሞገስንአግኝቼእንደሆነ፥ይህአንገተደንዳናሕዝብነውናጌታዬበመካከላችንይሂድጠማማነታችንንናኃጢአታችንንምይቅርበለን፥ለርስትህምተቀበለንአለ”ዘፀ34፥9

♥ ነህ1፥1-11

• ለእስራኤልበደልየዳንኤልጸሎት፤

♥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ኃጢአታችንና ስለ አባቶቻችን በደል ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ላሉትሁሉመሰደቢያሆነዋልናእንደጽድቅህሁሉቍጣህናመዓትህከከተማህከኢየሩሳሌምከቅዱስተራራህእንዲመለስእለምንሃለሁ።”ዳን9፥16

6.7 በደልና የሰው መንፈስ፥

በክፍል አንድ እንደተማርነው ሰው በመንፈስ፣ በነፍስና በስጋ የተዋቀረ ነው። እግዚአብሔር ነፍስን የሰጠን በምድራዊ አካላችን ስንኖር የራሱን መንፈስ ለሌሎች እንድንገልጥ ነው። ልክ አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተላልፈው መልካምና ክፉውን የምታሳውቀውን ፍሬ በበሉ ጊዜ ኃጢአት ወደ ሰው ዘር ገባ ።

♥ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉኃጢአትንስላደረጉሞትለሰውሁሉደረሰ፤”ሮሜ5፥12

† አዳም ከዲያብሎስ ጋር ለመስማማት ሲመርጥ ድካም ወደ ሰው ዘር በመግባቱ የሰውተፈጥሮሙሉለሙሉተለወጠ።

♥ “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱከመጀመሪያነፍሰገዳይነበረ፤እውነትምበእርሱስለሌለበእውነትአልቆመም።ሐሰትንሲናገርከራሱይናገራል፥ሐሰተኛየሐሰትምአባትነውና።”ዮሐ8፥44

♥ “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥በማይታዘዙትምልጆችላይአሁንለሚሠራውመንፈስአለቃእንደሆነውበአየርላይሥልጣንእንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችንደግሞ፥የሥጋችንንናየልቡናችንንፈቃድእያደረግን፥በሥጋችንምኞትበፊትእንኖርነበርንእንደሌሎቹምደግሞከፍጥረታችንየቁጣልጆችነበርን።”ኤፌ2፥1-3

6.4.1 የሰውን መንፈስ መረዳትሰው መንፈስን፣ ደመነፍስን፣ እንዲሁም ህሊናን ያካትታል። ከደህንነት በፊት መንፈሳችን

በኃጢአት ምክንያት የሞተና የክፉ መኖሪያ ነበር። ከደህንነት በኋላ መንፈሳችን በድጋሚ ስለተወለደ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሆኗል።

Page 102: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

92 93

አንድነት • በክርስቶስአንድየምንሆንበት

• አዲስፍጥረትየሚመሰረትበት

• የእግዚአብሔርንድምፅየምንሰማበት

• ከነፍሳችንጋርየምንገናኝበት

ደመነፍስ † ዌብስተር የተባለው መዝገበ ቃላት ደመነፍስን ያለምንም ምክንያት (ምንጭ) የሚገኝ

እውቀትይለዋል።ስድስተኛውየስሜትህዋስበመባልምይታወቃል።

• በደመነፍስየምናገኘውእውቀትበዙሪያችንማየትየማንችለውንነገርግንእየተደረገያለን ነገርእንድናውቅይረዳናል።

• ደመነፍሳችንመንፈሳዊውንማንነታችንንከተፈጥሯዊማንነታችንጋርየሚያገናኝአንቴናነው።

• ለምሳሌ፥አንዳንድጊዜሰዎችይደውላሉብለንአስበንየሚደውሉበትጊዜአለ፤ወይምመጥፎነገርሊከሰትእንደሆነሊሰማንይችላል።

• ደመነፍስመንፈስቅዱስየትንቢትንስጦታናየቃሉንእውቀትየሚያስቀምጥበትቦታነው።

ህሊና † ህሊናማለትአንድንሰውትክክልነውትክክልአይደለምብሎመልካሙንነገርእንዲያደርግ

ሰውየውላይግፊትየሚፈጠርየአዕምሮስሜትነው።

• ህሊናፈሪሀእግዚአብሔርናጥበብየሚገኝበትነው።

• ህሊናመጽሐፍቅዱስሳናነብወይንምሳይነገረንክፉናደጉንየምንለይበትቦታነው።

† ነገርግንህሊናችንበተደጋጋሚበምናደርገውዓመፅናኃጢአትሊደነዝዝይችላል።

♥ “ሕግየሌላቸውአሕዛብከባሕርያቸውየሕግንትእዛዝሲያደርጉ፥እነዚያሕግባይኖራቸውእንኳለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸውሲካሰስወይምሲያመካኝበልባቸውየተጻፈውንየሕግሥራያሳያሉ።”ሮሜ2፥14-16

6.4.2 የመንፈሳችን አዕምሮ † ይህከዚህበፊትያልተማርነውንመለኮታዊእውቀትየምንቀበልበትነው::

♥ “የክርስቶስአዕምሮስላለንስለእግዚአብሔርመንፈስየበለጠመረዳትእንችላለን“መንፈሳዊሰውግንሁሉንይመረምራልራሱግንበማንምአይመረመርም።እንዲያስተምረውየጌታንልብማንአውቆትነው?እኛግንየክርስቶስልብአለን።”1ኛቆሮ2፥15-16

♥ “የክብርአባትየጌታችንየኢየሱስክርስቶስአምላክእርሱንበማወቅየጥበብንናየመገለጥንመንፈስእንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆንበቅዱሳንምዘንድያለውየርስትክብርባለጠግነትምንእንዲሆንለምናምንከሁሉየሚበልጥየኃይሉታላቅነትምንእንዲሆንታውቁዘንድነው፤”ኤፌ1፥17-20

Page 103: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

93

የኃይል መቀመጫ † በእግዚአብሔርአምሳልስለተፈጠርንበውስጣችንያለውመንፈሳችንበኃይልየተሞላነው።

በጌታኢየሱሰአምነንመንፈስቅዱስንበተቀበልንጊዜደግሞመንፈሳችንበእግዚአብሔርኃይል ይሞላል። በዚህም ምክንያት ፈውሶች፣ ተአምራት እንዲሁም የተለያዩ አስደናቂምልክቶችየሚታወጁበትቦታነው

♥ “እንግዲህበእኛእንደሚሠራውኃይልመጠንከምንለምነውወይምከምናስበውሁሉይልቅእጅግአብልጦሊያደርግለሚቻለው፥…”አፌ3፥20

♥ “ለዚህምነገርደግሞ፥በእኔበኃይልእንደሚሠራእንደአሠራሩእየተጋደልሁ፥እደክማለሁ።”ቆላ1፥29

♥ “አትስገድላቸው፥አታምልካቸውምምበሚጠሉኝእስከሦስተኛናእስከአራተኛትውልድድረስየአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህትውልድድረስምሕረትንየማደርግእኔእግዚአብሔርአምላክህቀናተኛአምላክነኝና”ዘፀ20፥5

♥ “ጌታለእርሱየሆኑትንያውቃል፥ደግሞም፦የጌታንስምየሚጠራሁሉከዓመፅይራቅየሚለውማኅተምያለበትየተደላደለየእግዚአብሔርመሠረትቆሞአል።”2ኛጢሞ2፥19

ነገር ግን ውዱ አምላካችን እግዚአብሔር ልጆቹን በምንም ምክንያት ማጣት አይፈልግም። ስለዚህም እስከመጨረሻው ድረስ አይለቀንም። ነገር ግን በኃጢአታችን ምክንያት ያዝናል። ምርጫችንን ባይወደውም ይመክረናል፤ ይታገሰናል፤ ከዓመፃችን እስክንመለስ ይጠብቀናል። በንስሐ ስንመለስ ደግሞ እጆቹን ዘርግቶ ይቀበለናል።

♥ “ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትናለዓመፃባሪያዎችአድርጋችሁእንዳቀረባችሁ፥እንደዚሁብልቶቻችሁሊቀደሱለጽድቅባሪያዎችአድርጋችሁአሁንአቅርቡ።”ሮሜ6፥19

♥ “በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፋትይመለሳል።”ምሳ16፥6

♥ “እውነትንምታውቃላችሁእውነትምአርነትያወጣችኋልአላቸው።”ዮሐ8፥32

♥ “እግዚአብሔርታጋሽናምሕረቱየበዛ፥አበሳንናመተላለፍንይቅርየሚል፥ኃጢአተኞችንምከቶየሚያነፃ፥የአባቶችንኃጢአትእስከሦስትናእስከአራትትውልድድረስበልጆችላይየሚያመጣነውብለህእንደተናገርህ፥የጌታኃይልታላቅይሁን።”ዘኁ14፥17-18

♥ “እኔንምከበደሉበትኃጢአትሁሉአነፃቸዋለሁእኔንምየበደሉኝንያመፁብኝንምኃጢአታቸውንሁሉይቅርእላለሁ።”ኤር33፥8

♥ “እርሱግንስለመተላለፋችንቈሰለ፥ስለበደላችንምደቀቀየደኅንነታችንምተግሣጽበእርሱላይነበረ፥በእርሱምቍስልእኛተፈወስን።”ኢሳ53፥5

♥ “እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለእግዚአብሔርምየሁላችንንበደልበእርሱላይአኖረ።”ኢሳ53፥6

Page 104: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

94 95

♥ “ስለዚህምእርሱብዙዎችንይወርሳል፥ከኃያላንምጋርምርኮንይከፋፈላልነፍሱንለሞትአሳልፎሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለዓመፀኞችምማለደ።”ኢሳ53፥12

† በደልን ከሕይወታችን ስናስወግድ ከኃጢአት ነፃ መሆንና ከዚህ በፊት ተለማምደነውበማናውቀውመልኩየመንፈስፍሬዎችበሕይወታችንመገለጥይጀምራሉ።

♥ “ሆኖም፥ጌታለእርሱየሆኑትንያውቃል፥ደግሞም፦የጌታንስምየሚጠራሁሉከዓመፅይራቅየሚለውማኅተምያለበትየተደላደለየእግዚአብሔርመሠረትቆሞአል።ትልቅምቤትየእንጨትናየሸክላ እቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር እቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነፃ፥ ለክብር የሚሆንየተቀደሰምለጌታውምየሚጠቅምለበጎምሥራሁሉየተዘጋጀእቃይሆናል።”2ኛጢሞ2፥19-21

† ኤፌ4፥1-14በክርስቶስየሆነማንኛውምሰውአንድአካልንለመገንባትእንደሚያስፈልግናእንደተሰጠው ጸጋ እንዲሰራ ይናገራል። ምንም ነገር ሲሰራ ጠንካራ መሰረት ሊኖረውይገባልአለበለዚያትንሽነገርሲገፋውይወድቃል።አንድቤትሲገነባበማይገጥምድንጋይወይምበበሰበሰእንጨትከተሰራመጨረሻውመውደቅነው።ልክእንደዚህየክርስቶስንአካል ለመገንባት ኃጢአት አይገጥምም። አመፀኛ ልብ ከጌታ አካል ጋር አይገጥምም፤መጨረሻውምስለማይጠቅምመጣልይሆናል።

♥ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድሥልጣንንሰጣቸው፤እነርሱምከእግዚአብሔርተወለዱእንጂከደምወይምከሥጋፈቃድወይምከወንድፈቃድአልተወለዱም።”ዮሐ1፥12-13

የዘላለምን የሕይወት ስጦታ ክርስቶስን በመቀበል ስናገኝና በመንፈስ እንደ አዲስ ሰው ዳግም ስንወለድ ሰመያዊውን ዘረመል እንቀበላለን። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችን ካለው መንፈስ ጋር አንድ ይሆናል። በዚህም ምክንያት መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ማንነታችንን ማሳደግ ይጀምራል። እለት በእለትም እግዚአብሔርን እየመሰልን እናድጋለን።

በሳይንሳዊው ዓለም ከወላጆቻችን ጋር የሚያመሳስለንን ዘረመል ማቋረጥ/መስበር አንችልም። ልክ እንደዚያው የጌታ ልጆች ከሆንን በኋላ ይህንን ግንኙነት ማቋረጥ አንችልም። ነገር ግን በበሽታ ምክንያት ዘረመላችን ሊበላሽ ይችላል። እንደዚሁም በኃጢአት በሽታ ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ልናዛባው እንችላለን። ዓመፅም ይህንን ዘረመል ከሚበክሉት ኃጢአት አንዱ ነው። በዓመፃችን ፊታችንን ስናዞርበት ከአባታችን ጋር ያለንን ዝምድና እናበላሸዋለን። ወላጅን የመካድ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ቢችሉም ያለንን ቁርኝት ግን መለወጥ አይቻልም።

♥ “እግዚአብሔርታጋሽናምሕረቱየበዛ፥አበሳንናመተላለፍንይቅርየሚል፥ኃጢአተኞችንምከቶየሚያነፃ፥የአባቶችንኃጢአትእስከሦስትናእስከአራትትውልድድረስበልጆችላይየሚያመጣነውብለህእንደተናገርህ፥የጌታኃይልታላቅይሁን።”ዘኁ14፥18

♥ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትንእሰጣቸዋለሁ፥ለዘላለምምአይጠፉም፥ከእጄምማንምአይነጥቃቸውም።የሰጠኝአባቴከሁሉይበልጣል፥ከአባቴምእጅሊነጥቃቸውማንምአይችልም።ዮሐ10፥27-29

† ዳንኤል ኦሲቤ (Daniel Osigbe) የተባለው ፀሐፊ “The Secret Rebellion” በሚባልመጽሐፉላይእንደዚህዓይነትሀሳብንአስቀምጧል።

Page 105: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

95

“የቤተ-ክርስቲያን ዕድገትና ቅርፅ በመንፈስ ቅዱስና በእግዚአብሔር ቃል የሚመራ ነው። የክርስቶስ ሰውነት ማንነት ባለን በመንፈሳዊ በራሂ አካል /spiritual gene/ ይመሰረታል። ከአዳም እስከነኃጢአታችን ብንመጣም በክርስቶስ በማመናችን በደሙ አዲስ ፍጥረት ሆነናል። በዚህም ምክንያት አዲስ መንፈሳዊ ዘረመል ተሰጥቶናል። በአዲሱ ማንነታችንም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንድናድግና የመንፈስ ፍሬዎችን እንድናፈራ ሆኗል።”

♥ “እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭንመንፈስከሚሆንጌታእንደሚደረግያንመልክእንመስልዘንድከክብርወደክብርእንለወጣለን።”2ኛቆሮ3፥18

♥ “ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይምአንዳችየለውም፤ዮሐ14፥30

♥ “የዚያንጊዜምአለቆችናመሳፍንቱስለመንግሥቱበዳንኤልላይሰበብይፈልጉነበርነገርግንየታመነነበረና፥ስሕተትናበደልምአልተገኘበትምናበእርሱላይሰበብናበደልያገኙበትዘንድአልቻሉም።”ዳን6፥4

♥ “በቁጣችሁላይፀሐይአይግባ፥ለዲያብሎስምፈንታአትስጡት።”ኤፌ4፥27

ልክ እንደ ኢየሱስ ዓላማችን መሆን ያለበት ጠላት በራሳችን ኃጢአት፣ ሌሎች በእኛ ላይ ለሚያደርጉት በደል በምንሰጠው ምላሽ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በደል በእኛ ላይ ምንም ቦታ እንደሌለው እርግጠኛ መሆን ነው። ጳውሎስ በጢሞቴዎስ መልዕክቱ ላይ ከበደል እንድንለይ ይመክረናል።

♥ “እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነፃ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅምለበጎምሥራሁሉየተዘጋጀእቃይሆናል።”2ኛጢሞ2፥21

ይህንን ስናደርግ የክብር አቃዎች፣ ለጌታችን ጠቃሚዎች ለመልካም ስራ የተዘጋጀን እንሆናለን። • ዓመፅን እንደሚገባ ያልተረዳነውና በቂ ትምህርት ያላገኘንበት ምክንያት በደል፣ መተላለፍ እና

ኃጢአትበአንድላይተጨምቀውተመሳሳይትርጉምስለሚሰጣቸውነው።

• ዓመፅ ምን እንደሆነና በሕይወታችን ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያመጣ በጥልቀት ስንመለከትበደል፣ ኃጢአት እና መተላለፍ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ኅብረት እንዴት እንደሚያበላሹማወቅእንችላለን።ሶስቱምየተለያየትርጓሜአላቸው።

ኢየሱስ ለበደላችን፣ ለመተላለፋችን ዋጋ ከፍሏል። ♥ “እርሱግንስለመተላለፋችንቈሰለ፥ስለበደላችንምደቀቀየደኅንነታችንምተግሣጽበእርሱላይ

ነበረ፥በእርሱምቍስልእኛተፈወስን።”ኢሳ53፥5

♥ “እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለእግዚአብሔርምየሁላችንንበደልበእርሱላይአኖረ።”ኢሳ53፥6

♥ “ስለዚህምእርሱብዙዎችንይወርሳል፥ከኃያላንምጋርምርኮንይከፋፈላልነፍሱንለሞትአሳልፎሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለዓመፀኞችምማለደ።”ኢሳ53፥12

Page 106: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

96 97

• ኃጢአት፥ እግዚአብሔርንና ሌሎችን የሚያሳዝን ድርጊት ነው (መተላለፍ)።

• ዓመፅ፥ ልብን በማደንደን ከእግዚአብሔር መቃረን ነው (መቃወም)።

• በደል፥ ጠማማነት የሚያስከትል ድካም፣ ከእግዚአብሔር ዞር ማለት፣

ዓመፅ ነው (ማስከፋት)።

† ንጉስዳዊትበኃጢአት፣በዓመፅእናበመተላለፍመካከልያለውንልዩነትተናግሯል።

♥ “አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። ከበደሌፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴነውና።አንተንብቻበደልሁ፥በፊትህምክፋትንአደረግሁ፥በነገርህምትጸድቅዘንድበፍርድህምንጹሕትሆንዘንድ።እነሆ፥በዓመፃተፀነስሁ፥እናቴምበኃጢአትወለደችኝ።”መዝ51፥1-5

♥ ለሙሴ እንደተናገረውም፦“እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍንኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነፃ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከሦስትናእስከአራትትውልድምበልጅልጆችየሚያመጣአምላክነውሲልአወጀ።”ዘፀ34፥7

† እግዚአብሔርበኃጢአት፣በዓመፅናበመተላለፍምክንያትልዩነትንካደረገእኛምበእርሱመንገድ መሄድ አለብን። በዚህ መረዳት ካልኖርን ኃጢአታችንን ብቻ ተናዝዘን የበደልምሽግግንበሕይወታችንይኖራል።

6.8 ሕይወትን እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ መምራት

በምድር ላይ እንድንኖርበት በተሰጠን ጊዜ እግዚአብሔርን አስከብሮ መኖር የክርስቲያን ዋና ዓላማና የኑሮ ግብ መሆን አለበት። እንደተሰጠን ስልጣንና የልጅነት መብት ጨውና ብርሃን የመሆን ኃላፊነት አለብን። ይህም እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ያስቀመጠውን ሀሳቡን አሳክተን እንድናልፍ መውሰድ ካለብን ጥቂት እርምጃዎች መካከል ከዚህ በታች የተገለፁት ይገኛሉ።

• ቃሉንመብላት፤

• መዘመር፤መጾምናመጸለይ፤

• ወንጌልንመመስከር፤

• አጋንንትንማውጣት፤

• እግዚአብሔርንማመስገንናማምለክ፤

• ትኩረትንበምድራዊነገርላይሳይሆንበመንፈሳዊነገርላይማድረግ፤

• ለጌታየሚገባውንመስጠት(መባ፣አስራትእናበኩራትከጌታአለመስረቅ)

• እንደቃሉመኖር

• ወዘተ

Page 107: የባለቤትነት መብት - dirzon...ላየ እድሜያቸውን ለማስላት ይገደድ ይሆናል። የአዕምሯቸው ብስለትና የልባቸው ቅንነት

97

ማጠቃለያበእግዚአብሔር መልክና አምሳል መፈጠራችን የእርሱን ባህርይ እንድንላበስ አድርጎናል።

የእግዚአብሔር መልክ ቁሳዊ ባልሆነው በማይሞተው የሰው ማንነት ላይ ተንፀባርቋል። አዳምና ሄዋን የተከለከሉትን በማድረግ ኃጢአትን ወደ ገነት ካስገቡ በኋላ መንፈሳቸው ተበክሏል። ይህንንም ኃጢአት ለማጥራትና የነበረውን ጥምረት ሊመልስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቷል። የተበላሸውን ገጽታ በከፈለው ውድ መስዋዕትነት ወደ ሚገባው ፅድቅ መልሶታል።

ጠላት የተቀደደውን ጥቁር መጋረጃ ሊሰፋ በብዙ ይሞክራል። ከእውነተኛ ክርስቲያኖች ጋር የበረታ ውጊያን ይፈጥራል። በሚታይና በማይታይ ቁሳዊና መንፈሳዊ በሆነ የማጥቂያ ስልት በእግዚአብሔር ልጆች ላይ እንቅፋት ያስቀምጣል። የድሮ ማንነትን በማስታወስ፣ በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖን በመፍጠር፣ ልባችንን በመስበር፣ ተስፋ በማሳጣት፣ ማስተዋላችንን ለመጋረድ ይተጋል። በዓለም ላይ ላሉ ለሌሎች ሰዎች ብርሃንና ጨው መሆን ሲገባን በድቅድቅ ጨለማ ጣዕመ-ቢስ የሆነ ኑሮን እንድንገፋ ቀን ከሌት ይጥራል።

ክርስቶስን አምነን ሕይወቱን መኖር ስንጀምር የክፉ አሰራር በእጥፍ ጨምሮ ወደ ሕይወታችን ያመራል። በጌታ በኢየሱስ ነፃ የወጣ ነፍስ አሮጌ ማንነቱን ቆርጦ በመጣል ጠላት ለሚያዘጋጅልን ወጥመዶች አስቀድሞ ማየት የሚችል የተከፈቱ አይኖች እንዲኖሩን ያደርጋል። መንፈሳዊ ውጊያን ስንዋጋ ከማን ጋር እንደምንዋጋ፣ ለምን እንደምንዋጋ እንዲሁም እንዴት እንደምንዋጋ በማወቅ ራሳችንን ሁልጊዜ ዝግጁ አድርገን መገኘት አለብን። በዓለም ላይ ስንኖር ከስጋ ስራዎችና ከኃጢአት በመራቅ “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ” (ማቴ 10፥16) ይላልና። ጠላት የሚሰራባቸውን መንገዶች በመለየት የተጠራንበትን ዓላማ ግቡን እንዲመታ ግለ-ድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል።

አማኝ በምድር ላይ የሚኖረው ቆይታ በዓላማ መሆን አለበት። የክርስቲያን ሕይወት እግዚአብሔርን በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ መግለጥ መቻል አለበት። ይህም ጸጋ ከእግዚአብሔር የሚገኝ ብቻ ነው። መንገዱም ከሰማያዊው አባታችን ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት በማድረግ ነው። አማኞች ችላ ብለን የምናልፋቸውን ሁኔታዎች ለማስታወስና ከብዙው በጥቂቱ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ለማመላከት በተዘጋጀው በዚህ ፅሁፍ እንደተገለገላችሁ ተስፋዬ የላቀ ነው። የጥበብ ሁሉ ምንጭ የሆነው አምላካችን ውስጣዊ እይታችንን ይግለጥልን፤ ከጠላት ቀስትም ይጠብቀን። አሜን።